Wednesday 28 November 2012

የብር ምንዛሪ አቅም እየወረደ ነው

በሁለት ዓመት ከ10 በመቶ በላይ ቀንሷል
በዳዊት ታዬ
 
የአንድ ዶላር የምንዛሪ ዋጋ በ17 በመቶ ጨምሮ በ16.35 ብር እንዲመነዘር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መወሰኑ ይፋ ከተደረገበት መስከረም 2003 ዓ.ም. ወዲህ ባሉት ሁለት ዓመታት፣ የብር ምንዛሪ አቅም እየቀነሰ ከ10 በመቶ በላይ መውረዱ ተመለከተ፡፡በኅዳር 2004 ዓ.ም. የየዕለቱ የውጭ ምንዛሪ ዋጋን በሚያመለክተው መረጃ መሠረት የአንድ ዶላር አማካይ የምንዛሪ ዋጋ 17.211 ብር የነበረ ሲሆን፣ በኅዳር 2005 ዓ.ም. ያለው መረጃ የአንድ ዶላር የምንዛሪ ዋጋ ወደ 18.181 ብር ማደጉን ያሳያል፡፡

ከኅዳር 2003 ዓ.ም. እስከ ኅዳር 2004 ዓ.ም. የነበረው የምንዛሪ ዋጋ ከ5.3 በመቶ በላይ ሲጨምር፣ በ2005 በጀት ዓመት የኅዳር ወር የምንዛሪ ዋጋ በአማካይ ወደ 18.181 ብር ማደጉን ተከትሎ ከሌሎች መገበያያ ገንዘቦች አኳያ (በዋናነት ከዶላር) የብር የመግዛት አቅምን በአንድ ዓመት ከ5.56 በመቶ በላይ እንዲወርድ አድርጎታል፡፡ በአጠቃላይ ከኅዳር 2003 ዓ.ም. ወዲህ የብር የመግዛት አቅም በ30 ከመቶ እንዲወድቅ ምክንያት ሆኗል፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት የታየው የምንዛሪ ለውጥ ግን በመስከረም 2003 ዓ.ም. በብሔራዊ ባንክ በአንዴ ከተደረገው ጭማሪ በተቃራኒው ቀስ በቀስ በየዕለቱ ይካሄድ በነበረው የውጭ ምንዛሪ ግብይት ላይ ተመርኩዞ እየጨመረ የመጣ ነው፡፡ ቀስ በቀስ የታየው ለውጥ በፍጥነት እያደገ የመጣው ደግሞ ካለፈው መጋቢት 2004 ዓ.ም. ወዲህ መሆኑንም መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት የታየው የምንዛሪ ለውጥ ብሔራዊ ባንክ የብር ምንዛሪ ለውጥ በአንዴ ከማድረግ ይልቅ፣ ቀስ በቀስ እየጨመረ እንዲሄድ ማድረግ መምረጡን ያሳያል የሚሉ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች፣ በሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ከ10 በመቶ በላይ የደረሰው ጭማሪ ከፍተኛ እንደሆነም ይገልጻሉ፡፡

የብር ምንዛሪ ለውጡን በአንድ ጊዜ ከመለወጥ ባለፉት ሁለት ዓመታት እንደታየው ቀስ በቀስ እንዲለወጥ ማድረጉ በአንድ በኩል የተወሰነ ጠቀሜታ ቢኖረውም፣ የዋጋ ግሽበት እንዳይወርድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል ይላሉ፡፡

Friday 23 November 2012

“ባልና ሚስት ምንድን ናቸው?”

“ባልና ሚስት ምንድን ናቸው?” በሚል ንዑስ ርዕስ ስር፣ የባልና ሚስትን አካላዊና ስነ ልቦናዊ ጥምረት፣ የመንፈስ አንድነት “ባልና ሚስት አብረውና በደስታ ለመኖር የፈለጉ እንደሆነ እያንዳንዳቸው ሶስት ሶስት መሆን አለባቸው”  “መጀመሪያ ባልየው ሌት ተቀን እንደ ሎሌ ታጥቆ የሚሠራ÷ ለቤቱ የሚያስብ በአዳራሽ ሲገኝ ደግሞ ጌታ መስሎ÷ ተኮፍሶ÷ እንግዳውን የሚቀበል÷ ልጆቹን የሚያዝዝ÷ የቤቱን ሥነ-ሥርዓት የሚቃኝ÷ በመኝታ ቤት ግን ተጫዋች መሆን አለበት” 

 “ምሽት የማድቤት ገረድ÷ የሳሉን እመቤት÷ የመኝታ ቤት እብድ መሆን አለባት እንጂ በጠቅላላው የተኮፋፈሱ እንደሆነ ሦስት ባህሪ ከሌላቸው ባልና ምሸት አይሆኑም” ወሲብንና ስነልቦናዊ ጥምረትን በባለትዳሮች ላይ ያላቸውን ሰፊ ቦታ፣ በቅኔያዊ ጨዋታ በብልሃት ለዘብ አድርገው ያስረዱበት መንገድ በርግጥም የደራሲውን ልዩ ብቃት ያመለከተ ይመስለኛል፡፡ 

የአለማየሁ ሞገስ



Thursday 22 November 2012

ዝኆኑም ትንኙም ዝኆኑም ትንኙም

አንበሳ በሚገዛው አንድ ጫካ ውስጥ አያሌ እንስሳት ይኖሩ ነበር፡፡ አንድ ቀን አንበሳ ለአንድ የሥራ ጉዳይ ወደ ሌላ ሀገር ለመሄድ ተነሣ፡፡ የእርሱ መሄድ በእንስሳቱ ዘንድ በተሰማ ጊዜ የጫካውን ሕልውና በተመለከተ ጥያቄ ተነሣ፡፡ ጦሩን ማን ይመራል? ገንዘብ ማን ይይዛል? ምግብ ማን ያከፋፍላል? መልእክት ማን ይቀበላል? ዳኝነት ማን ይሰጣል? ሠራተኛ ማን ያሠማራል? ሹመት ማን ይሰጣል? እያሉ እንስሳቱ መጠያየቅ ጀመሩ፡፡ በዚያ ጊዜ አንበሳ ሁሉንም ነገር ጠቅልሎ ይዞት ስለነበር አሁን እርሱ ሲሄድ ነገር ዓለሙ ሁሉ ሊዛባ ደረሰ፡፡
አንበሳ ችግሩን ቢረዳውም ነገር ግን ለአንዱ እንስሳ ብቻ ሥልጣኑን ሰጥቶ መሄዱ እስከ ዛሬ ድረስ ከእርሱ በታች እኩል ሆነው የኖሩትን ታማኞቹን ማባላት መስሎ ታየው፡፡ ስለዚህም ‹ሥልጣን በተርታ ሥጋ በገበታ› ብሎ ሥልጣኑን ቆራርሶ ለሁሉም በየዐቅማቸው ለማካፈል ወሰነ፡፡ በዚህም መሠረት ነበርን የጦር ሚኒስትር፣ ዝንጀሮን ዋና ዳኛ፣ ጦጣን የገንዘብ ተቆጣጣሪ፣ ቀበሮን የሥጋ ኃላፊ፣ ዝሆንን ምግብ አከፋፋይ፣ አጋዘንን የሠራተኞች ተቆጣጣሪ፣ ተኩላን ፖሊስ አድርጎ ሰየማቸው፡፡
ሁሉም የጫካው እንስሳት ሹመት ሲደርሳቸው ሁለት እንስሳት ግን ምንም ሳያገኙ ቀሩ፡፡ ኤሊ እና ጥንቸል፡፡ አንበሳውም ‹‹ዔሊ እጅግ ዘገምተኛና ዛሬ ተነሥታ የዛሬ ሳምንት የምትደርስ ፍጡር ናት፡፡ ለእርሷ ሹመት መስጠት ማለት በሹመት ላይ መቀለድ ማለት ነው›› ሲል እንስሳቱ ሁሉ ሳቁ፡፡ ወደ ጥንቸልም ዞር ብሎ ‹አንቺ ሚጢጢ ፍጡር አሁን ላንቺ ሥልጣን ቢሰጥሽ ምን ታደርጊበታለሽ›› ሲል ተሳለቀባት፡፡ ይህም በእንስሳቱ ሳቅ ላይ ሌላ የሳቅ ዳረጎት ጨመረላቸው፡፡
አንበሳውም ወደ ጉዳዩ ሄደ፡፡

Mercy Mercy

Katrine Riis Kjær, Denmark, 2012
At first sight, adoption seems like a win-win situation: a poor orphan gets some loving parents and a good life. But the world of adoption is a question of supply and demand, with Ethiopia as a chief supplier of thousands of needy children. The fact that the well-being of the child is not always top priority becomes painfully clear in this tragic story about Masho and her little brother Roba. Far from being orphans, their sick parents give them up for adoption in the hope they'll have a better life. The two toddlers move to Denmark with their new parents, but are they better off now? For four years, Katrine Kjaer followed both parent couples in their growing sense of hopelessness. Danes Henriette and Gert are on the verge of despair over the rebellious Masho, who doesn't want to adjust to her new family. Ethiopians Sinkenesh and Husen are desperate because they're not receiving any news about their children, as the adoption agency promised. Kjaer records it all. Emotional moments such as the transfer of the children and the tensions in their home in Denmark are shot from a respectful distance. Without losing sight of the nuances, the film shows the downside to international adoption, the contrast between Ethiopia and Denmark, and the parallel pain of both parents and children.

Wednesday 21 November 2012

"የኢትዮጵያ ዘመናዊ የህፃናት የውጭ ንግድ"

ጉዲፈቻ ታሪክ በኢትዮጵያ በባህላዊ መንገድ ሲደረግ የቆየ ነው መቼ እንደተጀመረ በእርግጠኝነት ለማወቅ ባይቻልም በ18 ክፍለ ዘመን በኦሮሞ ብሔረሰብ እንደተጀመረ ይታሰባል። ጉዲፈቻ የሚለው ቃል የመጣው ከኦሮሚኛ ቋንቋ ሲሆን ትርጓሜውም ተፈጥሮዓዊ የወላጅነትና የልጅነት የሥጋ ዝምድና ሳይኖር ከሌላ ሰው አብራክ የተወለደን ልጅ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ጥቅሙን ጠብቆ እንደ አብራክ ክፋይ ልጅ ማሳደግ ማለት ነው። በኢትዮጵያ የጉዲፈቻ ሕግ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1952 ዓ.ም በወጣው የፍትሐብሔር ሕግ ማዕቀፍ ተሰጥቶታል ይህም ሕግ የሕፃኑን መብት የሚያስጠብቅ ሆኖ የተዘጋጀ ነው።
 
የጉዲፈቻ ዓላማ ከውርስ ሥርዓት ጋር በተያያዘ የዘር ሃረግን ለመቀጠል፤ የዝምድና ትስስር ለማጠናከር፤ ፖለቲካዊ ሃይማኖታዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን ለማግኝት፤ … ጥቂቶቹ ናቸው። ለምሳሌ በሀገራችንም የተለያዩ ጦርነቶች በጎሳዎች መካከል ሲነሱ የአንዱን ጎሳ ልጅ አንዱ ጉዲፈቻ ያደርጋል በዚህም ሰበብ በጎሳዎቹ መካከል ሰላም ይፈጠራል።
 
በተለያዩ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቀውሶች ምክንያት የድንበር ተሻጋሪ ጉዲፈቻ እየጨመረ መጥቷል። ሀገሮች ለጉዲፈቻ ልጆች ምንጮች የሚሆኑበት ምክንያት በርካታ ናቸው። በሃገራችን እ. ኤ. አ. በ2004 በተደረገ ጥናት ኢትዮጵያ ከቻይና፣ ጓቲማላ፣ ሩሲያና ሶሪያ ቀጥላ በአምስተኛ ደረጃ የጉዲፈቻ ምንጭ ሀገር ለመሆን መብቃቷ ታውቋል። እ. ኤ. አ. በ2006 ላይ የተለያዩ ሀገሮች እየቀነሱ በመምጣታቸው ኢትዮጵያ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። እ. ኤ. አ. በ2010 ደግሞ አብዛኞቹ ሃገሮች በከፍተኛ ደረጃ በመቀነሳቸው ኢትዮጵያ ሁለተኛ ሆናለች።

Tuesday 20 November 2012

Uenige om når et barn er norsk








Hvor lenge må et asylbarn være i Norge for være norsk nok for å få oppholdstillatelse? En splittet regjering behandlet tirsdag dette spørsmålet i Stortinget.
20. november 2012 kl. 20.58, oppdatert 20. november 2012 kl. 22.12 |kommentarer |

Stortinget debatterte regjeringens stortingsmelding «Barn på flukt», hvor regjeringen og Arbeiderpartiet nekter å sette en tidsgrense for å sikre at asylbarn skal få opphold.
– Det kommer vi ikke til å sette noe absolutt grense på. Det viktigste argumentet mot, er jo at en absolutt grense kanskje vil friste en del til å prøve å hale ut tiden, sier saksordfører i Arbeiderpartiet Lise Christoffersen.

Ønsker en avklaring i Høyesterett

Advokat Håkon Bodahl-Johansen. (Foto: Anne Lognvik/NRK)Advokaten til Verona Delic, Håkon Bodahl-Johansen, la fram detaljer for bakgrunnen for saken, i retten i dag.
Foto: Anne Lognvik/NRK
I dag startet Høyesterett behandlingen av saken til Verona Delic som sammen med familien er utvist fra Norge til Bosnia.

Sunday 18 November 2012

የሰማዕታት ቀን በኦስሎ

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በዛሬው ዕለት በኦስሎ በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት አዘጋጅነት ለወጣቱ ስለፍትህ ስለ ነፃነት ስለ ሰብአዊ መበት መከበር ሲል ውድ ህይወቱን ቤዛ ላደረገልን መምህር የኔሰው ገብሬ እና በግፍ ለታሰሩት ለተገደሉት የነፃነት ታጋዮች የሻማ ማብራት ስነ ስርዓት ተካሄዶል በዚሁ ስነ ስርዓት ላይ ዶ/ር ሙሉ ዓለም ባደረጉት ንግግር በውጭ ሀገር የምንኖር ኢትዮጵያውን  ከምንጊዜውም በበለጠ ህብረትና ወገናዊ ፍቅርን በመካከላችን በመመስረት በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን የሰብዓዊ መብት እረገጣ ሰለቸኝ ደከመን ሳንል ለህዝባችን ነፃ መውጣት መታገል አለብን ሲሉ ተናግረዋል በዝግጅቱ ላይ  የመታሰቢያ ግጥሞች ንግግሮች ተደርገዋል።
 
Nov.18.11.12

Saturday 17 November 2012

Norway refuses to grant Ethiopia’s fingerprint request of over 400 refugees

Saturday, 17 November 2012 06:48 
By MERGA YONAS 
 
The Norwegian government has disagreed with Ethiopia on the latter's request for fingerprints of the over 400 Ethiopian refugees residing in Norway, who were expected to be deported, as it is not in their repatriation agreement. On January 26, Torgeir Larsen, Secretary of state with Norwegian government and Ambassador Berhane Gebrekristos, Minister of Foreign Affairs, signed a Memorandum of Understanding to repatriate back Ethiopian citizens in Norway. Since March 15, the Norwegian government was in the process of sending back over 400 Ethiopian refugees living in the country without legal documents or resident permits.

Sources told the The Reporter that though the Ethiopian government requested as a precondition fingerprints of the Ethiopians who are set to be deported, the Norwegian government refused to get engaged as the request was not in their repatriation agreement.

The agreement was signed between the two countries to let citizens repatriate voluntarily, Ambassador Dina Mufti, spokesperson with the Ministry of Foreign Affairs told The Reporter. According to the agreement, the repatriation is going to be carred out by the Norwegian government.

“Thus, we don’t follow up the status and I don’t have any information regarding the fingerprint request,” Dina told The Reporter.

“In the first place there was no one who could voluntarily return back to Ethiopia, as many are political refuges and that is why the demonstration has kept on here in Norway,” an Ethiopian who resides in Norway told The Reporter in a telephone interview.

Wednesday 14 November 2012

ፍርደኛው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንዲወረስ ጥያቄ በቀረበበት ንብረቱ ጉዳይ አልከራከርም አለ

አቶ አንዱዓለም አራጌም ፍርድ ቤት ቀርበዋል
በታምሩ ጽጌ

በዚህም ምክንያት ወደ ፍርድ ቤት ከዛሬ በኋላ እንዳልቀርብ ለማረሚያ ቤት ትዕዛዝ ይሰጥልኝ፤” በማለት አመልክቷል፡፡
 
በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሶ በ18 ዓመታት ፅኑ እሥራት እንዲቀጣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ውሳኔ ያሳረፈበት ፍርደኛው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ዓቃቤ ሕግ እንዲወረስ ስለጠየቀበት የንብረት ጉዳይ ቤተሰቡም ሆነ እሱ መከራከር እንደማይፈልጉ ለፍርድ ቤቱ አስታወቀ፡፡ በነሐሴ ወር 2004 ዓ.ም. የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በሽብርተኝነት አዋጁ በተቀመጠው አንቀጽ መሠረት፣ “በሽብር ወንጀል የተቀጣ ግለሰብ ንብረት መወረስ እንዳለበት ያዛል” በሚል ለፍርድ ቤት ባቀረበው ጥያቄ መሠረት፣ ንብረታቸው እንዲወረስ ከተጠየቀባቸው ፍርደኞች መካከል በዕድሜ ልክ ፅኑ እሥራት እንዲቀጣ የተወሰነበት አንዱዓለም አራጌና ጋዜጠኛ እስክንድር ትናንትና ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር፡፡

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ የወንጀል ችሎት ቀርበው የነበሩት የአንድነት ፓርቲ አመራር አቶ አንዱዓለም አራጌና ባለቤታቸው ዶክተር ሰላም አስቻለው፣ እንዲወረስባቸው የተጠየቀውን አንድ የቤት መኪና በሚመለከት ተቃውሞ እንዳላቸው ለፍርድ ቤቱ በጽሑፍ አቅርበዋል፡፡

ሌላው ዓቃቤ ሕግ ንብረቱ እንዲወረስ ለፍርድ ቤት ጥያቄ ያቀረበበት፣ በሌለበት ጥፋተኛ ተብሎ በ15 ዓመታት ፅኑ እሥራት እንዲቀጣ የተወሰነበትና ኑሮውን በአሜሪካ ያደረገው አበበ በለው ሲሆን፣ ባለድርሻ ይሆናሉ ያላቸውን የባለቤቱ አድራሻ ማግኘት አለመቻሉን ለፍርድ ቤቱ አስታውቋል፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥበት አመልክቷል፡፡

በመቀጠል ጋዜጠኛ እስክንድር ከተቀመጠበት የተከሳሾች መቀመጫ ሳጥን ውስጥ ቆሞ የሚያቀርበው ሐሳብ እንዳለው በመግለጽ፣ “እኔም ሆንኩ ባለቤቴ በንብረት ውርስ ምክንያት መከራከር አንፈልግም፡፡ በዚህም ምክንያት ወደ ፍርድ ቤት ከዛሬ በኋላ እንዳልቀርብ ለማረሚያ ቤት ትዕዛዝ ይሰጥልኝ፤” በማለት አመልክቷል፡፡

Thursday 8 November 2012

ፀሎት

ልዑል እግዚአብሔር ሆይ ሃገሪን
በታማኝነት በቅንነት እንዳገለግል እርዳኝ
ልዑል እግዚአብሔር ሆይ ሃገሪን በታማኝነት በቅንነት እንዳገለግል እርዳኝ





Wednesday 7 November 2012

ዋይ ዋይ ሲሉ የርሃብን ጉንፍን ሲስሉ


ሕፃናት አካላዊ ማህበራዊና ስነ ልቦናዊ ጉዳት ከሚያደርሱ ነገሮች ሁሉ መጠበቅ አለባችው ሀገራችን ህፃናቱ ትምህርት ቤት ሲሄዱ የሚላስ የሚቀመስ በቤታችው ጠፍቶ ጠኔ አዙሮ እየደፍችው ነው የኢትዮዽያ መንግስት ተብየው  ኮምፒውተርን እንደምግብ አቅርቦላቸዋል





 

Why I hope kids in Ethiopia can teach the rest of us something profound about education.


                    Self-taught: Children in Ethiopia are learning to use tablets distributed by OLPC.
 
Seymour Papert, a computer scientist and pioneer in artificial intelligence, once said: “You cannot think about thinking unless you think about thinking about something.” Does this apply to learning? Maybe not.

Here is what I mean.

Stakkars Etiopiske Barn !!!

Et eksperimentet fant sted i noen utvalgte avsidesliggende landsbyer i Etiopia. Barna fikk utdelt små datamaskiner av typen Motorola Xooms, skriver publikasjonen MIT Technology Review.
Disse observasjoner villle være interessante om forfatteren snakket om ville aper og ikke om mennesker. Stakkars Etiopiske barn !!!
             
 
Leder:"Etiopiske barn fikk PC-er, begynte å utdanne seg selv"
 
Maskinene, såkalte tablets, var fra før utstyrt med flere undervisningsapplikasjoner, og batteriene ble ladet ved hjelp av solcellepaneler. Men de ble levert i lukket emballasje, uten noen instrukser for hvordan de skulle betjenes.
Forskerne trodde barna, som knapt hadde sett noen skrevne ord tidligere, ville være uforstående til datahjelpemidlene. Men etter bare fire minutter hadde ett av barna åpnet boksen og slått på datamaskinen.

Monday 5 November 2012

አልሠለጥን ያለው የዳያስፖራ ፖለቲካ

ዳዊት (እውነተኛ ስሙ እንዲገለጽ አይፈልግም) በኖርዌይ ለአምስት ዓመታት ያህል ቆይታ አድርጓል፡፡ በአሁኑ ወቅት ቤተሰቡን እዚያ ትቶ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ሥራዎች የተሰማራ ወጣት ነው፡፡ በተሰማራበት ሥራም ውጤታማ ሳይሆን አይቀርም ደስተኛ ነው፤ ቤተሰቡን ለማምጣት ካልሆነ በስተቀር ተመልሶ እዚያ አገር የመኖር ፍላጎት የለውም፡፡ በኖርዌይ ውስጥ በነበረው ቆይታ ብዙም መልካም ትውስታ ያለው አይመስልም፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ የግል ባንኮች መካከል ስሙ ከሚጠቀስ አንድ ታዋቂ ባንክ የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ ሆኖ በቂ የሚባል ደመወዝ እየተከፈለውና መኪና ተመድቦለት፣ እንዲሁም የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች እያገኘ መልካም የሚባል ኑሮ የሚኖር ሰው፣ በሥራ ምክንያት ወደ ኖርዌይ አቅንቶ እዚያው ስለመቅረቱ ዳዊት አውግቶናል፡፡

‹‹ዛሬ ነገ እየተባለ የፖለቲካ ጥገኝነቱ ምላሽ አግኝቶ እዚያው አገር የተሻለ ሥራ ሠርቶ ለመኖር የነበረው ምኞት ሳይሳካ የባንኩ ሰው ይኼው ሁለት ዓመት ሞልቶታል፤›› ይላል ያንን የመቅረት ዕርምጃ የወሰነበትን ቀን እየረገመ እንደሚኖር እያስታወሰ፡፡ በርካታ ኢትዮጵያውን ምንም የፖለቲካ ዕውቀትና ፍላጎት ሳይኖራቸው እዚያ አገር የመኖርያ ፈቃድ አግኝተው ለመኖርና ሕይወታቸውን ለመቀየር ሲሉ፣ ላቀረቡት የፖለቲካ ጥገኝነት ጥያቄ ምላሽ ሲጠባበቁ እየተሰቃዩ ይኖራሉ ይላል፡፡

Sunday 4 November 2012

ኢትዮጵያችንን እየሰጠናት ወይስ እየነጠቅናት?!

‹‹አገሬ ለእኔ ምን አደረገችልኝ ብለህ ከመጠየቅህ በፊት እኔ ለአገሬ ምን አደረግኩላት ብለህ ጠይቅ›› ብለው ነበር የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ፡፡
 
እኛም ደግመን ደጋግመን እንለዋለን፡፡ ‹‹ላድርግላት›› የሚል እየጠፋ ‹‹ታድርግልኝ›› የሚል እየበዛ ነውና፡፡ ‹‹የሰጪ›› ቁጥር እያነሰ ‹‹የነጣቂ›› ቁጥር እየበዛ ነውና፡፡

እስቲ እንደ መንግሥትም፣ እንደ ሕዝብም፣ እንደ ግለሰብም፣ እንደ ዜጋም ራሳችንን እንፈትሽ፡፡ የድርሻችንን እየተወጣን ነን? እስቲ መንግሥትን ከመፈተሻችን በፊት እንደ ሕዝብና እንደ ዜጋ ራሳችንን እንፈትሽ፡፡

ኢትዮጵያችን ከጉቦ፣ ከሙስናና ከአድልዎ ፀድታ ሕገ መንግሥቱን መሠረት አድርጋ የምትንቀሳቀስ አገር እንድትሆን እንመኛለን፡፡ ነገር ግን ራሳችን እነዚህን እኩይ ተግባራት እንታገላለን? ጉቦ ሰጪ ከሌለ ጉቦ ተቀባይ እንደማይኖር አውቀን እምቢ አንሰጥም ብለን በፅናት እንቆማለን? ጉቦ የሚሰጡትንና ጉቦ የሚቀበሉትን እናጋልጣለን? ፈርተን ወይም እኛም ጉዳያችን እንዲፈጸምልን ብለን ተባባሪ እንሆናለን?

እዚህ ላይ ከፍተኛ ጉድለትና ድክመት በዜጎችና በተለይም እንደ ሕዝብ እየታየብን ነው፡፡ ጠንክረን ሙስናን እየታገልን አይደለም፡፡ አገራችን ስትነጠቅ፣ ስትሰረቅና በሙስና ስትጨማለቅ የድርሻችን እየተጫወትን አንገኝም፡፡ ሌላው እንዲሠራው እንጂ እኛ ራሳችን ኃላፊነታችንን አንወጣም፡፡ አገራችን እንድትነጠቅ እየተባበርን ነን፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው ስለማንታገል፣ ለመብታችን ስለማንቆምና ግዴታችንን ስለማንፈጽም ነው፡፡

ወንጀል እንዲጠፋ እንፈልጋለን፡፡ መንግሥት ይህን ለምን አያደርግም፣ ፖሊሶች ለምን ዝም ይላሉ፣ ወንጀልኮ እየበዛ ነው፣ ሌብነት ተስፋፋ እንላለን፡፡ ሌላው ማድረግ ያለበትን አለማድረጉ ያስጠይቀዋል፡፡ ነገር ግን እኛ ራሳችንስ እንደ ዜጋና እንደ ሕዝብ ወንጀል ሲፈጸም ስናይ ምን ያህል እንታገላለን? ራሳችን ምን ያህል እናጋልጣለን? የመንግሥትና የሕዝብ ንብረት በየመንገዱ ሲዘረፍ ስናይ ፈርተን ዝም እንላለን ወይስ ደፍረን እናጋልጣለን? መኪና መንገድ ላይ ሲሰረቅ እያየን ዝም፣ የአገር የኤሌክትሪክ፣ የስልክ፣ የውኃ ቧንቧዎች፣ ሽቦዎችና የተለያዩ ዕቃዎች ሲሰረቁ ዝም እንላለን፡፡

ዜና ዜና ከአሥር ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከኢትዮጵያ 15 ቢሊዮን ዶላር መውጣቱ ተረጋገጠ

ካቻምና ብቻ 3.5 ቢሊዮን ዶላር ታጥቷል
 
እ.ኤ.አ. ከ2001 እስከ 2010 ባለው ጊዜ ውስጥ 15 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ ሕጋዊ በሆነና ባልሆነ መንገድ ከኢትዮጵያ እንዲወጣ ተደርጎ ወደ ውጭ ገበያዎች ማምራቱን በቅርቡ ይፋ የሆነ ሪፖርት አመለከተ፡፡ ይህ ችግር በመላ አፍሪካ ትኩረት እየሳበ እንደመጣ ታውቋል፡፡

የፋይናንስ ምንጭ በእጅጉ ከሚያስፈልጉዋቸው ታዳጊ አገሮች ወደ ሌሎች አገሮች ገንዘብን በማዘዋወርና በሕገወጥ የፋይናንስ ግብይት እየወጣ ያለውን ሀብት በተመለከተ እ.ኤ.አ. ከ2009 ጀምሮ ሲወጡ የነበሩ ሪፖርቶች የሚያረጋግጡት፣ ክስተቱ ትኩረት እየሳበ መምጣቱን ነው፡፡ ኢትዮጵያ ያላትን ውስን የውጭ ምንዛሪ መጠን ይኼው ከፍተኛ የካፒታል ማዛወር ወይም ማሸሽ ተግባር በእጅጉ እየታየባት በመምጣቱ፣ የመነጋገርያ አጀንዳ እንድትሆን አድርጓታል፡፡

ተሻሽለው የወጡ አኀዞች እንደሚያመለክቱት፣ እ.ኤ.አ. ከ1970 እስከ 2010 በነበሩት ሰላሳ ዓመታት 24 ቢሊዮን ዶላር ከኢትዮጵያ እንዲሸሽ ተደርጓል፡፡ ገንዘብ በከፍተኛ መጠን እየሸሸ መሆኑ ከተመዘገበባቸው ጊዜያት ትልቁን ድርሻ መያዝ የጀመረው እ.ኤ.አ ከ2000 በኋላ ያለው ሲሆን፣ በተለይ እ.ኤ.አ. በ2010 ብቻ 3.5 ቢሊዮን ዶላር በአገሪቱ ኢንቨስት ያደረጉ የውጭ ባለሀብቶች ያሸሹት ገንዘብ (ካለፈው ዓመት ኅዳር ወር አኳያ ከአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት በላይ ሆኖ ተመዝግቧል) በከፍተኛነቱ ሲጠቀስ፣ ከዚህ መጠን ቀጥሎ የተመዘገበው ከፍተኛ የገንዘብ ማሸሽ እ.ኤ.አ. በ2002 የታየው የ3.1 ቢሊዮን ዶላር ነው፡፡ በሪፖርቱ የቀረቡት መረጃዎች ሲፈተሹ፣ ባለፉት ሰላሳ ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ የካፒታል ማሸሽ የተመዘገበባቸው ጥቂት ዓመታት ሆነው ይገኛሉ፡፡

ካፒታል የማሸሽ መጠኑ እ.ኤ.አ. ከ2001 ጀምሮ በ2.1 ቢሊዮን ዶላር እየተመነደገ መምጣት ሲጀምር፣ 2002፣ 2003፣ 2004፣ 2007፣ 2009 እንዲሁም 2010 ላይ በእያንዳንዱ ዓመት የ1.4 ቢሊዮን ዶላር መጠን የመዘገበበት የገንዘብ መጠን ከአገሪቱ ወጥቷል፡፡

ሪፖርቱ ያካተታቸው ጊዜያት የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን የመጨረሻዎቹ አራት ዓመታት፣ እንዲሁም የደርግን የመጨረሻዎቹ አሥር ዓመታት ሲሆን፣ በእነዚህ ጊዜያት ከተመዘገበው የገንዘብ ማሸሽ በልጦ የተገኘው ግን ባለፉት አሥር ዓመታት የተመዘገበው መጠን ነው፡፡

እ.ኤ.አ. በ1982 ከአገሪቱ የወጣው የገንዘብ መጠን 2.8 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን፣ ይህም ከፍተኛው በመሆን ተመዝግቦ የቆየ መጠን ነበር፡፡ ይህ ቢባልም በ1981 1.5 ቢሊዮን ዶላር፣ በ1985 1.3 ቢሊዮን ዶላር እንዲሁም በ1987 1.9 ቢሊዮን ዶላር በመውጣቱ ይህንን ጊዜ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከአገሪቱ የሸሸበት ሁለተኛው ዘመን እንዲሆን አስችሎታል፡፡

ከሰሐራ በታች ከሚገኙ አገሮች 33 አገሮች በአጠቃላይ 814 ቢሊዮን ዶላር የሸሸ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 591 ቢሊዮን ዶላሩ በዚሁ ቀጣና ከሚገኙ ነዳጅ አምራች አገሮች እንዲወጣ የተደረገ ነው፡፡ ይህን ያህል መጠን ካፒታል እየሸሸ የሚገኘው ደግሞ የአገሮቹ የነዳጅ ገቢ እያደገ በመጣበት ጊዜ ሆኖ ሲመዘገብ፣ በተለይ ናይጄሪያ 311.4 ቢሊዮን ዶላር የሸሸባት ትልቋ አገር ሆኖ ተገኝታለች፡፡

በሪፖርቱ አስገራሚ የሆነው ሌላው ጉዳይ ደግሞ እየሸሸ የሚገኘው ካፒታል በቀጣናው በይፋ የተሰጠውን 659 ቢሊዮን ዶላር እንዲሁም ከውጭ በቀጥታ ከተገኘው የ306 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት በልጦ መገኘቱ ነው፡፡ ይበልጡን አስገራሚ የሆነው ደግሞ ከሰሐራ በታች ያለው አካበቢ ለተቀረው ዓለም አበዳሪ ሆኖ የተገኘበት አጋጣሚ ሲሆን፣ እየሸሸ ከሚገኘው ከፍተኛ ገንዘብ በተፃራሪ የቀጣናው የዕዳ መጠን 189 ቢሊዮን ዶላር ሆኖ በመገኘቱ ነው፡፡

ይህ ሪፖርት ከሌሎች በካፒታል ሽሽት ላይ ከተደረጉ ጥናቶች የተለየ እንዲሆን ካደረጉት ነጥቦች መካከል ያለደረሰኝ የሚካሄዱ የንግድ ልውውጦችን፣ እንዲሁም የሐዋላ ገቢዎች በአገሪቱ ኦፊሴላዊ የሒሳብ መዛግብት ውስጥ ተካተው አለመገኘታቸው የሚያስከትለውን ተፅዕኖ ማካተቱ ነው፡፡

ያለደረሰኝ የሚካሄዱ የወጪና ገቢ ንግድ ጉዳቶች ላኪዎች ሆነ ብለው ከገዙበት ዋጋ በታች ደረሰኝ ማቅረባቸው፣ እንዲሁም አስመጪዎች ከገዙበት ዋጋ በላይ የሚያሳይ ደረሰኝ ማምጣታቸው፣ ከአገሪቱ ለሚያፈተልከው ካፒታል ዓይነተኛው መሣርያ ስለመሆኑ ሪፖርቱ በጥልቀት ቃኝቶታል፡፡ በአንፃሩ የተገላቢጦሹን ማለትም ላኪዎች ከገዙበት ዋጋ በላይ፣ አስመጪዎችም ከገዙበት ዋጋ በታች አግባብነት የሌለው የግብይት ደረሰኝ ቢያቀርቡ ግን የወጣውን ካፒታል መልሶ ለማግኘት እንደሚረዳ ጥናቱ ይጠቁማል፡፡

ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያ አግባብነት በሌላቸው የግብይት ደረሰኞች ከመጎዳት ይልቅ ተጠቃሚ የሆነችበት አጋጣሚ መፈጠሩ የተመለከተው 7.1 ቢሊዮን ዶላር ወደ አገሪቱ ገቢ መሆኑን የሚያመላክት መረጃን በማስደገፍ ሲሆን፣ አጋጣሚው የተፈጠረውም ለወጪ ንግድ ከመሸጫ ዋጋ በላይ ለገቢ ንግዱም ከመግዣ ዋጋ በታች ደረሰኞች ለግብይት በመዋላቸው ነው፡፡ በተለይ ከተገዙበት ዋጋ በታች የሚቀርቡ ደረሰኞች ዋና አስተዋጽኦ እንዳላቸው ይታመናል፡፡ በተጨማሪም አገሪቱ በይፋዊ የክፍያ ሚዛኗ (የአገሪቱ ብድር ዕዳና ያበደረችው መጠን) ባታሳየውም ስድስት ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሐዋላ ተመልሶ ወደ አገሪቱ መግባቱ ተጠቅሷል፡፡

ጥናቱን ያካሄደው የማሳቹሴትስ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ምርምር አንስቲትዩት እንደሚያብራራው፣ የካፒታል ሽሽትን በሚመለከት ከዚህ ቀደም በተደረጉ ጥናቶች የቀረቡ አኀዞች መሠረታውያኑን የተዛቡ የንግድ ግብይት ሰነዶችን እንዲሁም ሐዋላን ያላካተቱ በመሆናቸው ትክክለኛውን አኀዝ አያመለክቱም፡፡ ከዚህ ቀደም የተደረጉ ጥናቶች ከአንድ አገር በሚወጣውና በሚገባው የካፒታል ፍሰት መጠን መካከል ያለውን ልዩነት መሠረት አድርገው ይቀርቡ የነበሩ በመሆናቸው፣ ኦፊሴላዊ ባልሆነ መንገድ በመካሄድ ከሰሐራ በታች ባሉ አገሮች ቁልፍ ሚና ያላቸውን የሐዋላና አግባብነት የጎደላቸው የግብይት ሰነዶችን በካፒታል ፍሰቱ ውስጥ አለማካተት የቀደምት ጥናቶች ደካማ ጎን መሆኑን ተቋሙ በሪፖርቱ አመላክቷል፡፡
Reporter News Paper

Saturday 3 November 2012

ፓርኪንግ ፓርኪንግ

አሜሪካን ሀገር ወደሚኖሩ ወዳጆቼ ቤት ሄጄ ነበር፡፡ ከተጋቡ ሁለት ዓመት ሆኗቸዋል፡፡ ቤታቸው ስገባ የቤቱም ዕቃ የቤቱም ሰዎች ዝምታ ውጧቸዋል፡፡ አባ አጋቶን ቤት የገባሁ ነው የመሰለኝ፡፡ እርሱ ክፉ ላለመናገር ሰባት ዓመት ድንጋይ በአፉ ጎርሶ በአርምሞ ተቀምጧል፡፡ ነገር ዓለሙ አላምር ሲለኝ ‹ምነው ያለ ወትሯችሁ ዝምታ ዋጣችሁ› ብዬ ተነፈስኩ፡፡ እዚህ ቤት የነበረውን ሳቅና ጨዋታ ስለማውቀው፡፡ ‹ሳቅና ጨዋታ ዝና ካማራችሁ› ሲባል አልሰማችሁም፡፡ የመለሰልኝም የለ፡፡ በኋላ ነገሩን ሳጠናው ሁለቱም ተኳርፈዋል ለካ፡፡ ‹‹ለመሆኑ እንዲህ ሳትነጋገሩ ስንት ጊዜ ተቀመጣችሁ› ብዬ ስጠይቅ ስድስት ወር ሆኗቸዋል፡፡ ሁሉም በየሥራው ይውላል፤ ማታ ይመጣል፤ ኪችን ገብቶ ያበስላል፤ በልቶ ቴሌ ቭዥን ያያል፤ ከዚያም ይተኛል፡፡ ቢል ሲመጣ ይህንን እኔ ከፍያለሁ ብሎ አንዱ ወረቀት ጽፎ ይሄዳል፤ ሌላው በተራው ይከፍላል፡፡ ይቺ ናት ትዳር፡፡

ድሮ የሰማሁትን ቀልድ ነበር ትዝ ያሰኙኝ፤ ባልና ሚስቱ ተኳርፋው አይነጋገሩም አሉ፡፡ ቤቱ እንደ መቃብር በጸጥታ ተውጦ ከርሟል፡፡ አንድ ቀን ባል ሌሊት አሥር ሰዓት የሚነሣበት ጉዳይ ገጠመው፡፡ ከተኛ መነሣት የሚከብደው ቢጤ ነበርና የመቀስቀሻውን ሰዓት ሊሞላ ሲስበው ተበላሽቷል፡፡ አዘነም፤ ተናደደም፡፡ ምን ያድርግ፡፡ ባለቤቱ ገና ከሥራ አልገባችም፡፡ ‹የወደዱትን ሲያጡ የጠሉትን ይመርጡ› ነውና፡፡ በቁራጭ ወረቀት ላይ ‹አሥር ሰዓት ላይ ቀስቅሽኝ› ብሎ ጽፎ በራስጌው ባለው ኮመዲኖ ላይ አስቀመጠና ተኛ፡፡ ሚስቱ ስትመጣ አየችውና ስቃ ተኛች፡፡ ልክ ከሌሊቱ አሥር ሰዓት ነቃችና በዚያው በቁራጭ ወረቀት ላይ ‹አሥር ሰዓት  ሆኗልና  ተነሣ› ብላ  ጽፋለት  ተኛች፡፡  እርሱ  ዕንቅልፉን  ለጥጦ  ለጥጦ  ሲነሣ ነግቷል፡፡  ተናደደ፤  ግን እንዳይናገራት ለካስ ተኳርፈዋል፡፡ እዚያው ወረቀት ላይ ‹በጣም ታሳዥኛለሽ› ብሎ ጻፈላት፡፡ 

ራዕይ የሌለው መሪ አልመርጥም! (እናንተስ?)

“የቁርጠኝነት ችግር የለብንም፤ የትኩረት እንጂ”

በአሁኑ ጊዜ በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ የሚሉ የመንግስት ባለስልጣናትና ካድሬዎች እንዲሁም የኢህአዴግ አባላት እንደ ፋሽን የያዙትን አነጋገር ሳታውቁት እንደማትቀሩ እገምታለሁ፡፡ ሁሉም ምን ይላል መሰላችሁ? “የመለስን ራዕይ ለማሳካት …” ብሎ ይጀምርና ይሄንኑ አባባሉን በየመሃሉ እየሸነቆረ ትክት አድርጐን ይሄዳል፡፡ ሰሞኑን አንዷ የመንግስት ሠራተኛ “ጠዋት ቀደም ብዬ ሥራ እገባለሁ፤ ማታ እስከ 11 እና 12 ሰዓት ቆይቼ እሰራለሁ” ስትል ተናገረች (“አበጀሁ” ያለችው ማን ነበረች?) ጉዱ የሚመጣው “ለምን ትሰራለች?” የሚል ጥያቄ ስትጠይቁ ነው፡፡ ይሄን ሁሉ የምትሰራው እኮ “የመለስን ራዕይ ለማሳካት” ነው፡፡
 
ግን እኮ እሳቸው ከ8 ሰዓት በላይ የማሰራት ራዕይ የነበራቸው አይመስለኝም፡፡ (ያለ ክፍያ ከሆነ እኮ የጉልበት ብዝበዛ ነው) ቆይ ግን “አዳሜ” የራሱ ራዕይ የለውም እንዴ? የመንግስት መሪዎችም ቢሆኑ እኮ “የመለስ ራዕይ” ላይ የራሳቸውን ጨምረው ካላጐለበቱት ብዙም የሚያዛልቅ አይደለም፡፡ “ድህነት ጠላታችን ነው” ብሎ መዋጋት የመለስ ራዕይ ነው ቢባል ተገቢ ነው፡፡ የህዳሴ ግድቡንም የመለስ ራዕይ ነው ብሎ ለስኬቱ መታተር ስህተት የለውም፡፡ በሰበብ አስባቡ “የታላቁን መሪ” ስም መጥራት ግን ተገቢ አይደለም (አረፍ ይበሉበት እንጂ!) እንዴ አንዳንዴ እኮ ራስን ችሎ መቆምም ያስፈልጋል፡፡ እንደውም የኢህአዴግ መሪዎች ከመለስ ራዕይ ውጭ የራሳችሁ ራዕይ ምንድነው ቢባሉ የሚመልሱትን ማወቅ እፈልጋለሁ፡፡ “የራሳችን ራዕይ የለንም” ካሉ ግን በ2007 ምርጫ ያገናኘን ብዬ አልፋቸዋለሁ፡፡ በድምፄ ጉድ እሰራቸዋለሁ (ዛቻ እኮ አይደለም!) ራዕይ የሌለው መሪ አልመርጥማ! (እናንተስ?)  እኔ የምለው … መዲናችን ልደቷን እያከበረች ነው የሚባል ነገር ሰማሁ ልበል (የትኛውን ልደት?) አምና 125ኛ ዓመቷን አከበረች አልተባለ እንዴ? አንዱ ወዳጄን ስጠይቀው ምን አለኝ መሰላችሁ … “እያረፈች ማክበር አትችልም?” ወቸ ጉድ … ደሞ ልደት ለማክበር የምን ማረፍ ነው! እሺ ማክበሩንስ ታክብር … ግን ስንተኛ ዓመቷን ነው የምታከብረው? ቆይ አዲስ አበባም ዕድሜዋን መደበቅ ጀመረች እንዴ? (“የወንድ ደሞዝና የሴት ዕድሜ አይጠየቅም” አሉ) ግን እኮ አምና 125ኛ ዓመቷ ከሆነ ዘንድሮ 126ኛ ዓመቷን መሆን አለበት! (ቀላል የማቲማቲክስ ስሌት ነው!)

Friday 2 November 2012

በህልሜ!

ከመሃመድ ሀሰን

40-60 ቤት ለመመዝገብ ሳር-ቤት አካባቢ ቀበሌ 03 ተሰልፍያለሁ፡፡ ትከሻዬን ሲከብደኝ ከኃላዬ የተሰለፈውን ሰው ለማየት ዞርኩኝ፡፡ አቶ ኃይለማርያም ናቸው፡፡ ክው አልኩኝ!

‹‹ምነው በሰላም ነው?›› አልኳቸው የተረጋጋሁ ለመምሰል እየሞከርኩ፡፡

‹‹በሰላም ነው...ያው ለ40-60 የቀበሌ መታወቂያ ለማሳደስና ቤት አልባ መሆኔን ማረጋገጫ ለማውጣት ነው፡፡›› ‹‹አንተስ?›› አሉኝ፡፡

‹‹እኔም እንደዚያው ነው››

‹‹ወረፋ ታስቀድመኛለህ!? በጠዋት ቤተመንግስት የቀጠርኳቸው አምባሳደሮች ስላሉብኝ ነው...! ››

‹‹ይቅርታ እኔ ራሴ ክላስ ትቼ ነው የመጣሁት እቸኩላለሁ›› አልኳቸው፡፡

‹‹ምን ይሻላል ባካችሁ!›› ብለው ተከዙ፡፡ ሲተክዙ ወደሰማይ አንጋጠው በመሆኑ ርዕይ የሚያዩ ይመስላሉ፡፡

‹‹የት ነው የምትሰራው?››

‹‹መቀሌ አስተማሪ ነኝ፡፡››

‹‹እርስዎስ?››

‹‹እኔም አርባምንጭ አስተማሪ ነበርኩ፡፡ አሁን እንኳ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን ክፍት የስራ ቦታ ወጥቶ እዛ ገብቻለሁ፡፡ በቲቪ አይተኸኝ አታውቅም?

‹‹ኸረ እኔ ቲቪ አላይም...››

‹‹እውነትህን ነው?››

‹‹ምን አስዋሸኝ፡፡ ረዥም ጊዜ ነው ቲቪ ካየሁ....እና ....አዲሱ ስራ አሪፍ ነው? ወደዱት?››

‹‹ምንም አይልም፣ ትንሽ ስራ ይበዛዋል፡፡ እንደ ዩኒቨርሲቲ ነጻነት የለውም፡፡ በጌታ ፍቃድ እወጠዋለሁ ብያለሁ››

‹‹መበርታት ነው እንግዲህ›› አልኳቸው፡፡

‹‹እኔ ምልህ ቤቱ በስንት ዓመት የሚደርሰን ይመስልሀል?››

‹‹ቶሎ የሚደርስ እንኳ አይመስለኝም፡፡ ግን ከዚህ በፊት ኮንዶሚንየም ሳልመዘገብ ስላመለጠኝ በድጋሚ እንዳልጸጸት ብዬ ነው የምምዘገበው››

‹‹እሱስ እውነትህን ነው፡፡ እኔ ምልህ! አራት ኪሎ አካባቢ ኮንዶሚንየም ኪራይ ይገኛል እንዴ ? ከስራዬ ጋር እዚያ አካባቢ ባገኝ ይቀርበኝ ነበር››

‹‹አራት ኪሎ ቱሪስት ጀርባ ኮንዶሚንየሞች አሉ መሰለኝ፡፡››

‹‹ስንት ይሆናል?››

‹‹ባለ ሁለት መኝታ እስከ 4ሺህ 500 አይሆንም ብለው ነው?››

‹‹በእየሱስ ስም!›› ደሞዜ ራሱ 6ሺ አይሞላም እኮ፡፡ ምን በልቼ ልኖር ነው?››

እንደምንም ማብቃቃት ነው እንግዲህ፡፡ ወይም ለምን ቀበና አካባቢ አይከራዩም፤ ዋጋ ረከስ ይላል፡፡ ለአራት ኪሎም ቅርብ ነው፡፡

‹‹እውነትህን ነው...ቀበና ጥሩ ሳይሆን አይቀርም፣ ባለ አራት መኝታ እዚያ አካባቢ ስንት አገኛለሁ?››
ከት ብዬ ሳቅሁ፡፡ ‹‹ባለ አራት መኝታ የሚባል ኮንዶሚንየም የለም፡፡ እየቀለዱ ነው አይደል?››

ኖኖ! እንዴት በዚህ ዘመን እቀልዳለሁ፡፡ ለምንድነው የሌለው?

‹‹አልተሰራማ!›› አልኳቸው፡፡

‹‹ለምን አልተሰራም?››

‹‹እኔ ምን አውቄ! አራት ኪሎ ነው የምሰራው አላሉም እንዴ! እርሶ ይንገሩኝ እንጂ፡፡››

‹‹አንተ ደሞ! ገና ስራ መጀመሬ ነው አልኩህ እኮ! ሶስት ሳምንትም አልሞላኝ፡፡››

‹‹ሁለት መኝታ ታዲያ ጥሩ እኮ ነው፣ አይበቃዎትም?፡፡››

ሶስት ሴት ልጆች አሉኝ፣ በሁለት መኝታ እንዴት ተኩኖ ይኖራል?

‹‹ያው ማብቃቃት ነው!››አልኳቸው፡፡

‹‹እኔ ምልህ!?ይሄ ሁሉ ግን ቤት የሌለው ነው?›› ነው እያጋነኑ ነው? እንዲህ ከሆነማ ቤት የሌለውን ከሚመዘገቡ ቤት ያላቸውን ቢመዘግቡ ለአሰራር ይመች ነበር፤ አይመስልህም?፡፡››

‹‹ትክክል ብለዋል!››

‹‹በዚህ ወረፋ ከሰዓትም የሚደርሰኝ አይመስለኝም!›› 4ኪሎ ደርሼ ብመለስ ይሻላል፡፡

‹‹ይቅርብዎ!ታክሲ አያገኙም፡፡ እዚሁ ተሰልፈው ቢጠብቁ ነው የሚሻልዎት››

‹‹አይ...የሚያደርሰኝ መኪና አለ›› ነጫጭ 3 ኮብራዎችን ከርቀት አሳዩኝ፡፡ ሌሎች ሶስት ጥቁር መነጽር ያደረጉ ወጠምሻዎች መኪናዎቹ ዙርያ ፈንጠርጠር ብለው ቆመዋል፡፡ ወደኔ እያዩ ገለማመጡኝ፡፡

‹‹ምንድናቸው እነዚያ››

‹‹ጠባቂዎቼ ናቸው››

‹‹ከምንድነው የሚጠብቅዎት?››

ፈገግ አሉ! ለመጀመርያ ጊዜ ፍንጭት መሆናቸውን አየሁ፡፡

Thursday 1 November 2012

የማሌዥያ ኩባንያ እርሻ በሱርማ ማኅበረሰብ ተጠቃ

 
በደቡብ ክልል ቤንች ማጂ ዞን የፓልም ዘይት ለማምረት 31 ሺሕ ሔክታር መሬት የወሰደው የማሌዥያ ኩባንያ በሱርማ ማኅበረሰብ በተደጋጋሚ በሚደርስበት ጥቃት ሥራውን በአግባቡ መሥራት እንዳልቻለ ተገለጸ፡፡ ለኩባንያው የተሰጠው የሳር መሬት ሲሆን ከብት አርቢ የሆነው የሱርማ ማኅበረሰብ ቦታውን ለግጦሽ ይጠቀምበታል፡፡

የፌዴራል መንግሥት ከደቡብ ክልል መንግሥት ጋር በመቀናጀት የሱርማን ማኅበረሰብ ከአርብቶ አደርነት ወደ አርሶ አደርነት ወይም ወደከፊል አርሶ አደርነት መቀየር የሚያስችል ዕቅድ አውጥቷል፡፡

ይህንን ዕቅዱን ለማስፈጸም 17 ሺሕ ቤቶችን ገንብቶ ለሱርማ ማኅበረሰብ አካላት ለማከፋፈል የሚያስችለውን ሥራ መጀመሩን የቤንች ማጂ ዞን የኢንቨስትመንት ማስፋፋት የሥራ ሒደት ባለቤት አቶ በላይ አበበ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ አንድ የሱርማ አርብቶ አደር ከ600 በላይ ከብቶች ይኖሩታል፡፡ እነዚህን ከብቶች ይዞ ውኃና ሳር ወዳለበት አካባቢ እንደ ወቅቱ ሁኔታ ይዘዋወራል፡፡

ለማሌዥያው ሊምሲዩጃን ኩባንያ የተሰጠው መሬት የሱርማ ማኅበረሰብ ለግጦሽ የሚጠቀምበት የሳር መሬት ነው፡፡

ሊምሲዩጃን ያካሄዳቸው የእርሻ ሥራዎች በማኅበረሰቡ ተደጋጋሚ ጥቃት እየተሰነዘረባቸው ነው፡፡ ባለፈው ረቡዕ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በሰበሰቡት የኢንቨስተሮች ስብሰባ የኩባንያው ተወካይ ይህንኑ አረጋግጠዋል፡፡

ተወካዩ እንዳሉት፣ የሱርማ አርብቶ አደሮች የሚያካሂዱትን ልማት በተደጋጋሚ አጥቅተዋል፡፡ ችግሩም ከበድ ያለ በመሆኑ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ መፍትሔ እንደሚፈልጉ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

አቶ ኃይለ ማርያም ለኩባንያው በሰጡት አስተያየት፣ የሱርማ ማኅበረሰብ ጥቃቱን ያደረሰው ኩባንያው የሚያካሂደው ሥራ እንደሚጠቅመው ግንዛቤ እንዲጨብጥ ባለመደረጉ ነው፡፡ ግንዛቤ እንዲጨብጥ ቢደረግ ከማንም በበለጠ ፕሮጀክቱን ይደግፋል ሲሉ አቶ ኃይለ ማርያም በአንድ ወቅት በአካባቢው ያጋጠማቸውን በመጥቀስ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የማሌዥያው ኩባንያ ከሁለት ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ ለፓልም ዘይት ልማት የጠየቀው 100 ሺሕ ሔክታር መሬት ነበር፡፡

ኩባንያው በዚህ መሬት ላይ የፓልም ዛፎችን በመትከል የምግብ ዘይት የማምረት ዕቅድ ይዟል፡፡ ነገር ግን መንግሥት የጠየቀውን መሬት በአንድ ጊዜ አላቀረበለትም፡፡ ምክንያቱም እንደ ሥራው አፈጻጸም እየታየ የጠየቀው መሬት ሊሰጠው ይገባል ከሚል አስተሳሰብ መሆኑን አቶ በላይ ገልጸዋል፡፡

ኩባንያው በአሁኑ ወቅት 31,299 ሔክታር መሬት ተሰጥቶታል፡፡ ይህንን ፕሮጀክት ለማካሄድ 3.72 ቢሊዮን ብር ካፒታል አስመዝግቧል፡፡