Monday 29 April 2013

በአባይ ግድብ ቦንድ ማሰባሰቢያ ሽያጭ ስም አምባሳደሯ የኢትዮጵያን ህዝብ ሃብትና ጊዜ አያባከኑ ነው


በአባይ ግድብ ቦንድ ማሰባሰቢያ ሽያጭ ስም የኢትዮጵያን ህዝብ ሃብትና ጊዜ አያባከኑ ነው በኖርዌይ ስታቫንገር ላይ April 20. 2013 ለማደረግ ታስቦ የነበረው የቦንድ ሽያጭ በገጠመው ከፍተኛ ተቃውሞ አለመደረጉ የሚታወስ  በኦስሎም ይህን መልዕክት

Hei Den Etiopiske ambassade i Stockholm inviterer alle til informasjon møte søndag 28. April ki.15:00 adr: Schweigaards gate 14 i Oslo Galleri, hovedtema Grand Abay Dam her må vi vise vår moralsk plikt ved å kjøpe bond det vi klarer. Det blir også diverse viktig informasjon og forklaring hvordan vi benytter vår fordeler som diaspora. Vennligst videre send informasjon til venner.

ለኢትዮጵያውያን ላኩ እኛም በተደረገልን ጥሪ መሰረት ጥሪውን አክብረን በሰዓቱ በቦታው ከአምባሳደራችን ጋር  በሃገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ለመወያየት ተገኝተን ነበር በኋላ ዝግጅቱ እንደተሰረዘ እና ወደ ራዲስ ሆቴል መዛውሩን ይህን መልዕክት

Hei Vi er flyttet dagens program til et trygg og trivelig sted Radisson Blu Hotel Adr. Holberg gate 30. bak slottet, trikk 11, 17, 18 var presis kl.15:00 alle deltagere må ha gyldig legitimasjon og forhånd melde plikt på tlf 00000 Vi har kun en felles nasjonal interesse som er å bekjempe fattigdom ved kjøp av Millennium dam bond, ellers ingen politiske motiv.
Velkommen

ላኩ  እኛም Radisson Blu Hotel ስንደርስ አትገቡም ተባልን  እኝም ኢትዮጵያዊያን ያልታደምንበት ስብስባ  ሳይደረግ  ሊቋጥ ችሎአል እነሱም አሁን ኢትዮጵያ ሃገራችን ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ለእኛ ማሳወቅ ግዴታ አለባቸው እኛም ሰለ ሃገራችን የማወቅ የመወያየት መብት አለን  አምባሳደሯ ከነተከታዮቿ የኢትዮጵያን ህዝብ ገንዘብ እና ጊዜ እያባከኑ የኢትዮጵያን ህዝብ ለዘመናት ያልተመለሱ ጥያቄዎች ሽሽት ህዝብ በረሃብ እያለቀ ከአንዱ አዳራሽ ወደ ሌላ ከሆቴል ሆቴል ያማርጡበታል  የአባይ ቦንድ ለመሽጥ  ነው ወይስ ለመዝናናት ነው የመጡት ህዝብን መናቅ የህዝብን ጥያቄ አለመመለስ በህግ ያስጠይቃል:: 

Thursday 25 April 2013

ወያኔ የከሸፈዉን ቦንድ ሽያጭ የተሳካ ገቢ ማሰባሰቢያ በኖርዌይ ስታቫንገር አድረኩ አለ

በኖርዌይ ስታቫንገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል 75 ሺ የኖርዌይ ክሮነር /ሩብ ሚሊዮን ብር/  ቦንድ መግዛታቸውን በስቶክሆልም የኢፌዲሪ ቆ/ጀ/ፅ/ቤት አስታወቀ ፅህፈት ቤቱ እንደገለፀው በኖርዌይ ስታቫንገር የሚኖሩ  ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያ በተለያየ ሽፋን የተሰባሰቡ ፀረ ሰላምና ፀረ ልማት ሃይሎች ያቀነባበሩት የተቃውሞ ሰልፍ ሳይገድባቸው ለህዳሴው ግድብ ግንባታ የሚውል ቦንድ በመግዛት ለአገራቸው ልማት ያላቸውን ቁርጠኝነት በተግባር አስመስክረዋል ብሏል፡፡ 


http://www.ertagov.com/amharic/index.php/component/k2/item/586
http://ethiowomen.blogspot.no/2013/04/tigray-cadres-meeting-disrupted-in.html

http://ethiowomen.blogspot.no/2013/04/blog-post_20.html




Sunday 21 April 2013

Tigray Cadres meeting disrupted in Norway

የኢትዮጵያዉያን ድምጽ ይሰማ
አባይን ከመገደብ ሰብዕዊ መብትጥሰት ይገደብ
በዘር በሃይማኖት በፖለቲካ ለጨፈጨፉችኋቸዉ ወገኖቻችን የህሊና ጸሎት እናድርግ  
ኢትዮጵያ ህዝብ ለዘመናት ያልተመለሱለትን ጥያቄዎች መልሱልን
ስለታሰሩትና ስለተፈናቀሉት ወገኖቻችን  ጥያቄ አለን  
አባይ ሃገራችን ነው አብረን እናለማለን  

Saturday 20 April 2013

አምባሳደር መብራት በየነ ከኖርዌይ ተባረረች

ኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ከተለያዮ የኖርዌይ ከተሞች ስታቫንገር ላይ ተሰባሰበው  የአባይን ቦንድ ለመሽጥ የመጡትን   ወያኔዎች አባረሩ የአባይን ቦንድ ለመሽጥ የመጣችው አምባሳደር መብራት በየነ ንግግር ስትጀምር ``የኢትዮጵያዉያን ድምጽ ይሰማ```` አባይን ከመገደብ ሰብዕዊ መብት ጥሰት ይገደብ`` በማለት የተለያዩ መፈክሮች በማሰማት ነዉ  ስብሰባዉ የተጀመረዉ በቅድሚያ ስልጣን ከያዛችሁ ጀምሮ በዘር በሃይማኖት በፖለቲካ ለጨፈጨፉችኋቸዉ ወገኖቻችን የህሊና ጸሎት እናድርግ  የኢትዮጵያ ህዝብ ለዘመናት ያልተመለሱለትን ጥያቄዎች መልሱልን ስለታሰሩትና ስለተፈናቀሉት ወገኖቻችን  ጥያቄ አለን  አባይ ሃገራችን ነው አብረን እናለማለን  በማለት ነበር አቋማቸውን ያስታወቁት   ውጥረቱም ተበብሶ አምባሳደሯ  በጸጥታ ሃይሎች እርዳታ አዳ ራሹ   ውርደቷን ተከናንባ ከነጀሌዎቿ  በፖሊስ ሃይል  አፍረው ተመልሰዋል ኢትዮጵያውያኑም የወያኔን ባንዲራ በኢትዮጵያ ባንዲራ ቀየረው በሃገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ተወያይተው   ለተፈናቀሉት ወገኖቻችንም የገቢ ማሰባሰቢያ አድርገው ሰብሰባቸውን አጠናቀዋል








http://www.aftenbladet.no/nyheter/lokalt/stavanger/Politiet-stoppet-mote-i-Tasta-bydelshus-3162548.html#.UXLv17WBrpe










Dr.Berhanu Nega message To All Ethiopian people


Thursday 18 April 2013

በኖርዌይ ታላቅ የታቃውሞ ሰልፍ ተደረገ

April 18/04/13
በኖርዌይ ታላቅ የታቃውሞ ሰልፍ ተደረገ በሃገሪቱ ስቱርቱንጌት ፓርላማ ፊትለፊት በተደረገው ሰልፍ ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል ሰልፉን ያስተባበሩት በኖርዌይ የሚገኙ  ኢትዮጵያውያን  በመተባበር ሲሆኑ በወገኖቻችን ላይ እየደረስ ያለውን መፈናቀል  አንደነት በመሆን በከፍተኛ ድምጽ የተለያዩ መፈክሮችም በማሰማት ተቃውሞቸውን ገልጸዋል  ከኢትዮጵያ ማህበረሰብ  ወክለው ከዲሞክራቲክ ለለውጥ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ዳዊት መኮንን እና  / ሙሉአደም ከዲሞክራቲክ ለለውጥ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት ሴቶች እና ወጣቶች ክፍል ከኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ / ሃብታሙ ከሙስሊሙ ማህበረሰብ የኢትዮጵያ ህዝብ እየደረሰበት ያለዉን ስቃይ እና ፍትህ ማጣት በንግግራቻው ገልጸዋል



አቶ ደምስ ለኖርዌይ የፓርላማ ተውካይ  ደብዳቤ ሲሰጡ






ሰልፉ በከፊል









Tuesday 16 April 2013

Ethiopian journalist Reeyot Alemu wins 2013 UNESCO-Guillermo Cano World Press Freedom Prize


Imprisoned Ethiopian journalist Reeyot Alemu is the winner of the 2013 UNESCO-Guillermo Cano World Press Freedom Prize. Ms Alemu was recommended by an independent international jury of media professionals in recognition of her “exceptional courage, resistance and commitment to freedom of expression.”


IWMF Ethiopian jorurnalist Reeyot Alemu win 2013 UNESCO-Guillerm Cano World Press Freedom Prize

The Jury took note of Reeyot Alemu’s contribution to numerous and independent publications. She wrote critically about political and social issues, focusing on the root causes of poverty, and gender equality. She worked for several independent media. In 2010 she founded her own publishing house and a monthly magazine called Change, both of which were subsequently closed. In June 2011, while working as a regular columnist for Feteh, a national weekly newspaper, Ms Alemu was arrested. She is currently serving a five year  sentence in Kality prison.
The UNESCO Guillermo Cano World Press Freedom Prize was created in 1997 by UNESCO’s Executive Board. It is awarded annually during the celebration of World Press Freedom Day on 3 May, which will take place this year in Costa Rica.
The Prize honours the work of an individual or an organization which has made a notable contribution to the defence and /or promotion of freedom of expression anywhere in the world, especially if risks have been involved. Candidates are proposed by UNESCO Member States, and regional or international organizations active in the fields of journalism and freedom of expression.Laureates are chosen by a jury whose members are appointed for a once renewable three-year term by the Director-General of UNESCO.

Monday 15 April 2013

አንቀጽ 32 ለማን ነው የሚሰራው

ከሞቀ ጎጆአቸዉ አለ አግባብ ለተፈናቀሉት ለህፃናት ለአራሶች ለእናቶች ለአቅመ ደካሞች ጭዉ ያለ ሜዳ ላይ ለተበተኑት ወገኖቻችን እንድረስላቸው 








Sunday 14 April 2013

ጋዜጠኛ እና መምህርት ርዕዮት አለሙ በዝግ ታስራ ህክምና ተከልክላ በጡት ካንሰር እየተሰቃየች ነው

በሽብር ተግባር ተፈርዶባት በእስር ላይ የምትገኘው ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ በማረሚያ ቤት ከሰዎች ጋር እንዳትገናኝ ለብቻዋ በዝግ ከታሰረች በኋላ፣ በከፍተኛ የጤና መታወክ ውስጥ መሆኗንና ይህም ለሕይወቷ አስጊ መሆኑን የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ በመባል የሚታወቀው ሲፒጄ የተሰኘው ዓለም አቀፍ ተቋም ለፍትሕ ሚኒስትሩ በላከው ደብዳቤ አሳሰበ፡፡
“ይህንን ደብዳቤ የምንጽፈው እ.ኤ.አ. በሰኔ 2011 በሽብር ተግባር ተፈርዶባት በእስር ላይ የምትገኘው ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ዝግ በሆነ አንድ ክፍል ውስጥ ከሰው እንዳትገናኝ በማረሚያ ቤቱ ከተደረገ በኋላ፣ የገጠማትን የጤና መታወክ ወደ እርሶ በማድረስ ትኩረት እንዲሰጣት ለማድረግ ነው፤” ይላል ሲፒጄ ለፍትሕ ሚኒስትሩ አቶ ብርሃን ኃይሉ በቀጥታ የላከውና በድረ ገጹ ላይ ያስቀመጠው ደብዳቤ፡፡ 


የጋዜጠኛዋ የቅርብ ሰዎች ለዓለም አቀፍ የሴቶች የሚዲያ ፋውንዴሽን  ርዕዮት ለሁለት ወራት በአንድ ክፍል ውስጥ ለብቻዋ ተዘግቶባት እንድትታሰር መደረጓን መግለጻቸውን ኮሚቴው በደብዳቤው አስረድቶ፣ እሱም በገለልተኛ አካላት ማጣራቱን አስታውቋል፡፡ 

ይህንን መረጃ በመንተራስ ገለልተኛ አካላት ሁኔታውን እንዲያጣሩ ማድረጉን የሚገልጸው ሲፒጄ፣ በዚህም እውነትነቱን እንዳረጋገጠ ለሚኒስትሩ በደብዳቤው አሳውቋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ርዕዮት የጡት ካንሰር ሕክምና የሚያስፈልጋት መሆኑ በተደረገላት ምርመራ በግልጽ የሚታወቅ ቢሆንም፣ ማረሚያ ቤት ከገባች ወዲህ የሕክምና ባለሙያ እንዳያያት መደረጉን ማረጋገጡንም በደብዳቤው ገልጿል፡፡

“ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶችን ለማክበርና ዲሞክራስያዊ ሥርዓትን ለመገንባት የገባችውን ቃል ጋዜጠኛ ርዕዮት ላለችበት ችግር መፍትሔ በመስጠት እንድታሟላ በጥብቅ እንጠይቅዎታለን፤” በማለት የሲፒጄ ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር ጆኤል ሲመን ለአቶ ብርሃን ኃይሉ የላኩት ደብዳቤ ያስረዳል፡፡ 

ርዕዮት ቀደም ሲል የተዘጋው የፍትሕ ጋዜጣ ዓምደኛ የነበረችና በውጭ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ሪቪው ድረ ገጽ ከአገር ውስጥ ትዘግብ የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ይህ ድረ ገጽ መንግሥት በሽብር የፈረጃቸው ግለሰብ የሚመሩትና ጋዜጠኛዋም መረጃዎችን ለግለሰቡ በመላክና ለዚህ ተግባሯም ገንዘብ በመቀበል ተጠርጥራ በሽብር ድርጊት በመከሰሷ፣ 14 ዓመት የተፈረደባት ሲሆን፣ በይግባኝ ባደረገችው ክርክር ወደ አምስት ዓመት ዝቅ እንዲልላት መወሰኑ ይታወሳል፡፡ 

Saturday 13 April 2013

Ethiopia Threatens Journalist With Solitary Confinement

April 10, 2013
His Excellency Berhan Hailu

Minister of Justice
P.O. Box 1370
Addis Ababa
Ethiopia

Via facsimile: +251-11-517-755


Dear Minister Birhan Hailu,
We are writing to bring to your attention the case of Ethiopian journalist and teacher Reeyot Alemu, whose health has deteriorated since her imprisonment in June 2011 on terrorism charges and who is now being threatened with solitary confinement. The Ethiopian Ministry of Justice has publicly subscribed to a vision in which "human and democratic rights are respected," yet Reeyot's full human rights are being denied to her in Kality Prison.
The Ethiopian High Court sentenced Reeyot, a columnist for the now-defunct independent weekly Feteh, to 14 years in prison on January 2012 under the country'santi-terrorism law. In August 2012, the Supreme Court acquitted her on two counts, but upheld the charge against her of participation in the promotion or communication of a terrorist act, and reduced her sentence to five years.
Prison authorities have threatened Reeyot with solitary confinement for two months as punishment for alleged bad behavior toward them and threatening to publicize human rights violations by prison guards, according to sources close to the journalist who spoke to the International Women's Media Foundation on condition of anonymity. CPJ has independently verified the information. Reeyot has also been denied access to adequate medical treatment after she was diagnosed with a tumor in her breast, the sources said.
We would like to draw your attention to the 2011 report by Juan E. Méndez, the United Nations special rapporteur on torture, in which he urged the prohibition of "the imposition of solitary confinement as punishment--either as part of a judicially imposed sentence or a disciplinary measure." We would also remind you that Ethiopia is a signatory to the United Nations Convention against Torture and Other Cruel, Inhuman or Degrading Treatment or Punishment and is legally bound to uphold these principles.
As a current member of the United Nations Human Rights Council and a signatory to the African Charter on Human and People's Rights and the International Covenant on Civil and Political Rights, Ethiopia has committed itself to upholding the human rights of all of its citizens. This includes the right to freedom of expression and speech, as well as protection from cruel and inhumane forms of punishment such as solitary confinement.
All of the charges against Reeyot were based on her journalistic activities--emails she had received from pro-opposition discussion groups and reports and photographs she had sent to opposition news sites. Reeyot, who received the International Women's Media Foundation Courage in Journalism Award in 2012, has covered key developmental issues in Ethiopia such as poverty, democratic opposition, and gender equality.
The prison sentence against Reeyot for performing her duties and exercising her rights as a journalist to ask questions and express opinions calls into question Ethiopia's commitment to the democratic values and human rights the country claims to uphold.
We urge you to fulfill Ethiopia's promise to build a humane and democratic state by withdrawing the threat of solitary confinement against Reeyot and ensuring her access to adequate medical care. No journalists should face detention or imprisonment in the exercise of their duty.
Yours sincerely,
Joel Simon

Executive Director



የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች ተመፅዋች ሆኑ


“ከእነ ቤተሠቤ እዚህ ለመድረስ ያየሁትን ፈተና ፈጣሪ ያውቀዋል፡፡ ቤተሰቤ ከቁጥር ሳይጐድል ለአገሬ መሬት በቅቻለሁና ከእንግዲህ የፈለገው ይሁን” አሉኝ፤ ከቤኒሻንጉል ክልል ያሶ ወረዳ ተፈናቅለው በፍኖተ ሰላም ድንጋያማ መጠለያ ውስጥ ያገኘኋቸው አዛውንት፡፡ በአማራ ክልል የከሠላ ወረዳ ተወላጅ የኾኑት አዛውንት፤ ኑሮ አልቃና ቢላቸው በ1997 ዓ.ም ሦስት ልጆቻቸውን ከትዳር አጋራቸው ጋር ይዘው፣የትውልድ ቀያቸውን ለቀው የተሻለ ሥራ ይገኝበታል ወደ ተባሉበት ቤንሻንጉል ክልል ያቀናሉ፡፡ ኑሮአቸውንም በቤኒሻንጉል ክልል ካደረጉ በኋላ ተጨማሪ አራት ልጆችን አፍርተው የቤተሠባቸውን ቁጥር ወደ ዘጠኝ ከፍ ያደርጋሉ፡፡ ላለፉት ስምንት ዓመታት ቀን ከሌት እየሠሩም ኑሮአቸውን መምራት ይቀጥላሉ፡፡ ለዓመታት ከኖሩበት መንደር በድንገት እንዲለቁ ሲገደዱ ግራ የተጋቡት አዛውንት የስምንት ልጆች አባት በመኾናቸው ሲፈናቀሉ ከፍተኛ ውጣ ውስጥ ከተታቸው፡፡ በቀላሉ የሚሳካላቸው አልኾነም፡፡

‹‹ ከያሶ ወረዳ ውጡ ተብለን ድብደባና እንግልት ሲደርስብን እንደ ሌሎቹ እመር ብዬ መሸሽ አልኾን አለኝ፡፡ ልጆቼንና ባለቤቴን እንዴት ላድርጋቸው? ከአንድ ቤት ዘጠኝ ሰው የትስ ነው መውደቂያችን? ስል ጭንቀት ገባኝ›› የአዛውንቱ ዐይኖች እንባ አቀረሩ፡፡ አሁን አዛውንቱ ብዙ ስቃይ አልፈው በአማራ ክልል ፍኖተ ሰላም ከተማ ከሌሎች 3500 ተፈናቃዮች ጋር ከእነ ቤተሠባቸው በችግር ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በሚኖሩበት አካባቢ የእርሻ ቦታ ባለማግኘታቸው የተሻለ ሥራ ፍለጋ ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ኑሮአቸውን ከአማራ ክልል ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያዛወሩ የአማራ ተወላጆች ካለፉት ሦስት ሣምንታት ጀምሮ በወረዳው ባለሥልጣናትና ፖሊሶች ከቀያቸው ተፈናቅለው በምስራቅ ጎጃም በጀቢጠናን ወረዳ ፍኖተ ሰላም ከተማ በሚገኝ መጠለያ ውስጥ እንደሚገኙ በደረሰን ጥቆማ መሰረት ወደዚያው አመራን፡፡ ከመጠለያው ወዲህ ከንፈሯ ክው ብሎ ደርቋል በጥቁር መናኛ ሻሽ እራሷን ጠፍንጋ አስራዋለች፡፡

Thursday 11 April 2013

ESAT Yesamintu Engida Interview With Photo Journalist Benyam Mengesha Part II March 2013 Ethiopia


የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር የመለስ ምስል ነው እንዴ?

የአቶ መለስ ዜናዊን ስምና ምስል መጠቀም የሚከለክልና የሚፈቅድ መመርያ ሊወጣ ነው
የአቶ መለስ ዜናዊን ስም፣ ምስልና ሥራዎቻቸውን በተለያዩ ሁኔታዎችና ጊዜያት መጠቀምን የሚከለክልና የሚፈቅድ የመመርያ ረቂቅ ቀረበ፡፡
የመመሪያው ረቂቅ ሊቀርብ የቻለው የመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን በአዋጅ ቁጥር 781/2005 አንቀጽ ዘጠኝ ንዑስ አንቀጽ ሁለት (ሰ) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት መሆኑን ረቂቁ ይገልጻል፡፡ 


የአቶ መለስ ማንኛውም ከመንግሥትና ከፓርቲ ሥራዎች ጋር ያልተያያዙ ምስሎች ወይም ፎቶግራፎች ባለቤትነት የቤተሰቦቻቸው መሆኑን የሚገልጸው ረቂቅ መመርያው፣ ማንኛውም ሰው ገንዘብ ለማሰባሰብ፣ ለሽያጭ፣ ለባዛር፣ ለጨረታ ወይም ለማንኛውም ዓይነት ጥቅም ማስገኛነት ሊሰቅል፣ ሊለጥፍ፣ ሊቀርጽ ወይም ሊያስቀምጥ እንደማይችል ይከለክላል፡፡ 

የአቶ መለስን ፍቅርና ክብር ለመግለጽ የሚፈልጉ ምስላቸውን በመኖሪያ ቤታቸው ግድግዳ ላይ ሊሰቅሉ፣ በአልበም ውስጥ፣ በቦርሳቸው፣ በኪሳቸው፣ በተሽከርካሪያቸው ወይም በሌላ የግል መጠቀሚያቸው ሊይዙ እንደሚችሉ ደግሞ መመርያው ይፈቅዳል፡፡ 

ከፋውንዴሽኑ ቦርድና ከቤተሰቡ በቅድሚያ ፈቃድ በመጠየቅ ስማቸውን ለአርዓያነት፣ ለማስተማሪያነትና ለመታሰቢያነት ማንኛውም ሰው መጠቀም እንደሚችሉ የመመርያው ረቂቅ ያስረዳል፡፡ በተለየ ሁኔታ ለሕዝባዊ ዓላማም ከሆነ ፈቃድ ጠይቆ ገንዘብ ማሰባሰብም እንደሚቻል በረቂቁ ተጠቁሟል፡፡ 

በአቶ መለስ ስም የታተሙም ሆነ ያልታተሙ ሥራዎች ለቤተሰባቸው እንደሚሆኑ የሚገልጸው ረቂቅ መመርያው፣ በመንግሥት ወይም በፓርቲ ኃላፊነታቸው የሠሯቸው ማናቸውም ሥራዎች ባለመብት መንግሥት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብና አባል ድርጅቶች መሆናቸውን ገልጿል፡፡

ለውይይት የቀረበው ረቂቅ መመርያው አራት ምዕራፎችና 19 አንቀጾች ሲኖሩት፣ ቦርዱ ተወይይቶበት እንደሚፀድቅ ተገልጿል፡፡