Sunday 29 September 2013

Teddy Afro chosen for World Cup 2014 Official Singer

In the grand tradition of music for the 2014 FIFA World Cup, Teddy Afro has been chosen to represent the world’s most popular sports competition. Teddy Afro’s Song will be featured as the official song for the 2014 World Cup for Africa.

According to the source from the popular local radio “EthiopikaLink” Teddy afro was selected by Coca Cola to reperesetn Africa for the 2014 FIFA World Cup song. It seems like Teddy Afro took Ethiopia to world cup already.
Teddy Afro’s finished Song and Video Clip that was shot in Kenya will be avaialble world wide very soon.
We at diretube staff like to Congratulate Teddy Afro and his team for this Great Achievement. DireTube will release the Video Clip when it is officially released.

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ለኢትዮጵያውያን፣ ለአባሎቹ እና ለደጋፊዎቹ ያስተላለፈው የምስጋና መልእክት














ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን እንደ ወያኔ ዘመን የተዋረዱበት የተናቁበትና የተበደሉበት ጊዜ የለም። በአሁኑ ወቅት አገሪቱና ህዝቧ ከፊታቸው የተጋረጠው ችግር የመሰረታዊ የዲሞክራሲና የሰብኣዊ መብቶች አለመከበር ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የሕልውና ጥያቄና ኢትዮጵያ እንደ አገር የመቀጠልና ያለመቀጠል ጉዳይ ሆኖዋል። በመሆኑም ዛሬ የነጻነት ታጋዮች ህይወታቸውን በመሰዋት አገራችንን እንደ አገር ለማስቀጠል እና ህዝቧን ነጻ ለማውጣት ቆርጠው ተነስተዋል። 

በመሆኑም በኖርዌይ የምንኖር ኢትዮጵያውያን ይህንን ወቅቱ የሚጠይቀውን ታሪካዊ እና አንጸባራቂ የትግል ድጋፍ ጥያቄ አቅማችን በፈቀደው መንገድ በቁርጠኝነት በመደገፍ ለግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል የድጋፍ ፕሮግራም በዛሬው ለት ማለትም ሰብቴምበር 28፣2013 ከቀኑ 16፣00 እስከ 01፣00 ሰአት በተሳካና፣ ባንጸባረቀ እንዲሁም የነጻነት ሓይሎችን ባኮራ እና አለምን ባስደመመ ታሪካዊ ሁኔታ ተገባዷል።

ለዚህ መሳካት የድጋፍ ድርጅችን ማህበረሰባችን ላሳየው ታሪካዊ እና ወቅታዊ አመርቂ ምላሽ አክብሮቱን እና አድናቆቱን እየገለጸ ለቀጣይም ወቅቱን ለጠበቀ ታሪካዊ አገርን የማዳን እና የደጀንነት ጥሪ የትግሉን ግንባር ቀደም ቦታ በመያዝ አስፈላጊውን መስዋእትነት እንደምንከፍል የተዘጋጀን መሆኑን አስመስክሯል።

በማያያዝም በተደጋጋሚ እዚህ በኖርዌይ ምድር አከርካሪያቸው የተሰበረው የወያኔ ቡችሎች እና ሎሌዎች የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይልን የድጋፍ ፕሮግራም ለማስተጓጎል ያደረጉት ሙከራ በማህበረሰባችን ሙሉ የነቃ ተሳትፎና ክትትል ከንቱ ሊሆን ያቻለ ሲሆን።

በማጠቃለያም ይህንን ከፍተኛ አላፊነት በመሸከም ፕሮግራሙ ለዚህ መሳካት ያበቃችሁ ያአብይ ኮሚቴና የተለያዩ የሰብ ኮሚቴዎች አባላት፣ በተለያየ ቡድን ለስራው መሳካት የተሰለፋችሁ ወገኖች፣ በመላ አለም እንዲሁም በኖርዌይ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን፣ የድርጅታችን አባላቶች እንዲሁም ደጋፊዎች በሙሉ የድጋፍ ድርጅታችን ለናንተ ያለውን አድናቆት እና አክብሮት በምስጋና ይገልጻል። 

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!
የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ
ኖርዌይ፣ ኦስሎ ሰፕቴምበር 29፣ 2013

Sunday 22 September 2013

ለፕሬዚዳንት ግርማ በወር በ530 ሺሕ ብር ቤት ለመከራየት የተፈረመው ውል ፈረሰ

የፕሬዚዳንትነት ቆይታቸውን በማጠናቀቅ ላለፉት 12 ዓመታት የቆዩበትን ብሔራዊ ቤተ መንግሥት ለአዲሱ ፕሬዚዳንት እንደሚያስረክቡ ለሚጠበቁት ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ መኖሪያ እንዲሆን በወር 530 ሺሕ ብር የሚከፈልበት ቤት ለመከራየት የተገባው ውል ተሰረዘ፡፡
ምንጮች እንደገለጹት፣ ፕሬዚዳንት ግርማ በቅርቡ ከቤተ መንግሥት ሲለቁ ከነቤተሰቦቻቸው እስከ ሕይወት ፍፃሜያቸው ይኖሩበታል ተብሎ የተመረጠውና በወር 530 ሺሕ ብር ለመክፈል ከቤቱ ባለቤት ጋር የተደረገው ስምምነት፣ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽሕፈት ቤት ቀርቦ ውል ታስሮበት ነበር፡፡ ሆኖም የኪራይ ስምምነቱ ውል ከተፈረመ ከሁለት ሳምንታት በኋላ የፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት ውሉ እንዲቋረጥ መወሰኑን አስታውቋል፡፡ 
አዲስ አበባ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ውስጥ የሚገኘውን ለፕሬዚዳንት ግርማ መኖሪያ የተመረጠውን ቤት ለመከራየት ከአከራዩ ጋር የኪራይ ውል ስምምነት ያደረገው  የፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት ነበር፡፡ ቀድሞም ቢሆን ስምምነቱ የተጋነነና ለG+1 መኖሪያ ቤት ይህን ያህል ዋጋ ይከፈላል የሚል ሙግት ቀርቦ እንደነበር ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ስምምነቱ በይፋ ከተፈረመ በኋላ ግን የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጭምር ኪራይ ተገቢ አይደለም በማለት ውሳኔ በማስተላለፋቸው፣ የፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት በውሉ ውስጥ የተካተቱትንና ውሉን ለማፍረስ ያስችሉኛል ያላቸውን አንቀጾች በመጥቀስ እንዲሰረዝ አድርጓል፡፡ ይህንንም የመኖሪያ ቤቱን ለማከራየት ውል ለገቡት ባለንብረት በደብዳቤ ማስታወቁንም ምንጮች ገልጸዋል፡፡ የኪራይ ስምምነቱን የመዘገበው የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽሕፈት ቤትም ውሉ መሰረዙን እንዲያውቅ የፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት ደብዳቤ ጽፏል ተብሏል፡፡ 
ሕጋዊ የውል ስምምነት ስለመደረጉ ማረጋገጫ የሰጠውና ምዝገባ ያካሄደው የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽሕፈት ቤት፣ ለፕሬዚዳንቱ መኖሪያ ተብሎ የኪራይ ስምምነት የተደረገበት ውል እንዲሰርዘው በደብዳቤ ተገልፆለታል ተብሏል፡፡ 
ተጋነነ የተባለው የቤት ኪራይ ውል የተፈጸመው በአገሪቱ ሕግ መሠረት ሥልጣናቸውን ለለቀቁት ፕሬዚዳንት ቀሪ ሕይወታቸውን በተሟላ ሁኔታ እንዲያሳልፉ አስፈላጊው ጥቅማ ጥቅም መጠበቅ ስላለበት ቢሆንም በዚህን ያህል ዋጋ ቤት መከራየት ተገቢ አለመሆኑን የሚገልጹም አሉ፡፡ 
እንደ ምንጮች ገለጻ ከሆነ ፕሬዚዳንቱ ከቤተ መንግሥት ሲወጡ ሊኖሩበት የሚችለውን ቤት ለማዘጋጀት የቤተ መንግሥት ጽሕፈት ቤት አምስት የተያዩ ቤቶችን በመምረጥ የተሻለ ነው ተብሎ የተመረጠው አሁን ውሉ እንዲቋረጥበት የተደረገው ቤት ነው ተብሏል፡፡ 
ከኃላፊነት የተነሱት የአገርና የመንግሥት መሪዎች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የምክር ቤት አባላትና ዳኞች የሚያገኙዋቸውን መብቶችና ጥቅሞች ለመወሰን የወጣው አዋጅ እንደሚደነግገውም ለተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ቤት እንደሚዘጋጅ ይጠቅሳል፡፡ 
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 4 መሠረት የመኖሪያ ቤት አገልግሎትን በተመለከተ የተጠቀሰው ከኃላፊነት የተነሳ ፕሬዚዳንት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ወይም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ለራሱና ለቤተሰቡ መኖሪያነት የሚያገለግል የሠራተኞች ደመወዝን ጨምሮ በመንግሥት ወጪ የሚተዳደር ከአራት እስከ አምስት መኝታ ክፍሎች ያሉት መኖሪያ ቤት የሚሰጠው መሆኑን ነው፡፡ 
ከሚሰጣቸው መኖሪያ ቤት ባሻገር ደረጃቸውን የጠበቁ ሦስት ለመጓጓዣ የሚያገለግሉ የመንግሥት ተሽከርካሪዎችም ይመደቡላቸዋል፡፡ ለተሽከርካሪው ሹፌር ደመወዝ፣ የነዳጅና የጥገና እንዲሁም ሌላ ወጪ በመንግሥት የሚሸፈን መሆኑንም ያመለክታል፡፡ 
ከኃላፊነቱ የሚነሱ ሦስት ከፍተኛ ኃላፊዎች በተለያዩ የሕዝባዊ አገልግሎቶች ላይ ከተሰማራ መኖሪያ ቤቱ በሚገኝበት ከተማ የቢሮ አገልግሎት እንደሚሰጠው የሚደነግግ ሲሆን፣ ባለመብቶቹ የሚመርጧቸውና መንግሥት ደመወዛቸውን የሚከፍላቸው አንድ ጸሐፊና አንድ ባለሙያ ጭምር ይኖራቸዋል፡፡ 
በዚሁ አዋጅ ድንጋጌ መሠረት ከኃላፊነት የተነሳ ፕሬዚዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር በሞት ሲለይ ጥቅማ ጥቅሙ ለቤተሰቦቻቸው ይተላለፋል፡፡ በዚሁ መሠረት በሞት ሲለዩ የግል ወጪ አበል ለባለቤቱ መክፈሉ የሚቀጥል ሲሆን፣ የባለመብቱ ባቤትም ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩም የመኖሪያ ቤት፣ የሕክምና ክፍያ የግል ደኅንነት ጥበቃ አገልግሎቶች እንደማይቋረጡበትም ይደነግጋል፡፡ 
ፕሬዚዳንት ግርማ የ12 ዓመታት የፕሬዚዳንት ዘመን መጠናቀቅን ተከትሎ በአዋጁ መሠረት መንግሥት የሚያዘጋጅላቸው ቤት አዲሱ ፕሬዚዳንት ማንነት ይፋ ከመሆኑ በፊት ይዘጋጃል ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡  

Tuesday 17 September 2013

2013 Sakharov Prize for Freedom of Thought - seven nominations

The 2013 Sakharov Prize nominees, presented at a joint meeting of the Foreign Affairs and Development committees and the Human Rights Subcommittee on Monday, are: 



Malala Yousafzai (Pakistan), 
Edward Snowden (USA), 
Reeyot Alemu and Eskinder Nega (Ethiopia), 
Ales Bialatski, Eduard Lobau and Mykola Statkevich (Belarus), 
Mikhail Khodorkovsky (Russia), 
the "Standing Man" protesters (Turkey), and 
the CNN Freedom Project: Ending Modern - Day Slavery (USA).

Reeyot Alemu and Eskinder Nega - nominated by Ana Maria Gomes (S&D, PT) and 40 other MEPs

These Ethiopian journalists are serving prison terms on terrorism charges. Ms Alemu was sentenced in January 2012 after writing columns critical of the government, and Mr Nega was sentenced six months later, after criticizing the prosecution of journalists and dissidents in Ethiopia and writing about how an Arab Spring-like democracy movement might arise there.

Sunday 15 September 2013

WE SIGNED: SAVE REEYOT ALEMU, IMPRISONED INTERNATIONAL AWARD WINNING JOURNALIST


Save Reeyot Alemu, Imprisoned International award winning journalist

The imprisoned Ethiopian journalist Reeyot Alemu ’s life is at risk. Your voice can save her life.  Prison administration is violating her rights to be visited by admirers, friends and family members except her parents.
To protest this gross human right violation she went on to hunger strike as of September 10 2013. Your voice makes a difference and can save her life


http://www.thepetitionsite.com/470/465/253/save-reeyot-alemu-imprisoned-international-award-winning-journalist/?taf_id=9998329&cid=fb_na

Saturday 14 September 2013

ርእዮት አለሙ ምግብ ካቆመች 4ኛ ቀናትን ደፈነች

እውቋ የብእር ሰው፣ የነጻነት ታጋይ፣ የዩኒስኮና የኢንተርናሽናል ውሜንስ  ሚዲያ ፋውንዴሽን አሸናፊ ጸሀፊና መምህርት ርእዮት አለሙ ዛሬም በረሀብ አድማው ገፍታበታለች። እህቷ እስከዳር አለሙ እንደገለጸችው ዛሬ እርሷና የርእዮት እጮኛ የሆነው ስለሺ ሀጎስ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ቢሄዱም እንዳይገቡ ተከልክለዋል።

እጮኛዋ ስለሺ ለሰአታት ታግቶ በማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች መደብደቡንም እስከዳር ተናግራለች  ርእዮት ከእናት፣ አበቷና የንስሀ አባታ በስተቀር ሌላ ሰው እንዳይጠይቃት በመደረጓ የረሀብ አድማውን መጀመሩዋ ይታወቃል። በአለም ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በርእዮት ላይ የሚደርሰውን የመብት አፈና እየተቃወሙ ነው።

Saturday 7 September 2013

አቶ አርከበ ዑቕባይና ወንድሙ አቶ ጌታቸው ዑቕባይ ከነቤተሰቦቻቸው አሜሪካ ገብተዋል

አብርሃ ደስታ ከመቀሌ
አቶ አርከበ ዑቕባይና ወንድሙ አቶ ጌታቸው ዑቕባይ ከነቤተሰቦቻቸው አሜሪካ ገብተዋል። አቶ ጌታቸው በትእምት (በመስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጂነሪንግ በኋም በሴመንት ፋብሪካ) ሓላፊ የነበረና ከወይዘሮ አዜብ መስፍን ተጣልቶ ስራው የለቀቀ ነው።
ወደ ሰሜን አሜሪካ ተጉዘው ከነበሩ የህወሓት አባላት ግማሾቹ ፈርተው አሜሪካ መቅረታቸው ታውቋል። ከነዚህ የጠፉ ባለስልጣናት መካከል የማረት ሐላፊው አቶ ተኽለወይኒ አሰፋ አንዱ መሆኑ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው (የተኽለወይኒ ራሴ አኣላረጋገጥኩም)።
ዓረና ትግራይ ፓርቲ ጉባኤው በደማቅ ሁኔታ እያካሄደ ነው።

አዜብ መስፍን ይታሰራሉ?

"አዜብን ማሰር፣ መለስን ከሞት ቀስቅሶ ለፍርድ ማቆም ነው"

መለስ ዜናዊ ሆን ብለው ለፖለቲካ ሚዛን መጠበቂያ ሲገለገሉበት በነበረው “የሙስና ባህር” ያልተነከረበት የለም። ባህሩ ውስጥ ያልዋኘ የለም። ከባህሩ ራሳቸውን ያገለሉ ጥቂቶች ቢኖሩም ወ/ሮ አዜብ መስፍን ግን የባህሩ ዋናው አጥማቂና የውሃው ባለቤት እንደሆኑ በርካታ ምስክሮች አሉ።
አቶ መለስ “ውርሳቸውን/ሌጋሲያቸውን” ትተው ካለፉ በኋላ አገሩን አከርፍቶት የነበረው የሙስና ባህር በስንጥር መነካካት ተጀመረና አሁን ቁንጮዎቹ ግድም ደርሶ እያሸበረ ነው። ይህንኑ የሙስና ማዕበል ተከትሎ የባለቤታቸውን ውርስ ታኮ ያደረጉት ወ/ሮ አዜብና በተሸናፊው የፖለቲካ መስመር ያሉ ሁሉ ተሸብረዋል። አንዳንድ ጥቆማዎችና የህዝብ አስተያየቶች እንደሚያመለክቱት ወ/ሮ አዜብ ታውከዋል።
ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሃላፊዎችና ከነሱ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉት “ባለሃብቶች” መካከል ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር እንደሚነግዱ የሚታወቁ በቁጥጥር ስር መዋላቸው የስጋታቸው መነሻና እምብርት ስለመሆኑ አብዛኞች ይስማማሉ። ከዚህም በተጨማሪ ያለታክስ በሚገቡ ምርቶች፣ ተሽከርካሪዎች፣ በቴሌ የህገወጥ ማስደወል ወንጀል፣ በጫት ኤክስፖርትና በኮንስትራክሽን ዘርፍ በስፋት ቢዝነስ እንደሚያጫውቱ የሚታወቁት ወ/ሮ አዜብ በገንዘብ የከበሩትን ያህል በርካታ ጠላት እንዳፈሩም የሚቀርቧቸው ይናገራሉ።
ኤፈርትን ለወ/ሮ አዜብ ያስረከቡት አቶ ስብሃት ነጋ በተደጋጋሚ ስለሙስና መናገር የጀመሩት አቶ መለስ አፈር ሳይቀምሱ ነበር። ወ/ሮ አዜብ የባለቤታቸውን ጡንቻና በዘመቻ በጀት ተመድቦለት “ባለራዕይ፣ ታላቁ መሪ” በሚል የተሰጣቸውን የሸቀጥ ስም ተገን አድርገው ሙስና ውስጥ መነከራቸውን የሚያውቁት አቶ ስብሃት ስም አይጥቀሱ እንጂ ነገራቸው ሁሉ ከወ/ሮ አዜብ ደጅ እንደነበር ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የሚናገሩት የአደባባይ ምስጢር ነው።
አቶ ስብሃት ነጋ ከመለስ ሞት በኋላ ይህንኑ አቋማቸውን አጠንክረው የገፉበት ቢሆንም በፖለቲካ አሰላለፋቸው ተሸናፊ በመሆናቸው ለማፈግፈግ ተገደው እንደነበር የሚናገሩ አሉ። ከውስጥ አዋቂዎች እንደሚሰማውና በተባራሪ እንደሚነገረው አቶ ስብሃት ዳግም አሸናፊውን ቡድን ተመልሰው ተቀላቅለዋል። ለዚህም ይመስላል እሳቸው ምን ያህል የጸዱ ስለመሆናቸው መረጃ ባይኖርም አሁን ከተጀመረው የሙስና ዘመቻ ጀርባ እንዳሉበት የሚጠቆመው። አንዳንዶች እንደሚሉት ህወሃት በትከፋፈለ ጊዜ (ዘመነ ህንፍሽፍሽ) አቶ አባይ ጸሐዬ ውህዳኑን ተቀላቅለው መረጃ ከሰበሰቡ በኋላ አቶ መለስን በመቀላቀል የተጫወቱትን የ”መንታ”/ደብል/ ስልት፣ የመለስ ሞትን ተከትሎ ለተነሳው የሃይል ሰልፍ ትንቅንቅ አቶ ስብሃት ነጋም ተጠቅመውበታል። በዚሁ ስልታዊ አካሄድም የእነ ዶ/ር ደብረጽዮን ክንፍ አሸናፊ ሆኖ እንዲወጣ አስችለዋል።

የሙስናው ጉዳይ

ክንፉ አሰፋ

በተንጣለለ ቪላ ውስጥ ከበድ ያሉ እንግዶች “ጸዳ” ባሉ ምግብና መጠጦች እየተስተናገዱ ነው። ታዋቂ ግለሰቦች፤ ባለስልጣናት እና አርቲስቶች የቀረበላቸውን ብፌ በልማታዊ ወጋቸው እያወራረዱ ሳሉ አንድ እንግዳ ነገር በመሃላቸው ተከሰተ።  ሞቅ ባለው የአይቴ ነጋ ገብረእግዚአብሄር ድግስ ላይ ያልተጋበዙ ሁለት ሰዎች ዘው ብለው ከግብዣው ክፍል ገቡ።  የፌዴራል ፖሊስ አባላት ነበሩ።
በዚህ ያልተለመደ ክስተት የአቶ ነጋ እንግዶች አልተደናገጡም ነበር። ይልቁንም  የፌዴራል ፖሊሶቹ ለተጨማሪ ጥበቃ የመጡ ነበር የመሰላቸው። አንድ ብርጌድ ያህል ጦር አስከትለው የመጡት ፖሊሶች ግን አቶ ነጋ ገብረእግዚአብሄርን አስጠሯቸው።  አቶ ነጋም ለጥሪው እንደወትሮው በመወጣጠርና ፍጹም ትእቢት በተሞላበት አነጋገር ምላሽ ሰጡ። በፖሊስ አባላቱ እና በአቶ ነጋ መካከል የሃይለ-ቃል ልውውጥ ተጀመረ። እሰጥ እገባው  አንድ፣ ሁለት እያለ ሄደና በመጨረሻ ተካረረ። በዚህ ሰዓት አቶ ነጋ ስልክ መደዋወል ያዙ። ከፍተኛ የሚባሉ ባለስልጣናትና ምኒስትሮች ጋ ደወሉ።  ከዚያም በመቀጠል፣ ጀነራሎች ጋ ደወሉ… የጦር መኮንኖች፣ የፓርቲ ባለስልጣናት… ሁሉም ጋ ተደወለ። የባለስልጣናቱ ምላሽ ግን ጥሩ እንዳልነበር ከአቶ ነጋ ፊት ላይ ይነበብ ነበር። ወዳጆቻቸው ሁሉ እንደ ቱኒዚያው ቤን አሊ በአንድ ጊዜ ከዷቸው።
“በል – ና – ውጣ!” አለ አንደኛው የፖሊስ አባል፣ የስልኩን ሽርጉድ በጥሞና ከተከታተለ በኋላ።
“ምን ማለትህ ነው? እኔኮ ነጋ ነኝ። ነጋ ታሪኩ!” አሉ። አነጋገራቸው የጀምስ ቦንድን ይመስል ነበር። በዚህ ጊዜ ታዲያ እጃቸውም አላረፈም። ከጎን ያሸጎጡትን መሳርያ ለማውጣትም ዳዳቸው።
በቅጽበት ግን ፌዴራል ፖሊሱ ቀደማቸው። በድንገት “ጯ!” የሚል ድምጽ አዳራሹን አናጋው። የፖሊሱ አይበሉባ የግራ መንጋጭላቸው ላይ ሲያርፍባቸው ጊዜ፤ አይቴ ነጋ ነገር አለሙ ተደበላለቀባቸውና እጅ መስጠትን መረጡ። ግብር ሊያበሉ በጠሯቸው የክብር እንግዶቻቸው ፊት፣ ከዚህ በላይ መዋረድ አልፈቀዱም።   ሁለት እጃቸውንም ወደ ፖሊሱ በመዘርጋት ለብረት ማሰርያው ራሳቸውን አመቻቹ። እጃቸው የኋሊት ከተጠፈረ በኋላም አቶ ነጋ እንዲህ አሉ። “በቃ! ህወሃት አበቃለት!”