በአዳማ ከተማ የጫት መሸጪያ ሱቆች በከፍተኛ ደረጃ እተስፋፉና የቃሚውም ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው ተባለ መኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ ከመለስተኛ አንስቶ እስከ አለም አቀፍ ሆቴሎች ድረስም በዚህ የጫት ማስቃምና የሺሻ ማስጨስ ተግባር ውስጥ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ የከተማው ነዋሪዎች ልጆቻችን በዚህ ችግር ውስጥ እየወደቁ ነው በዚህ ምክንያትም ለጎዳና ተዳዳሪነት የሚዳረጉና የታዳጊ ህፃናት ሴተኛ አዳሪነትም በከተማዋ እየተስፋፋ ነው ይላሉ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጠው በማሳሰብ።በዚህ ችግር ውስጥ የአዳማ ዩንቨርስቲ ተማሪዎችም ግንባር ቀደም ተሳታፊ እየሆኑ መምጣታቸው ጉዳዩን አሳሳቢ አድርጎታል ይህ የጫት አቅርቦት ጉዳይ የአዳማ ዩንቨርስቲን ጨምሮ በከተማው በሚገኙ ኮሌጆችና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አቅራቢያ ጭምር በብዛት ይስተዋላል በአዳማ አብዛኛዎቹ ሆቴሎች ውስጥ መቃሚያ ክፍሎችን በማዘጋጀት ለህገ-ወጥ ገቢ ማግኛ መጠቀም የተለመደ ነው ይባስ ብሎም አንዳንድ የከተማዋ ሆቴሎች ማስታወቂያዎችን ጭምር በመለጠፍ ማስቃሚያ ቦታ እንዳላቸው ያስተዋውቃሉ ቡናውን የሚያፈሉና ሺሻውን ለተጠቃሚዎቹ የሚያቀርቡት ደግሞ ታዳጊ ሴቶች ናቸው በተለይ አርብ ቅዳሜና እሁድ ለዚሁ ተግባር ከአዲስ አበባና ሌሎች የአቅራቢያ ከተሞች ወደ አዳማ የሚገባው ሰው ቁጥርም ከፍተኛ ነው ጉዳዩን አስመልክቶ የአዳማ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አህመድ የሱፍ ችግሩ መኖሩን አምነው ይህም ለከተማዋ ፀጥታ ጭምር አሳሳቢ መሆኑን ያነሳሉ ይህ ጉዳይ ከዚህ በፊት በከተማው አስፋፍቶት የነበረውን ወንጀል በማስታወስ አቶ አህመድ እንደሚሉትና ህብረተሰቡም እንዳነሳው በሆቴል ቤቶች የሚቅሙት የከተማ አስተዳደሩ ሰራተኞችም ጭምር ናቸው በመሆኑም በዚህ ድርጊት ውስጥ የተገኙ ሰራተኞችን ባለፈው ወር ከስራ አግደናል ይላሉ ምክትል ከንቲባው ይህንን ችግር ለመፍታትም ትልልቅ ሆቴሎችን ጨምሮ የተለያዩ ጫት በማስቃም ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ አካላትን ፈቃዳቸውን እስከመሰረዝና ከአዳማ ዩኒቨርስቲ ጋር በጋራ መስራት የሚቻልበትን ሁኔታ ለመጀመር እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ ነው ፡፡
ተጠርጣሪዎቹ የአካዳሚው ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ኃይለየሱስ፣ የአካዳሚው ሱፐርቫይዘር አቶ የኔዓለም ጌታቸው፣ መምህር ዓለማየሁ ገብሬ፣ መምህር ደበበ ጥሩነህ፣ አቶ መልካሙ ቀለብና አቶ ሳምሶን መኩሪያ ሲሆኑ፣ አካዳሚው ካራክተር ሆልማርክ አካዳሚ አክሲዮን ማኅበርም መከሰሱን የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ለሰባተኛ ወንጀል ችሎት ያቀረበው ክስ ያስረዳል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ የ10 እና የ11 ዓመት ዕድሜ ያላቸውን ሁለት ወንድ ሕፃናትን ከጥቅምት ወር መጀመሪያ 2005 ዓ.ም. ጀምሮ በምሳና በዕረፍት ጊዜ ተማሪዎች ከክፍል ሲወጡ፣ ወደ ባዶ ክፍል በመውሰድ በተደጋጋሚ እየተፈራረቁ የግብረሰዶም ድርጊት እንደፈጸሙባቸው ክሱ ያስረዳል፡፡ በተለያዩ ጊዜያት ዳይሬክተሩንና ሱፐርቫይዘሩን ጨምሮ ሌሎቹም መምህራንም በየካቲት ወር ሁለት ቀናት፣ እንዲሁም በሚያዝያ ወር በሕፃናቱ ላይ ድርጊቱን ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረው፣ የሕፃናት ክብር ድፍረት ወንጀል ተካፋይ በመሆን መከሰሳቸውን ክሱ ያብራራል፡፡
ካራክተር ሆልማርክ አካዳሚ አክሲዮን ማኅበር በሥሩ ያሉትን ሠራተኞችና ኃላፊዎች በአግባቡ መቆጣጠርና የሕፃናትን ጤንነትና አካልን በአግባቡ መጠበቅ ሲገባው ባለመፈጸሙ፣ በወንጀል ድርጊቱ ተካፋይነት ተጠርጥሮ መከሰሱን ክሱ ይገልጻል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት ቀርበው ድርጊቱን አለመፈጸማቸውን በመግለጽ የዋስትና መብታቸው እንዲጠበቅላቸው ቢጠይቁም፣ ድርጊቱ ከባድ መሆኑን በመግለጽ ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብታቸውን ውድቅ በማድረግ፣ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ለሰኔ 14 ቀን 2005 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ተጠርጣሪዎቹም በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ አዟል፡፡
http://www.ethiopianreporter.com/index.php/news/item/2189-%E1%88%98%E1%88%9D%E1%88%85%E1%88%AB%E1%8A%95-%E1%89%A0%E1%88%95%E1%8D%83%E1%8A%93%E1%89%B5-%E1%88%8B%E1%8B%AD-%E1%8C%8D%E1%89%A5%E1%88%A8%E1%88%B0%E1%8B%B6%E1%88%9D-%E1%89%A0%E1%88%98%E1%8D%88%E1%8C%B8%E1%88%9D-%E1%8B%88%E1%8A%95%E1%8C%80%E1%88%8D-%E1%89%B0%E1%8C%A0%E1%88%AD%E1%8C%A5%E1%88%A8%E1%8B%8D-%E1%89%B0%E1%8A%A8%E1%88%B0%E1%88%B1
http://www.ethiopianreporter.com/index.php/news/item/2189-%E1%88%98%E1%88%9D%E1%88%85%E1%88%AB%E1%8A%95-%E1%89%A0%E1%88%95%E1%8D%83%E1%8A%93%E1%89%B5-%E1%88%8B%E1%8B%AD-%E1%8C%8D%E1%89%A5%E1%88%A8%E1%88%B0%E1%8B%B6%E1%88%9D-%E1%89%A0%E1%88%98%E1%8D%88%E1%8C%B8%E1%88%9D-%E1%8B%88%E1%8A%95%E1%8C%80%E1%88%8D-%E1%89%B0%E1%8C%A0%E1%88%AD%E1%8C%A5%E1%88%A8%E1%8B%8D-%E1%89%B0%E1%8A%A8%E1%88%B0%E1%88%B1