Thursday, 21 November 2013

ዓለምአቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት በሳኡዲ አረቢያ

ዓለምአቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት በሳኡዲ አረቢያ

Global Alliance for the Rights of Ethiopians in Saudi Arabia


ህዳር 6 ቀን 2006 ዓ.ም.


አስቸኳይ መግለጫ


በቅርቡ፤ በተከታታይና በሚዘገንን ደረጃ በሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚካሄደውን እልቂት ለማስቆም ብሄራዊግብረ ኃይል እአ በ November 12, 2013 በተደረገ አስቸኳይ ስብሰባ ተመሰርቷል። 

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን፤ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለሰብአዊ መብቶች፤ ለሰዎች ክብርና የህይወት ክቡርነትየቆሙ ሁሉ የሳውዺ የጦር፤ የፖሊስ፤ የጥበቃና ሌሎች በመንግሥት የተደራጁ ወጣት ቡድኖች በሰላማዊ ኢትዮጵያዊያን ላይየሚያደርጉት ግድያ፤ አስገድዶ መደፈር፤ ግለሰቦችን በገመድ አንቆ ዛፍ ላይ መስቀል፤ ገረፋ፤ በ21ኛ መቶ ክፍለ ዘመንከሰለጠነ መንግሥት በማይጠበቅ ደረጃ ግለሰቦችን እንደ እንሰሳ አስሮ በመንገድ መጎተት ወዘተ ለህሊና የሚቀፍ ድርጊት እኛም በንፁሕ ኢትዮጵያዊያን ላይ መፈፀሙ አስቆጥቶናል፤ አሳዝኖላን፤ አበሳጭቶናል፤ ቀስቅሶናል፤ ለወገኖቻችን መብት እንድንነሳና ከሚመለከታቸው ጋር አብረን ድምጻችንን እንድናሰማ አስገድዶናል።

በመጀመሪያ ደረጃ የምንጠይቀው፤ የሳውዲ መንግሥት ሃላፊነቱን በመወጣት ይህ አሰቃቂ እልቂት እንዲቆም ማድረግ ነው።ከዚህ ጋር አብረን የምናሳስበው ለሰብእነትና ለሰው ክብር የቆመው የዓለም ህብረተሰብ ሁሉ ይህን አሰቃቂ ድርጊትተቀዳሚነት በመስጠት እንዲቆም ማድረግ የሞራል ሃላፊነት አለበት የሚል ነው። የኢትዮጵያዊያን ህይወት እንደ ማንኛውምሰባዊ ፍጡር ትልቅ ዋጋ ያለው መሆኑን እናሳስባለን። ይህን የተቀደሰ ዓላማ ስኬታማ ለማድረግ የሚከተሉትን ለሰብአዊ መብት፤ ለሰው ክብርና ነጻነት፤ለእውነተኛ እኩልነት የቆሙ ሶስት ግለሰቦች በአሰባሳቢነት መርጠናል፤

1. አቶ አበበ ገላው
2. አቶ ብርሃኑ ዳምጤ (አባ መላ) እና
3. አቶ ታማኝ በየነ

ኢትዮጵያዊያን፤ በተለይ ወጣት ወንዶችና ሴቶች በሳውዲ አረቢያና በሌሎች የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች በገፍየሚሰደዱበትና በሰላም ሰርተው ለመኖር የሚፈልጉበት ምክንያት በአገራቸው የስራ፤ በሰላም የመኖር፤ የራሳቸውን ስራየመፍጠር፤ መብታቸውን የማስከበር እድል ስለሌላቸው ነው። ስለሆነም፤ የሳውዲ አረብያ የጥበቃ፤ ፖሊስና ወጣት አፋኝቡድኖች በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደርጉት ግድያ፤ አፈናና፣ አስገድዶመድፈርና ማሳደድ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ፤ለህሊና የሚቀፍ፤ በተባበሩት መንግሥታት ውሎች የተከለከለ፤ የሰለጠነው ዓለም የማይቀበለው በሰብእነት ላይ የተፈፀመወንጀል ነው። ይህን አሰቃቂ ድርጊት የአይን ምስክሮች፤ የቢቢሲ፤ የአልጀዚራና የግል ታዛቢዎች በቪዲዮ ቀርፀው ለዓለምሕዝብ አሰራጭተውታል። ከዚህ የበለጠ ምስክር ሊኖር አይችልም። የሳውዲ አረቢያ መንግሥት ሆነ ብሎ የሚያደርገው ህገ  ወጥ ድርጊት መሆኑን አንጠራጠርም፤ ስለሆነም፤ ይህን አሰቃቂ ተግባር ማቆም ያለበት የሳውዲ አረቢያ መንግሥት መሆኑን  በጥብቅ እናሳስባለን።

ከላይ እንዳሳየነው፤ ኢትዮጵያዊያን አገራቸውን ለቀው እንዲሰደዱ፤ ሲሰደዱ አሰቃቂና ለህሊና የሚዘገንን ግድያ፤ እስራትናሌላ ኢ-ሰብአዊ ወንጀል የሚፈፀምባቸው ወደው አይደለም። አብዛኛው የኢትዮጵያ ወጣት ትውልድ በአገሩ ህይወቱንናቤተሰቡን የሚደግፍበት ስራ የለውም፤ የኑሮ ዋስትና የለውም። የሕግ የበላይነት ስለሌለ፤ ከሕግ ውጭ የሆነ አፈና፤ ግድያ፤እስራት፤ ኢ-ሰብአዊ ቅጣት፤ የውስጥና የውጭ ስደት፤ መባረር ወዘተ እጣው ሆኗል። ስለዚህ ነው ብዙ ሽህ ኢትዮጵያዊያንብዙ ሽህ ብር ከፍለው ለህይወታቸው አደጋን የሚጋብዝ ጉዞ የሚያደርጉት። አሰቃቂ ሆኖ ያገኘነው፤ ኑሯችንን እናሻሽል ይሆናል ብለው ያደረጉት ተስፋ ወደ ጨለማ መርቶ ለህይወታቸው መጥፊያ፤ ለአካለ ስንኩልነት፤ ለክብራቸው መገፈፊያ ወዘተ ምክንያት መሆኑ ነው። ይህ በሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን የመጣ “የባርነት” ሁኔታ መፈጠሩን ያመለክተናል፤መቆም አለበት የምንለው የእነዚህ ወገኖቻችን መዋረድ የሁላችንም ክብር መገፈፍ መሆኑን ስለምንረዳ ጭምር ነው።

ኢትዮጵያዊያን በያሉበት በመገናኛ ብዙሃን፤ በድህረገጾች፤ በሰላማዊ ሰልፍና በሌሎች መንገዶች የሚያሳዩት ጥረት የሚያኮራጅምር ነው። በዚሁ መሰረት የሳውዲ አረቢያ መንግሥት የሚያደርገውን አሰቃቂ ግፍለዓለም ህብረተሰብ ለማጋለጥ፤ወንጀሉን የፈፀሙ ሁሉ በሃላፊነት ለፍትህ ለማቅረብ የሚደረገው ተግባር በተከታታይና አስተማማኝነት ባለው ደረጃ እንዲካሄድ ቆርጠን ተነስተናል። የተቋቋመው ግብረ ኃይል ዋና ሚና በሳውዲ አረቢያ የሚካሄደውን ወንጀል ለሚመለከታቸው የዓለም ህብረተሰብ የሰብአዊ መብቶች፤ የፍትህ ተቋሞች፤ የለጋሽ ድርጅቶችና ሃላፊዎች ማሳወቅ፤ ቅስቀሳ  ማድረግ፤ የገንዘብና ሌላ ቁሳቁስ ድጋፍ ለወገኖቻችን ለማቅረብ ጥረት ማድራግን ይጨምራል። በዚህም መሰረት፤ ግብረኃይሉ፤ እውቅና፤ ተቀባይነትና አስተማማኝ የሆኑ የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶችን፤ ሊቆችን፤ ጠበቃዎችን ወዘተ፤ በመቅረብና በመቀስቀስ፤ የሳውዲ መንግሥት በሰብአዊነት ላይ ያደረገውንና የሚያደርገውን ወንጀል (Crimes against humanity)ለፍትህ ለማቅረብ የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል። በተጨማሪ፤ በሳውዲ አረቢያ ያለውን ሁኔታ በቀጥታ ለመመራመርናእውነተኛውን ዝርዝር ሁኔታና ስእል ለመገንዘብ አንድ ቡድን ለመላክ አቅዷል።

ይህ የተቀደሰና ሁሉም ኢትዮጵያዊያን፤ የሰው ክብርና መብቶች ደጋፊ የሆኑ ድርጅቶችና ግለሰቦች እንዲሁም መንግሥታትበያሉበት የሚጋሩት አስቸኳይ ጥሪ ፋታ አይሰጥም። ግድያው፤ ገረፋው፤ እስራቱ፤ የሴቶች ክብር ድፍረቱ ወዘተ የሁላችንምስለሆነ ዓለም አቀፍ ጥረት ያስፈልገዋል። ሁላችን ሌሎችን በመቀስቀስ ይህ ግፍ በፍጥነት እንዲቆም በተግባር ማሳየትየሞራል ግዴታችን ነው። ወንጀሉን የፈፀሙት የሳውዲ አረቢያ ባለስልጣናትና ሌሎች ተሳታፊዎች በሃላፊነት ተጠያቂ መሆንአለባቸው።

የሳውዲ መንግሥት ባለስልጣናት የኢትዮጵያዊያንን መብቶች ገፈው፤ ገድለው፤ አዋርደው፤ አሳደው፤ ሰቅለው፤ ክብር ገፈው በኢትዮጵያ ያላቸውን ዘላቂ ጥቅም ለማስከበር እንደማይችሉ ማመን አለባቸው። ይህን ማሳመን መቻል አለብን። የተፈጸመውን አሰቃቂ ግድያ፤ ድፍረትና ሰቆቃ ኢትዮጵያውያንና የዓለም ሕብረተሰብ እንዲያወግዝልን ድርጅታችን ጥሪውን ያቀርባል። በተጨማሪም፤ በኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ አስከፊና ኢሰብአዊ ድርጊት የፈጸሙት ሁሉ ተጠያቂ እንዲሆኑ እናሳስባለን። እንዲሁም፤ በመረጃና ተሞክሮ መጋራት፤ ኢትዮጵያውያንን ከሳውዲዎች ሰቆቃና ግድያ ለማትረፍ ስለሚያስፈልገው እርዳታ ሁሉ ኢትዮጵያውያንና ለሰብአዊ መብት የሚታገሉ ድርጅቶች እንዲተባበሩን ከአደራ ጋር እንጠይቃለን።

ይህን ለማድረግ የምንችለው ለዚህ ዓላማ በያለንበት ስንነሳ፤ አብረን ተባብረን ስንሰራ፤ ለወገኖቻችን መቆማችንን በተግባር  ስናሳይ፤ ዜና፤ ሃሳብ፤ እውቀት፤ ልምድ፤ ስንለዋወጥ፤ የገንዘብ ሆነ ሌላ አስተዋፅኦ ስናደርግ ነው። ይህን በተቀነባበረና ስልት  ባለው መንገድ ከሰራን በወገኖቻችን ላይ የደረሰውንና የሚደርሰውን እልቂት ለማቆም እንችላለን። የወገኖቻችንን ክብር
በመታደግ፤ የራሳችንን ክብር ለማስከበር እንችላለን።
ሁሉም ህይወት እኩል ዋጋ አለው!!!

Contact information:
Telephone: (877)RING-ETHIOPIA or (877)746 -4384
Email address: Alliance4rightsofethiopians.sa@gmail.com

Wednesday, 20 November 2013

አልበርት አነስታይን የኦቲዝም ተጠቂ ነበር…

ፈውስ ያልተገኘለት የጤና ችግር
አልበርት አነስታይን የኦቲዝም ተጠቂ ነበር…
በአገራችን ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ኦቲስቲክ ልጆች አሉ…
የአለማችን እውቁ ሳይንቲስት አልበርት አንስታይን የኦቲዝም ተጠቂ እንደነበር ይነገራል፡፡ በአገራችንም ከአመታት በፊት በድንቅ የሂሣብ ችሎታው ጉድ ያሰኘውና ገና በ16 ዓመቱ፣ በ1984 ዓ.ም ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሂሳብ ፎርሙላውን ያበረከተው እንድሪስ መሀመድ ኦውቲስቲክ ነው፡፡ ወጣቱ በአሁኑ ወቅት እጅግ በሚያሳዝንና በዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ህይወቱን እየገፋ ይገኛል፡፡
መንስኤውና መድሃኒቱ እስከዛሬም ድረስ ሊታወቅ ያልቻለውና በብዙ ተመራማሪዎች ጥናት እየተካሄደበት ያለው የኦቲዝም (የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ችግር) ዛሬ የበርካታ የዓለም ህዝቦች ራስ ምታት ሆኗል፡፡ በአለም ላይ ከ100 ልጆች አንዱ የዚህ ችግር ተጠቂ ሲሆኑ በአሜሪካ ብቻ 1ሚ 500ሺ ኦቲስቶች አሉ፡፡ በኢትዮጵያም ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ኦትስቲክ ልጆች መኖራቸው ይገመታል፡፡

ኦቲዝም የአዕምሮ ዕድገት መዛባት ሲሆን ይህም የአንጐልን የሥራ ሂደት በማወክ በአንጐላችን የሚከናወን የመረጃ አጠቃቀምን ያዛባል፡፡ የኦቲዝምን መንስኤ ለማወቅ ብዙ ጥረት ቢደረግም እስከዛሬ ድረስ ስለ መንስኤውና መፍትሔው በእርግጠኝነት ለመናገር አልተቻለም፡፡ ለችግሩ ቋሚ መፍትሔ ሊገኝ ባለመቻሉም  የችግሩ ተጠቂዎችን በልዩ የትምህርት ዘዴና እንክብካቤ ለውጥ እንዲያመጡ ማድረግ ብቸኛው አማራጭ ሆኗል፡፡

አንዳንድ ጥናቶች ለኦቲዝም መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ ብለው ካስቀመጧቸው ነጥቦች መካከል:-

አካባቢ በመርዛማ ኬሚካሎች መበከል
በእርግዝናና በወሊድ ወቅት የሚፈጠሩ ኢንፌክሽኖች
በአንጐል ውስጥ የሚገኝ የኬሚካል መጠን መዛባትና የሆርሞን አለመስተካከል
በዘር የሚተላለፍ መሆን እና በህፃናት አስተዳደግ ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ነገሮች የሚሉት ይገኙበታል፡፡

ህፃናት ከስድስት ወር ጀምሮ እስከ ሶስት ዓመት ዕድሜያቸው ድረስ የዚህ ችግር ተጠቂ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን ችግሩ የሚታወቀው ህፃኑ በሚያሳየው ባህርይና ሁኔታ እንጂ በሌላ የምርመራ ዘዴ አይደለም፡፡ ይሄም በህፃኑ ላይ ችግሩ ሳይታወቅ እንዲቆይ ያደርገዋል፡፡ ኦቲዝም ራሱን ችሎ ወይንም ከሌሎች ችግሮች ጋር በተጓዳኝነት የሚመጣ ሲሆን ከዚህ ችግር ጋር አብዛኛውን ጊዜ የሚጥል በሽታና መስማት የተሳነው መሆን ጐልቶ እንደሚታይ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ የኦቲዝም ችግር ያለባቸው ልጆች ከሚያሳዩዋቸው ባህርያት መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

በራሳቸው ዓለም የሚኖሩ በመሆኑ ሌላውን ለማወቅ ፍላጐት የላቸውም
ቃላት አውጥቶ መነጋገርና መግባባት ያቅታቸዋል

ሌሎች የተናገሩትን መደጋገም ይወዳሉ የሰሙትን ቃል /ዐረፍተ ነገር/ በሰሙት ድምፅና ቅላፄ መሠረት ደግመው መናገር ይችላሉ
በእናቶቻቸውም ሆነ በሌላ ሰው መታቀፍንና መነካትን አይፈልጉም መኪና፣ ገደል፣ ፎቅ፣ ፈፅሞ አይፈሩም ራሳቸውን ከግድግዳና ከሌሎች ግዑዝ ነገሮች ጋር በተደጋጋሚ ያጋጫሉ፤ እጃቸውን ይነክሳሉ፤ ፊታቸውን ይቧጭራሉ የመንቀዥቀዥ የመቁነጥነጥ ባህርይን ያሳያሉ ድንገት ስሜታቸው ይለዋወጣል፡፡ ከት ብለው ሊስቁ ወይንም ስቅስቅ ብለው ሊያለቅሱ ይችላሉ አብዛኛዎቹ የምግብ አበላል፣ የመፀዳጃ ቤት አጠቃቀምና የአለባበስ ሥርዓትን አያውቁም በጣም ረዥም ነገሮች ላይ መንጠልጠል፣ መዝለል ይወዳሉ

በአንዳንድ ነገሮች ላይ በጣም ፍርሃት ሲያሳዩ በሌላው ደግም የሚያስደንቅ ድፍረት ይኖራቸዋል፡፡ ለምሳሌ ከፊታቸው የቆመን ትልቅ  ነገር ተጋጭተው ሲያልፉት በጣም ጥቃቅን የሆኑ ነገሮች እንዳይገጯቸው ሲጠነቀቁና ሲፈሩ ይስተዋላሉ፡፡ የኦቲዝም ችግር ተጠቂ የሆኑ ልጆች፤ በአካላቸውና በገፅታቸው ላይ ምንም አይነት ለውጥ ስለማይኖራቸው፣ ችግራቸውን ቶሎ ለመረዳትና ተገቢ እንክብካቤ ለማድረግ አስቸጋሪ ይሆናሉ፡፡ ችግሩ ሁነኛና ዘላቂ ፈውስ ያልተገኘለት ቢሆንም የችግሩ ተጠቂዎችን በልዩ ስልጠና እና እንክብካቤ ለተሻለ ህይወት ማብቃት ይቻላል፡፡ ኦቲስቲክ ከሆኑ ሰዎች መካከልም እጅግ ከፍተኛ ብቃትና ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ሰዎች እንደነበሩ የታሪክ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ኦቲስቲክ ልጆች ያሏቸው ወላጆች በህብረተሰቡ ዘንድ የመገለል፣ በማህበራዊ ግንኙነቶች ውስጥ እንደ ልብ ተሣትፎ ለማድረግ እንዳይችሉ የመደረግ ችግርም ይገጥማቸዋል፡፡ ልጆቻቸው በችግሩ ምክንያት የሚያሳይዋቸው የተለያዩ ባህርያት ከሥነ ሥርዓት ጉድለት ጋር ስለሚያያዝባቸው ህብረተሰቡ ያገላቸዋል፡፡ ስለዚህም አንዳንድ ወላጆች ኦቲስቲክ ልጆች እንዳላቸው መናገርና ማሣየት አይፈልጉም፡፡ በተቻላቸው መጠን ልጆቹ ከቤት እንዳይወጡና ለሰው እንዳይታዩ በማድረግ፣ በቤት ውስጥ ዘግተው ወይንም አስረው ያስቀምጡዋቸዋል፡፡

ከጥቂት ዓመታት በፊት ከተወለደ ጊዜ ጀምሮ ወደ ውጪ እንዳይወጣና እንዳይታይ ተደርጐ በጨለማ ክፍል ውስጥ ያደገውና ከሃያ አምስት አመት እድሜው በኋላ ነፃነቱን ሊጐናፀፍ የቻለው አንድ ወጣት ታሪክ የዚህ ችግር ሁነኛ ማሣያ ነው፡፡ ኦቲዝም የዓለም ህዝብ ችግር ቢሆንም ስለ ችግሩ በስፋት ለመወያየትና መፍትሔ ለማፈላለግ ጥረት ሲደረግ በብዛት አይታይም፡፡ ከአስር ዓመታት በፊት በኒያ ፋውንዴሽን የተቋቋመውና ጆይ ኦቲዝምና ተዛማጅ ልዩ የእድገት ፍላጐት ያላቸው ልጆች ማዕከል፤ ለችግሩ የመፍትሔ አካል በመሆን እየሠራ ይገኛል፡፡ ማህበሩ የተቋቋመበትን 10ኛ ዓመት በአልና በአለም አቀፍ ደረጃ በያዝነው ወር እየተከበረ ያለውን የኦቲዝም ቀን ምክንያት በማድረግ ሰፊ ፕሮግራም አዘጋጅቷል፡፡ ካዛንቺስ በሚገኘው አዲሱ ራዲሰን ብሉ ሆቴል ሰሞኑን በተዘጋጀ ጋዜጠዊ መግለጫ የተጀመረው ፕሮግራም፤ በኢሲኤ አዳራሽ በሚደረግ ታላቅ ሲምፖዚየም፣ የእግር ጉዞና የሙዚቃ ዝግጅት የፋሽን ትርኢት የሚቀጥል ሲሆን በሸራተን አዲስ በሚከናወን የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ፕሮግራም ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡

“ተረዱን ተቀበሉን አካቱን” በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የዘንድሮ የኦቲዝም ቀን በዓል አስመልክቶ፣ የጆይ ኦቲዝምና ተዛማጅ ልዩ የእድገት ፍላጐት ያላቸው ልጆች ማዕከል መስራችና ማኔጅንግ ዳይሬክተር ወ/ሮ ዘሚ የኑስ እንደተናገሩት፤ “የኦቲዝም ችግር ለአመታት ምስጢር ሆኖ የቆየና የችግሩ ተጠቂ ልጆችም በቤት ውስጥ በገመድ ታስረው እስከመቀመጥ ድረስ እንዲደርሱ ያደረገ ችግር ነው፡፡

“እነዚህ ሕፃናት የሚደርስላቸውና ከታሰሩበት ገመድ ፈትቶ ነፃ በማውጣት፣ ህይወታቸውን በተስተካከለ መንገድ እንዲመሩ የሚያስችላቸው ስልጠናና እንክብካቤ ሊደረግላቸው ይገባል፡፡ ለዚህ ደግም እያንዳንዱ ሰብአዊ ፍጡር ኃላፊነት አለበት” ብለዋል፡፡ ልጆቹ በራሣቸው ዓለም ውስጥ የሚኖሩና የራሣቸው ባህርያት ያሉዋቸው በመሆኑ እነዚህን ባህርያት ተቀብለን ልንረዳቸውና ልንንከባከባቸው ይገባል፡፡ መንግስትም ሆነ የሚመለከታቸው አካላት፣ በጉዳዩ ላይ ትኩረት በመስጠት ልጆቹ ስልጠናና ትምህርት የሚያገኙባቸው ማዕከላት በየአካባቢው ማቋቋምና ልጆቹን መቀበል ይገባልም ብለዋል፡፡ በእሣቸው የተቋቋመው ማዕከል በአሁኑ ወቅት 68 ልጆችን ተቀብሎ ትምህርትና እንክብካቤ በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከ480 በላይ ልጆች በስልጠና እንደሚገኙና ከቦታቸው ውስንነት የተነሣም የሕብረተሰቡን ፍላጐት ለማሟላት እጅግ መቸገራቸውን ጠቁመዋል፡፡ መንግስት እነዚህን ልጆች ሊታደጋቸውና ቢያንስ በየክፍለ ከተማው አንድ የኦትስቲክ ልጆች ስልጠና ማዕከል መቋቋም እንደሚገባውም ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኙት ከሁለትና ሶስት የማይበልጡ ማዕከላት ልጆቻቸውን ለማስመዝገብና ስልጠና አግኝተው የተሻለ ህይወት እንዲኖሩ ለማድረግ ጥረት ያደርጉ የነበሩ በርካታ ወላጆች ጥረታቸው አለመሳካቱን ሲናገሩ ይሰማል፡፡ ለዘመናት በዝምታ ተቆልፈው፣ በር ተዘግቶባቸውና እንደ ልዩ የፈጣሪ ቁጣ እየታዩ ተገለው ይኖሩ የነበሩ ኦትስቲክ ልጆች፤ ዛሬ በተሻለ ሁኔታ አደባባይ ወጥተው ለመታየትና ለችግራቸው መፍትሔ ማግኘት እንዲችሉ የሚያደርጉ አካላት በመፈጠራቸው እንቅስቃሴውን በማሣደግ ልጆቹ የተሻለ ህይወት እንዲኖሩ በማስቻሉ በኩል መንግስትም ሆነ ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ከፍተኛ ጥረት ሊያደርጉ ይገባል፡፡ የህፃናቱ ስቃይና ሰቆቃ ሊገታና ከተደበቁበት ወጥተው ነፃ ህይወት መምራት ይኖርባቸዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ ሁላችንም ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል፡፡

Monday, 18 November 2013

DON'T IGNORE ABUSE OF ETHIOPIANS IN SAUDI ARABIA SAYS WORLD CLASS MODEL YORDANOS TESHAGER

Yordanos Teshager
[The Freeman Report]
Ethiopian Supermodel Yordanos Teshager was the second runner up for Miss Ethiopia in 2004. Since then she has gone on to grace catwalks for the likes of Rock & Republic, Osman Yousefzada and Giorgio Armani. She was featured in Vogue Italia in 2008 and served as UN Ambassador on a mission to Nigeria in 2012.
Black Star News recently sat down with the African beauty to discuss an issue that’s near and dear to her heart, and to millions of Ethiopians -- the recent attacks on Ethiopian migrant workers living in Saudi Arabia at the hands of Security agents there and the authorities. This is how our conversation went.
Black Star News: Please tell us about the recent events that have been taking place in Saudi Arabia against the Ethiopian migrant workers?
Yordanos Teshager: Recently the government of Saudi Arabia ordered that all immigrants living, and working within Saudi Arabia be deported back to their countries. Shortly after this order was issued, the Saudi Arabian authorities begin attacking the tens of thousands of Ethiopian migrant workers living within Saudi Arabia. This was followed by attacks from government backed youth gangs. The atrocities committed by the Saudi Arabian authorities, and youth gangs has now reached intolerable heights; the abuse, killings and dehumanization of defenseless Ethiopians calls for an urgent need for action.
BSN: Instead of the actions that the Saudi Arabian authorities have been taking against the workers, what do you think should have been done as an alternative?
YT: The Saudi Arabian authorities are taking very serious actions against the Ethiopian migrant workers living within their country. They have been killing the workers, physically abusing the workers and committing every other vile, inhumane act against the workers. Instead of the atrocious acts that they are committing against the workers, they should conduct their deportation in a more civilized, humane manner. Ethiopians are very loving, peaceful, hardworking people. The injustice that we are experiencing at the hands of the Saudi authorities should not be tolerated. It’s wrong to treat any group of human beings the way that we are being treated.
BSN: How do you feel this affects, not only the Ethiopians living in and outside of Saudi Arabia, but members of the African Diaspora as a whole?
YT: This affects all members of the African Diaspora, because if they get away with treating one set of our brothers and sisters in this manner, they will think its okay to treat all Africans the same way. We are all one people, there’s no such thing as African Americans, Jamaicans, Haitians, Ethiopians, Kenyans, Liberians, Nigerians, etc. We are one, and we all must come together to fight this great injustice. As the saying goes, “United we stand; divided we fall”
BSN: What are you hoping to see done to stop the heinous acts that are being committed against the workers by the Saudi Arabian authorities?
YT: I’m hoping to see people from all over the world speak out against what’s happening to the Ethiopian men, women and children who are living within Saudi Arabia. Any inhumane act against any living human being, affects all living human beings, whether you’re from Africa or not. We should all be appalled by what’s currently taking place in Saudi Arabia. I’m praying that all Ethiopians living within Saudi Arabia return home to Ethiopia without any further abuse. Until then, we must continue to raise our voices.
BSN: In closing. What message would you like to send to Saudi Arabian King Abdullah bin Aziz and UN Secretary-General Ban Ki-moon in hopes of bringing about your desired results?
YT: I would like to remind Saudi King Abdullah bin Aziz that Ethiopian King Negus granted refuge to the family of Prophet Muhammad, who arrived in Aksum while fleeing from their pagan persecutors.
[Prophet] Muhammad never forgot this and said that, no Muslim was to ever wage war against Ethiopia as a land or a people. How could you who claim to be a true Muslim forget what the Prophet said? And if you truly are a Muslim, you would immediately stop these attacks and allow all of the Ethiopians living within Saudi Arabia to return home without any further harm.
To UN Secretary-General Ban Ki-moon I say, to please do your job. Don’t sit back idly while tens of thousands of innocent Ethiopians are being abused, killed and dehumanized at the hands of the Saudi authorities. You have a duty as the UN Secretary-General, and if you’re not willing to perform your duty, step down and allow someone else who’s willing to properly perform that duty have your position.
[Interview conducted by: Edwin Freeman]
Actor|Writer|Producer
- See more at: http://www.blackstarnews.com/global-politics/africa/dont-ignore-abuse-of-ethiopians-in-saudi-arabia-says-world-class-model#sthash.anRc5aZ4.dpuf

Tuesday, 12 November 2013

The Misery of Ethiopians in Saudi Arabia - By Sadik Ahmed

የመጣኸዉ ባዶህን ነው! ባዶ ሆነህም ትመለሳለህ!...ኢንተ-ጃኢ-ፋዲ ወተርጃእ-ፋዲ...የሳዉዲዎች አመለካከት!
የፈለጋቹበት ዉሰዱን ግን አትደብድቡን...ይላል ኢትዮጵያዊዉ...ለካስ አትደብድቡን ማለቱ   




Sunday, 10 November 2013

Saudi police in Riyadh clash with migrant workers

Two people have been killed and scores wounded as Saudi police clashed with protesting foreign workers in a district of the capital, Riyadh.
A police statement said hundreds of people were arrested in the Manfuhah neighbourhood.
Video on social media websites showed security forces in riot gear using truncheons to disperse large crowds.
Last week police rounded up thousands of migrant workers after an amnesty linked to new employment rules expired.
Police said they intervened on Saturday after foreign workers in the Manfuhah district rioted, attacking Saudi and other foreign residents with rocks and knives.
Manfuhah is home to many migrants, mostly from east Africa.
One of the two people killed was a Saudi while the other was unidentified, police said. About 70 others were injured and there were some 560 arrests, officials added.
On Sunday, witnesses said police were surrounding the district while units from the National Guard and special forces were sent in.
Nearby, hundreds of men, women and children lined up with their belongings to board police buses taking them to an assembly centre before their deportation, AFP news agency reported.
Images showed other foreign workers leaving the Manfuhah area in taxis.
Last Monday, the authorities began rounding up thousands of illegal foreign workers following the expiry of a seven-month amnesty for them to formalise their status.
An Ethiopian was reported killed on Wednesday as Saudi police began moving illegal immigrants into camps. The government in Addis Ababa has said it is providing support for Ethiopian workers and is helping to repatriate its citizens.
Nearly a million Bangladeshis, Indians, Filipinos, Nepalis, Pakistanis and Yemenis are estimated to have left the country in the past three months.
Four million others obtained work permits before last Sunday's deadline.
Saudi Arabia has the Arab world's largest economy, but authorities are trying to reduce the 12% unemployment rate among native Saudis.
An estimated nine million migrant workers are in Saudi Arabia - more than half the workforce - filling manual, clerical, and service jobs.

Saturday, 9 November 2013

እባክዎ የእርዳታ እጅዎን ይዘርጉ

ኢትዮጵያ ውጪ እርዳታ ለሚያደርጉ ወገኖች
SWIFT CODE-CITIUS33
Beneficiary’s Bank: United Bank S.C
SWIFT Code-UNTEDETAA
Beneficiary: M/S AYALEW AND BIZUAYEHU FOR 
JOURNALIST EPHEREM BEYENE
A/C No.1370416020809010
URAEL Branch Addis Ababa Ethiopia 





እባክዎ የእርዳታ እጅዎን ይዘርጉ በቀረበባቸው ክስ ወደ አዋሳ የተጓዙት የኢትዮ ምህዳር ጋዜጠኞች፣አዋሳ ከተማ ውስጥ የተሳፈሩበት ባጃጅ ከሞተርሳይክል ጋር ተጋጭቶ ከፍተኛ አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡ ከፍተኛ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ኤፍሬም በየነ በማጅራቱ አካባቢ የአከርካሪ አጥንቱ ተሰብሯል፡፡ ከወገቡ በታች ሰውነቱን ማዘዝ አይችልም፡፡ ሳንባው ስለተጎዳ የሚተነፍሰው በመሳሪያ እየተረዳ ነው@የሃያ ሰባት ዓመቱ ጋዜጠኛ በአበባ ኮሪያ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ቢሆንም ወደ ውጪ ተልኮ ከፍተኛ ሕክምና ማድረግ እንዳለበት ታምኖበታል፡፡የሕክምና ወጪውን ለመሸፈን እሱና ቤተሰቡ ወይ አሰሪ ድርጅቱም አቅም ስለሌላቸው፣ ኢትዮጵያውያን የበጎ አድራጊ ወገኖቻችን፣ የእርዳታ እጃችሁን ትዘረጉልን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን። እርዳታዎን ሕብረት ባንክ ኡራኤል ቅርንጫፍ A/C 1370416020809010 ገቢ እንዲያደርጉልን እንጠይቃለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፡-
0911-81 42 22/ 0911-43 
56 73/ 0911-12 31 32
የእርዳታ 
አስተባባሪ ኮሚቴ