Monday, 29 April 2019

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የትንሣኤ በዓልን በማስመልከት ለክርስትና እምነት ተከታዮች ያስተላለፉት መልዕክት።

Image may contain: text
Image may contain: text



Image may contain: text




































ስኬት ከገንዘብ ይበልጣል

25 የስኬት ቁልፎች"

ስኬት ከገንዘብ ይበልጣል


የእውነተኛ ስኬት ቁልፍ

ስኬት የሞላበት ሕይወት ምንድን ነው? ለስፖርት አፍቃሪ ስኬት በአንድ ስፖርት ታዋቂ መሆን ነው፡፡ ለውበት አድናቂ ስኬት በሰው ሁሉ መወደድና መደነቅ ነው፡፡ ዝናን ለሚወድድ ሰው ዝነኛነት ከስኬት ጋር ይገናኝበታል፡፡ ስልጣን ወዳድ፣ ባለበት ተቋምም ሆነ ድርጅት ውስጥ ከፍተኛውን ስፍራ ማግኘት ስኬቱ ነው፡፡ ከእነዚህ ሁሉ ይልቅ ግን በብዙዎች ሃሳብ ውስጥ ስኬት ከሃብትና ከብልጽግና ጋር ግንኙነት አለው፡፡ በሌላ አባባል፣ ሰው ሁሉ፣ “ስኬታማነት ማለት ይህ ነው” ብሎ የሚያስበውን ነገር በገንዘብ ከመበልጸግ ጋር ማገናኘቱ አይቀርም፡፡ ስለዚህም፣ ስኬት ማለት ሃብታም መሆን ነው ብሎ የማያስብ ሰው ካለ ይገርማል፡፡


ዶ/ር ጃን ማክስዌል Your Road Map for Success በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ አንድ አስተማሪ ታሪክ አስፍረዋል፡፡ በ1923 ሺካጎ በምትባል የአሜሪካ ከተማ ውስጥ ሰባት የሚሆኑ በአለም ቀደምተኝነትን የያዙ የአገሪቱ ሃብታሞች ተሰብስበው ነበር ይባላል - ስለ ስኬትና ስለሃብት ለመወያየት፡፡ የእነዚህ ሰባት ባለሃብቶች ጥርቅም ሃብታቸው የአሜሪካንን የአገር ውስጠ ገቢ በጀት ይበልጥ እንደ ነበርም ይነገራል፡፡ እነዚህ ሰዎች በብዙዎች ሰዎች አንደበት የተሳካላቸው የተሰኙ ነበሩ፡፡ ፍጻሜአቸው ግን እንዲህ እንደነበረ ታሪክ ይነግረናል፡፡
ቻርልስ ሽዋብ (Charles Schwab – president of the largest independent still company) - በድህነት፣ በክስረትና በታላቅ ኃዘን ሞተ፡፡

አርተር ከተን (Arthur Cutten – greatest of the wheat speculetors) - ከአገሩ ውጪ በእዳ ተጠላለፍፎና ከስሮ ሞተ፡፡

ሪቻርድ ዊትኒ (Richard Witney – president of the New York Stock Exchange) - በኒው ዮርክ ከሚገኘው ሲንግ ሲንግ ከተሰኘው እስር ቤት ማቅቆ ልክ ሲፈታ ሞተ፡፡


አልበርት ፎል (Albert Fall – member of a U.S. president’s cabinet) - ከእስር ቤት በይቅርታ ተፈትቶ እቤቱ ሞተ፡፡

ጄሲ ሊቨርሞር (Jess Livermore – greatest “bear” on Wall Street) - ራሱን አጥፍቶ ሞት፡፡

ሊዎን ፍሬዠር (Leon Fraser – president of the Bank of International Settlement) - ራሱን አጥፍቶ ሞተ፡፡

ኢቫር ክሩገር (Ivar Kreuger – head of the world’s greatest monopoly) - ራሱን አጥፍቶ ሞተ፡፡

“የተወሰነ ደረጃ ከደረስኩ በኋላ የገባኝ ይህ ነው፤ ገንዘብ ዋጋ ቢስ ነው፡፡ ስኬት ከገንዘብ ይበልጣል” – (Aristotle Onassis – Greece Millionaire) ብዙ የገንዘብ ባለጠጎች በብዙ ሚልየን የሚቆጠር ብርን አካብተው እንኳ ስኬትን አሁንም በብርቱ ሲፈልጓት ይታያሉ፡፡ ስለዚህም ብዙዎች ይህንን እውነት ወደማመን መጥተዋል - የብር ብልጥግና ብቻውን ስኬት ማለት አይደለም፡፡ሃብት ከስኬት ጋር የማይገናኝበት ብዙ ምክንያቶች አሉ፡፡


ለምሳሌ፣ ቀደም ብለን እንዳየነው፣ በብዙ ሃብት የተሞሉ ሰዎች መጨረሻቸው አሳዛኝ እንደሆነ ስንመለከት ስኬትን ከተለየ እይታ እንድናየው እንገደዳለን፡፡ በተቃራኒው፣ ምንም ያህል በሰው እይታ የሚሞላ ንብረት ሳይኖራቸው የሰላምና ለሰው የሚተርፍ ሕይወት ጠግበው የሚኖሩና ኖረውም በክብር የሞቱ ሰዎች ቁጥር እጅግ ብዙ መሆኑ አሁንም ለስኬት ያለንን እይታ እንድንጠይቅ ይጋብዘናል፡፡ በገንዘብ መበልጸግ ከስኬት ክፍል እንደ አንዱ ሊቆጠር ይችላል እንጂ የስኬት ጥጉ አይደለም፡፡ የገንዘብ ብልጽግና ከሌሎች የስኬት “ንጥረ ነገሮች” ጋር ተዳብሎ ሲገኝ ብቻ ነው ስኬት ሊባል የሚችለው፡፡

ይህንን ለምሳሌ እንመልከት፡- በሰሜን አሜሪካ በተደረገው ጥናት 80 በመቶ የሚሆኑ የሎተሪ አሸናፊዎች በአምስት አመት ውስጥ ራሳቸውን በክስረት ውስጥ እንደሚያገኙትና እንዲያውም አንዳንዶቹ የጎዳና ተዳዳሪዎች እስከ መሆን እንደሚዘቅጡ መረጃ ያሳያል፡፡ እነዚህ ሰዎች በእጃቸው በድንገት የገባውን ሃብት የሚመጥን ስኬታማ አመለካከት ቀድሞውኑ ስላልነበራቸው ተመለሰው ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው ያዘቅጣሉ፣ አንድ አንዴም ከዛ ወደ ወረደ ሁኔታ! አየህ፣ ገንዘብ ስኬታማነትን አያመጣም፣ ስኬታማነት ግን የገንዘብን ብልጽግና ሊያመጣ ይችላል፡

By Dr. Mehret Debebe