Saturday, 11 April 2020

መሪነት የሚገለጠው በአገልጋይነት ነው


መሪነት የሚገለጠው በአገልጋይነት ነው። ከአጠገብህ ቆሜ ለማገልገል ያገኘሁት እድል ክብሬ ነው።
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር፣
የሰጠኸንን አንድ ሺህ ኪሎግራም የምግብ ዱቄት ለኮሮና ፈተና መቋቋሚያ በመላው ከተማችን ባሰናዳናቸው የምግብ ባንኮች አስቀምጠን ለደሃው እንደርስበታለን። ድጋፍህ ፈተናውን ለማለፍ በእጅጉ ይረዳናል። እናመሰግናለን።








Wednesday, 8 April 2020

የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሮና ወረርሽኝ እየተባባሰ በመምጣቱ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ ዐውጇል፡፡

ክቡራትና ክቡራን ኢትዮጵያውያን

እየተመለከታችሁትና እየታዘባችሁት እንደሆነው ዓለም በአስቸጋሪ የፈተና ምእራፍ እያለፈች ነው፡፡ ዓለም ይሄንን መሰል ነገር ሲገጥማት ከመቶ ዓመት በኋላ የመጀመሪያ ነገር ነው፡፡ 

የኢትዮጵያ መንግሥት ኮሮና (ኮቪድ -19) የዓለም ሁለንተናዊ ችግር ሆኖ ብቅ ካለበት ጊዜ ጀምሮ ደረጃ በደረጃ የመፍትሔ ርምጃዎችን ሲወስድ ቆይቷል፡፡ ሕዝቡ ግንዛቤ እንዲያገኝ፣ የሕክምና ተቋማት እንዲዘጋጁ፣ የመከላከያና የሕክምና መሣሪያዎች ከውጭ እንዲገቡ፣ የማቆያ ሥፍራዎች እንዲዘጋጁ፣ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ፤ አብዛኞቹ የመንግሥት ሠራተኞች በቤት እንዲወሰኑ፣ ብዙ ሕዝብ ሊሰበሰብባቸው የሚችሉ ሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ተቋማት አገልግሎታቸውን ሕዝብ ሊሰበሰብ በማይችልበት መንገድ እንዲከውኑ፣ በአብዛኛው ሥፍራዎች የሕዝብ ትራንስፖርት እንዲቋረጥ፣ ለአስቸጋሪ ጊዜ የሚሆን ሀብት የማሰባሰብ ሥራ እንዲሠራ ተደርጓል፡፡

መንግሥት የኮሮና ወረርሽኝን በተመለከተ የሚከተለው ስትራቴጂ በመከላከል ላይ ያተኮረ ነው፡፡
1. ኅብረተሰቡን አስተባብሮ በባለሞያዎች ምክር መሠረት ለመከላከል መቻል
2. ከመከላከል ያለፈ ነገር ሲመጣ ለማከም የሚያስችሉ ዐቅሞችን ማዳበር፡፡
3. የከፋው ነገር ከመጣም አስቀድሞ በመዘጋጀት እንደየ አስፈላጊነቱ ተገቢ ውሳኔዎችን እያሳለፉ መሄድ፡፡ 

እስካሁንም በዚህ መንገድ ነው የተጓዝነው፡፡
አሁን ያሉን መረጃዎች እንደሚያሳዩት በቫይረሱ የተያዙ ወገኖች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው፡፡ ይሄም በመሆኑ ሁላችንም ያለንን ዐቅም ሁሉ አስተባብረን ወገኖቻችንን ከዚህ ወረርሽኝ ለመከላከልና የታመሙትንም ለማዳን ማዋል አለብን፡፡ ያለንበት ጊዜ ሕዝብና ሀገርን ለማዳን ሲባል አስቸጋሪ የተባሉ ውሳኔዎችን መወሰን ያለብን ጊዜ ነው፡፡ ይህም ውሳኔ፣ እንደ ግለሰብ፣ እንደ ማኅበረሰብ፣ እንደ ተቋምና እንደ መንግሥት የሚወሰኑ ናቸው፡፡ 

ይህ ውሳኔ በዛሬው ትውልድ ላይ ብቻ የምንወስነው ውሳኔ አይደለም፡፡ በልጅ ልጆቻችን ላይ ጭምር የምንወስነው ነው፡፡ በዛሬዋ ኢትዮጵያ ላይ የምንወስነው ብቻ አይደለም፤ በነገዋና በከነገ ወዲያዋ ኢትዮጵያ ላይ ጭምር የምንወስነው ውሳኔ ነው፡፡ የኛ የመሪዎቹ ውሳኔ ብቻ ሳይሆን የእያንዳንዱ ዜጋ ውሳኔ በታሪክ የሚመዘገብ ነው፡፡ 

ይሄንን አስቸጋሪ ጊዜ ልናልፈው የምንችለው በአካል ተራርቀን በመንፈስ ግን አንድ ሆነን ከቆምን ብቻ ነው፡፡ የያንዳንዳችን ሀብት የሁላችን፣ የእያንዳንዳችንም ችግር የሁላችን መሆን አለበት፡፡ አንዱ በልቶ ሌላው ተርቦ፣ አንዱ ሠርቶ ሌላው ሥራ አጥቶ፣ አንዱ መኖሪያ አግኝቶ ሌላው ውጭ አድሮ፣ አንዱ አትርፎ ሌላው ከሥሮ ይሄንን ችግር ለማለፍ ፈጽሞ አይቻልም፡፡ ምክንያቱም ይህ ችግር የመጣው በህልውናችን ላይ በመሆኑ፡፡ ይህ ችግር የተጋረጠው ሰው ሆኖ በመኖርና ባለመኖር ላይ በመሆኑ፡፡

መንግሥት ችግሩን በደረሰበት ልክ ለመቋቋም ተዘጋጅቷል፡፡ የምንወስዳቸው ውሳኔዎች ክብደት እንደ ችግሩ ክብደት የሚወሰን ነው፡፡ ታሪክ እዚህ አድርሶናል፡፡ ሀገርና ትውልድ በእጃችን ላይ ነው፡፡ በዚህ ዘመን በምንሠራው ሥራ ወይ እንመሰገናለን ወይ እንወቀሳለን፡፡ ከምንም በላይ ግን በጊዜውና በዐቅማችን ማድረግ ያለብንን ካላደረግን የበለጠ እንወቀሳለን፡፡ ይህ ደግሞ ሁላችንንም ኢትዮጵያውያንን የሚመለከት ነው፡፡ ከተረፍን አብረን ነው፡፡ ከከሠርንም አብረን ነው፡፡ 

የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሮና ወረርሽኝ እየተባባሰ በመምጣጡ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ ዐውጇል፡፡ ይህም በሕገ መንግሥቱ ዐንቀጽ 93 መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ ይሄንን መሳይ ዐዋጅ ብዙ ሀገሮች ካወጁ ሰንብተዋል፡፡ እኛ እስክንዘጋጅና ሁኔታው የግድ እስኪለን ጠብቀናል፡፡ ጊዜው ሲጠይቅ ግን ዐውጀናል፡፡ ሀገርን ለማዳንና ትውልድን ለመታደግ ከዚህ በላይ ልንወስን እንደምችልም መታወቅ አለበት፡፡ ዜጎቻችንም ከዚህ በላይ ግዴታቸውን ለመወጣት ወገባቸውን አጥብቀው መጠበቅ አለባቸው፡፡ 

በዚህ ወቅት ሁላችሁም ችግሩን ለመቋቋም ከሚሠሩት አካላት ጋር አብራችሁ እንድትቆሙ ጥሪ አቀርባለሁ፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ችግሩን ለማባባስ የሚሠሩ ካሉ ግን፣ በሕጉ መሠረት የማያዳግም ርምጃ እንወስዳለን፡፡ 

ወገኖቼ፤

ኢትዮጵያውያን የሚያምርብን መረዳዳቱና መደጋጋፉ ነው፡፡ ድኾችን እንርዳ፡፡ በአካባቢያችን ላሉት ዐቅመ ደካሞች እንድረስላቸው፡፡ የቤት ተከራዮቻችንን ዕዳ እንካፈላቸው፡፡ ከቻልን አናስከፍላቸው፤ ካልቻልን ቅናሽ እናድርግላቸው፡፡ ያም ካልሆነ ይህ ጊዜ እስኪያልፍ እንታገሣቸው፡፡ በዚህ ወቅት ተከራዮችን ከቤት ማስወጣት ፈጣሪም፣ ታሪክም ሕግም ይቅር የማይሉት ወንጀል ነው፡፡ ማናችን አልፈን ማናችን እንደምንተርፍ ለማናውቅበት ጊዜ ከመተባበር የተሻለ መሻገሪያ የለንም፡፡ የግል ባለሀብቶች የሠራተኞቻቸው ሕይወት እንዲያስጨንቃቸው አደራ እላለሁ፡፡ መንግሥት የኢኮኖሚ ችግሮቻችንን ለመፍታት አስፈላጊውን ሁሉ እየወሰነ አብሯችሁ እንደሚሆን በዚህ አጋጣሚ እገልጥላችኋለሁ፡፡ 

ለሌሎች ወገኖቻቸውና ለሀገራቸው ሲሉ ቤታቸውን፣ ሆቴላቸውን፣ አዳራሾቻቸውን፣ የእምነት ተቋሞቻቸውን፣ መኪኖቻቸውን፣ ገንዘባቸውንና እህላቸውን የሰጡ ዜጎቻችንን ስናይ ይሄንን አስቸጋሪ ወቅት ከፈጣሪ ጋር ሆነን ልናልፈው እንደምንችል ርግጠኞች እንሆናለን፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ከወገኖቻቸው መከራ ለማትረፍ የሚሽቀዳደሙ፣ ከመከራ እንኳን የማይማሩ ሰዎችን ስናይ መንገዱ ከባድ እንዳይሆንብን እንሠጋለን፡፡ በጎ አድራጊዎችን የምናመሰግነውን ያህል መንገዳችን

የሕክምና ባለሞያዎቻችንን በሚቻለው ሁሉ እንርዳ፡፡ ያለ እነርሱ ግንባር ቀደምነት ትግሉን ልናሸንፍ አንችልም፡፡ የሕክምና ባለሞያዎችን ማክበር፣ ማመስገንና በጉዟቸው ሁሉ መተባበር ከእያንዳንዳችን ይጠበቃል፡፡ ለሕክምና ባለሞያዎች ተገቢውን ሁሉ አለማድረግ እጅን በእጅ እንደመቁረጥ ነው፡፡ ከእነርሱ በተጨማሪ የመከላከያ አባላት፣ የፖሊስ ሠራዊት አባላት፣ የኤሌክትሪክ ኃይልና የውኃ አቅርቦት እንዳይስተጓጎል የሚሠሩ ባለሞያዎች፣ የሚዲያ ባለሞያዎች፣ የመገናኛ መሥመሮቻችን ላይ 24 ሰዓት የሚያገለግሉ ዜጎች፣ እኛ ቤት እንድንውል እነርሱ ውጭ የሚውሉ ሠራተኞች ተገቢው ምስጋናና ድጋፍ ከቤተሰባቸውም፣ ከማኅበረሰባቸውም ያስፈልጋቸዋል፡፡

በዚሁ አጋጣሚ አርሶ አደሮቻችን የበልግ ወቅት እንዳያልፍብን ራሳቸውን ከቫይረሱ እየተጠነቀቁ በምርት ሥራ ላይ ጠንክረው እንዲሳተፉ አደራ እላቸዋለሁ፡፡ ከቫይረሱ ባልተናነሰ የእርሻ ምርት መቀነስና የእርሻ ምርት አለመኖር ሀገራችንንና ሕዝቧን ይጎዳል፡፡ እናንተ ሀገር መጋቢዎች ስለሆናችሁ፣ እየተጠነቀቃችሁ ካለፈው የተሻለ ምርት ለማምረት ትጉ፡፡ መንግሥትም አስፈላጊውን ሁሉ ሞያዊና ድጋፍ ያደርግላችኋል፡፡

የኢንዱስትሪ ምርቶቻችንም ፈጽመው መቆም የለባቸውም፡፡ ለሠራተኞቻችን ሕይወት እየተጠነቀቅን፣ በወረርሽኙ ምክንያት የሚያጋጥመንን ተግዳሮት ሁሉ እየተቋቋምን በፋብሪካ ምርቶች ላይ የተቻለንን ሁሉ ጥረት እናድርግ፡፡ በተለይም ከውጭ የምናመጣቸውን ምርቶች ለመተካት ለሚደረገው ጥረት መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግላችሁ እገልጥላችኋለሁ፡፡ በተለይ ግን በምርት ዝውውር ጊዜ ከፍተኛ የሆነውን የመጨረሻ ጥንቃቄ እንዲደረግ ለአፍታም ቢሆን እንዳትዘነጉት ይሁን፡፡ 

ይህ ጊዜ ያልፋል፡፡ ሀገራችን ከዚህ የሚስተካከሉና ከዚህም የሚብሱ ፈተናዎችን አልፋለች፡፡ ዓለማችን በየዘመናቱ የከፉ ተግዳሮቶችን አልፋ ነው እዚህ ዘመን የደረሰችው፡፡ የሚሰጡንን መመሪያዎች በሚገባ እናክብር፣ የጤና ባለሞያዎች የሚሉንን ለሕይወታችን ስንል እንስማ፡፡ በኮሮና አይቀለድም፡፡ ጉዳዩ ከመኖርና ካለመኖር ጋር የተያያዘ ነው፡፡ 

ይሄንን ፈተና ለማለፍ ባለ ሦስት መዓዘን ትብብር ያስፈልገናል፡፡ ወደ ጎን እኛ እርስ በርሳችን፡፡ እያንዳንዳችን ደግሞ ከፈጣሪያችን ጋር፡፡ እኔ ከሌላው ወገኔ ጋር፣ ሌላው ወገኔ ከእኔ ጋር፣ እኔና ሌላው ወገኔ ከፈጣሪ ጋር የምንገናኝበት መሥመር መቼም መቋረጥ የለበትም፡፡ 

በርትተንና ተረባርበን የሚጠበቅብንን እናድርግ፣ ጸንተንና በተሰበረ ልብ ሆነን ወደ ፈጣሪ እንለምን፡፡ ፈጣሪ ከእኛ ጋር ነው፡፡ መከራውን ያቀልልናል፤ ፈተናውን ያሳልፈናል፤ ማዕበሉን ያሻግረናል ብለን እናምናለን፡፡ የሃይማኖት አባቶች ያዘዙንን ጥንቃቄ እየፈጸምን ያዘዙንንም ጸሎት ተግተን እንጸልይ፡፡

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
መጋቢት 30/ 2012 ዓ.ም

Tuesday, 31 March 2020

የጤና ባለሙያዎች ራሳቸውን ከኮሮና ቫይረስ እንዲጠብቁ የሚለበስ ልብስ (PPE) ያዘጋጀው ወጣት ኢትዮጵያዊ ኢንጂነር!

የጤና ባለሙያዎች ራሳቸውን ከኮሮና ቫይረስ እንዲጠብቁ የሚለበስ ልብስ (PPE) ያዘጋጀው ወጣት ኢትዮጵያዊ ኢንጂነር!
.
የማስተዋውቃችሁ ኢንጂነር ሳሮን ለሁሉም አርአያ መሆን የሚችልና ሊደገፍ የሚገባው ወጣት ነው። ይህ የምታዩት ልብስ በራሱ ተነሳሽነት ጥናት አድርጎ ፣ በራሱ ወጪ ያዘጋጀው ነው። ለቫይረሱ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ ጤናው ላይ የሚሰሩ ያገሩን ልጆች ለማገዝ ካለው መልካም ሐሳብ ነው ይህን ያደረገው። በፎቶው ላይ ለብሶት የምታዩትን አንዱን ልብስ ከውጭ ለማስገባት ከ2,000 እስከ 3,000 የኢትዮጵያ ብር ያስፈልጋል።
.
ኢንጂነር ሳሮን ግን ዋጋውን በ1/4ኛ ቀንሶት በ500 የኢትዮጵያ ብር ገደማ አንድ የፕላስቲክ ልብስ ማዘጋጀት እንደቻለ ነው የነገረኝ። ከተማሩ አይቀር እንዲህ ላገር መትረፍ ያኮራል።
.
እሱን ቀጥታ የምታገኙት በስልክ ቁጥሩ 0917807480 ሲሆን ጥያቄ ካላችሁም በኮመንት ልትጽፉልኝ ትችላላችሁ።
.
ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አዕምሮ



Monday, 30 March 2020

ይቺ ጥቁር ፍሬ አትለያችሁ ከሞት በቀር ለሁሉም በሽታ ፈውስ ይዛለች።"




1ኛ. የማስታወስ ችሎታንና ፈጣን የግንዛቤ አቅምን ለማጎልበት
አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት፣ 100 ሚሊ ሊትር የፈላ ናእናእ (Nena) ተክል ጋር ተቀላቅሎ ለአሥር ተከታታይ ቀናት መውሰድ፡፡የማስታወስ ችሎታንን ያሳድጋል።በነገሮች ላይ ፈጣን የግንዛቤ አቅማችንን ያጎለብታል።

2ኛ. ለሳልና ለአስም
በዘይቱ ደረትንና ጀርባን ማሸት በቀን ሦስት የሾርባ ማንኪያ መጠጣት፣ ሁለት ማንኪያ በሙቅ ውኃ ውስጥ ጨምሮ እንፋሎቱን መሳብ ይረዳል፡፡

3ኛ. የመጫጫንና ስንፍናን ለማስወገድ
አንድ የሾርባ ማንኪያ ዘይት በአንድ ብርጭቆ ብርቱካን ጭማቂ ውስጥ ጨምሮ ጧት ጧት ለአሥር ተከታታይ ቀናት መውሰድ ልዩነቱን ያገኙታል፡፡

4ኛ. ለእርጋታ
አንድ የሾርባ ማንኪያ ትክክለኛውን የጥቁር አዝሙድ ዘይት በባዶ ሆድ መውሰድ ቀኑን ሙሉ መረጋጋትና ንቃት ያጎናጽፋል፡፡ እንዲሁም ከራት በኋላ ወደ መኝታ ከማምራት በፊት አንድ የሾርባ ማንኪያ ትክክለኛውን የጥቁር አዝሙድ ዘይት መውሰድ ለሊቱን ሙሉ የተረጋጋና ደስ የሚያሰኝ እንቅልፍ ያስገኛል፡፡ሌላ አማራጭ አንድ ትልቅ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ሲኒ ቡና ውስጥ ጨምሮ መጠጣት፡፡ የአእምሮ ጭንቀትን አስወግዶ መረጋጋትን ያስገኛል፡፡

5ኛ. ለኩላሊ ትጠጠር (የስኳር ሕመም ያለባቸው ማርን መተው ነው)
ሩብ ኪሎ ጥሬ ጥቁር አዝሙድ፣ ሩብ ኪሎ ንጹሕ ማር ማዘጋጀት፡፡ ጥቁር አዝሙድን በሚገባ መፍጨትና ከማር ጋር ቀይጦ በሚገባ ማዋሀድ፡፡ ከዚያም ሁለት ማንኪያ ከቅይጡ ቀንሶ በአንድ ብርጭቆ የሞቀ ውኃ ውስጥ ጨምሮ በጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ሻይ ማንኪያ በማከል በባዶ ሆድ መጠጣት፡፡

6ኛ. ለብሩሕ ገጽና ለውበት
አንድ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ማንኪያ የወይራ ዘይት ጋር አዋሕዶ ፊትን መቀባት አንድ ሰዓት ቆይቶ በውኃና በሳሙና መታጠብ ልዩነቱን በጉልህ ያገኙታል፡፡

7ኛ. #ከበሽታ_ሁሉ_ለመጠበቅ
አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከአንድ ማንኪያ ማር ጋር አዋሕዶ ያለማቋረጥ ጧት ጧት መውሰድ በሕይወት ዘመንዎ ሙሉ ጤነኛና የሐኪም እርዳታ የማያሻው ሰው ይወጣዎታል፡፡

8ኛ. በጭንና ጭን መካከል የቆዳ መቆጣት ሲያጋጥም
በቅድሚያ አካባቢውን በውኃና በሳሙና በሚገባ ማጠብ፣ ቀጥሎ በሚገባ ማድረቅና በጥቁር አዝሙድ ዘይት ማታ ቀብቶ ማደርና ለሦስት ተከታታይ ቀናት ይህንኑ መፈጸም፡፡ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ውጤቱን ያዩታል፡፡

9ኛ. ለልብና ለደም ሥሮች ሕመም
የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከትኩስ መጠጥ ጋር በተከታታይ መውሰድ ስብን ለማሟሟትና የደም ሥሮችን ለማስፋት ይረዳል፡፡

10ኛ. ለለምፅና ለመሳሰሉት
ተጠቂውን የሰውነት ክፍል በቱፋሕ (ፖም) ወይም አፕል ኮምጣጤ ማሸት ከዚያም የጥቁር አዝሙድ ዘይት ለ15 ቀናት መቀባት፡፡

11ኛ. ለቁርጥማት ፣ ሮማቲዝምና የጀርባ ሕመም የተወሰነ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በጥቂቱ በማሞቅ የታመመውን አካል አጥንትን ዘልቆ እስኪሰማ ድረስ በዘይቱ በደንብ መታሸት በቀን ሦስት ጊዜ አንድ የሾርባ ማንኪያ ዘይት መጠጣት፡፡

12ኛ. ለራስምታት
በጥቁር አዝሙድ ዘይት ግንባርንና በጆሮ አካባቢ ያለውን አካል ማሸት ለሦስት ተከታታይ ቀናት አንድ ሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በባዶ ሆድ መጠጣት፡፡

13ኛ. ለጨጓራና ለአሲድ
አንድ ኩባያ ወተት የአንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በቀን ሦስት ጊዜ መውሰድ፡፡ ከሦስት ቀናት በኋላ በሽታው ሙሉ በሙሉ ይወገዳል፡፡

14ኛ. ለራስ ማዞርና ለጆሮ ሕመም
አንድ ጠብታ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ጆሮ ውስጥ መጨመር በሻይ መልክ አዘጋጅቶ መጠጣት፡፡

15ኛ. ለቆዳ መቅረፍ
በዚህ አይነቱ ሕመም የተጠቃው የአካል ክፍል በጥቁር አዝሙድ ዘይት መቀባት ሕመሙ እስኪወገድ ድረስ ይህንኑ መቀጠል፡፡
16ኛ. ለብጉር
ጥቁር አዝሙድ አድቅቆ መፍጨት የሰሊጥ ዘይትና አንድ ማንኪያ የስንዴ ዱቄት ጨምሮ በአንድነት መለወስ ማታ ማታ ተቀብቶ ማደርና ጠዋት ለብ ባለ ውኃና በሳሙና መታጠብ፡፡

17ኛ. ለስብራት አፋጣኝ ጥገና
የምስርና የሽንኩርት ሾርባ፣ ቅቅል እንቁላል፣ አንድ ትልቅ ማንኪያ የደቀቀ ጥቁር አዝሙድ በአንድነት ቀላቅሎ ቢያንስ አንድ ቀን ወስዶ በቀጣዩ ቀን አርፎ እንደገና በሁለተኛው ቀን መውሰድ፤ ስብራቱ የዘመናዊ ሕክምና በጀሶ ከታሰረ በኋላ በአቅራቢያ ያለውን አካል በጥቁር አዝሙድ ዘይት ማሸት፤ እስሩ ከተፈታ በኋላ ደግሞ ለብ ባለ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በየቀኑ ማሸት ነው፡፡

18ኛ. ለጠባሳና ለመሳሰሉት
አንድ እፍኝ ጥቁር አዝሙድ በሚገባ ማፍላት የተጎዳውን አካል ማጠብና ለሩብ ሰዓት በተዘጋጀው ፍል ጥቁር አዝሙድ ውስጥ መንከር፡፡ አካሉን ማንቀሳቀስ፡፡ ሳይሸፈን አድካሚ እንቅስቃሴ ሳያደርጉ መቆየት፡፡ ከመኝታ በፊት በየቀኑ ይህን መደጋገም፡፡

19ኛ. ለደም ብዛት
ትኩስ መጠጥ ባሰኘው መጠን ጥቂት የጥቁር አዝሙድ ዘይት ጠብታዎችን ጨምሮ መጠጣት፡፡ በተጨማሪም ገላውን ጥቁር አዝሙድ በመቀባት ቢያንስ በየሳምንቱ አንድ ጊዜ የፀሐይ ሙቀት ቢወስዱ ምንኛ ጥሩ ነበር፡፡

20ኛ. ለኩላሊት ኢንፌክሽን
የጥቁር አዝሙድ ዱቄት በወይራ ዘይት ለውሶ ሕመም በሚሰማበት ቦታ መለጠፍ፤ በተጨማሪም አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ በየቀኑ በባዶ ሆድ ለአንድ ሳምንት ጥሬውን መቃም፣ ከዚያ በኋላ ኢንፌክሽኑ ይወገዳል፡፡

21ኛ. ለሐሞት ከረጢት
አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ፣ ሩብ ማንኪያ የተፈጨ ሬት፣ አንድ ኩባያ ማር ጋር መለወስና ጧትና ማታ መብላት፡፡ ፊትዎ ቅላት እስኪያሳይና ችግሩ እስኪወገድ ድረስ ይህንኑ መፈጸም፡፡ በየዕለቱ በባዶ ሆድ አንድ ሲኒ የወይራ ዘይት መጠጣት አይርሱ፡፡

22ኛ. ለልብና ለደም ዝውውር ችግር
የልብ ሕመምተኛ ሰው በማናቸውም ወቅት እንደ ምግብም፣ እንደመጠጥም እንደአስፈላጊነቱ መውሰድ ይኖርበታል፡፡

23ኛ. ለትውከት
ጥቁር አዝሙድ ከቅርንፉድ ጋር በደንብ ማፍላት ማጣፈጫዎች ሳይጨምሩ በቀን ሦስት ጊዜ መጠጣት፡፡ ሁለተኛ ዙር መጠጣት አያስፈልግም፡፡
24ኛ. ለቃርና ለመሳሰሉት
የተወሰኑ የጥቁር አዝሙድ ቅባት ጠብታዎች በአንድ ኩባያ ትኩስ ወተት ውስጥ ጨምሮ በማር አጣፍጦ መጠጣት፡፡ የቃር ስሜትዎ እንዳልነበር ሆኖ ይጠፋል፡፡ በእንግሊዘኛ (Lettuce) የተሰኘውን ተክል በብዛት መብላትንም አይዘንጉ፡፡

25ኛ. ለዓይን በሽታ
በጥቁር አዝሙድ ዘይት በዓይንና በጆሮ መካከል ያለውን የሰውነት አካል ከመኝታ በፊት ማሸት በማናቸውም ትኩስ መጠጥ ውስጥ አልያም የሥራ ሥር ጭማቂ እንደ ካሮት የመሳሰሉት ውስጥ ጥቂት ጠብታዎች ጨምሮ መጠጣት ነው፡፡

26ኛ. የምግብ ፍላጎትን ለማሳደግ
ከምግብ በፊት ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ አንድ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ቅመሙን በጥርሶችዎ ማድቀቅ፣ ከዚያም ጥቂት ኮምጣጤ ጠብታዎች የተቀላቀለበት አንድ ስኒ ቀዝቃዛ ውኃ ያወራርዱት፡፡

27ኛ. ለቅማልና ለቅጫም
ጥቁር አዝሙድ አድቅቆ መፍጨት በኮምጣጤ ለውሶ ለመታሻ በሚያገለግል መልኩ ማዘጋጀት ፀጉርን ተላጭቶ መቀባት አሊያም ቆዳው ድረስ ዘልቆ እንዲገባ ማድረግና ለሩብ ሰዓት ለፀሐይ ማጋለጥ፡፡ ከአምስት ሰዓታት በኋላ መታጠብ፡፡ ለአንድ ሳምንት ያህል ይህንኑ ደጋግሞ መፈጸም፡፡

28ኛ. ለጥርስ፣ለቶንስልና ለጉሮሮ ሕመም
የጥቁር አዝሙድ አፍልቶ መጉመጥመጥና ለጉሮሮ ችግር እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ አንድ ማንኪያ አዘጋጅቶ ለብ ባለ ውኃ ውስጥ ጨምሮ መጠጣትና በዘይቱም የጉሮሮን ውጫዊ አካል መቀባት በውስጥ ደግሞ መንጋጋን መቀባት፡፡

29ኛ. ከደም ላይ ኮሊስትሮን (ስብን) ለማስወገድ አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዱቄት አንድ ማንኪያ የእኸሊ ቅጠል ከአንድ ስኒ ንጹሕ ማር ጋር ለውሶ በባዶ ሆድ መብላት፡፡

30ኛ. ለሽንት መታቀብ ችግር
ከእምብርት በታች ያለውን የሰውነት አካል በጥቁር አዝሙድ ቅባት ከመኝታ በፊት ማሸት፡፡ አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በአንድ ኩባያ ውኃ አፍልቶ በማር አጣፍጦ ከመኝታ በፊት በእለቱ መጠጣት፡፡

31ኛ. ፊት ላይ እንደ ቡጉር ክብ ሆኖ ለሚወጣ አተርን ያክል ጠጣር ነገር
በሽታ በሽታው የሰፈረበትን አካባቢ በረጅላ (Purslane) ተክል በሚገባ ማሸት ከዚያም የጥቁር አዝሙድ ዘይት 15 ቀናት መቀባት በቀን ሦስት ጊዜ አንድ አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት መጠጣት፡፡

32ኛ. ለሚያስነጥስ
ከባሕር ዛፍ የተጨመቀ ዘይት 40% ከጥቁር አዝሙድ ዘይት ጋር ደባልቆ በሁለቱም አፍንጫ በቀን ሦስት አራት ጊዜ ጠብታ ማድረግ ነው፡፡
ምንጭ፡- ዶ/ር አብዱልናስር አብደላህ

Friday, 27 March 2020

የኮሮና ቫይረስን በሳይንሳዊ ምርምር በተደገፈ የሀገር በቀል እውቀት ከዘመናዊ ሳይንስ ጋር በማቀናጀት ቫይረሱን ለማከም የተሰራው መድሃኒት መሰረታዊ የምርምር ሂደት በማለፍ ተደጋጋሚ የቤተ ሙከራ ሞዴሊንግ ሂደቶችን በስኬት አልፏል፡፡





የኮሮና ቫይረስን በሳይንሳዊ ምርምር በተደገፈ የሀገር በቀል እውቀት ከዘመናዊ ሳይንስ ጋር በማቀናጀት ቫይረሱን ለማከም የተሰራው መድሃኒት መሰረታዊ የምርምር ሂደት በማለፍ ተደጋጋሚ የቤተ ሙከራ ሞዴሊንግ ሂደቶችን በስኬት አልፏል፡፡
ምርምሩ የኮሮና ቫይረስ በዓለም ላይ መከሰቱ ከተሰማ ጊዜ ጀምሮ ከተለያዩ በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጪ ከሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን ሲካሄድ የቆየ ሲሆን ተደጋጋሚ የምርመር ሂደት አልፎ ወደ ምርት እና ቀጣይ የእንስሳት ፍተሻ እና ክሊኒካል ፍተሻ ስራዎች እንዲሸጋገር ተደርጓል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር ኢንጂ.)፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰና ከኢትዮጵያዊያን የባህል ሃኪሞች ጋር እና የህክምና ተመራማሪዎች ጋር በመሆን የሀገር በቀል እውቀቶችን በሳይንሳዊ ሂደቶች በማሳለፍ ለዘመን አመጣሹ ኮሮና ቫይረስ( ኮቪድ -19) ወረርሽኝ ህክምና የተዘጋጀውን መድሃኒት ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችላቸውን ስራ በመስራት ላይ ይገኛሉ።
መድሃኒቱ የመከላከል አቅም የሚጨምር፣ መርዛማነት የሌለው እና አዋጭነቱ የተረጋገጠ ነው፡፡
የምርምር ሂደቱ ተጠናቅቆ ወደ ምርት ለመግባት ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን ዝርዝር መረጃዎችን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ይሰጣል፡፡

Tuesday, 24 March 2020

Contagion



ከኮሮና ቫይረስ ጀርባ ያለው የማይሻር እውነት! የ2003 ዓ/ም #የContagion ፊልም ስለኮሮና በሽታ ትንቢት ( በ አንዲ ላው ) ከዛሬ 9 ዓመታት በፊት እ.አ.አ 2011 በእኛ አቆጣጠር 2003 ዓ/ም Contagion የተባለ ፊልም ይፋ ሆነ፡፡ ፊልሙ ሙሉ በሙሉ የሚያጠነጥነው አንድ ከየት እንደመጣ ባልታወቀ ቫይረስ ላይ ነው፡፡ የፊልሙ መቼት በቻይና፣ እንግሊዝ፣ አሜሪካ… ሲሆን የቫይረሱ መነሻ መቼት ደግሞ ቻይና ነበር፡፡ ይህ ፊልም፣ አንዲት የምታስል እንስት ሴት በአውሮፕላን ወደ ቤቷ ታመራና ቤት ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየተንቀጠቀጠች አረፋም እየደፈቀች ስትሞት ይጀምራል፡፡ በኋላ እንደምጠቅሰው፣ እንስቷ ከአንድ የአሳማ በላች ሼፍ ቫይረሱ ለመጀመርያ ጊዜ እንደያዛት እንመለከታለን፡፡ ቫይረሱም ከዛች የመጀመርያ ቀን ጀምሮ ሲነሣ እናያለን፡፡



ዋናው ዓላማዬ በዚህ ፊልም ስለ ቫይረሱ እንዴት እንደነገሩን ማሳየት ነውና ወደሱ እናምራ !

1. በፊልሙ ላይ ቫይረሱ ከቻይና እንደተነሳ ይታያል፡፡ የኮሮና ቫይረስ መነሻም ቻይና እንደሆነ ልብ በሉ፡፡

2. በፊልሙ ላይ ቫይረሱ የማሳል፣ የማስነጠስና የትኩሳት ባሕርይ እንዳለው ይታያል፡፡ የኮሮና ቫይረስ ምልክትን ልብ በሉ፡፡

3. በፊልሙ ላይ በቫይረሱ የተጠቃ ሰው የሚነካውን ማንኛውም ዕቃ ሌላ ሰው ቢነካ በቫይረሱ እንደሚጠቃ ያሳያል፡፡ የኮሮና ቫይረስ መተላለፊያን ልብ በሉ፡፡

4. በፊልሙ ላይ ቫይረሱ የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቃ ቫይረስ እንደሆነ ይታያል፡፡ የኮሮና ቫይረስ ዋና ታርጌቱን ልብ በሉ፡፡

5. በፊልሙ ላይ ቫይረሱ በመተንፈሻ አካላት ላይ ካሉት Receptor ሴሎች ላይ ልክ እንደ ቁልፍ እንደሚሰካ ይታያል፡፡ የኮሮና ቫይረስን ተመሳሳይ ባሕርይ ልብ በሉ፡፡

6. በፊልሙ ላይ ቻይናዊያንን ወክሎ የምናየው አንድ ቻይናዊ ካራክተር ቫይረሱ በአሜሪካኖች ሆን ተብሎ እንደተለቀቀና የዓለም የጤና ድርጅትም ዐውቆ እንደደበቀው ሲናገር ይታያል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የቻይናና የአሜሪካ ሰጣ ገባ ልብ በሉ፡፡

7. በፊልሙ ላይ በቫይረሱ ምክንያት ት/ቤቶች፣ የንግድ ሱቆች ሲዘጉ ይታያል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ያለውን ሁኔታ ልብ በሉ፡፡

8. በፊልሙ ላይ ቫይረሱ በተከሰተበት ጊዜ የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጥቁር እንደነበረ ይታያል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የኮሮና ቫይረስ ሲከሰት የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ጥቁር ያውም አፍሪካዊ ያውም ኢትዮጵያዊ መሆኑ አጋጣሚ ይመስልሃል?

9. በፊልሙ ላይ ቫይረሱ የተነሣው በአንድ ሌሊት አንድ ዛፍ በግሬንደር ሲቆረጥ የተበጠበጡት የሌሊት ወፎች መንቀሳቀስ ይጀምሩና አንድ ሙዝ መሰል ምግብን በአፋቸው ቆርጠው ሲጥሉና ያንን ምግብም አንድ አሳማ ሲመገብ፣ ይህን አሳማ ደግሞ ቻይናዊው ሼፍ ቆራርጦ ለምግብ በማዘጋጀት ላይ እንዳለ የቫይረሱ መጀመሪያ ተጠቂ የሆነችው ካራክተር ሼፉን ሰላም ስትለው ቫይረሱ እንደተነሣ ይታያል፡፡ የኮሮና ቫይረስ አመጣጥም በሌሊት ወፍ ምክንያት ነው የሚለውን ተረት ተረት ልብ በል፡፡

10. በፊልሙ ላይ ቫይረሱን ለመከላከል ብቸኛ መፍትሔ ተደርጎ የቀረበው እጅን መታጠብ፣ አለመጨባበጥ፣ ፊትን አለመነካካትና ተነጥሎ መቆየት ነው፡፡ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ተደርጎ የተነገሩንን መንገዶች ልብ በሉ፡፡

ፊልሙ ወደፊት የሚመጣውን አስቀምጧል..!?

**ሚስጥራ ብድኖቹ ብልህ ናቸው፡፡ ሊያደርጉ ያሰቡትን እያንዳንዱን ሴራ ቁልጭ አድርገው አስቀድመው በማሳየት አስተዋይ ሰዎችን በፍርሃት ብቻ የማሽመድመድ ሴራን ተክነውበታል፡፡ ** ወደፊት ይምጣ አይምጣ የማይታወቁ ጥቂት ነገሮችን ደግሞ እንዲህ አሳይተውናል፤

1. በፊልሙ ላይ ከ26 ሚልየን በላይ ሕዝብ እንደሚያልቅ ይታያል፡፡

2. በፊልሙ ላይ ብዙ ሚልየን ሕዝብ ካለቀ በኋላ በአፍንጫ የሚወሰድ መድኃኒት እንደሚያገኙ ይታያል፡፡

3. በፊልሙ ላይ የተገኘው መድኃኒት ለዓለም ሕዝብ ሁሉ ስለማይበቃ የሰዎችን የልደት ቀን በዕጣ በማውጣት ዕጣው የወጣላቸውን ብቻ መድኃኒቱን ሲያስወስዱ ይታያል፡፡

4. በፊልሙ ላይ ተገኘ የተባለው መድኃኒት ሕዝቡን ለተጨማሪ በሽታዎች የሚዳርግ እንደሆነ ጋዜጠኛ ሆኖ ከተወነው ካራክተር አፍ ሲወራ ይታያል፡፡

እነዚህ ገና ሊመጣ ያለውን ሊያሳዩ የሚችሉ ከሴራዊ ፊልማቸው የተወሰዱ ዐሳቦች ናቸው፡፡ ዕድሜ ከሰጠን ወደፊት እያስተያየን የምንታዘባቸው ይሆናል፡፡ ""በአጠቃላይ.. ሚስጢራዊ ቡድኖቹ Order Out of Chaos በሚባል መርሐቸው አንድን ሴራ መፈፀም ሲፈልጉ ያን ሴራ ከመፈፀማቸው በፊት በፊልማቸው ይነግሩናል፡፡ በዚህ ፊልም ያየነውም እሱን ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ያለውን ሁኔታ ቁልጭ አድርገው አሳይተውናል፡፡""

ኮሮና ቫይረስ አንዳንዴ ከፈጣሪ የተላከ ቁጣ አንዳንዴም ከእንሳስት የመጣ በሽታ እንደሆነ ብዙዎቻችን እያመነታን እንከራከራለን፡፡ እውነታው ግን እርሱ አይደለም፡፡ ብዙ የዓለም ሕዝቦች ለሚገዙለት ለሰይጣናዊ መንፈስ ቃል የገቡት ሚስጢራዊ ቡድኖቹ .. እንዲህ አይነት ገዳይ በሽታዎችን ለመፈብረክ ከምድር በታች በተገነቡት ምሥጢራዊ የበሽታ መፈብረኪያ ፋብሪካዎቻቸው የዓለምን ሕዝብ የሚቀንሱ በሽታዎችን እያመረቱ ይገኛሉ፡፡ በአሁን ሰዓት የዓለም ሕዝብ ካያቸው በየትኛውም ዘመን ከተነሡ ችግሮች እጅግ አስቸጋሪ የሆነ ቫይረስን ነው ያመረቱት፡፡

<<በችግር-እርምጃ-መፍትሔ በተባለ ዕቅዳቸው መሠረት አንድን ችግር ከፈጠሩ በኋላ፤ መፍትሔ ብለው ሕዝቡን በሚያሳምኑት ግን መፍትሔ ባልሆነ መንገድ #ሌላ_ተያያዥ_ሴራ_ያክላሉ፡፡>> በአሁኑ ሰዓት የሚታየውም ይህ ነው፡፡ ለኮሮና ቫይረስ መፍትሔ ብለው ያቀረቡዋቸው መንገዶች ከማኅበራዊነት ይልቅ በግላዊነት እንድናምን የሚያደርጉ፣ ብቸኝነትን እንድንለማመድና ከሀገራዊ ፍቅር የወጣን ራስ ወዳድ እንድንሆን የሚያደርጉ፣ ባሕሎችን በመሸርሸር ባሕል የለሽ እንድንሆን የሚያደርጉ መንገዶች ናቸው፡፡ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ!!!

በክርስትና፣ ቤተክርስትያን የሚደረጉ ሥርዓቶችን፣ መስቀል መሳለም፣ ቅጥር መሳም… ወ.ዘ.ተ እንዲቀሩ በእስልምናም ተሰብስቦ መስገድ እንዲቀሩ የሚያደርግ የመፍትሔ ዐሳቦችን ዘወትር በየሚድያው እየተነገሩ ነው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ መንፈሳዊ ሥርዓቶችን ቤት ቁጭ ብለን በቲቪ እንድንፈፅምም ሲነገር ተመልክተናል፡፡ እነዚህ ለጊዜው አሪፍ መፍትሔ የሚመስሉ፣ በረጅም ጊዜ ዕቅድ ግን እጅግ ተንኮል ያለባቸውን መፍትሔዎችን ዘወትር በሚድያዎቻቸው ሊያሳምኑን ይሞክራሉ፡፡ እውነታው ግን ይህ ነው፤ #እምነትና_ባሕል_የለሽ_ትውልድን_ መፍጠር፡፡ እውነታው ግን ይህ ነው፤ ባህላዊና ሃይማኖታዊ ሥርዓቶችን መሸርሸር፡፡ ከዚህ ሌላ እውነት የለም፡፡ ለማንኛውም መፍትሔዎቹን አትጠቀሙ አልልም፡፡ መጠንቀቅም መልካም ነው። ግን ሴራውን ተረዱ፣ ተገንዘቡ፡፡ ሴራውን መረዳት ብቻ ሳይሆን ተጠቀሙበት፡፡ ውጤቱ አሁን አይታይም፡፡ ምናልባት ከደረስን በልጆቻችን እናየው ይሆናል እንጂ፡፡
"is that Corona virus biological weapon or Not " ???
ለማንኛውም ይህን ፊልም ተመልከቱት ።!!

Friday, 20 March 2020

ስለ ኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ሊያውቁት የሚገባ መሰረታዊ መረጃ

ስለ ኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ህብረተሰቡ ግንዛቤ አግኝቶ በሽታውን የመከላከልና ስርጭቱን የመቆጣጠር ስራ ላይ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ለማድረግ ከሰታንፎርድ ሆስፒታል የቦርድ አባል የተገኘን መረጃ እንዲህ አቅርበነዋል፡፡
ስለ ኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ሊያውቁት የሚገባ መሰረታዊ መረጃ
1. በአፍንጫዎ ፈሳሽ እና ሲያስሉ አክታ የሚኖርዎት ከሆነ ህመምዎ የተለመደው ጉንፋን ነው፡፡
2. በኮሮና ቫይረስ (COVID-19) የሚመጣ ተዛማች በሽታ ሳምባን የሚያጠቃ ሲሆን ምልክቱም አፍንጫ ላይ ፈሳሽ (እርጥበት) የሌለው ደረቅ ሳል ነው፡፡
3. ይህ ኮሮና ቫይረስ (COVID-19) በመባል የሚታወቀው አዲስ በሽታ አምጪ ቫይረስ ሙቀትን የሚቋቋም አይደለም፡፡ በ 26/27 ድግሪ ሴንቲግሬድ በሆነ የሙቀት መጠን የሚሞት ነው፡፡ የፀሐይ ሙቀትን ይጠላል፡፡
4. በቫይረሱ የተጠቃ አንድ ሰው ቢያስነጥስ፤ ቫይረሱ መሬት ሳያርፍ በአየር ላይ መነሳፈፍና መጓዝ የሚችለው ለ10 ጫማ ያክል ነው፡፡ ቫይረሱ አየር ወለድ ቫይረስ አይደለም፡፡
5. ኮሮና ቫይረስ (COVID-19) በብረት ነገሮች ላይ ቢያስ ለ12 ሰዓታት ያህል በህይወት መቆየት የሚችል ሲሆን ስርጭቱን ለመከላከል እና በቫይረሱ እንዳይጠቁ ማንኛውንም ብረት ነክ ዕቃ በነኩ ቁጥር ወዲያውኑ እጅን በንጽህና መጠበቂያ ኬሚካል (ሳሙና) በደንብ መታጠብ ያስፈልጋል፡፡ በጨርቅ ነክ (fabric) ላይ ከ6-12 ሰአታት በህይወት ሊቆይ ይችላል፡፡ ነገር ግን የተለመደው የልብስ ማጠቢያ ሳሙና ይገድለዋል፡፡
6. የሞቀ ውሃን መጠጣት ሁሉንም የቫይረስ አይነቶች ለማዳከም ውጤታማ ነው፡፡ ስለሆነም ፈሳሾችን ከበረዶ ጋር ላለመጠጣት ይሞክሩ።
7. ኮሮኖ ቫይረስ በእጅ ላይ ከ5-10 ደቂቃዎች ብቻ በህይወት ሊቆይ ይችላል፡፡ ስለሆነም እጅን ደጋግመው በሳሙና በደንብ ይታጠቡ፡፡ ከታጠቡም በኋላ ወዲያውኑ በሚመደርጉት እንቅስቃሴ እጅ ላይ ቫይረሱ ሊኖር ስለሚችል ሳያውቁት ዓይንን ሊያሹ፤ አፍንጫን ሊነካኩና ሌሎች መሰል ነገሮችን ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ከነዚህ ድርጊቶችም ይቆጠቡ፡፡
8. ሞቅ ባለ ውሃ ትንሽ ጨው በመጨመር አፍን መጉመጥመጥ እና ከኢንፌክሽን ነጻ ማድረግ ቫይረሱን ለመከላከል አንድ መንገድ አድርጎ መጠቀም ይገባል፡፡
በኮሮና ቫይረስ (COVID-19) የተጠቃ ሰው ምልክቶቹ ምንድን ናቸው
1. ቫይረሱ መጀመሪያ ጉሮሮን ያጠቃል፡፡ ስለዚህ ለ3 ወይም 4 ቀናት የሚቆይ የጉሮሮ ህመም ይኖራል፡፡
2. ከፍተኛ ትኩሳት ያመጣል፡፡
3. ከዚያም ቫይረሱ ከአፍንጫ ፈሳሽ ጋር ይዋሃድና አየርን ከአፍንጫ/ ከአፍ/ ወደ ሳንባ የሚያመላልሰውን ቱቦ (trachea) ያጠቃል፡፡ በመቀጠልም ሳንባ ውስጥ ይገባና የሳንባ ምች (pneumonia) ያስከትላል፡፡ ይህ ሂደት 5 ወይም 6 ተጨማሪ ቀናት ይወስዳል።
4. የሳንባ ምቹ ከፍተኛ ትኩሳት እና የመተንፈስ ችግር ያስከትላል፡፡
5. በኮሮና ምክንያት የሚመጣው የአፍንጫ መታፈን በጉንፋን ምከንያት ከሚያጋጥመው የተለመደ ዓይነት መታፈን ጋር ተመሳሳይ አይደለም፡፡ የመዘጋት፤ አየር የማጠርና ራስን መቆጣጠር ያልቻሉ እንደሆነ ይሰማዎታል፡፡ በዚህ ጊዜ አፋጣኝ ትኩረት እና ክትትል ያስፈልግዎታል፡፡
የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ህመምን በሚያክሙ የጃፓን ሐኪሞች የተሰጠ ጥብቅ ምክር
1. ሁሉም ሰው አፉ እና ጉሮሮው እርጥብ መሆናቸውን ማረጋገጥ አለበት፡፡ በፍፁም መድረቅ የለባቸውም፡፡ ቢያንስ በየ15 ደቂቃ ጥቂት ውሃ ይጎንጩ፡፡ ምክንያቱም ቫይረሱ ወደ አፍዎ ቢገባም እንኳን የሚጠጡት ውሃ ወይም ሌሎች ፈሳሾች ጉሮሮዎን በማጠብ ወደ ሆድ ውስጥ ያስገባቸዋል፡፡ ቫይረሱ ወደ ሆድ አንድ ጊዜ ከገባ በኋላ በጨጓራ ውስጥ ያለው አሲድ ቫይረሱን ሙሉ በሙሉ ይገድለዋል፡፡ በመደበኛነት በቂ ውሃ የማይጠጡ ከሆነ ቫይረሱ ወደ አየር ማስገቢያ ቧንቧ፤ ከዚያም ወደ ሳንባ ውስጥ ሊገባ ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ በጣም አደገኛ ነው፡፡
2. አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ለብዙ ቀናት ምንም ዓይነት የኢንፌክሽን ምልክት ለብዙ ቀናት ላያሳይ ይችላል፡፡ ታዲያ አንድ ሰው በበሽታው መያዙን እንዴት ሊያውቅ ይችላል? በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ትኩሳት እና / ወይም ሳል ኖሯቸው ወደ ሆስፒታል በወቅቱ ሲሄዱ አብዛኛውን ጊዜ ግማሽ ሳንባቸው (50%) በቫይረሱ ተጎድቶ (fibrosis) ነው የሚገኘው፡፡ ይህ ደግሞ በጣም የረፈደ ነው፡፡ የሳንባ ግማሽ (50%) በቫይረሱ ከተጎዳ በኋላ (fibrosis ከሆነ) ሊቀለበስ አይችልም። ስለሆነም ምልክቱ ከጅምሩ የታየባቸው ሰዎች በአስቸኳይ ወደ ሆስፒታል መሄድ ለባቸው፡፡
ራስን መፈተሸ ዘዴ
በዚህ ረገድ የታይዋን ባለሙያዎች ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ((COVID-19)) ላለመያዛቸው በቀላሉ ራሳቸውን የሚፈትሹበት ዘዴን እንዲህ ይመክራሉ፡፡ በየቀኑ ጠዋት ጠዋት አየር በረጅሙ ያስገቡ እና ወደ ውጪ ሳያስወጡ ከ10 ሰከንድ በላይ ለሆነ ጊዜ ይዘው ለመቆየት ይሞክሩ፡፡ ይህን ልምምድ ያለ ሳል፤ ያለ መጨናነቅ፤ ያለ መወጣጠር እና ሌላም ማድረግ ከቻሉ፤ ሳንበዎ በኢንፌክሽን ያልተጠቃ (no Fibrosis) መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ በእንዲህ ያለ አስቸጋሪ ጊዜ፣ እባክዎን በየቀኑ ጠዋት ጠዋት ንፁህ አየር ባለበት አካባቢ የዚህ አይነት ልምምዶችን በመስራት የሳንባዎን ጤንነት ያረጋግጡ ፡፡
በኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ስርጭትን ለመቀነስና በበሽታው ላለመያዝ ሊደረግ የሚገባው ጥንቃቄ
1. ሰዎች በሚያስነጥሱበት እና በሚያስሉበት ወቅት አፍና አፍንጫን በሶፍት ወይም በክርን መሸፈን፤
2. እጃችንን በሳሙና እና በበቂ ውሃ መታጠብ፤
3. ከሌሎች ሰዎች ጋር ንኪኪን ማቆም (ለምሳሌም አለመጨባበጥ፤ ሰዎች በብዘት የሚሰባሰቡበትና መጨናነቅ ያለበት ቦታ አለመገኘት የመሳሰሉት)፤
4. የተጠቀምንበትን ሶፍት ወደ መፀዳጃ ቤት በመጨመር ከፍሳሹ ጋር እንዲወገድ ማድረግ፤
5. በፈሳሽ ነገሮችን (ውሃ) ቶሎ ቶሎ መጠጣት / መጎንጨት፡፡
ይህን መረጃ ለስራ ባልደረባዎ፣ ለጓደኛዎ እና ለቤተሰብዎ ያካፍሉ፡፡ ሁሉም ጥንቃቄ ያድርግ፡፡ በሃገራችን የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የሚረዱ ጥንቃቄዎችን በማድረግ የዓለም ስጋት የሆነውን ወረርሽኝ የመቆጣጠር ስራ ላይ የበኩላችንን ድርሻ እንወጣ፡፡
ማሳሰቢያ፡- ምልክቱ የታየባቸው ሰዎች ቢያጋጥምዎ ወዲያውኑ በ 8335 ነጻ የስልክ መስመር ላይ በመደወል ሪፖርት ያድርጉ፡፡

የመረጃው ምንጭ፡- Stanford Hospital Board Member!!