Monday, 16 December 2013

10ሩ የማንዴላ ድንቅ አባባሎች

1,የአመታት እስር ነፃ ከመውጣት አያግደንም፡፡ የአመታት ጭቆናና ግፍም አያስቆመንም፤ እናም  ትግላችንን አናቆምም፡፡

2, ህይወትን እናንተ ከምትወዱት ባነሰ ደረጃ የምወድ አይደለሁ፤ ሆኖም በተፈጥሮ ያገኘሁትን መብት መሸጥ እንዲሁም ህዝቤ በተፈጥሮ ያገኘውን ነፃ የመሆን መብት የመሸጥ ፍላጎት የለኝም፡፡ (እ.ኤ.አ 1984-1989 የአፓርታይድ ፕሬዝዳንት የነበሩት ፒትረ ዊለልመ ቦንታ ከእስር ወጥቶ ትግሉን በመተው አርፎ እንዲቀመጥ ሲጠይቁት የሰጠው ምላሽ)

3.ፊታችሁ የቆምኩት እንደነብይ ሳይሆን እንደ ትሁት አገልጋያችሁ ነው፡፡ እዚህ እንቆም ያበቃኝ ያለመታከት በጀግንነት የከፈላችሁት ዋጋ ነው፡፡ ስለሆነም ቀሪው እድሜዬ በናንተ እጅ ነው፡፡ (ከእስር ሲወጣ የተናገረው) 

4.ከእስር ከወጣሁ ጀምሮ ይበልጥ የተገነዘብኩት ትክክለኞቹ ታሪክ ሰሪዎች የሀገራችን ተራ ዜጎች መሆናቸውን ነው፤ ወደ ፊት በሁሉም ውሳኔዎች ላይ የሚኖራቸው ተሳትፎ እውነተኛው የዴሞክራሲና የነፃነት ዋስትናችን ነው፡፡ (ከእስር ሲወጣ የተናገረው)

5.ወደ ፊት ለምናደርገው ውሳኔ ያለፈው ተሞክሮ ግብአት ሊሆነን ይችላል፤ ሆኖም ምርጫችንን አይወስነውም፡፡ ያለፈውን በመመልከት መልካሙን በመያዝ መጥፎውን ወደኋላ እንተዋለን፡፡ 

6.ትግል ህይወቴ ነው፤ እስከ ህይወቴ ማብቂያ ለነፃነት እታገላለሁ፡፡

7.ለብዙሀኑ ድምፅ እንቆማለን እንጂ ለጥቁሮች የበላይነት አንቆምም፡፡

8.ወደ ነፃነት የሚደረግ ቀላል ጉዞ የለም፤ የምንፈልገው የተራራ አምባ ላይ ከመውጣችን አስቀድሞ የትም ቢሆን ብዙዎቻችን በተደጋጋሚ በሞት ሸለቆ ማለፍ ግድ ይለናል፡፡ (በኤ.ኤን.ሲ ኮንፈረነስ ላይ የተናገረው) 

9.አንድ ታላቅ ኮረብታን ስወጣ የሚገለጥልኝ ምስጢር ሌሎች የምወጣቸው በርካታ ኮረብቶች እንዳሉ ነው፡፡ 

10.የሰው መልካምነት ሊከለል የሚችል ሆኖም የማይጠፋ ብርሃን ነው፡፡

No comments:

Post a Comment