Friday, 30 May 2014

ካርልኃይንስ በኧም አረፉ

በወጣትና በጎልማሳነታቸዉ ዘመን በተጫዎቷቸዉ ፊልሞች ኦስትሪያና ጀርመን ዉስጥ ከፍተኛ አድናቆትና ያተረፉት በኧም ኢትዮጵያ ዉስጥ ችግረኞችን የሚረዳዉን ሜንሽን ፉር ሜንሽን የተሠኘዉን ግብረ-ሠናይ ድርጅት የመሠረቱና ለረጅም ጊዜ የመሩ በጎ አድራጊም ነበሩ


ኦስትሪያዊዉ የፊልም ተዋኝና በጎ የአድራጊ ድርጅት መሥራች ካርልሐይንስ በኧም አረፉ። 86 ዓመታቸዉ ነበር።በወጣትና በጎልማሳነታቸዉ ዘመን በተጫዎቷቸዉ ፊልሞች ኦስትሪያና ጀርመን ዉስጥ ከፍተኛ አድናቆትና ያተረፉት በኧም ኢትዮጵያ ዉስጥ ችግረኞችን የሚረዳዉን ሜንሽን ፉር ሜንሽን የተሠኘዉን ግብረ-ሠናይ ድርጅት የመሠረቱና ለረጅም ጊዜ የመሩ በጎ አድራጊም ነበሩ። በኧም የመሠረቱትና የመሩት ድርጅት ኢትዮጵያ ዉስጥ ሰወስት ሆስፒታሎችን ጨምሮ አንድ መቶ የጤና ተቋማትን፤ ከሰወስት መቶ ስልሳ በላይ ትምሕርት ቤቶችን አስገንብቷል። ታዋቂዉ የቀድሞ ፊልም ተዋናይና «ሰዎች ለሰዎች» የተሰኘዉ የርዳታ ድርጅት መሥራች የ86 ዓመቱ ካርል ኃይንስ በኧም ትናንት ምሽት በኦስትርያ ዛልስቡርግ ከተማ አጠገብ በምትገኘዉ ጎርዲግ ከተማ ዉስጥ ማረፋቸዉን የከተማዉ ቃል አቀባይ ገልጿል። «ሜንሽን ፎር ሜንሽን» የተሰኘዉ ግብረሰናይ ድርጅት መሥራች ካርል ኃይንስ በኧም በጎርጎረሳዉያኑ 1950 ዓ,ም ሲሲ በተሰኘዉ ፊልም ላይ ንጉስ ፍራንዝ ዮሴፍ በሚል፤ ገጸ-ባህሪ እጅግ ከፍተኛ እዉቅናን ማግኘታቸዉ ይታወቃል። ትዉልዳቸዉ በጀርመን ዳርምሽታት ከተማ የሆነዉ ካርል ኃይንዝ በኧም፤ ለረጅም ግዜ ታመዉ የአልጋ ቁራኛ እንደነበሩም ተመልክቶአል። በዚህም ኢትዮጵያዉያንን ለመርዳት ያቋቋሙት «ሰዎች ለሰዎች» የተሰኘዉን ድርጅት ኢትዮጵያዊት ባለቤታቸዉ ወ/ሮ አልማዝ በኧም ለጥቂት ዓመታት በዋና ተጠሪነት ሲያስተዳድሩ ከቆዩ በኃላ፤ ከባለፈዉ ዓመት ታሕሳስ ወር ጀምሮ ባለቤታቸዉን ካርል ኃይንዝ በኧምን ለማስታመም፤ ድርጅቱን በዋና ኃላፊነት መምራት ማቆማቸዉ ይታወቃል። ድርጅታቸዉ በመሥራቹ ሞት የተሠማዉን ሐዘን ገልጿል። 


Sunday, 18 May 2014

Sudan woman faces death for apostasy



Meriam Yehya Ibrahim Ishag told the judge: "I am a Christian and I never committed apostasy"

A Sudanese court has sentenced a woman to hang for apostasy - the abandonment of her religious faith - after she married a Christian man.
Amnesty International condemned the sentence, handed down by a judge in Khartoum, as "appalling and abhorrent".
Local media report the sentence on the woman, who is pregnant, would not be carried out for two years after she had given birth.
Sudan has a majority Muslim population, which is governed by Islamic law.
"We gave you three days to recant but you insist on not returning to Islam. I sentence you to be hanged to death," the judge told the woman, AFP reports.
Western embassies and rights groups had urged Sudan to respect the right of the pregnant woman to choose her religion.
The judge also sentenced the woman to 100 lashes after convicting her of adultery - because her marriage to a Christian man was not valid under Islamic law.
This will reportedly be carried out when she has recovered from giving birth.
Earlier in the hearing, an Islamic cleric spoke with her in a caged dock for about 30 minutes, AFP reports.
Then she calmly told the judge: "I am a Christian and I never committed apostasy."
Rival protesters
Amnesty International said the woman, Meriam Yehya Ibrahim Ishag, was raised as an Orthodox Christian, her mother's religion, because her father, a Muslim, was reportedly absent during her childhood.
In court, the judge addressed her by her Muslim name, Adraf Al-Hadi Mohammed Abdullah.
She was convicted of adultery on the grounds that her marriage to a Christian man from South Sudan was void under Sudan's version of Islamic law, which says Muslim women cannot marry non-Muslims.
The woman was originally sentenced to death on Sunday but given until Thursday to return to Islam.
There were small groups of protesters outside the court - both her supporters and those who back the punishment.
About 50 people chanting "No to executing Meriam" were confronted by a smaller group who supported the verdict, but there was no violence.
Amnesty's Sudan researcher Manar Idriss condemned the punishments, saying apostasy and adultery should not be considered crimes.
"The fact that a woman has been sentenced to death for her religious choice, and to flogging for being married to a man of an allegedly different religion is appalling and abhorrent," he said.
The BBC's Osman Mohamed, in Khartoum, says death sentences are rarely carried out in Sudan.
Her lawyers plan an appeal to a higher court to get the sentence overturned.
On Tuesday, the embassies of the United States, Canada, the United Kingdom and the Netherlands issued a joint statement expressing "deep concern" about the case and urging Sudan to respect the right to freedom of religion, AFP says.
The woman was arrested and charged with adultery in August 2013, and the court added the charge of apostasy in February 2014 when she said she was a Christian and not a Muslim, Amnesty said.
The group called for her immediate release.
She is said to be eight months' pregnant.

የውጭ ብድርና ዕርዳታ ያለሥራ ከተከማቹ የመንግሥት ንብረቶች ጋር ተመጣጣኝ ሆኗል›› የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን

-የንብረት አስተዳደር ችግር አሳሳቢ ሆኗል
በመንግሥት መሥርያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች ያለሥራ ተከማችተው የሚገኙ ንብረቶች አገሪቱ በየዓመቱ በዕርዳታና በብድር ከምታገኘው ገንዘብ እንደማይተናነስ፣ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጥናት አመለከተ፡፡
ኮሚሽኑ የመንግሥት መሥርያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች የንብረት አስተዳደር ለሙስናና ለብልሹ አሠራር ያለው ተጋላጭነት ላይ ያዘጋጀው የዳሰሳ ጥናት እንደሚያመለክተው፣ ከአገሪቱ አጠቃላይ ምርት ድርሻ ውስጥ እስከ 14 በመቶ የሚደርሱት የተለያዩ አገራዊ ተግባራትን ለማከናወን በግብዓትነት የሚያገለግሉ ቋሚና አላቂ ንብረቶች ናቸው፡፡ የመንግሥት ተቋማት ከሚመደብላቸው በጀት ውስጥ ከ60 አስከ 70 በመቶ የሚሆነው ለዕቃና ለአገልግሎት ግዥ ተግባር የሚውል ቢሆንም፣ ከፍተኛ በጀት የፈሰሰበት የመንግሥት ንብረት ከብክነት፣ ከብልሽትና ከስርቆት ለመከላከል የተሰጠው ትኩረት አናሳ መሆኑን ጥናቱ ይጠቁማል፡፡ 
በጥናቱ ላይ ለመወያየት በተዘጋጀው መድረክ የተገኙት የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ወዶ አጦ እንደተናገሩት፣ በመንግሥት ተቋማት ውስጥ የሚታየው የንብረት አስተዳደር የሙስና ተጋላጭነትና ብልሹ አሠራር አሳሳቢ ሆኗል፡፡ 
በየተቋማቱ ጥራታቸውን ያልጠበቁ ምርቶች ግዥ በከፍተኛ ወጪ እንደሚፈጸም፣ የተገዙ ንብረቶች ከአያያዝ ጉድለት ተገቢውን አገልግሎት ሳይሰጡ ለብክነትና ለግለሰቦች የግል ጥቅም ማግኛ መዋላቸውንም አቶ ወዶ አስረድተዋል፡፡
በመንግሥት ተቋማት በሚታየው የንብረት አስተዳደር ለሙስና ተጋላጭነትና ብልሹ አሠራር ላይ ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ከተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎች ጋር የተወያዩት ምክትል ኮሚሽነር አቶ ወዶ፣ ‹‹ከምንም በላይ የራሳችሁን ጓዳ መፈተሽ አለባችሁ፡፡ ችግሩ የጋራና አሳሳቢ ነው፡፡ ሆኖም መቅረፍ ይቻላል፤›› ብለዋል፡፡ 
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴን ወክለው የተገኙት ወይዘሮ ሣራ ብሩ፣ በመንግሥት ተቋማት ላይ የሚታየው የንብረት አስተዳደር ችግር ሁልጊዜም የሚነገር ሆኖም በተነገረው ልክ ባለመሠራቱ ችግሩን መፍታት አለመቻሉን አስገንዝበዋል፡፡ በንብረት አስተዳደር ላይ ለሚታየው ብልሹ አሠራር ከታችኛው ሠራተኛ እስከ ኃላፊው ድረስ ተጠያቂ አለማድረግም ችግሩን አስፋፍቶታል ብለዋል፡፡
የመንግሥትና የሕዝብ ሀብትና ንብረት ያላግባብ እየባከነ በመሆኑ ምክንያት በመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና በልማት ድርጅቶች የንብረት አስተዳደር ላይ በኮሚሽኑ የተዘጋጀው የዳሰሳ ጥናት እንደሚያመለክተው፣ በተለያዩ ጊዜያት ወደ ኮሚሽኑ የሚቀርቡ መረጃዎችን መሠረት በማድረግ የተሠሩ የአሠራር ሥርዓት ጥናቶችና የምርመራ ሥራ ውጤቶች በንብረት አስተዳደር ላይ የአሠራር ክፍተቶች እንዳሉና በዚህም የተነሳ ከፍተኛ የአገር ሀብት ብክነት መኖሩን አመላክተዋል፡፡
ኮሚሽኑ በአንዳንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች ላይ ያከናወናቸውን የአሠራር ሥርዓት ጥናቶችና በተጨማሪነት ያካሄዳቸውን የዳሰሳ ጥናቶች መሠረት በማድረግ ባዘጋጀው ዳሰሳ ጥናት መሠረት፣ አብዛኞቹ የተቋማት ኃላፊዎች ንብረቶች እንዲገዙ ከማድረግ በዘለለ የተገዙትን ንብረቶች በአግባቡ ተቆጣጥሮ የመረከብ፣ መዝግቦና ጠብቆ የመያዝ፣ ለተገቢው ሥራ በአግባቡ የመጠቀምና የአገልግሎት ጊዜያቸው ሲያበቃ ለማስወገድ ተገቢውን ክትትልና ትኩረት እንደማይሰጡ ታይቷል፡፡
በተቋማቱ ንብረቶች ተገዝተው ሲገቡ ጠንካራና ወጥነት ያለው የቁጥጥር ሥርዓት አለመኖር፣ ንብረቶች ለብልሽት፣ ለብክነት፣ ለቁጥጥር በማያመችና ለስርቆት በተጋለጠ ሁኔታ የሚያዙ መሆናቸው፣ ወጪ የተደረጉ ንብረቶች ለተጠየቁበት ተግባር መዋላቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል አሠራር አለመኖር፣ ወጥነት ያለውና የተደራጀ የቋሚ ንብረቶች የቁጥር አሰጣጥ፣ መዝግቦ የመያዝና የቁጥጥር ሥርዓት አለመኖሩንም ጥናቱ አመልክቷል፡፡
ለተቋማቱ ሥራ የማያገለግሉ ንብረቶች ለረዥም ጊዜ ሥራ ላይ ሳይውሉ አከማችቶ መያዝ፣ የዕቃ ገቢ፣ ወጪ መጠየቂያና ወጪ ማድረጊያ ሰነዶች በአግባቡ አለመጠቀም፣ አገልግሎት የማይሰጡ አሮጌ ንብረቶች በሰነድ ተመዝግበው የሚያዙበትና በየጊዜው የሚወገድበት አሠራር አለመኖር፣ የንብረት ማሰባሰብና መልሶ የመጠቀም መመርያ አለመኖር፣ ከፍተኛ ዋጋ የሚያወጡ ቋሚ ንብረቶች በሰነድ መዝግቦ አለመያዝና በኃላፊነት ተረክቦ የሚያስተዳድር አካል አለመኖር፣ በተገቢ ሙያተኛ አለማሠራትና የውስጥ የቁጥጥር ሥርዓት ጠንካራ አለመሆን በተቋማቱ የታዩ ዋና ችግሮች መሆናቸው ተዘርዝሯል፡፡    
 

Tuesday, 13 May 2014

EPRDF - TPLF Government quietly disintegrating (IO)

The general election looming ahead in 2015 is already casting a shadow over the Ethiopian government, whose sole uniting bond would seem to be its praise for the memory of its late Prime Minister Meles Zenawi. His portraits are on all the walls in Addis Ababa, which was not the case when he was alive, and in the Federal Assembly a video projector plays his speeches with the aim of inspiring the new MPs. And yet, since Meles Zenawi died in August 2012, the federal government has been rudderless, lacking a descendent. His successor as Prime Minister, Haile Mariam Desalegn, has neither the grip nor the political clout and has not managed to impose himself on the other political leaders. He frequently has to be content with merely dealing with everyday business. While it is true the Ethiopian State, whose tradition goes back a long way, has not fallen into decadence, the different factions and regionalist tendencies are making federal power increasingly fragmented.
Divisions produce inertia - Going beyond appearances, the ruling coalition Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) is in an embryonic crisis state. Its central core, the Tigray People’s Liberation Front (TPLF), is deeply divided between the “provincial” faction led by Tigray Regional State President Abay Woldu, and the “modern nationalist” faction headed by Deputy Prime Minister Debretsion Gebremichael, not to forget the various other Tigrayan sub-factions such as those of the elderly Marxist Sebhat Nega and the Meles Zenawi’s widow Azeb Mesfin. Facing this inter-Tigrayan squabble, the Amhara in the ANDM and the Oromo in the OPDO (two of the parties in the ruling coalition) are watching from the wings, biding their time before they go into the arena. This freezes the decision-making power, as each faction does not want to make the wrong decision and yield an advantage to its rivals. In early April, speaking on a live TV debate (a rare event in itself),Amare Aregawi the editor of The Reporter asked the Prime Minister who is it that makes the decisions in his office and whether he is capable of making any himself. Much to the surprise of the viewers who are used to seeing decisiveness on their screens, Haile Mariam Desalegn mumbled an unconvincing response, confirming that the question had indeed struck home.
The economy and diplomacy are broken - Ethiopian diplomacy suffers from a lack of leadership at the top of country. Questions about the situation in Somalia are left to the head of the Ethiopian army which is intervening directly in its neighbour’s territory. In the case of the IGAD mediation in the South Sudan crisis, the former foreign affairs minister Seyoum Mesfin was recalled from his post of ambassador to Beijing to lead the mediation. He nevertheless played a fairly effective role of mediator, which was largely taken over by the Ugandan President Yoweri Museveni even though Ethiopia did at the time hold the presidency of IGAD. Similar blockages have produced similar effects in the management of the State-owned companies. The telephone network run by Ethio Telecom (formerlyETC) provides a very poor service, mainly because of frequent electricity outages which also affect the water distribution system when the electric pumps stop running. The cause is breakdowns of the aging transformers purchased second-hand from India by the Ethiopian Electric Power Corporation(EEPCO) several years ago. Today, EEPCO and ETC are squabbling over who should pay the cost of renovating the electricity system, a problem which Debretsion Gebremichael, the chairman of the EEPCO and ETC boards, has been unable to settle.
Regionalism becoming more intense - Since the end of April, the federal police have brutally repressed student protests against the Master Plan in several universities in the Oromia Regional State. This Master Plan involves the expansion of Addis Ababa whose mayor, Diriba Kuma, is also an Oromo. In the students’ view, this project would eat into Oromo land and reduce the area their language is used. This regionalist exacerbation is illustrated by certain of the student slogans, proclaiming “Oromia for the Oromos“ and by the start of misdemeanours against Amhara farmers obliged to leave their land and take refuge in Addis Ababa. Certain TPLF officials have no qualms to explain that in their view, some ultra-regionalist elements of the ruling OPDO are discreetly fuelling this student protest movement against the Master Plan

የኢህአዴግ ብሔርተኝነትና የተቀናጀ ማሰተር ፕላን…? በግርማ ሠይፉ ማሩ (የተከበሩ የፓርላማ አባል)

 የጣና ሀይቅ የጎንደር ነው ወይስ የጎጃም? የሚል የይገባኛል ጥያቄ እንዳለ ያወቅሁት በደርግ የመጨረሻ ዘመን ምስራቅ ጎጃም እና ምዕራብ ጉጃም የሚል የአሰተዳደር አካባቢ የተመሰረተ ሰሞን ነው፡፡ በዚያን ጊዜ ጢስ አባይ ፏፏቴን ለማየት እየሄድን እያለ አብሮን ያለው ጎንደሬ ጓደኛችን አካባቢው የጎንደር መሆኑን ለማረጋገጥ ማየት ያለብን እረኛውን መሆኑን ነገረን፡፡ እረኛን አይቶ መሬቱን የጎንደር ወይስ የጎጃም ተብሎ እንዴት ይለያል ብለን በአግራሞት ተመለከትነው፡፡ እረኛው የሚጠብቃቸው በጎቹ እረኛቸውን ተከትለው የሚሄዱ ከሆነ ጎንደሬዎች ናቸው አለን፡፡ እንዳለንም በጎቹ እረኛውን ተከትለው ሲሄዱ ተመልክተን፡፡ ፈጠን ብዬ ሄጄ እረኛውን ጎንደሬ ነህ ወይስ ጎጃሜ? ስለው ጎንደሬ ነኝ አለኝ፡፡ ታዲያ አሁን ይህ አካባቢ ጣናን ጨምሮ ምዕራብ ጎጃም ተባለ ምን ይሰማችኋል? ብዬ ጥያቄ አሰከተልኩበት፡፡ እረኛው ለዕድሜ ልኬ የሚሆን ትምህርት ሰጠኝ፡፡ “ዋ! ውሃም መሬቱም እዚሁ ድሮ ያለበት አይደለ?” አለኝ በሚያስደንቅ ፍጥነት፡፡

የተማረው ጓደኛዬ የጎንደር መሬትና ውሃ ለጎጃም ተሰጠ ብሎ ሲብሰለሰል እረኛው ችግር የለም የት ይሄዳል ብሎ ከተማረው ጓደኛዬ የተሻለ መልስ ሰጠኝ፡፡ የጎንደር መሬት ለትግራይ ተሰጠ የሚለውን የክልል ድንበር ችግር ብዙም ሰሜት የማይሰጠኝ የትም ቢሆን መሬቱ በኢትዮጵያ ግዛት ክልል በመሆኑ ይመስለኛል፡፡ ይህ የጎንደር እረኛ ያስተማረኝ ሊሆን ይችላል፡፡ ከእረኛ ለመማር ዝግጁ ከሆነን ማለቴ ነው፡፡ በተጨማሪም በኢትዮጵያዊነቴ እንጂ በዘር ተቆጥሮ የሚሰጠኝ መሬት ስለማልፈልግ ነው፡፡ ወደዚህ ትዝታ የመረኛ በቅርቡ በአዲስ አበባ እና ፊንፊኔ ዙሪያ የሚገኙ የኦሮሚያ ከተሞች የተቀናጀ ማስተር ፕላን አስመልክቶ ደም አፋሳሽ ድጋፍና ታቃውሞ መነሳቱ ነው፡፡
የከተማ ኮንስትራክሽን እና ቤቶች ሚንሰትር አቶ መኩሪያ ኃይሌ ለምክር ቤት ቀርበው ሪፖርት ሲያቀርቡ ይህን ጉዳይ በሚመለከት “የአዲስ አበባና ፊንፊና ዙሪያ ከተሞች የተዘጋጀው የተቀኛጀ ፕላን ዝግጅት ይህን ያህል ጫጫታ የፈጠረው የኢህአዴግ ፖሊሲ ውጤት ነው ብለው ያምናሉ? መቼም ይህን ጉዳይ በተቃዋሚዎች አያሳብቡም” የሚል አሰተያየት አዘል ጥያቄ አቅርቤ ነበር፡፡ ሚኒሰትሩ መልስ ሲሰጡ ለልማት በጋራ መቆም እንዳለብን ገልፀው በአሁኑ ጊዜ እገሌ ነው ጥፋተኛ ማለት ተገቢ እንዳልሆነ ነገር ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን በዓለም ዕይታ መነፅር ውስጥ መሆናችንን በመጥቀስ በተፈጠረው ሁኔታ ደሰተኛ እንዳልሆኑ የሚገልፅ ሰሜታቸውን መደበቅ ተሰኖዋቸው ነበር፡፡ እንዲህም ሆኖ ግን ከቅላፂያቸው ተቃዋሚን ለመከሰስ ፍላጎታቸውን መረዳት አያሰቸግርም ነበር፡፡ በእኔ እምነት ለዚህ ለተነሳው ተቃውሞ መንስዔዎች የኢህአዴግ የተሳሳቱ ፖሊሲዎች ናቸው ብዬ አምናለሁ፡፡
አሁን በዩኒቨርሲት የሚገኙት ወጣቶች በሙሉ ማለት ይቻላል የኢህአዴግ ትውልዶች ናቸው፡፡ በኢህአዴግ የትምህርት ፖሊሲና አጠቃላይ ፖሊሲ አቅጣጫ ኢትዮጵያዊነትን እያኮሰሰ ጎጠኝነትን እያሞገሱ የመጡ ናቸው፡፡ የኦሮሚያ ልጆች ከክልላቸው ወጥተው ከሰሜን እሰከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ተቀጥረው መስራት እንዲሁም ኢንቨስት አድርገው ቀጣሪ ሊሆኑ እንደሚችሉ አልተማሩም፡፡ አብዛኛዎቹ ክልሎችም እንደዚሁ ናቸው፡፡ በተለየ ሁኔታ ይህ እየተመቻቻላቸው ካሉት በስተቀር፡፡ ይህ በኢህአዴግ አገላለፅ ጠባብነት የሚለው ሲሆን የዚህ ምንጩ ደግሞ እራሱ የኢህአዴግ ፖሊሲ ነው፡  እነዚህ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከዚህ አሰተሳሰብ ተነስተው የአዲስ አበባ መሰተዳድር ከፊንፊኔ ዙሪያ ከተሞች ጋር የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተዘጋጀ ሲባሉ የእኛ የሚሉት የኦሮሚያ መሬት የእኛ በማይሏቸው ሌሎች ኢትዮጵያዊያኖች መሬታቸው የመቀማት ስሜት ቢያድርባቸው ልንፈርድባቸው ይገባም፡፡ ልክ ናቸው ማለት ግን አይደለም፡፡ የዛሬዎቹ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የወደፊት ሀገር ተረካቢዎች ጢስ አባይ ፏፏቴ ዳር ከሚገኘው እረኛ ባልተሻለ ደረጃ እንዲሆኑ ያደረጋቸው የኢህአዴግ የትምህርት እና የፖለቲካ ስርዓት በትውልድ ገዳይነት መጠየቅ ካለበት አንዱ በዚህ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ አቶ መኩሪያ የዚህ ስርዓት አሰፈፃሚ ሰለሆኑ ጥያቄዬን ለመመለስ በመረጡበት አግባብ ወደፊት ታሪክ ይፈርደናል ብለዋል፡፡ ለታሪክ ፍርድ እንዲመች እነዚህን ጥያቄዎች እናንሳ፡፡ በትግራይ ክልል ስንት ኦሮሞ ኢንቨሰተሮች አሉ? በኦሮሚያ ስንት ትግሬ ኢነቨሰተሮች አሉ? ብለን ብንጠየቅ መልሱ ግልፅ ነው፡፡ በጋምቤላ ውስጥ ካሉት ኢንቨሰተሮች ምን ያህል ኦሮሞዎች አሉ? ለነዚህ ጥያቄዎች የሚገኘው መልስ ግልፅ ነው፡፡ ከነዚህ ጥያቄዎች የሚገኘው መልስ የተሳሳቱ የኦሮሞ ብሔረተኞች ኢትዮጵያ የጋራችን እንዳልሆነች የሚያደርጉት ቅስቀሳና ተግባር መገለጫ ነው፡፡ የኦህዴድ ጎምቱ ባለስልጣናት ትልቁ ግባቸው በፌዴራል ስልጣን ወይም ኦሮሚያ ብቻ ነው አማራጫቸው፡፡ ልጆቻቸውን ደግሞ ከኢትዮጵያ ውጭ እንዲኖሩ አድርገው እያዘጋጁ ነው፡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኢህአዴግ ያስተማራቸውን ብሄረተኝነት ልክ መስሎዋቸው ይሁን ወይም በማነኛውም ምክንያት የፈለጉትን ሃሣብ የመደግፍና የመቃወም መብት አላቸው፡፡ ይህን መብታቸውን በስላማዊ መንገድ እስከገለፁ ድረስ ኢህአዴግ የሚውስድው የግድያ፣ እስር፣ ከትምህርት የማፈናቀልና የማፈን ተግባር በምንም መመዘኛ ተቀባይነት እንደሌለው መታወቅ ይኖርበታል፡፡ አሰቀያሚው የመንግሰት ምክንያት ደግሞ የተገደሉት ባንክ ሲዘርፉ ነው መባሉ ነው፡፡ሰዎች ከሚሞቱ የአምቦ ባንክ ቢዘረፍ ይሻል ነበር፡፡ ዜጎች የተሳሳተ ሃሳብንም ቢሆን የመደገፍ መብት የግል ውሳኒያቸው መሆን አለበት፡፡ ከተሳሳተ መንገድ መመለሻው መንገድም ውይይትና የሃሳብ ፍጭት እንጂ በጠመንጃ የሚታገዝ ጡጫ መሆኑ ያሳዝናል፡፡ ኢህአዴግ ከዚህ ዓይነት የግጭት አፈታት ሰልት እንዲሁም የእኔ ብቻ መንገድ ልክ ነው ከሚል አሰተሳሰብ መውጣት ለዚህች ሀገር ትንሳዔ አንድ እርምጃ ይሆናል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ገድለው ሲያበቁ ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦች መፅናናትን መመኘት ሌላ አቁስል የሆነ ሰልቃ ነው፡፡

የኢህአዴግ መንግሰት ምን ታይቶ እንደሆነ ባይታወቅም የአዲስ አበባና የፊንፊኔ ዙሪያ ከተሞች የተቀናጀ ማስተር ፕላን ከእራሱ የኦህዴድ/ኢህአዴግ አባላትን ጨምሮ በኦሮሚያ ስም የተደራጀን ፓርቲ ነን የሚሉ በሙሉ ተቃውመውታል፡፡ ለተቃውሞው መነሻ በእርግጥ የህዝብ ጥቅም ከሆነ ህዝብ የሚጠቀመው እነዚህ ከተሞች ተቀናጅተው በጋራ ተመጋግበው ለማደግ ሲወሰኑ ብቻ ነው፡፡ አሁን ያለው ዓለም አቅፍ ተሞክሮ በአንድ ሀገር ክልል አይደለም በሁለት ሉዓላዊ ሀገሮች ማዕክልም የጋራ የመልማት ሰትራቴጂ የግድ የሚል ሆኖዋል፡፡ የኢህአዴግ የተቀናጀ ልማት ስትራቴጂ ምፀት የሚመስለው በኦህዴድ ጋሻ ጃግሬነት የተገነባው የጠባብነት መገላጫ “አኖሌ” ሀውልት ምረቃ ማግሰት መሆኑ የኢህአዴግ ዘላቂ ሰትራቴጂው በኢትዮጵያዊነት ጥላ ሰር ማሰተባበር ይሁን ማለያየት ግልፅ አለመሆኑ ነው፡፡ ኢህአዴግ ግራ ገብቶት ግራ የሚያጋባ ሰርዓት ነው፡፡  ግርማ ሠይፉ ማሩ በህገ መንግሰት ድንጋጌ አዲሰ አበባ በኦሮሚያ ክልል ዙሪያ መገኘቷን ተቀብሎ አዲስ አበባና ኦሮሚያን በሚያሰተሳሰሩ ጉዳዮች ኦሮሚያ ልዩ ጥቅም እንደምታገኝ እና ይህም በህግ እንደሚወሰን ተደንግጎዋል፡፡ የኦሮሚያን ክልል ተጠቃሚነት በተሻለ ማረጋገጥ የሚችላው የመስረተ ልማትና ሌሎች ጂክ ትብብሮች ማሰብ ካልተጀመረ የኦሮሞን ህዝብ እንዴት ለመጥቀም እንደሚታሰብ አይገባኝም፡፡ በኦሮሚያ ጉዳይ ላይ ለጊዜውም ቢሆን ወሳኝነት ያለው ኦህዴድ ሁል ጊዜ ሀገራዊ ዕይታውን በጠባብነት ሰሜት (በተሳሳተ ያለን በቂ ነው በሚል ትልቅነት መኮፈስ) የተጀቦነ ነው፡፡ ለምሳሌ የግል የፋይናንስ ድርጅቶችን ለመገዳደር ከመንግሰት ባንኮች በተጨማሪ በክልል መንግሰታት የሚታገዙ “የግልባንክ ተብዬዎች” ተቋቁመዋል የእዚህን ባንኮች ሰያሜ ስንመለከት የአማራ ክልል ድጋፍ ያለው “አባይ ባንክ” አማራ ባንክ የሚል አማራጭ ቀርቦ ውድቅ መደረጉን በመድረኩ ላይ ከነበሩ ሰዎች ሰምተናል፣ ትግራይ ክልል እንደ ሁሌም ትግራይ ባንክ በአሳባቸውም አልመጣም “አንበሳ ባንክ” ነው ያሉት፡፡ በተመሳሳይ የደቡብ ክልልም “ደቡብ ግሎባል ባንክ” ይበል እንጂ ጉራጌ፣ ሲዳማ ወይም ወላይታ ለማለት አልፈለጉም የደቡብ በራሱ የዚህ ዓይነት ሰያሜ ለመስጠት አስቸጋሪ መሆኑ ሳይዘነጋ ማለቴ ነው፡፡ የኦሮሚያ ክልል ስትራቴጅስቶች ግን “ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል” በማለት ከአዲሰ አበባና ከኦሮሚያ ውጭ መንቀሳቀስ እድሉን የሚያጠብ ጠባብ ውሳኔ ወሰኑ፡፡ ኦሮሚያን ሊገልፅ የሚችል ሌላ ተራራ፣ ወንዝ፣ ታሪካዊ ቦታ ወይም የገበያ መስፋፋትን የማይገድብ ስያሜ የሌለ ይመስል ማለቴ ነው፡፡ የኦሮሚያ ስትራቴጂስቶች በዚህ ደረጃ ሲሳሳቱ በኢህአዴግ ዘመን በጠባብ ብሔረተኝነት ያደጉት ወጣቶች የተቀናጀ እቅድ ቢቃወሙ ሊገርመን አይገባም፡፡ ኢህአዴግም የዘራወን እያጨደ መሆኑን መዘንጋት የለበትም፡፡
ዮኒቨርሲቲዎች በፌዴራል መንግሰት ስር ሆነው የሁሉም ኢትዮጵያዊያን መሆኑ ቢታወቀም ለዚህ ጉዳይ በተቃውሞ የተነሱት ለምን በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ብቻ ሆኖ? ብሎ መጠየቅም ያሰፈልጋል፡፡ በዚሁ የዘር ፖለቲካ የተነሳ የኦሮሚያ ክልል  ጆች ምርጫቸው በአብዛኛው በክልላቸው እንዲሆን ይፈልጋሉ፣ ከምራቃም በኋላ መመደብ የሚፈልጉት በኦሮሚያ ክልል ብቻ ነው፡፡ በእርግጥ ይህ ለኦሮሞ ልጆች ይጠቅማል ወይ? የኦሮሞ ብሔርተኛ ነን የሚሉ ሁሉ መልስ ሊሰጡበት የሚገባ ጥያቄ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተዛማጅነት ያለው በቤቴ የገጠመኝን ታሪክ በአጭሩ ላካፍላችሁ፡፡ የአክሰቴ ልጅ እኔ ቤት እየኖረ ሰበታ ሁለተኛ ደረጃ ምህርቱን ለመከታተል ይመጣል፡፡ በትምህርት ቤት ውስጥ በምርጫ ኦሮሚፋ እና አማርኛ ትምህርት ይሰጣል፡፡ ኦሮሚፋ አቀላጥፎ የሚናገረው የአክሰቴ ልጅ አሁንም ኦሮሚፋ ክፍለ ጊዜን እንደመረጠ ሲነግረኝ ለምን? ብዬ ሞገትኩት፡፡ መልሱም “ቋንቋውን ንቆ የነፍጠኛ ቋንቋ መረጠ ብለው ይጠምዱኛል” ነው ያለኝ፡፡ ኦሮሞ ያልሆኑት የሰበታ ልጆች ምን መረጡ? አልኩት አሰከትዬ፡፡
“እነርሱም ኦሮሚፋ ነው የመረጡት” አለኝ፡፡ ልዩነቱን አስረዳሁት አማርኛ በደንብ የሚችሉት ኦሮሚፋ ሲመርጡ እነርሱ የወደፊት ዕድላቸውን ወደ ሙሉ ኢትዮጵያ ሲያሳድጉ አንተ ግን እጣ ፈንታህን በኦሮሚያ ላይ ብቻ አደረከው፡፡ ምርጫው ያንተ ነው አልኩት፡፡ በምርጫው ቀጠለ፡፡ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ሲጨርስም ጅማ ዩኒቨርሲቲ መረጠ፡፡ ጅማ ለስራ ሄጄ ከዩኒቨርሲቲ አሰጠርቼ ከጓደኞቹ ጋር ሳገኘው ሁሉም ጓደኞቹ ኦሮሚፋ ተናጋሪ ናቸው፡፡ አንድ አንዶቹ በፍፁም አማርኛ የሚጠየፉ፡፡ እነዚህ ልጆች እንዴት አድርገው የኢትዮጵያዊነት ፕሮጀክት ሊጥማቸው ይችላል፡፡ የኦሮሞ ብሔርተኞችን በድጋሚ ልጠይቅ ይህ ተግባር የኦሮሚያ ልጆችን ይጠቅማል ወይ? ለአክሰቴ ልጅና ለጓደኞቹ በወቅቱ የነገርኳቸው መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያን የሚመራው ከትግርኛ አሰበልጦ ወይም እኩል አማርኛ ስለሚናገር ነው፡፡ በኢትዮጵያችን የኦሮሞ ልጆች ትልቅ የሚባለውን ቦታ ለማያዝ አማርኛን ጠየፍ የሞኝ ምርጫ ነው ነበር ያልኳቸው፡፡

በተመሳሳይ የኦህዴድ ካድሬዎች የአዲስ አበባና ፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ከተሞች የተቀናጅ ማስተር ፕላንን ለምን ተቃወሙት? የሚለውን መመርመር ይኖርብናል፡፡ እነዚህ ከተሞች በፈራቃ ካድሬዎች እየተመደቡ የድርሻቸውን የሚመዘብሩበት፣ ሲበቃቸው በዝውውር ስም የሚነሱበት እና ካድሬው ሁሉ ተራ ቢደርሰኝ ብሎ የሚጠብቅባቸው መሆናቸው አንዱ ነው፡፡ የተቀናጃ ማስተር ፕላን የሚባለው ይህን ዕድል ሊዘጋ ይችላል፡፡ ምን አልባትም በካድሬነት ሳይሆን በእውቀት የሚተገበር ሊሆን ስለሚችል ፍርሃታቸውን በህገ መንግሰት ይቃረናል በሚልና ለህዝብ መፈናቀል ይፈጥራል በሚል የሸፍጥ ሽፋን ነው የሚቃወሙት፡፡ እነዚህ ካድሬዎች መቼ ነው ስለ ህገ መንግሰትና የህዝብ ጥቅም ቆመው የሚያውቁት? አሁን ግን ለግል ጥቅማቸው ህዝብና ህገ መንግሰትን ከለላ አድርገው ተቃውሞ እያሰሙ ነው፡፡ ተማሪዎችን ከለላ አድርገው፡፡ ለማነኛውም የካድሬ ተቃውሞ አንዴ ተጠርቶ ሰኪገመገም እና ከዚህ በፊት የሰራውን ወንጀል እስኪያስታውሱት ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ይታገሳል፡፡ በተቃወመበት አፉ ውዳሴ ሲያወረድ በቅርቡ እንሰማለን፡፡ አሳዛኙ ግን ምንም ውስጥ የሌሉትን፣ በጠባብ ብሔረተኝነት ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች ለአደጋ እንዲጋለጡ ማድረጋቸው ነው፡፡ የመንግሰትንም ትዕግሰት አልባነት የሚያጋልጥ ድርጊት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ማለቴ ነው፡፡ ለማነኛውም የአዲስ አበባና በዙሪያ የሚገኙ የኦሮሚያ ከተሞች የተቀናጀ ልማት ብዙ ነገር እንድንማር የሚያደርግ ነው፡፡ ኢህአዴግ ዜጎችን በኢትዮጵያዊነት እና በብሔረተኝነት የማሰተባበር ፈተና ውስጥ መውደቁን፤ የዘራው የጠባብ ብሔረተኝነት ፖሊሲ በተለይ በኦሮሚያ ነብስ ዘርቶ ለእድገት እንቅፋት መሆኑን፤ ቋንቋ መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝም ወደ ፊትም ከዚህ ዓይነት ችግር የሚላቀቅ እንዳልሆነ፤ ወዘተ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ኦህዴዶች የኦሮሞ ልጆች በኢትዮጵያ ፖለቲካ፣ ኤኮኖሚም ሆነ ማህበራዊ ግንኙነቶች የላቀ ተሳታፊ በመሆን ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ማድረጋቸውን በዚህ አጋጣሚ ልናስታውሳቸው ይገባል፡፡ የኦሮሞ ልጆች ጠቅላይ ሚኒሰትር ለመሆን መዘጋጀት ይኖርባቸዋል …… ፕሬዝዳንት መሆን ይበቃቸዋል፡፡

ቸር ይግጠመን!!!!

ግርማ ሠይፉ ማሩ

Saturday, 3 May 2014

Ethiopia protest: Ambo students killed in Oromia state

At least nine students have died during days of protests in Ethiopia's Oromia state, the government has said.
However, a witness told the BBC that 47 were killed by the security forces.
She said the protests in Ambo, 125km (80 miles) west of Addis Ababa began last Friday over plans to expand the capital into Oromia state.
The government did not say how most of the deaths had been caused but the Ambo resident said she had seen the army firing live ammunition.
"I saw more than 20 bodies on the streets," she said.
"I am hiding in my house because I am scared."
The Ambo resident said that four students had been killed on Monday and another 43 in a huge security crackdown on Tuesday, after a huge demonstration including many non-students.
Since then, the town's streets have been deserted, she said, with banks and shops closed and no transport.
She said teaching had been suspended at Ambo University, where the protests began, and students prevented from leaving.
In a statement, the government said eight people had died during violent protests led by "anti-peace forces" in the towns of Ambo and Tokeekutayu, as well as Meda Welabu University, also in Oromia state.
It said one person had been killed "in a related development" when a hand grenade was thrown at students watching a football match.
The statement blamed the protests on "baseless rumours" being spread about the "integrated development master plan" for the capital.
BBC Ethiopia analyst Hewete Haileselassie says some ethnic Oromos feel the government is dominated by members of the Tigre and Amhara communities and they would be loath to see the size of "their" territory diminish with the expansion of Addis Ababa, which is claimed by both Oromos and Amharas.

Analysis

The student protestors are from Ethiopia's biggest ethnic group, the Oromo, numbering around 27 million people.
Oromia is the country's largest region, completely surrounding the capital Addis Ababa, although the city is itself part of the Amhara region.
Its people speak their own language - Oromifa - and see themselves as very different from the Amhara.
The protesters believe they face losing their regional and cultural identity if plans to extend Addis Ababa's administrative control into parts of Oromia get the go-ahead.
Some have also raised fears of the potential for land grabs.
The so called "master-plan" for Addis Ababa is currently out for public consultation and the government says people are being given opportunities to raise their concerns.
Officials say the plan has been well publicised and will bring city services to poor rural areas.
The protestors claim they merely wanted to raise questions about the plan - but were answered with violence and intimidation.

Thursday, 1 May 2014

Ethiopian Security Forces opened fired and killed 30 people.



 
Ethiopian security Forces opened fire during the  students nonviolent protest rally at western oromia Ambo town.
Eye witnesses said more than 30 people including 8 students killed and several wounded by security forces. the peaceful protestors opposing the alleged "integrated Master Plan of Addis Ababa".The peaceful protest continued in different oromia region.