Wednesday, 28 October 2015

Samuel Ogden Edison

እናትነት እና ተምሳሌት

በአምፖል የፈጠራ ውጤቱ የምናውቀው ቶማስ አልቫ ኤድሰን አንድ ቀን ከትምህርት ቤቱ ወደ ቤት የተመለሰው መምህሩ የሰጠውን ወረቀት ይዞ ነበር፡፡ እናም ኤድሰን ለእናቱ እንዲህ አላት “መምህሬ ይሄን ወረቀት ለእናትህ ብቻ ስጣት ብሎ ሰጠኝ” በማለት ወረቀቱን አቀበላት፡፡ እናት እንባ በአይኖቿ ሞልቶ በወረቀቱ ላይ የሰፈረውን ሀሳብ ለልጇ አነበበችለት፡፡ ያነበበችለት ሀሳብም ይህ ነበር “ልጅሽ በአስተሳሰቡ ምጡቅ (ጀኒየስ) ነው፡፡ ይሄ ትምህርት ቤት ለእሱ አይመጥነውም፡፡ ለእሱ ብቁ የሆኑ መምህራኖችም ትምህርት ቤቱ የሌለው በመሆኑ እባክሽ አንቸው አስተምሪው ይላል” በማለት እንባዋን እየጠራረገች ወረቀቱን አጣጥፋ መሳቢያ ውስጥ ከተተችው፡፡


እናቱ ካረፈች ከብዙ ዓመታት በኋላ ኤድሰን በክፈለ ዘመኑ ካሉ የፈጠራ ውጤት ባለቤቶች አንዱና ቀዳሚው ከሆነ በኋላ አንድ ቀን እናቱ እቃዎቿን የምታስቀምጥበትን መሳቢያ ማገላበጥ ጀመረ፡፡ ባጋጣሚ የተጣጠፈች ወረቀት ከመሳቢያው አካባቢ ተሰክታ ይመለከትና አንስቶ ከፈታት፡፡ ወረቁ ልጅ እያለ ከመምህሩ ለእናቱ ብቻ እንዲሰጥ ታዞ የተሰጠው ወረቀት እንደነበር አውቋል፡፡ ከፍቶ ሲያነበውም ወረቀቱ ላይ የሰፈረው ሀሳብ እንዲህ ይላል “ልጅሽ የአእምሮ ችግር ያለበትና ዘገምተኛ ነው፡፡ ከዚህ በኋላም ወደ ትምህርት ቤቱ እንዲመጣ አንፈቅድለትም” ይላል፡፡ ኤድሰን ለሰዓታት ካለቀሰ በኋላ ደያሪውን ከፍቶ እዲህ ሲል ጻፈ “ቶማስ አልቫ ኤድሰን አእምሮው ዘገምተኛ የተባለ ልጅ ነበር፡፡ ነገር ግን በጀግናዋና በልዩዋ እናቴ የምእተ ዓመቱ ጂኔስ ሁኛለሁ፡፡”

እናትን መግለጽ እጅግ አዳጋች ነው፡፡ በፊደል ለመግለጽ የሚያዳግት ተፈጥሯዊ ጸጋ እናትነት ይመስለኛል፡፡ እጅ አትስጡ፤ በፍጹም ተስፋ አትቁረጡ በራሳችሁ ተማመኑ፣ ማንኛውንም ትግል ሁለት ጊዜ ነው የምናሸንፈው ቀዳሚውም በአእምሮ ውስጥ የሚያልቀው ነው ይለናል ቶማስ ኤድሰን፡፡ እኔ በሙከራየ አልወደኩም፤ የማይሰሩ አስር ሽህ መንገዶችን ለይቻለሁ እንጅ ይላል ተስፋ ላለመቁረጥ በአይነተኛ ተምሳሌትነት ቀድሞ ሊጠቀስ የሚችለው ቶማስ አልቫ ኤድሰን፡፡

No comments:

Post a Comment