መሪን መስደብ የለመደ አፋችን አድናቆትን ከሶስት ወር በላይ ሊታገስ አልቻለም! እንደጠሉ መኖር እንጂ እንዳከበሩ መዝለቅ ለኛ አልተሰጠም! .... እቺ በመከራ የተሞላችን ሐገር መምራት፣ የዚህን የተለያየ ፍላጎት ያለውን ማህበረሰብ አቻችሎ መዝለቅ እጅግ ከባድ ነው! ቀና ሲሉ ትእቢተኛ፣ ዝቅ ሲሉ ፈሪ ሲስቁ ለስላሳ ሲቆጡ አምባገነን እያለ ቁጭ ብሎ ስም ሲያወጣ የሚውል እልፍ ስራ ፈት ያለባትን ሐገር መምራት ቀንበር የመሸከም ያህል መከራ ነው! ጨለምተኝነት እንደተቃውሞ፣ ሽርደዳና አሉባልታ እንደትችት በሚቆጠርባት ሐገር መሪ መሆን ማለት በእሳት ላይ መራመድ ነው!
አብይ አህመድ ከነስህተቱ ፣ ከነችግሩ፣ ትናንትም ዛሬም የምኮራበት፣ የምደግፈው፣ የምታዘዘው፣ መሪዬ ነው! ለኢትዮጵያ ከአብይ የተሻለ ሰው ካለህ አምጣና ሞግተኝ!
No comments:
Post a Comment