This Blog Is Intended To Raise Platform For Dialoguing And Discussing The Practical Issues Related With Women And Children in Ethiopia.
Tuesday, 10 December 2019
ኢትዮጵያዊቷ ፍረወይኒ መብራህቱ የዓመቱ የCNN ጀግና ተብላ ተሸለመች
ኢትዮጵያዊቷ ፍረወይኒ መብራህቱ የዓመቱ የCNN ጀግና ተብላ ተሸለመች፡፡
ፍረወይኒ መብራህቱ ሽልማቱን ያገኘችው ዳግም አገልግሎት ላይ የሚውል የሴቶች ንፅሕና መጠበቂያ ምርቶችን በማቅረቧና ላለፉት 13 ዓመታት በሴቶች የወር አበባ ላይ ያለውን የተሳሳተ አመለካከት ለማረም የሚያግዙ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በመስራቷ መሆኑን የCNN ዘገባ ያሳያል።
ፍረወይኒ CNN የተባለዉ የአሜሪካ የቴሌቭዥን ጣብያ የ2019 ዓ.ም የአለማችን 10 ጀግኖች ብሎ ከመረጣቸው እጩዎች መካከል አንዷ ሆና የቆየች ሲሆን፤ በዛሬዉ ዕለት ደግሞ አሸናፊ መሆኗን የቴሌቪዥን ጣቢያዉ አስታዉቋል።
ዳግም አገልግሎት የሚሰጡት የሴቶች ንፅሕና መጠበቂያ ምርቶች በመቐለ በሚገኘው ማርያም ሳባ ተብሎ በሚታወቅ ማምረቻ ተቋም ተመርተው በኢትዮጵያ ትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብና አፋር ክልሎች ለሚገኙ ሴቶች ይደርሳሉ። እስካሁን ድረስም ለአንድ ሚልዮን ገደማ በገጠሩ የኢትዮጵያ ክፍል ለሚኖሩ እንዲሁም በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ዓቅም ላላቸው ልጃገረዶች ከበጎ አድራጊ ተቋማት ጋር በመተባበር በነፃ አቅርባለች፡፡ ሲል የመቀሌዉ ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለስላሴ ዘግቧል።
በዚህም ሴት ተማሪዎች በወር አበባ ወቅት ከትምህርት ገበታ የመቅረት አጋጣሚ እንዲሁም ሌሎች ተዛማጅ ችግሮች መቀነሳቸውን ጥናቶች ያመለክታሉ።
ፍረወይኒ ውድድሩን በማሸፏ የ100 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ተሸላሚ ሆናለች፡፡
DW AMHARIC
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment