Friday, 13 March 2020

ኮሮናን ተጠንቀቀው ግን አትርበትበት!

ኮሮናን ተጠንቀቀው ግን አትርበትበት!
«ዘውድአለም ታደሠ»

ሰዉ እንዴት ነው እንዲህ በመኖር ሱስ የተለከፈው ባካችሁ? ውጪ ሐገር ሳኒታይዘርና ሶፍት ለመሸመት ድብድብ ተጀምሯል አሉ። እዚም ይኸው ገባ ከመባሉ ህዝቤ ፋርማሲ በር ላይ ማስክ ለመግዛት ይጋፋልሃል! (ማስክ ግን በሽታውን አያቆመውምኮ) ሰው ሁሉ ተደናግጧል። አንድ ደቂቃ ወስዶ ግን ስለበሽታው ምንነት ማጣራት የሚፈልግ ሰው የለም። መረጃዎችን ማገላበጥ የለም። በቃ ፍርሃት ብቻ።

ለማንኛውም for ur info አካሉ የሚጎድለው ሳይታሰብ ኢትዮጵያ ውስጥ በአመት አምስት ሺ ሰው በመኪና አደጋ ብቻ ይሞታል። እስካሁን አለም ላይ በኮሮና በሽታ ከተያዙት ውስጥ ግን የሞቱት አምስት ሺ አይደርሱም። 
መረጃዎች እንደሚጠቁሙት እስካሁን በበሽታው ከተያዙት ውስጥ ሊሞቱ ይችላሉ ተብሎ የሚገመቱት 1% ብቻ ናቸው። (ሊያው በእድሜ የገፉት) ሌሎቹ survive ያደርጋሉ ተብሏል። ከ 135 ሺ ሰዎች ውስጥ ከሰባ ሺ በላይ የሚሆኑት አገግመዋል! ምድረ የእድር ጡሩምባ ነፊ ጋዜጠኛ ለህዝቡ ትክክለኛውን መረጃ ስጥ! መቅሰፍት የመጣብን አስመስለህ ፈርተህ ህዝቡን አታስፈራራ! 



ባሻዬ የሰለጠኑት ሐገራት ሐገር ይያዝ ያሉት ለዜጎቻቸው በሚሰጡት value ነው። በኖርማል ጉንፋን አሜሪካ ውስጥ ብቻ 2.5 ሚሊየን ሰው ተይዞ 30 ሺ ሰው ይሞታልኮ። ኮሮና አንድ አመት መፍትሄ ሳይገኝለት ቢቆይ የመን ያለፈው አመት በኮሌራ ያለቀውን ግማሽ ያህል ሰው አይገድልም። ነጮቹ ግን አንድም ሰው በነሱ Negligency እንዲሞትባቸው አይፈልጉም that's it. 

ትናንት አውስትራሊያውያን «ኡኡ አለቅን» ሲሉ ሰማሁና “ስንት ሰው ሞተ?” ስል የሟቾቹ ቁጥር ባለፈው ሻሸመኔ ላይ ጃዋርን ለመቀበል ተረጋግጠው ከሞቱት ሰዎች አይበልጥም ሲሉኝ ለመሳቅም አቅም አነሰኝ መንግስታቸው የስራ ቦታዎች እንዲዘጉ አዟል። በሽታው በቁጥጥር ስር እስኪውል ድረስ ለ small business ኦች መቶ ሺ ዶላር ለዜጋው ደግሞ ለሻይ ለቡና የምትሆን 700 ዶላር እደጉማለሁ እናንተ ብቻ ከቤት አትውጡብኝ ብሏል )የአፍሪካ መሪዎች ቢሆኑ አንድ ሰው ከስራ ይቅርና ውርድ ከራሴ ነው ሚሉት  አይ የእንጀራ እናት ሐገር ጦቢያ ደግሞኮ እምዬ ምናምን እንልሻለን ማይ ፍሬንድ እኔ ላዘናጋህ አይደለም ይሄን ምልህ። ዋቃ ጉራቻ በሽታውን ከቦርደር ይመልስልን እንጂ "ከተፀዳዳህ በኋላ እጅህን ታጠብ" ተብሎ የሚመከር ህዝብ፣ አውቶቢስ ውስጥ ተጠባብቆ ሳይፈልግ እየተሳሳመ የሚጓዝ ህዝብ ተጠንቅቆ እንደማይተርፍ ይገባኛል። እኔ እያልኩህ ያለሁት አታካብድ ነው! Over act አታድርግ ነው ምልህ። አፍሪካ ውስጥ መኖር በራሱ life expectancy ህን በ 50% ያወርደዋል። ጥቁር አምበሳ ምናምን ሂድና የ አንድ ሺ ብር መድሃኒት መግዣ አጥቶ የሚሞተውን ህዝብ ቆጥረህ ተመለስና ስለኮሮና አውራኝ። 

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖረው 70% ወጣት ሃይል ነው ሲሉህ “ሽማግሌዎቹስ የት ሄዱ?” ብለህ ጠይቅ። በጅጅጋ የሚገባ ኮንትሮባንድ መድሃኒት እየዋጥክማ መሸምገል ይናፍቅሃል!  95 % ህዝባችንኮ ኩላሊቱ ፌል ቢያደርግ አንድ ወር ዳያለሲስ የሚያደርግበት ፍራንክ የለውም (እስቲ ብሔርህ ያሳክምህ እንደሆን እናያለን ኢትዮጵያ ውስጥ ሰው አማኝ የሆነው ወዶ ይመስልሃል እንዴ? በየጠበሉና በየቸርቹ አንጋጦ ፈውስ የሚጠባበቀው ምእመንኮ አብዛኛው መታከሚያ አጥቶ ነው ካርድ አውጣ፣ ራጅ ተነሳ፣ ወደማይለው ፈጣሪው ሚያቀናው። 

ማይ ብራዘር እስቲ የፈረደበት ጎግልን What are the most common diseases in Ethiopia? ብለህ ጠይቀው malaria ና diarrhea ብሎ ይመልስልሃል። ወባና ተቅማጥ ማለቱ እኮ ነው። ኮሮና ራሱ ኢትዮጵያ ውስጥ ተቅማጥ ስንት ሰው ይገድላል ብሎ ዶክተር ቴዲን ቢጠይቅ ደንግጦ እዛች ሐገር ድርሽ አልልም ማለቱ አይቀርም እና ምን ልልህ መሰለህ ባሻዬ? .... አትጨማለቅ! ፍርሃትህን በልክ አድርገው። በዚያ ላይ እስካሁን አንድ ጥቁር ነው በኮሮና የሞተው እየተባለ ነው እሱም internal cause ሊኖርበት ይችላል። ነጮቹ ኮሮና አፍሪካ ውስጥ ያን ያህል ያልተስፋፋው ከጄኔቲክ ልዩነት ወይም ዌይዘሩ ሊሆን ይችላል እያሉ ነው። እኔ ግን አይመስለኝም።
ማይ ብራዘር ከጀርምና ባክቴሪያ ጋር አፈር ፈጭተህ አድገህማ ተራ flue አይገድልህም ኮሮና ሰውነትህ ውስጥ ቢገባ ውስጥህ ያሉት ባክቴሪያዎች ፀጉሩን እያሻሹ “እቡቡቡቡ ዬማን ልጅ ነሺሺ ” እያሉ ሊያጫውቱት ሁሉ ይችላሉ ለማንኛውም አላህንም እመን ግመልህንም እሰር ነው ምልህ 

No comments:

Post a Comment