Monday, 25 February 2013

Helen Zewdu-Ethiopian Woman Activist-2013



ESAT FUND RAISING EVENT-2013, PART-3

THE BRIGHT, ACTIVIST DAUGHTER OF ETHIOPIA, HELEN ZEWDU, BLESS YOU
THANKS FOR ALL THE WORK YOU HAVE PUT INTO MAKING THE ESAT EVENT-2013 A SUCCESS! YOUR WORK IS APPRECIATED. 

Tuesday, 19 February 2013

ኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ጓደኛ የለኝም













ናታን እሸቴ በዛሬው ዕለት ኦስሎ ፍርድ ቤት ቀረበ በበርገን ከንቲባ እና በበርገን የስነ ጥበብ ደጋፊዎቹ ታጅቦ ነዉ ፍርድ ቤት የመጣዉ

 ኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ጓደኛ የለኝም የእኔ ጓደኞች ያሉት ኖርዌይ ነው በማለት  የእኔ ጓደኞች  በማለት በስዕል ገልጿችዋል  ለሚደግፈው የብራን የእግር ኳስ ቡድንም ወደፊት በማለት መልካም ምኞቱን ገልጾአል መልካም ዕድል ናታን እሸቴ



Wednesday, 13 February 2013

ፋና ወጊው ኢሳት





ሄለን ዘውዱ የኢሳት ገቢ ማሰባሰቢያ በኖርዌይ ከአደረኩት ግግር የተወሰደ

የተከበራችሁ እንግዶቻችን  
ክቡር አርቲስት ታማኝ በየነ

የኢሳትን አላማ በመደገፍ ጥሪያችንን አክብራችሁ በመገኘታችሁ በኢሳት  ስም እንኳን ደህና መጣችሁ እያልኩ ይህንን ዝግጅት ለማዘጋጀት ለረዳን ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና አቀርባለሁ  
ኢሳት የኢትዮጵያ ህዝብ ለዘመናት የተጠማውን መረጃ  የወያኔን አፈና ተቋቁሞ ለኢትዮጵያ ህዝብ ተደራሽነቱን አስመስክሮአል

አለም ወደ አንድ መንደር በመጣችበት በዚህ ዘመን  መንግስት አልባዋ ሱማሌ እንኳን በነጳነት independetly በግል የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የራዲዮ  እና የቲቪ ጣቢያዎች ባለቤት ናት መገናኛ ብዙሃን የአንድ ሃገር የዲሞክራሲ ደረጃ ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ዕድገትም መሰረት ነው

በቅርቡ ዘ ኢኮኖሚስት የተባለው ዓለም አቀፍ ወርሃዊ መጵሄት እንደዘገበው የስካንዲኒቪያ ሃገሮች ከሌሎች የበለጰጉ ሃገሮች ልቀው የሚገኙት በሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ዕድገታቸው ነው ብሎ ዘግቦአል ስለዚህም የፖለቲካ ትግላችን የሚዲያ ግንባር ቀደምተነት ያገናዘበ መሆን ገባዋል
ላሃገራችን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ነጳነት ፋና ወጊ የሆነው ኢሳት አስተማማኝ  የመረጃዎች ምንጭ ሆኖ እንዲቀጥል ሁላችንም ኢሳትን በመርዳት የዜግነት ግዴታችንን  እንወጣ

ሃገራችንን ኢትዮጵያ እግዚአብሔር ይባርክልን

Monday, 11 February 2013

ኦስሎ በታማኝ በየነ ደምቃ አመሽች


የኢሳት ኖርዌይ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ዕሑድ የካቲት 10  ቀን 2013 በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል አዳራሹን ሞልተው በጉጉት የጠበቁት የኖርዌይ ኢትዮጵያውያንም ተወዳጁ የኪነ ጥበብ ሰው ታማኝ በየነ ወደ አዳራሹ ሲገባ በጋለ ስሜት  ደማቅ አቀባበል አድርገውለታል  የተለያዩ የእንኳን ደህና መጣህ  ንግግሮች ተደርገዋል
ተወዳጁ የኪነ ጥበብ ሰው ታማኝ በየነ  በሃገርና በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለው የመብት ረገጣ አስመልክቶ በመረጃ የተደገፉ ትንታኔዎችን አቅርቧል።
በቀጣይ የጥበብ ሰው አርቲስት ታማኝ በየነ ወደ ዋናው የገቢ ማሰባሰቢያ የጨረታ መርሃ ግብር ተሸጋገረ ለጨረታ የቀረበው የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ነበር ጨረታውን ለማሸነፍ የነበረው ፉክክር ሞቅ ያለ ነበር ሞቅ አድርጉት እያለ ሞቅ ባለ ዋጋ ባለ ዕድሉ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ  በክብር ተረክበውታል
በአርቲስት እንዳለ እና በወጣቶች የተዝጋጀ የምርጫ 97 ድምፃችን ይመለስ በሚል ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው የተገደሉ ወጣት ሰላሚዊ ሰልፈኞችን ሁኔታ ያስታወስ ታሪካዊ ድራማ እና  በየዝግጅቱ ጣልቃ አዝናኝ ሙዚቃዎች ቀርቦአል።  ኢትዮጵያዊነት አንድነት እና ፍቅር የታየበት የተዋጣለት ዝግጅት ነበር

Wednesday, 6 February 2013

የዜጎች መብት የሚጣስባት ሃገር

የኢትዮጵያ ቴሌቭዢን 
ራሱ  ከሳሽ 
ራሱ ዳኛ 
ራሱ ዐቃቢ ህግ 
ራሱ ፖሊስ



Sunday, 3 February 2013

የኢሳት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት


የካቲት 10.2013 የኢሳት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ከቀኑ 16:00 እስከ 02:00 ሰአት

የካቲት 10.2013 ለሚደረገው ለእሳት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ኮሚቴ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል::

እንደዚሁም ለዝግጅቱ የሚውሉ ከተለያዩ የሃገር ወዳድና የኢሳት ደጋፊ ኢትዮጵያዊ ግለሰቦች የተለገሱ የጨረታ እናየቶምቦላ እቃዎችን በዝግጅቱ ላይ ለማቅረብ የዝግጅት ኮሚቴው የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎችን በማረግ ላይ እንገኛለን::

እነዚህ ዝግጅቶች በሚደረጉበት እለት በስልክ በመደወል ኢሳትን ለመደገፍም ሆነ ጨረታው ላይ መሳተፍ ለምትፈጉ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያውያን ወዳጆች በሙሉ ዝግጅቱን በቀጥታ በፓልቶልክ የምናስተላልፍና እንዲሁም በሰአቱ የቀጥታ የስልክ መስመር 0047 459 26 772 በመደወል የበኩልዎትን ማድረግ እንደሚችሉ እናሳስባለን::
እንዲሁም በዝግጅቱ ላይ
የተለያዩ ጣእም ያላቸው የባህልና ዘመናዊ ሙዚቃዎችና ተወዛዋዦች ከባህላዊ ዘፋኝና ዲጄ ጋር ተዘጋጅቶልዎታል::
በግሩም ባለሙያዎች የተከሸነ የባህል ምግብ ከመጠጥ ጋር
የተለያዩ አዝናኝና አነቃቂ ዝግጅቶች በማዘጋጀት ላይ እንገኛለን::

ለጨረታና ለሎተሪ ከቀረቡት እቃዎች ውስጥ

1. ኦሪጅናል የኢትዮጵያ እንጀራ መጋገሪያ የኤለክትሪክ ምጣድ
2. የተለያዩ መጠን ያላቸው  USB 8gb and 16gb
3. ዘመናዊ የቡና ማፊያ ማሽን


የኢሳት የገንዘብ ማሰባሰቢያ አዘጋጅ ኮሚቴ ኦስሎ

Saturday, 2 February 2013

Ethiopian Journalist Arrested For Covering Muslim Protests

Nairobi, February 1, 2013--Ethiopian security forces have detained for two weeks without charge the editor of a newsmagazine and accused him of incitement to terrorism, according to local journalists. The Committee to Protect Journalists calls on authorities to release Solomon Kebede immediately and halt their harassment of journalists affiliated with the weekly Ye Muslimoch Guday.
Police in Addis Ababa, the capital, on January 17 arrested Kebede, managing editor of the now-defunct paper Ye Muslimoch Guday ("Muslim Affairs"), and took him to theMaekelawi federal detention center. Solomon's health is in poor condition and he has been held without access to a lawyer, the journalists said. A court date has been set for February 13.
Local journalists told CPJ they believed the arrest was linked to Solomon's columns that had criticized perceived government intrusion in religious affairs. Solomon had covered demonstrations staged last year by Muslims protesting alleged interference in Islamic Council elections. The protests were a highly sensitive issue for the government, which feared a hardline Islamist influence within the predominantly Christian country, news reports said.