Wednesday, 13 February 2013

ፋና ወጊው ኢሳት





ሄለን ዘውዱ የኢሳት ገቢ ማሰባሰቢያ በኖርዌይ ከአደረኩት ግግር የተወሰደ

የተከበራችሁ እንግዶቻችን  
ክቡር አርቲስት ታማኝ በየነ

የኢሳትን አላማ በመደገፍ ጥሪያችንን አክብራችሁ በመገኘታችሁ በኢሳት  ስም እንኳን ደህና መጣችሁ እያልኩ ይህንን ዝግጅት ለማዘጋጀት ለረዳን ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና አቀርባለሁ  
ኢሳት የኢትዮጵያ ህዝብ ለዘመናት የተጠማውን መረጃ  የወያኔን አፈና ተቋቁሞ ለኢትዮጵያ ህዝብ ተደራሽነቱን አስመስክሮአል

አለም ወደ አንድ መንደር በመጣችበት በዚህ ዘመን  መንግስት አልባዋ ሱማሌ እንኳን በነጳነት independetly በግል የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የራዲዮ  እና የቲቪ ጣቢያዎች ባለቤት ናት መገናኛ ብዙሃን የአንድ ሃገር የዲሞክራሲ ደረጃ ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ዕድገትም መሰረት ነው

በቅርቡ ዘ ኢኮኖሚስት የተባለው ዓለም አቀፍ ወርሃዊ መጵሄት እንደዘገበው የስካንዲኒቪያ ሃገሮች ከሌሎች የበለጰጉ ሃገሮች ልቀው የሚገኙት በሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ዕድገታቸው ነው ብሎ ዘግቦአል ስለዚህም የፖለቲካ ትግላችን የሚዲያ ግንባር ቀደምተነት ያገናዘበ መሆን ገባዋል
ላሃገራችን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ነጳነት ፋና ወጊ የሆነው ኢሳት አስተማማኝ  የመረጃዎች ምንጭ ሆኖ እንዲቀጥል ሁላችንም ኢሳትን በመርዳት የዜግነት ግዴታችንን  እንወጣ

ሃገራችንን ኢትዮጵያ እግዚአብሔር ይባርክልን

No comments:

Post a Comment