የካቲት 10.2013 የኢሳት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ከቀኑ 16:00 እስከ 02:00 ሰአት
የካቲት 10.2013 ለሚደረገው ለእሳት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ኮሚቴ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል::
እንደዚሁም ለዝግጅቱ የሚውሉ ከተለያዩ የሃገር ወዳድና የኢሳት ደጋፊ ኢትዮጵያዊ ግለሰቦች የተለገሱ የጨረታ እናየቶምቦላ እቃዎችን በዝግጅቱ ላይ ለማቅረብ የዝግጅት ኮሚቴው የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎችን በማረግ ላይ እንገኛለን::
እነዚህ ዝግጅቶች በሚደረጉበት እለት በስልክ በመደወል ኢሳትን ለመደገፍም ሆነ ጨረታው ላይ መሳተፍ ለምትፈጉ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያውያን ወዳጆች በሙሉ ዝግጅቱን በቀጥታ በፓልቶልክ የምናስተላልፍና እንዲሁም በሰአቱ የቀጥታ የስልክ መስመር 0047 459 26 772 በመደወል የበኩልዎትን ማድረግ እንደሚችሉ እናሳስባለን::
እንዲሁም በዝግጅቱ ላይ
• የተለያዩ ጣእም ያላቸው የባህልና ዘመናዊ ሙዚቃዎችና ተወዛዋዦች ከባህላዊ ዘፋኝና ዲጄ ጋር ተዘጋጅቶልዎታል::
• በግሩም ባለሙያዎች የተከሸነ የባህል ምግብ ከመጠጥ ጋር
• የተለያዩ አዝናኝና አነቃቂ ዝግጅቶች በማዘጋጀት ላይ እንገኛለን::
ለጨረታና ለሎተሪ ከቀረቡት እቃዎች ውስጥ
1. ኦሪጅናል የኢትዮጵያ እንጀራ መጋገሪያ የኤለክትሪክ ምጣድ
2. የተለያዩ መጠን ያላቸው USB 8gb and 16gb
3. ዘመናዊ የቡና ማፊያ ማሽን
የኢሳት የገንዘብ ማሰባሰቢያ አዘጋጅ ኮሚቴ ኦስሎ
No comments:
Post a Comment