Sunday, 30 December 2012

በሱዳን በኩል የሚካሄደው ሕገወጥ ንግድ እየተባባሰ መምጣቱ ተጠቆመ

ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር በሚያዋስናት ጠረፍ በኩል ሕገወጥ የገቢና ወጪ ንግድ መስፋፋቱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያ ከሱዳን በኩል የምትዋሰንባቸው ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝና አማራ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ የጠረፍ ከተሞች በርካታ ሸቀጦች፣ የቁም እንስሳት፣ ደንና የደን ውጤቶች በገፍ እንደሚወጡ ታውቋል፡፡

በቤንሻንጉል ጉምዝ በከፍተኛ ደረጃ የሚወጣውን የቁም እንስሳት ከፍተኛ መጠን ያለው የቁም ከብት አሁንም በጉባ በኩል እየወጣ መሆኑ ይነገራል፡፡ በተጨማሪም በጋምቤላና በቤንሻንጉል ጉምዝ በኩል ቡና በብዛት ከአገር እየወጣ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡ በአማራ ክልል መተማ በኩል የደን ውጤቶችና የቁም እንስሳት በከፍተኛ መጠን ከአገር እንደሚወጡ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

እነዚህን ሸቀጦች ለማስወጣት ለጭቃና ለጎርበጥባጣ መንገድ የማይበገሩ መርሰዲስ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ የጠረፍ ንግድ በተለይ ሥጋ ላኪዎችንና የቆዳ ፋብሪካዎችን እየጎዳና ከገበያ እያስወጣ እንደሆነ ይናገራል፡፡ ምክንያቱም ከጠረፍ ወደ መካከለኛው ገበያ መቅረብ የነበረበት የቁም ከብት በድንበር በኩል በሕገወጥ መንገድ እየወጣ በመሆኑ ነው፡፡

የዘርፉ ሕጋዊ ነጋዴዎች ይህንን ችግራቸውን በተደጋጋሚ ለመንግሥት ቢያቀርቡም፣ ጉዳዩ እየተወሳሰበ እንጂ መፍትሔ ማግኘት አለመቻላቸውን ይገልጻሉ፡፡

Saturday, 29 December 2012

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሴራውን ጀመረ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በሚያዝያ ለሚደረገው የአዲስ አበባና የአካባቢ ምርጫ ፓርቲዎች የውድድር ምልክት የሚወስዱበትን ጊዜ በሁለት ቀናት እንዳራዘመ ሲገልፅ ፓርቲዎች በበኩላቸው የውድድር ምልክት መውሰጃ ቀነ ገደብ አልነበረውም አሉ፡፡ ምርጫ ቦርድ ከትናት በስቲያ ፓርቲዎችን ለውድድር ለማነሳሳት በሚል የውድድር ምልክት የሚወስዱበትን ጊዜ በሁለት ቀን በማራዘም ዛሬ ታህሳስ 20 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ በቦርዱ ፅ/ቤት በመገኘት ምልክታቸውን እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የምርጫ የጊዜ ሰሌዳውን በተመለከተ ከምርጫ ቦርድ ጋር መወያየት እንደሚፈልጉ ሲገልፁ የቆዩት 33ቱ ፓርቲዎች ምርጫ ቦርድ ያስቀመጠውን የጊዜ ቀነ ገደብ እንደማይቀበሉት የገለፁት  ቀነ ገደቡ ፓርቲዎችን እርስ በርስ ለመከፋፈልና ለመለያየት የሚደረግ ሴራ ነው ብለዋል፡፡

በምርጫው የጊዜ ሰሌዳ ላይ አለመስማማታችንና በምርጫ ምልክቱ ዙሪያ ውይይት እያካሄድን እንደሆነ ምርጫ ቦርድ ያውቃል ያሉት አቶ አስራት፤ ቀን ገደብ ማስቀመጥ የቦርዱ ስልጣንና ሃላፊነትን አይደለም ብለዋል፡፡ ቦርዱ የውድድር ምልክቱን ቀነ ገደብ ያስቀመጠው ለምርጫው አስቦ ሳይሆን ፓርቲዎችን ለመከፋፈል እንደሆነ አቶ አስራት ተናግረዋል፡፡

Sunday, 23 December 2012

በኩዌት በሳዑዲ ዓረቢያና ጅዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሰው ኃይልን በርካሽ ዋጋ ሊያቀርብ እንደሚችል በአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ማስታወቂያው እያስነገረ ነው፡፡

Hellen Zewdu
 
ሰው በፈለገበት ቦታና አገር የመዘዋወር መብቱ በሕገ መንግሥቱ ተረጋግጦለታል፡፡ በኮንትራት በቤት ሠራተኝነት ወደ አረብ አገሮች የሚሄዱ ኢትዮጵያዉያን የሚደርስባቸዉ በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ መባባሱ ይሰማል።   ኢትዮጵያውያኑ ላይ ከፍተኛ  የሆነ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ  ጉዳት እየደረሰ ነው። ለዚህም በዋነኛነት ማሳያ የሚሆነው በተለያዩ የዓረብ አገሮች በቤት ሠራተኛነት በሚሄዱት እህቶቻችን ላይ የሚታየው የሞት፣ የአካል መጉደል፣ የመደፈርና ያለደመወዝ ማባረር ጥቂቶች ናቸው፡፡ በዚህ ዓመት እንኳን ከዓለም ደቻሳ ጀምሮ  በድብደባ ህይወታቸውን ያጡትን  ለከፍተኛ የአካል ጉዳት የተዳረጉትን የተደፈሩትን ከፎቅ የተወረወሩትን ለአእምሮ መቃወስ የተዳረጉት የትየለሌ ናቸው ኢትዮጵያዉያን የኮንትራት ሰራተኞች በአሰሪወቻቸው የሚደርስባቸውን ጥቃት ታዋቂ የሳዉዲ ጋዜጦች ሳይቀሩ በዝርዝር እየዘገቡት ነው፡፡

የወገኖቻችን እንግልት የሚጀምረው አገራቸው ላይ ነው፡፡ የሳዑዲ ዓረቢያ ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያውያንም በዜጎቻችን ላይ ክብራቸውን ጭምር የሚነካ ተግባር የሚፈጽሙ አሉ፡፡ በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች በደላላዎች እየተደለሉ ከየቀያቸው እየተፈናቀሉ ዜጎቻችን ለጉዳት እየተዳረጉ ነው፡፡ ሁሉም ነገር አልጋ ባልጋ እንደሆነና ወርቅ ተነጥፎ እንደሚጠብቃቸው በመስበክ ወጎኖቻችንን እያስጨረሱ ነው፡፡ ከእነዚህ ደላሎች በስተጀርባ የመንግስት እጅ አለበት መንግሥት ዜጎችን ከመጠበቅና ካለበት ኃላፊነት አንጻር እሱም ተጠያቂ ነው፡፡ ዕድሜያቸው እንዳልሞላ እየታወቀ ከ13-15 ዓመትን ልጅን 23-26 ዓመት በማለት  በማጣራትና አይቶም መገመት ሲቻል ፓስፖርት ይሰጧቸዋል የሚያስደነግጥ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ወደ ሳዑዲና ኩዌት ለመሄድ የሚመጡት መጻፍ፣ ማንበብ የማይችሉና መታወቂያና ፓስፖርት መሆኑን መለየት የማይችሉ ናቸው፡፡ ፓስፖርት እስከሚያወጡና የሕክምና ምርመራ እስከሚደረግላቸው ድረስ ብዙ ችግሮችን ያሳልፋሉ ሁሉም ነገር ተሳክቶላቸው እስከሚሄዱ ድረስ የደላሎቹ የወሲብ መፈጸሚያ ይሆናሉ፡፡ የጤና ምርመራ ሲደረግላቸውም የHIV ተጠቂ ሆነው ይገኛሉ ውጤታቸው ሲነገራቸው እንደ ውርደት ስለሚቆጥሩት ተመልሰው ወደቀያቸው መግባትን ይተዉና ራሳቸውን በመሸጥ ለመተዳደር ይሞክራሉ፡፡ በሽታውንም ያስተላልፋሉ ላልተፈለገ እርግዝና ለ አደንዛዥ ዕፆች ተጋላጭ እየሆኑ ነው፡፡

Saturday, 22 December 2012

ቅ/ሲኖዶስ የሠየመው የፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ ዓለም አቀፍ ተቃውሞ ቀስቅሷል

ዕርቀ ሰላሙ ይቅደም›› የሚሉ ጳጳሳት የሲኖዶሱን ውሳኔ አንቀበለውም ብለዋል

የላሊበላው ውዝግብ ወደ አላስፈላጊ ግጭት እንዳያመራ ተሰግቷል

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የስድስተኛውን ፓትርያሪክ ምርጫ ዝግጅት የሚመራና እስከ ጥር መጨረሻ ዕጩዎችን የሚያቀርብ አስመራጭ ኮሚቴ መሠየሙ በቤተ ክርስቲያኒቱ ካህናትና ምእመናን ዘንድ ዓለም አቀፍ ተቃውሞ መቀስቀሱ ተገለጸ። ‹‹የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ያገባኛል›› በሚል መርሕ በዋናነት በማኅበራዊ ሚዲያዎችና ብሎጎች እየተገለጸ ያለው ይኸው ተቃውሞ፤ የቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት የሚረጋገጥበት የዕርቁ ጉባኤ ‹‹የአባቶች ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ ምእመናኑን ያገለለ ሊኾን አይገባም›› በሚል የካህናቱና ምእመናኑ ድምፅ እንዲደመጥ የሚወተውት ነው፡፡

የቅ/ሲኖዶሱ አባላት የኾኑ ሊቃነ ጳጳሳትን ጭምር ያካተተው የዚህ ተቃውሞ መነሻ÷ የአስመራጭ ኮሚቴው መቋቋም በሀገር ውስጥ በሚኖሩትና በውጭ አገር በስደት በሚገኙት አባቶች መካከል ለሚካሄደው የዕርቀ ሰላም ውይይት መሰናክል ይኾናል በሚል ነው፡፡የቅ/ሲኖዶሱ የዕርቀ ሰላም ልኡክ በመኾን ወደ አሜሪካ ከተጓዙትና በዳላስ ቴክሳስ ከኅዳር 26 - 30 ቀን 2005 ዓ.ም በሰላምና አንድነት ጉባኤ አመቻችነት በተካሄደው የዕርቀ ሰላም ውይይት ላይ የተሳተፉት የደቡብ ወሎ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ ከትናንት በስቲያ ምሽት ለአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ በሰጡት አስተያየት÷ ቅ/ሲኖዶሱ እንደላካቸውና በሰላሙ ጉዳይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋገሩ ‹‹ስንዝር ያህል መራመዳቸውን›› ገልጸዋል፡፡ የዕርቀ ሰላም ልኡካኑ ይህን እያደረጉ ባለበት ኹኔታ ስለ ፓትርያሪክ ምርጫ መወያየትና አስመራጭ ኮሚቴ ማቋቋም ‹‹ኾኗል ብለን አናምንበትም፤ ኾኖ ከተገኘ ግን አንቀበለውም፤ እንቃወመዋለን›› ብለዋል - በቅ/ሲኖዶሱ ውሳኔ ቅር የተሰኙት ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ፡፡

በሰሜን አሜሪካ የዋሽንግተን ዲሲ እና ካሊፎርኒያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በበኩላቸው÷ የጥቅምት ቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የወሰነው የፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ደንብ ተዘጋጅቶ የአሁኑ ስብሰባ እንዲጠራ እንጂ አስመራጭ ኮሚቴ ማቋቋም አዲስ ሐሳብ መኾኑን ለሬዲዮው በሰጡት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል፡፡ በጥር ወር አጋማሽ በካሊፎርኒያ ሎሳንጀለስ ቀጣይ የሰላም ጉባኤ ለማካሄድ ቀጠሮ መያዙን ያስታወሱት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል፤ የኮሚቴው መቋቋም የዕርቁን ሂደት እንዳያበላሸው ስጋት እንዳላቸው በመግለጽ ቅ/ሲኖዶሱ ከዕርቀ ሰላም ጉባኤው በፊት ሰፋ ያለ ሥራ ከማከናወን እንዲከለከል አሳስበዋል፡፡

Friday, 21 December 2012

የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” የምሥረታ መግለጫና ሃገራዊ ጥሪ

ታህሳስ 11 2005

የወያኔን ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ በትጥቅ ትግል ለማስወገድ “የግንቦት7 ሕዝባዊ ኃይል” የሚል ስያሜ የሰጠነውን፣ በሃገር ወዳድና ለህዝብ ተቆርቋሪ በሆኑ ወጣቶች፣ ምሁራንና ዜጎች የተሞላውን ድርጅት መመሥረታችንበዛሬው እለት ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በይፋ እናበስራልን።
 
ግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል፣ የሕዝብ ሉዓላዊ የሥልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባት፤ የዜጎች መብቶች፣ ሃገራዊ አንድነት፣ ደህንነትና ጥቅም የተከበሩባት ጠንካራና ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እውን ሆና የማየትን ራዕይ የሰነቀ ድርጅት ነው።
 
የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ወያኔን በኃይል የማስወገድ፤ ሰላማዊና ዲሞክራሲ የሥልጣን ሽግግር በሃገሪቱ እንዲኖር የማስቻል እና ከማንኛዉም የፓለቲካ ድርጅት ጋር ያልወገኑ ነፃ፣ ጠንካራና ብቃት ያላቸው ህገ-መንግሥታዊ የመከላከያ፣ የፓሊስና የደህንነት ተቋማት እንዲኖሩ አስተዋጽዖ የማድረግ ተልዕኮ ይዞ የተነሳ የኢትዮጵያ ሕዝብ አለኝታ ነው።
 
የግንቦት7 ሕዝባዊ ኃይል ራዕይና ተልዕኮ የተቀዳው በቀጥታ ሕዝብ በህይወቱ በደሙ በስቃይና በመከራ ውድ መስዋዕትነት ከከፈለለት የ1997 ብሄራዊ ምርጫ ነው።

Thursday, 20 December 2012

Ethiopia Four Journalists Win Free Speech Prize

 
(New York) - Four Ethiopian journalists have received the prestigious Hellman/Hammett award for 2012 in recognition of their efforts to promote free expression in Ethiopia, one of the world’s most restricted media environments.
 
Eskinder Nega Fenta, an independent journalist and blogger; Reeyot Alemu Gobebo of the disbanded weekly newspaper Feteh; Woubshet Taye Abebe of the now-closed weekly newspaper Awramba Times; and Mesfin Negash of Addis Neger Online were among a diverse group of 41 writers and journalists from 19 countries to receive the award in 2012. Eskinder, Reeyot, and Woubshet are imprisoned in Ethiopia; Mesfin fled in 2009. All four journalists were convicted in 2012 under Ethiopia’s draconian anti-terrorism law.
 
“The four jailed and exiled journalists exemplify the courage and dire situation of independent journalism in Ethiopia today,” said Leslie Lefkow, deputy Africa director at Human Rights Watch. “Their ordeals illustrate the price of speaking freely in a country where free speech is no longer tolerated.”
 
The Hellman/Hammett grants, administered by Human Rights Watch, are awarded annually to writers and journalists around the world who have been targets of political persecution and human rights abuses. The prize is named after two American writers who were harassed during the 1950s anti-communism investigations. Lillian Hellman suffered professionally and had trouble finding work while Dashiell Hammett spent time in prison. A distinguished selection committee awards the grants to honor and support journalists whose work, activities, and lives are suppressed by repressive government action.

Wednesday, 19 December 2012

Eskinder Nega Is Currently Appealing His Conviction And Sentencing

Update: Eskinder Nega is currently appealing his conviction and sentencing. On December 19, 2012, the Ethiopian Federal Supreme Court postponed hearing his appeal for the second time. The appeal hearing is scheduled to resume January 18, 2013. Please follow us on Twitter @freedomnoworg for breaking news.
 
Eskinder NegaEskinder Nega, 43, is a prominent Ethiopian journalist who was convicted and sentenced to 18 years in prison on terrorism charges. Prior to his detention, Mr. Nega was a widely published independent journalist and a well-known critic of Prime Minister Meles Zenawi’s government. Mr. Nega is married and the father of one son.
 
Mr. Nega began his work as an independent journalist in 1993 when he founded the Ethiopis newspaper. While Ethiopis and many of the other publications where Mr. Nega later worked were banned, he continued to write articles criticizing the Ethiopian regime’s abuses of power.
 
As a result of his critical reporting, the government has detained Mr. Nega on eight different occasions. In 2005, authorities arrested Mr. Nega and his then-pregnant wife, Serkalem Fasil, who is herself an independent publisher, during a nationwide crackdown following the country’s disputed elections. Mr. Nega was charged with treason and genocide and detained for 17 months before Ethiopia’s High Court released him after a series of negotiations. After releasing Mr. Nega in 2007, the government blocked him from publishing in the country. However, Mr. Nega continued to contribute to online media outlets abroad.