Sunday, 30 December 2012

በሱዳን በኩል የሚካሄደው ሕገወጥ ንግድ እየተባባሰ መምጣቱ ተጠቆመ

ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር በሚያዋስናት ጠረፍ በኩል ሕገወጥ የገቢና ወጪ ንግድ መስፋፋቱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያ ከሱዳን በኩል የምትዋሰንባቸው ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝና አማራ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ የጠረፍ ከተሞች በርካታ ሸቀጦች፣ የቁም እንስሳት፣ ደንና የደን ውጤቶች በገፍ እንደሚወጡ ታውቋል፡፡

በቤንሻንጉል ጉምዝ በከፍተኛ ደረጃ የሚወጣውን የቁም እንስሳት ከፍተኛ መጠን ያለው የቁም ከብት አሁንም በጉባ በኩል እየወጣ መሆኑ ይነገራል፡፡ በተጨማሪም በጋምቤላና በቤንሻንጉል ጉምዝ በኩል ቡና በብዛት ከአገር እየወጣ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡ በአማራ ክልል መተማ በኩል የደን ውጤቶችና የቁም እንስሳት በከፍተኛ መጠን ከአገር እንደሚወጡ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

እነዚህን ሸቀጦች ለማስወጣት ለጭቃና ለጎርበጥባጣ መንገድ የማይበገሩ መርሰዲስ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ የጠረፍ ንግድ በተለይ ሥጋ ላኪዎችንና የቆዳ ፋብሪካዎችን እየጎዳና ከገበያ እያስወጣ እንደሆነ ይናገራል፡፡ ምክንያቱም ከጠረፍ ወደ መካከለኛው ገበያ መቅረብ የነበረበት የቁም ከብት በድንበር በኩል በሕገወጥ መንገድ እየወጣ በመሆኑ ነው፡፡

የዘርፉ ሕጋዊ ነጋዴዎች ይህንን ችግራቸውን በተደጋጋሚ ለመንግሥት ቢያቀርቡም፣ ጉዳዩ እየተወሳሰበ እንጂ መፍትሔ ማግኘት አለመቻላቸውን ይገልጻሉ፡፡

No comments:

Post a Comment