Saturday, 29 December 2012

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሴራውን ጀመረ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በሚያዝያ ለሚደረገው የአዲስ አበባና የአካባቢ ምርጫ ፓርቲዎች የውድድር ምልክት የሚወስዱበትን ጊዜ በሁለት ቀናት እንዳራዘመ ሲገልፅ ፓርቲዎች በበኩላቸው የውድድር ምልክት መውሰጃ ቀነ ገደብ አልነበረውም አሉ፡፡ ምርጫ ቦርድ ከትናት በስቲያ ፓርቲዎችን ለውድድር ለማነሳሳት በሚል የውድድር ምልክት የሚወስዱበትን ጊዜ በሁለት ቀን በማራዘም ዛሬ ታህሳስ 20 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ በቦርዱ ፅ/ቤት በመገኘት ምልክታቸውን እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የምርጫ የጊዜ ሰሌዳውን በተመለከተ ከምርጫ ቦርድ ጋር መወያየት እንደሚፈልጉ ሲገልፁ የቆዩት 33ቱ ፓርቲዎች ምርጫ ቦርድ ያስቀመጠውን የጊዜ ቀነ ገደብ እንደማይቀበሉት የገለፁት  ቀነ ገደቡ ፓርቲዎችን እርስ በርስ ለመከፋፈልና ለመለያየት የሚደረግ ሴራ ነው ብለዋል፡፡

በምርጫው የጊዜ ሰሌዳ ላይ አለመስማማታችንና በምርጫ ምልክቱ ዙሪያ ውይይት እያካሄድን እንደሆነ ምርጫ ቦርድ ያውቃል ያሉት አቶ አስራት፤ ቀን ገደብ ማስቀመጥ የቦርዱ ስልጣንና ሃላፊነትን አይደለም ብለዋል፡፡ ቦርዱ የውድድር ምልክቱን ቀነ ገደብ ያስቀመጠው ለምርጫው አስቦ ሳይሆን ፓርቲዎችን ለመከፋፈል እንደሆነ አቶ አስራት ተናግረዋል፡፡

No comments:

Post a Comment