አዲስ አበባ ታህሳስ 5 2005 ወጣት አርቲስት ህይወቴ አበበ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች። ባለትዳርና የአንዲት ሴት ልጅ እናት የነበረችው አርቲስት ህይወቴ ፥ ታማ በጳውሎስ ሆስፒታል በህክምና ስትረዳ ቆይታ ነው በተወለደች በ31 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው። አርቲስቷ የመቃብር ቁልፎችንና የሰርጉ ዋዜማን ጨምሮ በተለያዩ የመድረክ ቲያትሮች ላይ ሰርታለች። ባለታክሲው፣ ባለቀለም ህልሞችና ሰውዬው ፊልሞች ላይም የሰራች ሲሆን ፥ በርካታ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይም በመሪ ተዋናይነት ጭምር መስራቷን ነው የባልደረባችን ዘካሪያስ ብርሃኑ ዘገባ የሚያመለክተው። ካለፉት ሶስት ወራት በፊት ጀምሮ ኑሮዋን በኡጋንዳ ካምፓላ አድርጋ የነበረችው አርቲስት ህይወቴ የቀብር ስነ ስርዓት ነገ በአዳማ ከተማ ይፈጸማል።
No comments:
Post a Comment