Wednesday, 26 February 2014

ብሶት በርክቷል!


26 FEBRUARY 2014 ተጻፈ በ  
በአሁኑ ጊዜ በየቦታው የተጠራቀሙ ብሶቶች ይሰማሉ፡፡ ከመንግሥታዊ ተቋማት የተዝረከረከ አገልግሎት አሰጣጥ ጀምሮ እስከ ዋናው የአገሪቱ የፖለቲካ ሥነ ምኅዳር ድረስ ብሶት በርክቷል፡፡
የኑሮ ውድነቱ አዕምሮውን የሚያናውጠው ሕዝብ፣ የመልካም አስተዳደር እጦትና የሰብዓዊ መብት መጓደል እያንገሸገሸው ነው፡፡ ሕዝቡ መንግሥት ምን እስኪሆን ድረስ ነው የሚጠብቀው እያለ በየቦታው ያጉረመርማል፡፡ ይኼ አሉባልታ ሳይሆን እውነት ነው፡፡ በተጨባጭ የሚታይ፡፡  
እንዲህ ዓይነቱ የብሶት አቤቱታ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ለተሰገሰጉ ራስ ወዳዶችና ስግብግቦች ላይዋጥላቸው ይችላል፡፡ ነገር ግን እውነቱ ይኼ ነው፡፡ በተደጋጋሚ ሕዝቡ የመልካም አስተዳደር ችግር ሲገጥመው፣ ‹‹ይኼ የኪራይ ሰብሳቢዎችና ፀረ ሕዝቦች ሟርት ነው›› እየተባለ ሲድበሰበስ ይሰማል፡፡ ችግሩ አፍጥጦ ወጥቶ መላወሻ ሲታጣ ግን፣ ‹‹የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ ተግተን እንሠራለን›› የሚል ማስተዛዘኛ አይሉት ማደናገሪያ ይቀርባል፡፡ አሁን በተጨባጭ እየታየ ያለው መልካም አስተዳደር የሚባለው ጽንሰ ሐሳብ መቀለጃ መሆኑ ብቻ ነው፡፡ 
ሕዝቡ የፍትሕ ያለህ እያለ በየደረሰበት ሲያነባ ላይ ላዩን ችግሩ መኖሩን እያመኑ መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ ችግሩን ማባባስ የተመረጠ ይመስላል፡፡ በፍትሕ እጦት የሚንገላታው ዜጋ መንግሥት ከዛሬ ነገ መፍትሔ ያፈላልግልኛል ብሎ ሲጠብቅ ውጤቱ በዜሮ ተባዝቶ እየቀረበለት ነው፡፡ በፍትሕ ሥርዓቱ ውስጥ የተሰገሰጉ ግለሰቦችና ቡድኖች ሕዝቡን ከማስለቀስ አልፈው ተስፋ እያስቆረጡት ነው፡፡ 
በሰብዓዊ መብት ጥሰት ምክንያት አቤቱታ ሲቀርብ ፈጽሞ አይፈጸምም በሚባልበት አገር ውስጥ በርካታ እሮሮዎች እየተደመጡ ናቸው፡፡ ሐሳብን በነፃነት ከመግለጽ ጀምሮ የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን የሚያቀርቡ ዜጎች በጠላትነት ይፈረጃሉ፡፡ ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን ለማስከበር ላይ ታች ሲሉ በሕገወጥ መንገድ ይሰቃያሉ፡፡ መብትን በሰላማዊ መንገድ መጠየቅ ከነውር በላይ እየታየ ዜጎችን ወደ ሕገወጥነት የሚመራ አሻጥር ይከናወናል፡፡ በመንግሥት መዋቅሮች ውስጥ የተሰገሰጉ እነዚህ ኃይሎች ዜጋ በአገሩ እንዳይኮራና ስደት ውስጥ እንዲዘፈቅ እያደረጉ ናቸው፡፡ 
አገራቸውን በቅንነት ለማገልገል የሚፈልጉ ወገኖች በእንዲህ ዓይነቶቹ ራስ ወዳዶችና ስግብግቦች እየተሸፈኑ ዜጎች ለእንግልት ሲዳረጉ ጠያቂ ያለ አይመስልም፡፡ ለአገራቸው አኩሪ ተግባር መፈጸም የሚችሉ የተማሩና ልምድ ያካበቱ ወገኖች ወደ ዳር እየተገፉ፣ ለጥቅማቸው ብቻ ያደሩ ወገኖች መንበሩን ሲቆናጠጡ አገር እየተጎዳች መሆኗ እየተረሳ ነው፡፡ ሕዝቡ በውስጡ ብሶት ተሸክሞ ሲዞር ችግሩን ከማድበስበስ ባለፈ በግልጽ ለመነጋገርና ለመፍታት የሚሞክር አለመታየቱ ከማስገረምም በላይ ነው፡፡
የኑሮ ውድነቱ የሕዝቡን ወገብ አጉብጦት መከራ እያሳየው ተገኘ የሚባለው የኢኮኖሚ ዕድገት አኃዝ ብቻ እንዲነገር የሚፈልጉ ወገኖች አሉ፡፡ ዕድገቱ በሕዝቡ ዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጣ ከመታገል ይልቅ የማይጨበጥ ሐተታ ላይ የሚያተኩሩ መብዛታቸው በእጅጉ ያስገርማል፡፡ የኑሮ ውድነቱ ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ እያለ መንግሥት ሕዝቡ ላይ እንዴት ኢንቨስት ማድረግ ይኖርበታል ከሚለው ወገናዊ መጨነቅ ይልቅ፣ ‹‹ኑሮ ውድነቱ የዕድገቱ ውጤት ነው›› በማለት ግድየለሽ መሆንም በስፋት ይታያል፡፡ ይህ ሁሉ የሚከናወነው ደግሞ ከራሳቸው ጥቅም ባሻገር መመልከት በተሳናቸው ኃይሎች ነው፡፡ 
ምንም እንኳ በርካታ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች እየተከናወኑ ቢሆንም፣ በዚህ ዘመን ውኃ እንዴት ለ15 ቀናት ይጠፋል? የኤሌክትሪክ ኃይል በዋና ከተማዋና በሌሎች አካባቢዎች በቀን ሦስትና አራት ጊዜ እንዴት ይቆራረጣል? የሞባይል ኔትወርክና የኢንተርኔት አገልግሎት እንዴት ብርቅ ይሆናሉ? በተለያዩ መንግሥታዊ ድርጅቶች የሚሰጠው አገልግሎት ቀርፋፋነትና የጥራት መጓደል እስከመቼ ይቀጥላል? ሕዝቡ በትራንስፖርት እጦት በዝናብና በፀሐይ ሲደበደብ እንዴት ዝም ይባላል? በርካታ ችግሮችን ማንሳት ይቻላል፡፡ 
የፖለቲካውን አካባቢ ስናየው ደግሞ በጥላቻና በጭፍንነት የተሞላ ከመሆኑም በላይ፣ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የሚባለው መታወቂያ ፈጽሞ የተረሳበት ይመስላል፡፡ ምንም እንኳ የፖለቲካ ዋነኛ ግቡ ሥልጣን ነው ቢባልም፣ ፖለቲካው ሠፈር የሚታየው ግን ራስ ወዳድነትና ተራ ብልጣ ብልጥነት ነው፡፡ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ምሰሶዎች የሚባሉት መሠረታዊ ጉዳዮች ተረስተዋል፡፡ ነፃነትን ማረጋገጥ፣ በምርጫ አማካይነት የሕዝብ ትክክለኛ ተወካዮችን መሰየምና ፍትሕን ማረጋገጥ የተቻለበት አይመስልም፡፡ ይህ ችግር ገዥውን ፓርቲና ተቃዋሚዎቹን የሚመለከት ነው፡፡ ነገር ግን ገዥው ፓርቲ የአገሪቱን የመንግሥት ሥልጣን ሙሉ በሙሉ እንደመቆጣጠሩ መጠን ከችግሩ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል፡፡ በአገሪቱ ተቃዋሚዎች ለምን አልተጠናከሩም ሲባል፣ ችግሩ የእነሱ ብቻ ሳይሆን የገዥው ፓርቲ ጭምር መሆኑን ማሰብ ይገባል፡፡ የፖለቲካ ሥነ ምኅዳሩ ጠበበ ሲባል እነዚህ ወገኖች የመጫወቻ ሜዳ እያጡ መሆኑን ማመን የግድ ይላል፡፡ በእንዲህ ዓይነቱ የተወጣጠረ ሁኔታ ውስጥ ስለዲሞክራሲም ሆነ ሰብዓዊ መብት ማሰብ ያስቸግራል፡፡ ፖለቲካው ነፃነትና ዲሞክራሲን ማንፀባረቅ ሲገባው ደም ደም ይሸታል፡፡ 
የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁን እየታየ ካለው የልማት ትሩፋት በፍትሐዊ መንገድ ተጠቃሚ ነው ወይ ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡ የአገሪቱ ኢኮኖሚ የሚያመነጨው ሀብት በምን ያህል መንገድ ሕዝቡ ዘንድ እየደረሰ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ የሕዝብ ውክልና አለኝ የሚል መንግሥት በግልጽ ይህንን ለሕዝቡ ሊያሳየው ግድ ይለዋል፡፡ የተለያዩ አውራ ጎዳናዎች፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎች፣ የባቡር መስመሮች፣ የቴሌኮም ዝርጋታዎች፣ ወዘተ እየተከናወኑ ነው ሲባል ሥርጭታቸው ፍትሐዊ መሆኑ ሊረጋገጥ ይገባል፡፡ ስለመሠረተ ልማት ግንባታዎች ሲነገር የሚሰማ ሕዝብ ውኃ፣ ኤሌክትሪክ፣ ስልክና መሰል አገልግሎቶች በየቀኑ ሲቆራረጡበት ጥያቄ ያነሳል፡፡ ይህ ጥያቄ በበቂ ሁኔታ ምላሽ ማግኘት አለበት፡፡ 
በአሁኑ ጊዜ በርካታ ምላሽ ያላገኙ የሕዝብ ብሶቶች ተከማችተዋል፡፡ ሰላማዊና የተረጋጋ ድባብ ቢኖር እንኳን ደስተኝነት የማይሰማው ሕዝብ በሰላም ወጥቶ ስለመግባቱ እርግጠኛ አይሆንም፡፡ የመንግሥታዊ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ‹‹አበረታች›› መሆኑ በመንግሥት የመገናኛ ብዙኃን የሚነገረው ሕዝብ በተጨባጭ ካላየው የምሬቱ መጠን ይጨምራል፡፡ ፍትሕ አለ እየተባለ በፍትሕ እጦት የሚንገላታ ሕዝብ ነጋ ጠባ እያለቀሰ እንባውን የሚያብስለት ከሌለ ብሶቱ ይከማቻል፡፡ በገዛ አገሩ ሳይሸማቀቅ የፈለገውን አመለካከት ማራመድ የተሳነው ወገን ብሶቱ ጣራ ይነካል፡፡ በሕግ የተረጋገጠለት መብት በአደባባይ የሚጣስበት ወገን ትዕግሥቱ ይሟጠጣል፡፡ የነፃነት አየርን ማጣጣም እየፈለገ መታፈን የሚሰማው ዜጋ ተስፋ ይቆርጣል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ውስጥ ብሶትን የሚያባብሱ ኃይሎች በርክተዋል፡፡ በፓርቲና በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የተደላደሉና የራሳቸውን ጥቅም ብቻ የሚያሳድዱ ኃይሎች ሕዝቡን እያስለቀሱ ናቸው፡፡ በሐሰተኛ ሪፖርት የተዛባ መረጃ እያቀረቡ ተጨባጩን ሁኔታ የሚያድበሰብሱ በዝተዋል፡፡ ከራሳቸው ቡድን ፍላጎት ውጪ ምንም ዓይነት ነገር ማየት የማይፈልጉ ወገኖች የአገሪቱን ገጽታ እያበላሹ ናቸው፡፡ በዚያው ልክ ደግሞ ሕዝቡን እያስለቀሱ ናቸው፡፡ ሃይ ባይ በማጣታቸውም በአገሪቱ ውስጥ ብሶት ተከማችቷል፡፡ ይህ ብሶት ከዕለት ወደ ዕለት እየተወጠረ ነው፡፡ እዚህ ላይ አገራቸውን በቅንነት እያገለገሉ ላሉ ዜጐች አክብሮት እየተቸራቸው፣ እነዚህ ወገኖች ስንዴውን ከእንክርዳዱ እንዲለዩ ጥሪ ይቀርብላቸዋል፡፡ ብሶት እየተከማቸ ነው፡፡ ልብ ያለው ልብ ይበል!

Tuesday, 25 February 2014

Petition asking Switzerland to conduct fair trial for Ethiopian Copilot Hailemedhen Abera

Fair trial for Ethiopian copilot Hailemedhen Abera

Petition asking Switzerland to conduct fair trial for Ethiopian Copilot Hailemedhen Abera

Free Co-pilot Hailemedhin Abera Tegegne

To : Switss Court and Justice System

Fair trial for Ethiopian co pilot Hailemedhen Abera

A repressive state pollutes the spirit of its people; only few are brave enough to live out through the pages of history. Copilot Hailemedhen Abera chose to breathe a clean air of a prison cell rather than his high paying job in a land lead by anarchists.

Opposing dictatorship in Ethiopia is like knocking your self against speedy train. That is  what copilot Hailemedhen Abera chose to do. He chose to do what many are terrified but few dare to try in a totalitarian Chinese backed state Ethiopia. At the end the winner will be the people but Ethiopian dictators does not seem to think so. The sky would fall, the earth will shake, and no one will be able to stop the upcoming mass movement in Ethiopia. It is time for the world to make a choice, the choice is simple. It is a choice between right and wrong. The sick mental state of ethnic federalism by Ethiopian dictators and the dirty blood money they have accumulated have left its mark on their rationality. Ethiopians have continued forced migration as a result of endless repression. Many has told the west about the worst humanitarian condition in Ethiopia but the west is not interested to hear such a reality , rather continued supporting genocide , ethnic cleansing and land grabbing in Ethiopia. The Diaspora communities living in different part of the world have been shouting about the gross human right violation in the totalitarian state Ethiopia. Ethiopians are forced to flee their country; only this time the hero Copilot has hijacked a plane to show the world the agony of the people. The fully state owned Ethiopian airlines copilot Hailemedhen Abera has left an absolute necessary message to the world. Hailemedhen broke a huge fear factor in Ethiopian politics without hurting a single soul.

The action taken by the Copilot opposes all the falsehood in Ethiopia. The state owned Ethiopian airlines CEO mr Tewolde Gebremariam  who highly affiliated with the ruling minority ethnic political party TPLF ( Tigray people liberation Front )is known for staffing the airline by the ruling party supporters and Tigray Ethnic minorities . With the help of national intelligence and security service (NISS) ethnic and political related firing and imprisonment is common in the airline. With the help of national intelligence and security service (NISS) .The political firing of VP Marketing Yeneneh Tekleyes and more than 120 Amhara/Oromo ethnic employees of the airline with a travel ban restriction followed by imprisonment has been exposed to the world.

Through this petition, we would like to call on the Swiss authorities to lodge a fair trial for Ethiopian Copilot Hailemedhen Abera and in doing so allow the voice of Ethiopian people heard and focus on the essential values of democracy.
There for we the Ethiopian people request.
  • A fair trial for Copilot Hailemedhin Abera as his choice of Switzerland is for the extraordinary justice system. We pledge the justice department to give a huge weight for the cause of the action which is democracy valued highly   by the Swiss voters.
  • Take in to consideration the fact that Hailemedhen intention was never to harm the passengers onboard.
  • Reject Ethiopian government request of his immediate extraditions to Ethiopia .This is a direct threat of the justice system and democratic values of the world in general and that of Swiss voters in particular.


Ethiopian Insider Freedom Blogger    Contact the petition author
*First name
*Last name
*City
*Country
*Email address
Show your signature in public?
Your email address will never be displayed in public or released to third parties.

Sunday, 23 February 2014

‹‹ለመጥፋት የተዘጋጀ ሰው የአራት መቶ ሺሕ ብር መኪና ገዝቶ ገንዘቡን አያባክንም››

ዶ/ር እንዳላማው አበራ፣ የረዳት አብራሪ ኃይለመድኅን አበራ ታላቅ ወንድም

ሰሞኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረዳት አብራሪው መጠለፉ የሕዝቡ መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ በአገር ውስጥና በውጭ አገር የሚገኙ ዜጎችና መገናኛ ብዙኃን በማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይ የተለያዩ መላምቶችን አስቀምጠዋል፡፡ ከሥነ ልቡና ቀውስ እስከ ፖለቲካ አጀንዳ በምክንያትነት የቀረበበት ረዳት አብራሪ ኃይለመድኅን አበራ ነው፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት በሆነው ቦይንግ 767 አውሮፕላን በረራ ቁጥር ‹‹ET 702›› ላይ ስለፈጸመው የጠለፋ ሙከራ ጥበበ ሥላሴ ጥጋቡ  ከረዳት አብራሪው ታላቅ ወንድም ዶ/ር እንዳላማው አበራ ጋር ቆይታ አድርጋለች፡፡ ‹‹ከኢሕአፓው ታጋይ ብርሃነ መስቀል ረዳ የአውሮፕላን ጠለፋ ጋር ተመሳሰለ›› ሲሉ አንዳንድ ወገኖች አስተያየት ከሰጡበት የረዳት አብራሪ ኃይለመድኅን ድርጊት በመነሳት ከባህርይው፣ ከአስተዳደጉና ከቤተሰባዊ ግንኙነት ጋር ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ የተደረገው ቃለ ምልልስ እንዲህ ተጠናቅሯል፡፡

ሪፖርተር፡- ቤተሰቡ የሚገኝበትን ሁኔታ ገልጸውልን ወደ ውይይቱ ብንገባስ?

ዶ/ር እንዳላማው፡- እንግዲህ እንደተወራው በቅርቡ አጎታችን ሞቶ ሐዘን ላይ ነው የቆየነው፡፡ እናታችን ወንድሟን ቀብራ ተዝካር እያወጣች እያለ ነው፣ አሁን ደግሞ ልጇ አውሮፕላን ጠለፈ ተብሎ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋሉን የምትሰማው፡፡

ሪፖርተር፡- ከወንድምዎ ረዳት አብራሪ ኃይለመድኅን አበራ ጋር ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኛችሁት መቼ ነው?

ዶ/ር እንዳላማው፡- የአጎታችን ቀብር ላይ ነበር የተገናኘነው፡፡ አጎታችን ዶ/ር እምሩ ሥዩም ይባላሉ፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ነበሩ፡፡ በድንገት በገጠማቸው ሕመም ሕይወታቸው አልፏል፡፡ ታህሣሥ 26 ቀን 2006 ዓ.ም. ይመስለኛል ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኘነው፡፡ እኔ ሱዳን ነው የምሠራው፡፡ ዓርብና ቅዳሜ ዕረፍት በመሆኑ መጥቼ ነው የአጎቴን መሞት የተረዳሁት፡፡ 

ሪፖርተር፡- የአጎታችሁ አሟሟት ከብዙ ነገሮች ጋር እየተያያዘ ነው፡፡ መንስዔው ምን ነበር?

ዶ/ር እንዳላማው፡- ምክንያቱ ከልብ ሕመም ጋር የተገናኘ ነው፡፡ የሚኖረው ኅብር ሬስቶራንት ጀርባ ባለ የዩኒቨርሲቲ መምህራን መኖሪያ አፓርታማ ላይ ነበር፡፡ የእግር ጉዞ አድርጎ ታክሲ እንደተሳፈረ ነው ድንገት የሞተው፡፡ ባለታክሲው በጥርጣሬ ተይዞ ተመርምሮ ነው የተለቀቀው፡፡ እኛም ምንም የምንጠረጥረው ነገር ባለመኖሩ በሕመም ነው የሞተው ብለን አስከሬኑን ፈርመን ተቀብለናል፡፡ አሁን የምንሰማው ወሬ ሰው ገድሎት ነው፣ እንዲህ ነው እንዲያ ነው… የሚለው ትክክል አይደለም፡፡ እኔ ራሴ አስከሬኑን አይቼዋለሁ፡፡ ሕልፈቱ በሌላ ምክንያት ሳይሆን ከነበረበት የቆየ የደም ግፊትና የልብ ሕመም ጋር የተያያዘ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- የአጎታችሁ ሞት ለረዳት አብራሪው አውሮፕላን መጥለፍ ውሳኔ ምክንያት እንደሆነ በስፋት ይነገራል፡፡ ይህ እንደተባለው ተፅዕኖ ፈጥሮ ይሆን?

ዶ/ር እንዳላማው፡- እኛ እንደ ቤተሰብ ያልወደድነው ነገር ይህንን ምክንያት ማድረግ ነው፡፡ በእርግጥ ኃይለመድኅን ከአጎቱ ጋር በጣም ቅርበት ነበረው፡፡ እሱ ብቻ ሳይሆን ሁላችንም ቅርበት ነበረን፡፡ እንደ ወንድማችን ነበር የምናየው፡፡ እሱም እንደዚያው ነበር፡፡ ያደገው እኛ ቤት ነው፡፡ በሌላ ምክንያት ሳይሆን አባታችን እሱን ማስተማር ስለፈለገ ነበር፡፡ እናም ከአጎታችን ጋር የነበረን ቅርበት በጣም የጠነከረ ነው፡፡ ሁላችንም የምናማክረው እሱን ነበር፡፡ ያደግነው ደልጊ የምትባል መንደር ውስጥ ነበር፡፡ ደልጊ ከሰባቱ የጣና ደሴቶች አንዷ ናት፡፡ ኑሯችን በጣና ዙሪያ ነበር፡፡ 

ሪፖርተር፡- እስቲ ስለቤተሰቦቻችሁ ሁኔታ በዝርዝር አጫውቱን?

ዶ/ር እንዳላማው፡- የመጀመርያ ልጅ እንዳላማው፣ በመቀጠል ሃይማኖት፣ መድኃኒት፣ ተክለመድኅን፣ መንበረመድኅን፣ ተወልደመድኅን፣ ብርሃነመድኅን… እነዚህ ደልጊ የተወለዱ ናቸው፡፡ ነዋየመድኅን (አሁን በፊዚክስ ፒኤችዲ እየሠራች ነው)፣ ሕይወት… አጠቃላይ አሥራ አንድ ነን፡፡ ኃይለመድኅን ዘጠነኛ ልጅ ነው፡፡ እንዳላማውና ሃይማኖት ሐኪሞች ስንሆን ሌሎቹ ፊዚክስ፣ አርክቴክቸር፣ ወዘተ ያጠኑ ናቸው፡፡ ቤተሰቦቻችን በትምህርት ላይ ጠንካራ ዕምነት ስላላቸውና እኛም በትምህርት ውጤታማ በመሆናችን የተነሳ፣ አንዳንድ ሰዎች ይህ ቤተሰብ ራሱ አበራ ዩኒቨርሲቲ ነው መባል ያለበት ይላሉ፡፡ በአጠቃላይ ስድስት ሴቶችና አምስት ወንዶች ነን፡፡ 

ሪፖርተር፡- ኃይለመድኅን በልጅነቱ እንዴት ያለ ልጅ ነበር? ከእርስዎ ጋርስ ቀረቤታችሁ ምን ያህል ነው?

ዶ/ር እንዳላማው፡- እሱ ሲወለድ ጊዜ እኔ ተማሪ ነበርኩኝና ብዙም የጋራ ጊዜ አልነበረንም፡፡ የበለጠ የተግባባነው እኔ እዚህ ሥራ ቀይሬ ስመጣና እሱም አርክቴክቸር ትምህርት ቤት ሲገባ ነበር፡፡ ወቅቱም በ1993 ዓ.ም. ነበር፡፡ ኃይለመድኅን፣ ሕይወትና ትንሣዔ በጣም ይቀራረባሉ፡፡ በልጅነቱ በጣም ብሩህ አዕምሮ  (Intelligence) እንደነበረውና ንቁ ልጅ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ በአራት ዓመቱ መጽሐፍ ያነብ ነበር፡፡ አስታውሳለሁ ልጅ እያለ ፀጉሩን ይላጭና አንድ ጓደኛዬ ‹‹ዛሬ ደግሞ ጅል መስለሀል›› ሲለው፣ ‹‹ኧረ! እንደዚህ ከሆነማ ሁሉም ወታደር ጅል ነዋ!›› ብሎ አስቆናል፡፡ እዚህም እያለ በጣም ጥሩ የሚባል ማኅበራዊ ግንኙነት ነበረው፡፡ በተለይ አርክቴክቸር ትምህርት ቤት እያለ ከተማሪዎች ጋር ይግባባ ነበር፡፡ ነገር ግን በጣም  ብዙ ሰው በተሰበሰበበት መሳተፍ ደስ አይለውም ነበር፡፡ በባህሪው ግን በጣም ለሰው ተቆርቋሪ ነው፡፡ ሰው ከተቸገረ ከአቅሙ በላይ ነው የሚያስበው፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው በገንዘብ መረዳት አለበት ከተባለ ከሚችለው በላይ አስተዋጽኦ ማድረግ ይፈልጋል፡፡ 

ሪፖርተር፡- እንግዲህ ኃይለመድኅን የአውሮፕላን አብራሪ የሆነው የአርክቴክቸር ትምህርቱን አቋርጦ ነው፡፡ ምናልባት ለበረራ የነበረው ፍቅር እንዴት ይገለጻል? ውሳኔውንስ እንዴት ተቀበላችሁት?

ዶ/ር እንዳላማው፡- አሥራ አንደኛ ክፍል እያለ ምን መሆን ትፈልጋለህ ስለው ፓይለት መሆን ነው የምፈልገው ይል ነበር፡፡ በአርክቴክቸር በሚመረቅበት ዓመት ዕድሜው ወደ 25 ነበር፡፡ አንድ ሴሚስተር ሲቀረው ነው ያቋረጠው፡፡ ትምህርቱን ያልጨረሰው የዕድሜ ጉዳይ ስለነበር ነው፡፡ ልጨርስ ቢል ዕድሜው ከሃያ አምስት ያልፋል ለዚህ ነበር ያቋረጠው፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአብራሪነት የዕድሜ ገደብ እንደሚያስቀምጥና ከሃያ አምስት ዓመት በላይ እንደማይቀበልም ያኔ ነበር የተገነዘብኩት፡፡ 

ሪፖርተር፡- የበረራ ትምህርቱን ከጀመረና የአየር መንገዱ ባልደረባ ከሆነ በኋላስ ስለነበረው ሁኔታ ምን የሚሉት አለ? አንዳች የማይመቸው ነገር ነበር እንዴ?

ዶ/ር እንዳላማው፡- እኔ በዚህ በኩል ብዙ የማውቀው ነገር የለም፡፡ ምናልባት ታናናሽ እህቶቻችን የበለጠ ያውቁ ይሆናል፡፡ በዚያ ላይ እኔ ላለፉት ስድስት ዓመታት ካርቱም ነው የምኖረው፡፡ አዲስ አበባ የምመጣው ቤተሰብ ለማየት ነው፡፡ ስለዚህ እሱ አየር መንገድ ሥራ ከጀመረ በኋላ ብዙም አልተገናኘንም፡፡ በአጋጣሚ ነው ልንገናኝ የምንችለው፡፡ 

ሪፖርተር፡- የአውሮፕላን ጠለፋውን እንዴት ነው የሰሙት?

ዶ/ር እንዳላማው፡- ባለፈው እሑድ የአጎታችን ተዝካር ነበር፡፡ ለተዝካሩ የተጠራው ሰው መጥቶ በጥሩ መስተንግዶ ተሸኘ፡፡ ከዚያም በአካባቢው ባህል መሠረት ቤተ ዘመድ ተሰብስቦ ሰኞ ጠዋት ተለቅሶ ነው የተለያየነው፡፡ ከዚያም ወደ ባህር ዳር ጉዞ ጀመርን፡፡ ጉዞ ጀምረን መንገድ ላይ ጎማ ተንፍሶ ቆመን ሳለ ነበር የአውሮፕላኑን መጠለፍ በሬዲዮ የሰማነው፡፡ ከዚያም ለአጐታችን ልጅ ለዓለሙ ስልክ ተደውሎ ጠላፊው ረዳት ፓይለቱ መሆኑን አሰማን፡፡ በቦታው እኔ፣ አባታችንና የአጎታችን ልጅ ዓለሙ አብረን ነበርን፡፡ እኛ በጊዜው የኃይለመድኅንን የበረራ ፕሮግራም በውል አናውቅም ነበርና እሱን አላሰብነውም፡፡ 

ሪፖርተር፡- ቤተሰብ እሱ መሆኑን ሲሰማ እንዴት ነበር ሁኔታው?

ዶ/ር እንዳላማው፡- በጣም ነበር የተደናገጥነው፡፡ በመጀመርያ ይህን ለማድረግ የሚያስችለው ምንም ፍንጭ ማግኘት አልተቻለም፡፡ በዚህ የተነሳ ነው፣ አይ በዚያ ምክንያት ነው ለማለት የሚያስችለን ነገር ያልነበረው፡፡ ለተወሰነ ጊዜም በድንጋጤ ተውጠን መነጋገር አልቻልንም ነበር፡፡ መጨረሻ ሁሉም የየራሱን መላምት ማምጣት ጀመረ፡፡ ቅጽበታዊ በሆነ አጋጣሚ ነው የሚል ነበር፡፡ ፓይለቱ ሲወጣ በሩን ቆልፎበት ነው የሚለው አነጋገር በጉርምስና ስሜት ከሰውዬው ጋር ተጋጭቶ ሊሆን ይችላል የሚለው ነገር አመዘነ ማለት ነው፡፡ ወሬው ግን ከቁጥጥር ውጪ ሆነ፡፡ እኛ ከእሱ መረጃ የምናገኝበት ምንም ዓይነት መንገድ የለም፡፡ ሁነኛ ምንጭ የሌላቸው ወሬዎችም መዛመት ጀመሩ፡፡ ያ ወሬ ደግሞ በቤተሰባችን ግንኙነት ላይ ችግር ፈጥሮ ነበር፡፡ አሁንም ያለው ሁኔታ ጥሩ አይደለም፡፡ ይኼን ያለው ማን ነው? ያን ያለው ማን ነው? መባባሉ ችግሩን አባባሰው፡፡ እናም ጥሩ የሚመስለኝ ከእሱ በቀጥታ ብንሰማ ነው፡፡ አሁን ባለን መረጃ የስዊዘርላንድ መንግሥት ጠበቃ ሳይመድብለት አይቀርም፡፡ እናም ጠበቃው ከእሱ የሰማውን እስኪነግረን ድረስ በትዕግሥት ብንጠብቅ ጥሩ ነው፡፡ በሌላ በኩል ይህንን ጠለፋ ለሌላ አጀንዳ መጠቀሚያ አድርጎ መሯሯጥ ቢገታ ጥሩ ነው፡፡ ምክንያቱም በቤተሰቡ ላይ ችግር ያመጣል፡፡ መለመን ካለብንም ሕዝቡን የምንለው ነገር እባካችሁ ከራሱ እስከምንሰማ ድረስ እንዲህ ነው፣ እንደዚያ ነው ማለቱን ብናቆም፡፡ 

ሪፖርተር፡- በመረጃ ደረጃ በስፋት የሚሰማው የታናሽ እህታችሁ ትንሣኤ አበራ መረጃ ነው፡፡ እሷስ ከምን ተነስታ ይሆን መረጃውን የሰጠችው?

ዶ/ር እንዳላማው፡- የጻፈችው በራሷ ነው፡፡ የጻፈቻቸው ነገሮችም እውነት ናቸው፡፡ ያው ከነበራቸው ቅርበት ነው፡፡ ሰው ይከታተለኛል፣ ምናምን ይኼ ከሥነ ልቦናው ጋር በተያያዘ የተባለው ነገር ነበር፡፡ ከእኔ ጋር የተገናኘነው ከወር በፊት ነበር፡፡ ከእህቶቹ ጋር ግን በቅርብ ተገናኝተዋል፡፡ የሚኖረው ገርጂ አካባቢ ነው፡፡ ሕይወትና ትንሣኤም እዚያው ናቸው፡፡ እናም ካልበረረ በአካል ወይም በስልክ ቀን በቀን ይገናኛሉ፡፡ እናም እሷ ያለችው እውነት ነው፡፡ ይኼ እውነት ነው ሲባል ግን በምክንያትነት መደምደሙ ግን ትክክል አይደለም፡፡ የአጎታችን ሞትም በምክንያትነት መቅረቡ ትክክል አይሆንም፡፡ በእርግጥ ሐዘኑ ከባድ ነው፡፡ ብዙ ነገር ነው ያጎደለብን ይኼ አይጠረጠርም፡፡ ይህም የሚያባብስ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ይህንንም አንድ የሥነ ልቦና ባለሙያ ሊያብራራው ይገባል እንጂ፣ እንዲሁ በመላምት የአጎቱ ሞት ድብርቱን አባባሰው፣ ከዚያም ‹‹ፓራኖይድ›› ሆነ ምናምን ማለቱና መተንተኑ ከሙያ ክልል ውጪ ስለሆነ ለምንም ነገር አይበጅም፡፡ ቀጥታ ተያያዥነት ያለው ነገር የለም፡፡

ሪፖርተር፡- እሱ የሚከታተሉኝ ሰዎች አሉ የሚለውን እንዴት ትረዱታላችሁ?

ዶ/ር እንዳላማው፡- ማወቅ ይከብዳል ግን አንድ ነገር ነው፡፡ ለምሣሌ እኔ ወይ በጥቅም ወይ በሆነ ነገር ተነስቼ ብጋጭ ለቤተሰቦቼ እንዲህ እንዲህ ነው ብዬ ልናገር እችላለሁ፡፡ እንግዲህ ይህ የሁላችንም ማኅበራዊ ግንኙነት ውጤት ነው፡፡ ሰዎች ይከታተሉኛል የሚለው ነገር ግን ምናልባት ረቀቅ ያለ ወይም በተጨባጭ የሚታይ ላይሆን ይችላል፡፡ ለምሳሌ አንዳንድ ሰዎች ከፍርኃት በመነጨ ኤፍቢአይ፣ ሲአይኤ ይከታተለኛል ይላሉ፡፡ ኬጂቢ ወይም ያልታወቀ ኃይል… ወዘተ… በዚህ መንገድ በግምት እንሂድ ከተባለ በተጨባጭ የሚከታተሉት ሰዎች የነበሩ አይመስለኝም፡፡ 

ሪፖርተር፡- ምናልባት ግን ከዚህ ጋር በተያያዘ በውጪው ዓለም የምንሰማቸው ነገሮች አሉ፡፡ አንዳንድ ታዋቂ ሰዎች (ባለሙያዎች) መንግሥታዊ ወይም የፀጥታ ኃይል የመፍራት ነገር አለ፡፡ በእርግጥም የፀጥታ አካላት የሚከታተሏቸው ግለሰቦችም ይኖራሉ፡፡ ምናልባት የእሱ የፖለቲካ አቋም ይታወቅ ይሆን?

ዶ/ር እንዳላማው፡- እኔ እስከማውቀው ድረስ የየትኛውም የፖለቲካ ቡድን አባል አልነበረም፡፡ እንዲያውም ብዙ ጊዜ ቤት ውስጥ በምናደርገው ውይይት የመንግሥትን አቋም የመደገፍ አዝማሚያ ነው የሚያሳየው፡፡ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ የተፈጠረ አዲስ ነገር ካለ በበኩሌ አላውቅም፡፡ ይኖራልም ብዬ አልገምትም፡፡ በዚህ ላይ እርግጠኛ ሆኜ መናገር አልችልም፡፡ በመሥሪያ ቤቱ ውስጥ ባለው ነገር (ኦፊስ ፖለቲክስ) ግን ምን እንዳለ የማውቀው የለም፡፡ በቢሮ ውስጥ መገለል፣ አድልኦና መሰል ችግሮች ገጥመውት ይሁን አይሁን አይታወቅም፡፡ ለእኔም ሆነ ለሌሎቹ የነገራቸው ነገር የለም፡፡ አድልኦና መገለሉ ተፈጽሞ እንኳን ቢሆን ያ ይከታተሉኛል ምናምን ከሚለው ነገር ጋር እንዴት ሊያያዝ እንደሚችልም የሚገባኝ ነገር የለም፡፡

ሪፖርተር፡- ከሥነ ልቦናው ጋር በተያያዘ ባለሙያ አይቶት ነበር እንዴ? ትንሣኤም የሥነ ልቦናው ሁኔታ በእሷም ላይ የሚታይ እንደነበር ፍንጭ ሰጥታለች፡፡

ዶ/ር እንዳላማው፡- መጨረሻ ያገኙት መድኃኒትና ሕይወት ናቸው፡፡ እናም ከመሄዱ በፊት መክረውታል፡፡ ባለሙያ እንዲያማክርም አሳስበውታል፡፡

ሪፖርተር፡- ከእርስዎ ጋር በተገናኛችሁ ጊዜ ግን የሆነ የተለየ ነገር አልታየበትም?

ዶ/ር እንዳላማው፡- ከእኔ ጋር የተገናኘነው ለአጎታችን ለቅሶ ነበር፡፡ እንዲያውም እኔና እሱ ቀብር አልደረስንም ነበር፡፡ በዚያን ቀን በተነሳነው ፎቶግራፍ እንደሚታየው እሱ የተለየ ነገር ውስጥ ስለመኖሩ ፊቱ ላይ የሚነበብ ነገር የለም፡፡ እንዲያውም ምን ዓይነት መልዕክት ደርሶት እንደነበር ባላውቅም፣ የሆነ የሚያስቅ ነገር እንደገጠመው ነው የምገምተው፡፡

ሪፖርተር፡- መጠጥና ሌሎች ተያያዥ ልማዶች ነበሩበት?

ዶ/ር እንዳላማው፡- መጠጥ አይጠጣም፡፡ አልፎ አልፎ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ ቢራ መጠጣት የለመደ ይመስለኛል፡፡

ሪፖርተር፡- እስቲ ስለመጨረሻ ግንኙነታችሁ በደንብ ይንገሩን?

ዶ/ር እንዳላማው፡- ቅድም እንዳልኩት እኔና እሱ ዘግይተን ሐሙስ ቀን ነው በለቅሶው ላይ የተገኘነው፡፡ አስከሬኑ ማታውኑ በዩኒቨርሲቲ መኪና ተጭኖ መጣ፡፡ እኔ ትንሽ አሞኝ ነበር፡፡ እሱ ግን ደህና ነበር የሚመስለው፡፡ አሁን ትንሣኤ ያለችው ነገር ከዚያ በኋላ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- እንድ እህታችሁ መንበረ ሳትሆን አትቀርም ትዊተር ላይ ባሰፈረችው ጽሑፍ፣ ‹‹ውጭ አገር መኖር አይፈልግም፣ እኔን እንኳን በአገሬ እንድኖር ነበር የሚመክረኝ፤›› ብላ ነበር፡፡ ታዲያ ለምን ይሆን በስዊዘርላንድ ጥገኝነት መጠየቁ የተሰማው?

ዶ/ር እንዳላማው፡- ውጭ አገር መኖር አይፈልግም፡፡ እዚህ አገር ውስጥ ከሚገጣጠሙት ውስጥ አዲስ መኪና  ከገዛ ሦስት ወራት አይሞሉትም፡፡ እንዲህ ዓይነት ንብረት የገዛ ሰው ደግሞ ውጭ አገር ሄዶ ለመኖር የሚያስብ አይመስለኝም፡፡ ከቤቱ ውስጥ አንድ ዕቃ አላነሳም፡፡ ላፕቶፑን እንኳን አልያዘም፡፡ የተለመደችውን የበረራ ሻንጣ ብቻ ነው የያዘው፡፡ ተዘጋጅቶ እንዳላደረገው የሚያሳዩ ሰላሳ ምክንያቶች አሉ፡፡ የተዘጋጀበት ቢሆን ኖሮ በጣም ለሚቀርቡት እህቶቹ ንብረቱን ይሰጣቸው ነበር፡፡ 400,000 ሺሕ ብር የሚያወጣ መኪና በመግዛትም ገንዘቡን አያባክንም፡፡

ሪፖርተር፡- የሴት ጓደኛ ነበረችው?

ዶ/ር እንዳላማው፡- ለእኔ ያስተዋወቀኝ ሰው የለም፡፡ ግን እገምታለሁ፡፡ እህቶቹ በተለይ ሕይወት ይህን በደንብ ታውቃለች፡፡ ይህን ተከትሎም ብዙ ነገር ይሰማል፡፡ አንዲት ኢንተርኔት ካፌ ካላት ሴት ጋር ግንኙነት አለው ተብሏል፡፡ እንግዲህ ከሆነ ጥሩ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ሕይወቱና ማንነቱ እንዲህ መነጋገሪያ በመሆኑ እናንተ ምን ይሰማችኋል?

ዶ/ር እንዳላማው፡- የእሱ ሕይወት ብቻ አይደለም፡፡  የቤተሰቡንም ሕይወት ነው የሚነካው፡፡ አባታችን አራጣ አበዳሪ እንደነበሩም ተገልጿል፡፡ ይህ ቅጥፈት ነው፡፡ እውነት እንኳን ሆኖ ቢሆን ከዚህ ጉዳይ ጋር የሚያገናኘው ምን እንደሆነ አይገባኝም፡፡ ሊያስረዱኝ የሚችሉ ሰዎች ካሉም ይገርመኛል፡፡ በዚህ በጣም አዝነናል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የደረጃ ዕድገት ጠይቆ ተከልክሏል የሚል ነገርም ሰምቻለሁ፡፡ የዚህ ወሬ መሠረት ግን ከየት እንደሆነ አልተገለጸም፡፡ ከዚህ ጋርም የሚያያዝበት አመክንዮ አልተቀመጠም፡፡ በተለይ ጉዳዩን ከፖለቲካ ጋር የሚያገናኙትም በርክተዋል፡፡ ቤተሰቡ ባለፀጋ መሆኑና እኛም በትምህርት የላቅን መሆናችን በግነት ነው የሚወራው፡፡ ከትንሿ ሕይወት በስተቀር ሁላችንም በመንግሥት ትምህርት ቤት ባህር ዳር ጣና ሐይቅ ነው የጨረስነው፡፡ ውጤታችንም በጣም ጥሩ የሚባል ነው፡፡ 

Saturday, 22 February 2014

The Brother Speaks Out

22 FEBRUARY 2014 WRITTEN BY  
This week the hijacking of an Ethiopian Airlines plane, flight number ET-702, and the first officer behind the hijacking, Hailemedhin Abera, have dominated the news.

Endalamaw Abera the oldest brother of Hailemedhin
After it was revealed the mainstream and social media have been speculating as to why he did it. Reasons include doubts about his mental health up to resilience against injustice and oppression. Some compared him with the former Ethiopian People's Revolutionary Party (EPRP) leader, Berhanemeskel Redda, who hijacked an airplane, while others said that he was a troubled individual. Family members have responded on social media, like Facebook and Twitter, that their brother is a good man and not a criminal. Regarding these speculations and other pertinent issues, Tibebeselassie Tigabu of The Reporter spoke with Endalamaw Abera (MD), the oldest brother of Hailemedhin. Excerpts:
 When did you last see Haillemedhin?
Dr. Endalamaw: I saw him at my uncle’s, Emiru Seyoum, funeral on January 4.  He passed away that day. We actually went together. I came from Sudan, Khartoum
There has been speculation about his death, and it has been said that it was directly related to the hijacking?
He died of a cardiac condition. He was being treated at the Addis Cardiac Hospital. The incident happened while he was in a taxi. His house is located around Bole in the apartments behind Heber Restaurant. On that day he walked to Dembel area and took a taxi after that. 
Around Gibi Gabriel church he passed away while he was in a taxi. All the passengers were taken to be investigated by the police. Looking at his body there was no strangling or that type of symptom, and there was no detection or physical sign that it was a homicide. So we actually signed and took his body. Now after the hijacking rumors have been going on in the town that his death was a mystery. They say it was unrevealed and some try to make it a conspiracy theory out of it. We believe it was a natural death. He suffered from high blood pressure and also had cardiac problems. 
Was he close to Hailemedhin? Some put it as a cause and effect relationship, was he affected that much?
That is the part we do not like. Were they very close? Yes, they were. Without the presence of our parents he was the acting parent. He gave us advice in anything. If we trace our achievements academically he is greatly involved in them. Even when I introduced him to people I did not say he was my uncle, I said he was my brother, and the same also went for him. He was my mother’s brother, and what many people do not know is that he grew up in our house. My parents raised him. My father wanted him to have a better education so he came to Delgi port; which takes five hours by boat from Tana. Our life was around Tana. We are 11 children; six women, five male. Seven of us were born in Delgi, and the others in Bahirdar. Hailemedhin is the ninth child and was born on July 31, 1983. With one exception we all attended high school, Bahirdar Tana hayik highschool. We had good grades. He finished high school at 17. He had good friends and a normal life.
 There are two medical doctors in our family (Endalamawu and Medhanit), two computer engineers (Tewoldemedhin and Birhanemedhin), an air craft maintenance engineer (Teklemedhin), an economy and nursing graduate (Menberemedhin), a physics PhD student (Newayemedhin), a computer science graduate (Hiwot) and the last one, Tnsae, dropped out from the literature department. Getting to the main point, we are deeply saddened and affected by it, but drawing conclusions of cause and effect is wrong.
What kind of child was Hailemedhin growing up? Was he close to you?
We were not that close. When he was born I was a second year medical student in Gondar. We actually became close when I came to Addis Ababa where he was an architecture student; 13 years ago. We reconnected and became close then. Hailemedhin also said that. But he was very close with his two sisters, Hiwot and Tnsae. As a child he was very active, very intelligent. I remember him as a child only four years old, his hair was shaved and we were teasing him, and he said, ‘In that case soldiers are fools’. His social life was OK but he was a bit shy, feeling uncomfortable at large gatherings. He was very generous, very caring and sometimes he did more than his capacity. Especially when it came to money, he helped people out. 
When he quit architecture and joined piloting, how did you take his decision? Did you support it?
When he was in grade 11 I asked him what he wanted to be, and he did not even hesitate, he answered by saying pilot. I thought it was not that serious. He joined architecture school and on his graduating year he was 25. There was a piloting exam, he took it and passed. He said he was going to quit and take piloting training. He was only left with one semester and I asked him why was he not going to finish it. Apparently he said there is an age limitation to take training, and you cannot qualify if you are over 25. He said if I finish I will be over 25, which means I cannot enroll in to the training. So we were OK with it.
Did he talk about his job environment? Were there any hostilities in his work place? 
I don’t clearly know. For the past six years I have been in Khartoum. After he started his job at Ethiopian Airlines I was on and off. I come here every three months, that’s when we meet. His younger sisters might know. 
How did you and the rest of the family hear about the hijacking?
Last week, on Sunday, it was the death commemoration of our uncle, Emiru Seyoum P.h.D. We went to Sahgura; his and also my mother’s birth place. After the ceremony on Monday all the relatives started our journey to Bahirdar. We stopped with tire problems and heard the news on Radio Fana that a plane had been hijacked. Someone called my cousin, Alemu, and told him it was the co-pilot. After a while we heard the news.
How did you feel about the situation?
We did not know what to feel. We could not suspect that he would do something like this, it was shocking. There was nothing that could make us speculate as to why he did it. For a couple of hours we could not talk. We sat down solemnly. We did not know how to react. So everyone started speculating. We agreed that it was probably a temporary conflict with the pilot. So we thought it was a reaction of the moment. After that we could not control the rumors. The sources are not known, some of it was fabricated. It also created a problem in our family’s communication. We started interrogating each other. Our condition is still not good. We are not in peace. What I think is that we have to hear directly from him. We also heard that the Swiss government is going to give him a lawyer. So if it is true we want to hear from the lawyer. He still has not communicated with us. Many tried to link the hijacking to a political agenda and this should stop. It is creating a serious problem for our family. It is not only worrying us but also messing up our relationships as a family. We are pleading with people to stop the speculation.
Part of the speculation came out from a statement by your sister, Tnsae. She wrote on Facebook describing his mental status. How do you regard this speculation? How did she come to this conclusion? Did he see a psychiatrist?
She wrote it without consulting us. After she wrote it we started to look back and it was all true. He was suspicious of his environment. He felt that people were following him. He also tried to capture the people who followed him using different technology. He was close to Tnsae and Hiwot, and they live close by. They meet every day. What she said was true but it does not mean it is cause and effect. People should not conclude it. It is like trying to relate the incident with our uncle’s death. In medicine and law there is a concept of aggravating factor. These reasons might be aggravating reasons. But a psychiatric has to say that. It is not me, a journalist, or someone else who can speculate and decide. They are out of their professional boundaries. It is not good for everyone, for the family, for the police and also for his case. 
What about if there were people who were following him?
It is very difficult to know. If you take our social life we might create enemies because of a conflict of interest. This might create tension. But on the other hand, in medical terms, people following is a common denominator. Sometimes it is not even people, they become abstract institutions. There are people who say the CIA, FBI, or an unknown power follows me. If we take it on this instance, I don’t think there was anyone following him.
Was he politically involved? 
As far as my knowledge is concerned he was not a member of any political party. When we discuss issues he is actually a supporter of the existing government in this country. I don’t know if there are special cases that happened in the past couple of weeks. I don’t think there is or will be something new. I can’t talk about it. Talking about office politics, I don’t know is the answer. He did not tell me if he was discriminated in the office. I also did not hear from any members of the family. 
Had he been to see a psychiatrist?
The last people who saw him were Hiwot and Medhanit. I think they advised him to go talk to a specialist. 
Was he acting different recently? Any new behavior?
This is the last picture, taken at our uncle’s funeral (in this picture Hailemedhin is laughing, holding his phone). I don’t think he was depressed. He does not drink that much. It is only occasionally that he drinks. In my opinion he did not show any signs of depression or something new. 
One of your sisters, Menberemedhin, also posted on Twitter, saying that he did not want to live outside of his country, and he even advised her to return. Is this ironic as he is now asking for asylum? How do you reconcile the two?
He does not want to live outside of his country. He actually bought a new car worth four hundred thousand birr three months ago. He paid half of the down payment. He did not take any of his stuff. He took only a small travelling bag; he did not even take his laptop. There are many reasons that show he was not prepared to leave. Why would a person buy a car if he was preparing to ask for asylum? Why would he waste his money? He could have taken it with him.
Does he have a girlfriend?
He did not introduce me to anyone. I assume so. I read he has been seeing someone who owns an internet café. If that is true it is good.
His life is being greatly scrutinized. How do you feel about that?
It is not only his life.  It is also the family’s life which is under scrutiny. Unnecessary details and also fictitious writings are there. There are rumors such as my father was a money lender. This is all false information, and we will get back to that once the dust settles. I don’t know how it is even related. This is not only factual error but also defamation. It is not even connected. They said he has a grievance because he was not promoted, but why did they not research? Some groups are using it for political purposes. To do that they are exaggerating our lives, how we are from rich family. Our achievements are exaggerated.  
What are the possible scenarios that await him? What should be done?
The Swiss officials should give priority to his health and we hope that they would do that. After his health the law has its own way of dealing with things. Until then people should stop speculating and drawing conclusions. People only see 11 of us, but our cousins are more than 700 from my father’s side. My grandfather’s descendants reach to the fifth generation. We have a reunion every five years, and also from my mother’s side there are 200 of them. Our relatives are dispersed all over the world. They are all affected by this. The media also should respect our family’s privacy. I wish him good things. We should not see him as a criminal. Let’s first see him as someone who needs help. I hope good things will come of it.

Friday, 21 February 2014

Pregnant woman who says she was gang-raped in Sudan now faces death penalty after being accused of adultery because she waited to report the crime

  • The Ethiopian teenager was three months pregnant when she was attacked
  •  She was raped by seven men in Omdurman, Sudan in August last yea
  • The rape was filmed and later spread on social media by the perpetrator
  • The married woman is now facing the death penalty for adultery


PUBLISHED: 10:18 GMT, 19 February 2014 | UPDATED: 12:24 GMT, 19 February 2014


A nine-months pregnant teenager who claims she was raped by seven men in Sudan is now facing the death penalty after being charged with adultery.

The married Ethiopian woman was just 18 years old, and three months pregnant, when she was subjected to the attack in August last year.

She says she was searching for a new home in Omdurman,  near the capital Khartoum, and one of the seven accused lured her into an empty property on the premises of renting it out to her and her husband.


Unbelievable brutality: The pregnant Ethiopian teenager was raped by seven men after being lured into an empty building near the Sudanese capital of Khartoum, on the premise of renting the property (stock image)

She was attacked and held down while a group of men, reportedly aged between 18 and 22, took turns in raping her, according to the Strategic Initiative for Women in the Horn of Africa (SIHA) network.

Her ordeal was filmed by one of the perpetrators and was circulated on social media via WhatsApp several months after the attack.

When the video of the rape surfaced, the woman and the alleged rapists were arrested and accused of making and distributing indecent material and indecent behaviour.

After first being denied bail, and later charged with prostitution and adultery, the woman is now being prevented from making a formal complaint of rape.

Sudanese media reporting the case has tried to undermine the woman's story by claiming she has HIV and is a prostitute, SIHA said.


 The woman is being held by police and refused to report the rape by the Sudanese Attorney General as she is being investigated for adultery and incident behaviour (stock image)

'The intention to place culpability on the part of the victim is of great concern and seeks to deflect and reduce accountability of the perpetrators, but more disturbing is that the charge of adultery carries with it the potential sentence of death by stoning if found guilty,' SIHA said.

'There have even been cynical attempts to falsely claim that the men were accidently prescribed hallucinogenic drugs by a chemist beforehand.'

'Impunity and silence on crimes of sexual violence committed against IDPs [internally displaced persons], migrants and impoverished women in Sudan has been a pattern for years,' Hala Alkarib, regional director of the SIHA network, told the Guardian.

'Successful prosecution of rape is the exception as opposed to the norm and most certainly does not reflect the level of incidence.

'Instead victims face the risk that they will instead be prosecuted for adultery, being re-vicitmised by the judicial system, and threatened with the ultimate sentence of death by stoning.'

According to SIHA, the Attorney General has denied her the right to report the rape as she is currently under investigation for the other charges.

The Attorney General also argues that she should have reported the rape at the time of the attack.

However the woman has told her lawyer that the group of men who attacked her threatened to kill her if she told anyone, and as a result, she was too scared to report it.

She was further deterred by the fact that she told a police officer who found her shortly after the attack what had happened, who dismissed her story.

The police officer decided against pursuing an investigation as it was Eid Al Fitr, a public holiday in the Muslim country, SIHA said. He has been charged with negligence.

The teenager was arrested on the 17th of January and despite being close to giving birth, she has since been sleeping on a concrete floor in a cell at a local police station.

Two attempts to secure bail for her on health grounds have been refused.
A total of ten individuals, including another police officer who helped spread the video, are currently on trial related to this case.