Thursday, 7 March 2013

በራስ ወዳዶችና በስግብግቦች ምክንያት የተቃጡብንን እነዚህን ወራሪዎች በፅናት እንመክታቸው


የነገው ሃገር ተረካቢ ሴት ህጻናት ልጆች በባለስልጣናት ጀሌዎች እያጠፉ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው ዙሪያችንን የተከበብነው ጊዜያቸውን እየጠበቁ በሚፈነዱ አደገኛ የሱስ ቦምቦች ነው እነዚህ ቦምቦች የተቀበሩባቸው ሥፍራዎች ደግሞ ፍፁም በራስ ወዳድነት በተተበተቡ የወያኔ ባለስልጣናት ጀሌዎች ቡድኖች የሚመሩ ናቸው፡፡ በሙስና አዕምሯቸው በተሰለበ ሹሞች ይሁንታ የሚንቀሳቀሱ ናቸው፡፡ በሙስና የተለከፉ ባለስልጣናት ራስ ወዳዶች የበላይነት እየያዙ የአዲሱን ትውልድ ራዕይ እያጨናገፉ ናቸው፡፡ ራዕይ አልባዎች ከራሳቸው ጥቅም በላይ የአገር ጉዳይ ገዝፎ ስለማይታያቸው የዕድገት ፀሮች ናቸው፡፡ ወጣቱን ትውልድ በሃይማኖት በስነምግባር ተኮትኩቶ እንዳያድግ እየገደሉት ነው ደንታ ቢስነትና ራስ ወዳድነት ከቁጥጥር በላይ በሆኑበት በዚህ ጊዜ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን እጅ ለእጅ መያያዝ አለባቸው፡፡ ማኅበራዊ ኃላፊነት በራስ ወዳድነትና በስግብግብነት ላይ የበላይነት እንዲይዝ ከልባችን እንነሳ፡፡ አንዳችን በሌላችን ላይ ጣታችንን እየቀሰርን ከምንወነጃጀል ወጣቱን ትውልድ እንታደገው፡፡ የራቁት ዳንስ ቤቶች እንደ አሸን እየፈሉ ነው፡፡ ከርካሹ ካናቢስ ጀምሮ እስከ ውዱ ሔሮይን ድረስ አገሩን ግዛታቸው ያደረጉት ይመስላሉ፡፡ ልቅ የወሲብ ግንኙነትና ግብረ ሰዶማዊነት በአስደንጋጭ መጠን እየስተዋለ ነው፡፡ ለእነዚህ ርካሽና አልባሌ ድርጊቶች የሚወጣው ገንዘብ ቢሰላ ምን ያህል ዕድገት ይመዘገብ ነበር ያሰኛል፡፡ 

የገዢዉ ፓርቲ ባለስልጣናት ታክስ በማጭበርበር፣ በዚህ ደሃ ሕዝብ ላይ የስንጥቅ ስንጥቅ ትርፍ በማጋበስ፣ ጥራት የጎደላቸው ምርቶችና አገልግሎቶችን በማቅረብ፣ በየመጠጥ ቤቱና በሱስ ማስያዥያ ቦታዎች በመዘፈቅ አገርንና ትውልዱን ከማሰናከል ሊታቀቡ ይገባል፡፡ ኮድ ሦስት እና አራት ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን በየራቁት ዳንስ ቤት እየገተሩና አልኮል እየተጎነጩ የታዳጊውን ትውልድ ራዕይ ማጥፋት የተጠናወታቸው በርካታ የወያኔ ጀሌዎች አሉ፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙባቸው ከተሞች እየዘመቱ በገንዘባቸው አማካይነት የነገውን አገር ተረካቢ ዜጎች ዕድል ማጨለም ሱስ የሆነባቸው እነዚህ ኃላፊነት የማይሰማቸው የወያኔ ጀሌዎች ናቸው ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ተቋማት የሚልከው ትምህርት እንዲያገኙ ነው የባለስልጣናት ልጆች በአውሮፓና በአሜሪካ ተንደላቀው ሲማሩ ሌላውን በገዛ ሃገሩ ልጆቹን ማስተማር አልቻለም

ኢትዮጵያ ሃገራችንን እግዚአብሄር ይባርክ

No comments:

Post a Comment