Friday, 8 March 2013

አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በኦስሎ ውስጥ በደመቀ ሁኔታ ተከበረ


ለም አቀፍ የሴቶች ቀን ኦስሎ ውስጥ በደመቀ ሁኔታ ተከበረ  የኖርዌይ ንግስት ሶኒያ ሃራልሰን  እና የመጀመሪያዋ የውጭ ዜጋ የባህል ምኒስትር የሆነችዉ ሃዲያ ታጂክ በተገኙበት በፎልክ ቴያትር ተከበረ በዝግጅቱ ላይ ንግስት ሶኒያ ሃራልሰን  እና ምኒስትር  ሃዲያ ታጂክ በየተራ ንግግር አድርገዋል ኢትዮጵያዊቷ በዝግጅት መሪነት በጋዝጤኝነት  በድምጻዊነት የምትታወቀው  ሃና ወሰኔ ዝግጅቱን በመምራት አና በበማዜም ለዝግጅቱ ድምቀት ሰጥተዋለች 

ድሞክራቲክ ለለውጥ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት በኖርዌይ የሴቶች ክፍል የኢትዮጵያዊነት መገለጫ ሆነው ሃገር ልብስ በመዋብ ዝግጅቱን አድምቀውታል ዛሬም ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ይሰደዳሉ ይገደላሉ ይደፈራሉ ይታሰራሉ ይደበደባሉ  የባለስልጣናት የወሲብ መጠቀሚያ ሆነዋል ለእድገታቸው መሰረት የሚሆን የነፃነት አየር ለመተንፈስ ገና አልታደሉም  በማለት አስከፊውን የሴቶች ሁኔታ በበራሪ ወረቀቶች መልዕክት አስተላልፈዋል 

የዝግጅቱ መዝጊያ የሆነው ሰልፍ ላይ ለፖለቲካ እስረኞቹ ለጋዜጠኛ ሪዮት አለሙና ሌሊሳ ወዳጆ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ደጃፍ የሚደርስላት አጥታ ህይወቷ ላለፈው የልጆች አናት አለም ደቻሳ በአረብ ሃገራት ህይወታችውን ላጡት አካላቸው ለጎደለው ለተሰደዱት ዛሬም ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ለሚገኙት የሽማ ማብራት ስነ ስርዓት ድሞክራቲክ ለለውጥ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት በኖርዌይ የሴቶች ክፍል ተደርጎላቸዋል በሃገራችን ሴቶች በሴትነታቸው  መንግስት አያደረሰ ያለውን ስተደደር በደል በመፈክሮች አሰምተዋል በውቅታዊ ጉዳዮች ላይም ውይይት ተደርጓል






No comments:

Post a Comment