Friday, 24 May 2013



Democratic Change in Ethiopia Support Organization Norway

DCESON

ቀን 23/05/13 ዓ.ም 

ሰማያዊ ፓርቲ በግንቦት 17 2005 ዓ.ም የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ በመደገፍ ከዲሞክራሲያዊ ለውጥ 
በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ የተሰጠ አቋም መግለጫ!

የሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት ፅ/ቤት ፊት ለፊት ጥቁር በመልበስ እና ፍፁም ሰላማዊ የሆነ ሰልፍ ለማድረግ ማቀዱ ይታወቃል በመሆኑም እንዲህ አይነት ሰላማዊ የህዝብ የመብት፣ የፍትህ እና የዲሞክራሲ ጥያቄን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የሚደግፈው መሆኑን ስንገልጽ::

በተለይ የሰማያዊ ፓርቲ “በአገዛዙ ምላሽ የተነፈጋቸው የተለያዩ አንገብጋቢና መሰረታዊ የሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ የመብት፣ የፍትህ እና የዲሞክራሲ ጥያቄዎችን የዓለም ዓቀፍ ማሕበረሰብ ትኩረት እንዲሰጣቸው በሚል ሃሳብ በአዲስ አበባ የሚከበረውን የአፍሪካ ሕብረት 50ኛ ዓመት በዓልን አጋጣሚ በመጠቀም ድምፃቸውን ለአለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ለሃገር መሪዎች እና ለታላላቅ ሚዲያዎች ለማሰማት በማቀዳቸው ከጎናቸው ሆነን ድጋፋችንን እንገልፃለን::

እንደሚታወቀው የወያኔ አገዛዝ ባፀደቀው ህገመንግስቱ ላይ የመሰብሰብ፥ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት የተደነገገ ሲሆን፥ ከ1997 ምርጫ በኋላበግልፅ በከፍተኛ ደረጃ በውርደት የተሸነፈው የወያኔአገዛዝ በአቶ መለስ ዜናዊ ትእዛዝ ብቻ ለራሳቸው በሚያመች ሁኔታ ያረቀቁት ህገመንግስቱ ከተሻረ በኋላ የዜጎች የመሰብሰብ፥ ሰላማዊ ሰልፍ የማረግ እንዲሁም ተዛማች መብቶች ከተገፈፈ እነሆ ስምንት አመታት ተቆጥሯል::

በመሆኑም ይህንንአንገብጋቢና መሰረታዊ የሆነየመብት፣ የፍትህ እና የዲሞክራሲ ጥያቄ ሁሉም ነጻነት የተጠማ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ሊደግፈው ይገባል ብለን እናምናለን፣ ሰለሆነም ሙሉ አጋርነታችንን ለማሳየት የየዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዎይ የሥራ አስፈጻሚዎች፣ አባላት እንዲሁም ደጋፊዎች ቀኑን የጥቁር ልብስ በመልበስ ለሰማያዊ ፓርቲ ጥያቄ ድጋፍችንን እናሳያለን፣ በማያያዝም በኖርዌይ ለሚኖሩ መላ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ ቀኑን የጥቁር ልብስ በመልበስ ለሰማያዊ ፓርቲ ጥያቄ ድጋፋችሁን እንድታሳዩ ድርጅታችን ጥሪውን ያቀርባል::

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ
ኖርዌይ፣ ኦስሎ፣ ግንቦት 23፣ 2013

No comments:

Post a Comment