Sunday, 30 December 2012

በሱዳን በኩል የሚካሄደው ሕገወጥ ንግድ እየተባባሰ መምጣቱ ተጠቆመ

ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር በሚያዋስናት ጠረፍ በኩል ሕገወጥ የገቢና ወጪ ንግድ መስፋፋቱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያ ከሱዳን በኩል የምትዋሰንባቸው ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝና አማራ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ የጠረፍ ከተሞች በርካታ ሸቀጦች፣ የቁም እንስሳት፣ ደንና የደን ውጤቶች በገፍ እንደሚወጡ ታውቋል፡፡

በቤንሻንጉል ጉምዝ በከፍተኛ ደረጃ የሚወጣውን የቁም እንስሳት ከፍተኛ መጠን ያለው የቁም ከብት አሁንም በጉባ በኩል እየወጣ መሆኑ ይነገራል፡፡ በተጨማሪም በጋምቤላና በቤንሻንጉል ጉምዝ በኩል ቡና በብዛት ከአገር እየወጣ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡ በአማራ ክልል መተማ በኩል የደን ውጤቶችና የቁም እንስሳት በከፍተኛ መጠን ከአገር እንደሚወጡ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

እነዚህን ሸቀጦች ለማስወጣት ለጭቃና ለጎርበጥባጣ መንገድ የማይበገሩ መርሰዲስ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ የጠረፍ ንግድ በተለይ ሥጋ ላኪዎችንና የቆዳ ፋብሪካዎችን እየጎዳና ከገበያ እያስወጣ እንደሆነ ይናገራል፡፡ ምክንያቱም ከጠረፍ ወደ መካከለኛው ገበያ መቅረብ የነበረበት የቁም ከብት በድንበር በኩል በሕገወጥ መንገድ እየወጣ በመሆኑ ነው፡፡

የዘርፉ ሕጋዊ ነጋዴዎች ይህንን ችግራቸውን በተደጋጋሚ ለመንግሥት ቢያቀርቡም፣ ጉዳዩ እየተወሳሰበ እንጂ መፍትሔ ማግኘት አለመቻላቸውን ይገልጻሉ፡፡

Saturday, 29 December 2012

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሴራውን ጀመረ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በሚያዝያ ለሚደረገው የአዲስ አበባና የአካባቢ ምርጫ ፓርቲዎች የውድድር ምልክት የሚወስዱበትን ጊዜ በሁለት ቀናት እንዳራዘመ ሲገልፅ ፓርቲዎች በበኩላቸው የውድድር ምልክት መውሰጃ ቀነ ገደብ አልነበረውም አሉ፡፡ ምርጫ ቦርድ ከትናት በስቲያ ፓርቲዎችን ለውድድር ለማነሳሳት በሚል የውድድር ምልክት የሚወስዱበትን ጊዜ በሁለት ቀን በማራዘም ዛሬ ታህሳስ 20 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ በቦርዱ ፅ/ቤት በመገኘት ምልክታቸውን እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የምርጫ የጊዜ ሰሌዳውን በተመለከተ ከምርጫ ቦርድ ጋር መወያየት እንደሚፈልጉ ሲገልፁ የቆዩት 33ቱ ፓርቲዎች ምርጫ ቦርድ ያስቀመጠውን የጊዜ ቀነ ገደብ እንደማይቀበሉት የገለፁት  ቀነ ገደቡ ፓርቲዎችን እርስ በርስ ለመከፋፈልና ለመለያየት የሚደረግ ሴራ ነው ብለዋል፡፡

በምርጫው የጊዜ ሰሌዳ ላይ አለመስማማታችንና በምርጫ ምልክቱ ዙሪያ ውይይት እያካሄድን እንደሆነ ምርጫ ቦርድ ያውቃል ያሉት አቶ አስራት፤ ቀን ገደብ ማስቀመጥ የቦርዱ ስልጣንና ሃላፊነትን አይደለም ብለዋል፡፡ ቦርዱ የውድድር ምልክቱን ቀነ ገደብ ያስቀመጠው ለምርጫው አስቦ ሳይሆን ፓርቲዎችን ለመከፋፈል እንደሆነ አቶ አስራት ተናግረዋል፡፡

Sunday, 23 December 2012

በኩዌት በሳዑዲ ዓረቢያና ጅዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሰው ኃይልን በርካሽ ዋጋ ሊያቀርብ እንደሚችል በአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ማስታወቂያው እያስነገረ ነው፡፡

Hellen Zewdu
 
ሰው በፈለገበት ቦታና አገር የመዘዋወር መብቱ በሕገ መንግሥቱ ተረጋግጦለታል፡፡ በኮንትራት በቤት ሠራተኝነት ወደ አረብ አገሮች የሚሄዱ ኢትዮጵያዉያን የሚደርስባቸዉ በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ መባባሱ ይሰማል።   ኢትዮጵያውያኑ ላይ ከፍተኛ  የሆነ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ  ጉዳት እየደረሰ ነው። ለዚህም በዋነኛነት ማሳያ የሚሆነው በተለያዩ የዓረብ አገሮች በቤት ሠራተኛነት በሚሄዱት እህቶቻችን ላይ የሚታየው የሞት፣ የአካል መጉደል፣ የመደፈርና ያለደመወዝ ማባረር ጥቂቶች ናቸው፡፡ በዚህ ዓመት እንኳን ከዓለም ደቻሳ ጀምሮ  በድብደባ ህይወታቸውን ያጡትን  ለከፍተኛ የአካል ጉዳት የተዳረጉትን የተደፈሩትን ከፎቅ የተወረወሩትን ለአእምሮ መቃወስ የተዳረጉት የትየለሌ ናቸው ኢትዮጵያዉያን የኮንትራት ሰራተኞች በአሰሪወቻቸው የሚደርስባቸውን ጥቃት ታዋቂ የሳዉዲ ጋዜጦች ሳይቀሩ በዝርዝር እየዘገቡት ነው፡፡

የወገኖቻችን እንግልት የሚጀምረው አገራቸው ላይ ነው፡፡ የሳዑዲ ዓረቢያ ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያውያንም በዜጎቻችን ላይ ክብራቸውን ጭምር የሚነካ ተግባር የሚፈጽሙ አሉ፡፡ በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች በደላላዎች እየተደለሉ ከየቀያቸው እየተፈናቀሉ ዜጎቻችን ለጉዳት እየተዳረጉ ነው፡፡ ሁሉም ነገር አልጋ ባልጋ እንደሆነና ወርቅ ተነጥፎ እንደሚጠብቃቸው በመስበክ ወጎኖቻችንን እያስጨረሱ ነው፡፡ ከእነዚህ ደላሎች በስተጀርባ የመንግስት እጅ አለበት መንግሥት ዜጎችን ከመጠበቅና ካለበት ኃላፊነት አንጻር እሱም ተጠያቂ ነው፡፡ ዕድሜያቸው እንዳልሞላ እየታወቀ ከ13-15 ዓመትን ልጅን 23-26 ዓመት በማለት  በማጣራትና አይቶም መገመት ሲቻል ፓስፖርት ይሰጧቸዋል የሚያስደነግጥ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ወደ ሳዑዲና ኩዌት ለመሄድ የሚመጡት መጻፍ፣ ማንበብ የማይችሉና መታወቂያና ፓስፖርት መሆኑን መለየት የማይችሉ ናቸው፡፡ ፓስፖርት እስከሚያወጡና የሕክምና ምርመራ እስከሚደረግላቸው ድረስ ብዙ ችግሮችን ያሳልፋሉ ሁሉም ነገር ተሳክቶላቸው እስከሚሄዱ ድረስ የደላሎቹ የወሲብ መፈጸሚያ ይሆናሉ፡፡ የጤና ምርመራ ሲደረግላቸውም የHIV ተጠቂ ሆነው ይገኛሉ ውጤታቸው ሲነገራቸው እንደ ውርደት ስለሚቆጥሩት ተመልሰው ወደቀያቸው መግባትን ይተዉና ራሳቸውን በመሸጥ ለመተዳደር ይሞክራሉ፡፡ በሽታውንም ያስተላልፋሉ ላልተፈለገ እርግዝና ለ አደንዛዥ ዕፆች ተጋላጭ እየሆኑ ነው፡፡

Saturday, 22 December 2012

ቅ/ሲኖዶስ የሠየመው የፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ ዓለም አቀፍ ተቃውሞ ቀስቅሷል

ዕርቀ ሰላሙ ይቅደም›› የሚሉ ጳጳሳት የሲኖዶሱን ውሳኔ አንቀበለውም ብለዋል

የላሊበላው ውዝግብ ወደ አላስፈላጊ ግጭት እንዳያመራ ተሰግቷል

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የስድስተኛውን ፓትርያሪክ ምርጫ ዝግጅት የሚመራና እስከ ጥር መጨረሻ ዕጩዎችን የሚያቀርብ አስመራጭ ኮሚቴ መሠየሙ በቤተ ክርስቲያኒቱ ካህናትና ምእመናን ዘንድ ዓለም አቀፍ ተቃውሞ መቀስቀሱ ተገለጸ። ‹‹የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ያገባኛል›› በሚል መርሕ በዋናነት በማኅበራዊ ሚዲያዎችና ብሎጎች እየተገለጸ ያለው ይኸው ተቃውሞ፤ የቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት የሚረጋገጥበት የዕርቁ ጉባኤ ‹‹የአባቶች ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ ምእመናኑን ያገለለ ሊኾን አይገባም›› በሚል የካህናቱና ምእመናኑ ድምፅ እንዲደመጥ የሚወተውት ነው፡፡

የቅ/ሲኖዶሱ አባላት የኾኑ ሊቃነ ጳጳሳትን ጭምር ያካተተው የዚህ ተቃውሞ መነሻ÷ የአስመራጭ ኮሚቴው መቋቋም በሀገር ውስጥ በሚኖሩትና በውጭ አገር በስደት በሚገኙት አባቶች መካከል ለሚካሄደው የዕርቀ ሰላም ውይይት መሰናክል ይኾናል በሚል ነው፡፡የቅ/ሲኖዶሱ የዕርቀ ሰላም ልኡክ በመኾን ወደ አሜሪካ ከተጓዙትና በዳላስ ቴክሳስ ከኅዳር 26 - 30 ቀን 2005 ዓ.ም በሰላምና አንድነት ጉባኤ አመቻችነት በተካሄደው የዕርቀ ሰላም ውይይት ላይ የተሳተፉት የደቡብ ወሎ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ ከትናንት በስቲያ ምሽት ለአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ በሰጡት አስተያየት÷ ቅ/ሲኖዶሱ እንደላካቸውና በሰላሙ ጉዳይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋገሩ ‹‹ስንዝር ያህል መራመዳቸውን›› ገልጸዋል፡፡ የዕርቀ ሰላም ልኡካኑ ይህን እያደረጉ ባለበት ኹኔታ ስለ ፓትርያሪክ ምርጫ መወያየትና አስመራጭ ኮሚቴ ማቋቋም ‹‹ኾኗል ብለን አናምንበትም፤ ኾኖ ከተገኘ ግን አንቀበለውም፤ እንቃወመዋለን›› ብለዋል - በቅ/ሲኖዶሱ ውሳኔ ቅር የተሰኙት ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ፡፡

በሰሜን አሜሪካ የዋሽንግተን ዲሲ እና ካሊፎርኒያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በበኩላቸው÷ የጥቅምት ቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የወሰነው የፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ደንብ ተዘጋጅቶ የአሁኑ ስብሰባ እንዲጠራ እንጂ አስመራጭ ኮሚቴ ማቋቋም አዲስ ሐሳብ መኾኑን ለሬዲዮው በሰጡት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል፡፡ በጥር ወር አጋማሽ በካሊፎርኒያ ሎሳንጀለስ ቀጣይ የሰላም ጉባኤ ለማካሄድ ቀጠሮ መያዙን ያስታወሱት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል፤ የኮሚቴው መቋቋም የዕርቁን ሂደት እንዳያበላሸው ስጋት እንዳላቸው በመግለጽ ቅ/ሲኖዶሱ ከዕርቀ ሰላም ጉባኤው በፊት ሰፋ ያለ ሥራ ከማከናወን እንዲከለከል አሳስበዋል፡፡

Friday, 21 December 2012

የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” የምሥረታ መግለጫና ሃገራዊ ጥሪ

ታህሳስ 11 2005

የወያኔን ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ በትጥቅ ትግል ለማስወገድ “የግንቦት7 ሕዝባዊ ኃይል” የሚል ስያሜ የሰጠነውን፣ በሃገር ወዳድና ለህዝብ ተቆርቋሪ በሆኑ ወጣቶች፣ ምሁራንና ዜጎች የተሞላውን ድርጅት መመሥረታችንበዛሬው እለት ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በይፋ እናበስራልን።
 
ግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል፣ የሕዝብ ሉዓላዊ የሥልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባት፤ የዜጎች መብቶች፣ ሃገራዊ አንድነት፣ ደህንነትና ጥቅም የተከበሩባት ጠንካራና ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እውን ሆና የማየትን ራዕይ የሰነቀ ድርጅት ነው።
 
የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ወያኔን በኃይል የማስወገድ፤ ሰላማዊና ዲሞክራሲ የሥልጣን ሽግግር በሃገሪቱ እንዲኖር የማስቻል እና ከማንኛዉም የፓለቲካ ድርጅት ጋር ያልወገኑ ነፃ፣ ጠንካራና ብቃት ያላቸው ህገ-መንግሥታዊ የመከላከያ፣ የፓሊስና የደህንነት ተቋማት እንዲኖሩ አስተዋጽዖ የማድረግ ተልዕኮ ይዞ የተነሳ የኢትዮጵያ ሕዝብ አለኝታ ነው።
 
የግንቦት7 ሕዝባዊ ኃይል ራዕይና ተልዕኮ የተቀዳው በቀጥታ ሕዝብ በህይወቱ በደሙ በስቃይና በመከራ ውድ መስዋዕትነት ከከፈለለት የ1997 ብሄራዊ ምርጫ ነው።

Thursday, 20 December 2012

Ethiopia Four Journalists Win Free Speech Prize

 
(New York) - Four Ethiopian journalists have received the prestigious Hellman/Hammett award for 2012 in recognition of their efforts to promote free expression in Ethiopia, one of the world’s most restricted media environments.
 
Eskinder Nega Fenta, an independent journalist and blogger; Reeyot Alemu Gobebo of the disbanded weekly newspaper Feteh; Woubshet Taye Abebe of the now-closed weekly newspaper Awramba Times; and Mesfin Negash of Addis Neger Online were among a diverse group of 41 writers and journalists from 19 countries to receive the award in 2012. Eskinder, Reeyot, and Woubshet are imprisoned in Ethiopia; Mesfin fled in 2009. All four journalists were convicted in 2012 under Ethiopia’s draconian anti-terrorism law.
 
“The four jailed and exiled journalists exemplify the courage and dire situation of independent journalism in Ethiopia today,” said Leslie Lefkow, deputy Africa director at Human Rights Watch. “Their ordeals illustrate the price of speaking freely in a country where free speech is no longer tolerated.”
 
The Hellman/Hammett grants, administered by Human Rights Watch, are awarded annually to writers and journalists around the world who have been targets of political persecution and human rights abuses. The prize is named after two American writers who were harassed during the 1950s anti-communism investigations. Lillian Hellman suffered professionally and had trouble finding work while Dashiell Hammett spent time in prison. A distinguished selection committee awards the grants to honor and support journalists whose work, activities, and lives are suppressed by repressive government action.

Wednesday, 19 December 2012

Eskinder Nega Is Currently Appealing His Conviction And Sentencing

Update: Eskinder Nega is currently appealing his conviction and sentencing. On December 19, 2012, the Ethiopian Federal Supreme Court postponed hearing his appeal for the second time. The appeal hearing is scheduled to resume January 18, 2013. Please follow us on Twitter @freedomnoworg for breaking news.
 
Eskinder NegaEskinder Nega, 43, is a prominent Ethiopian journalist who was convicted and sentenced to 18 years in prison on terrorism charges. Prior to his detention, Mr. Nega was a widely published independent journalist and a well-known critic of Prime Minister Meles Zenawi’s government. Mr. Nega is married and the father of one son.
 
Mr. Nega began his work as an independent journalist in 1993 when he founded the Ethiopis newspaper. While Ethiopis and many of the other publications where Mr. Nega later worked were banned, he continued to write articles criticizing the Ethiopian regime’s abuses of power.
 
As a result of his critical reporting, the government has detained Mr. Nega on eight different occasions. In 2005, authorities arrested Mr. Nega and his then-pregnant wife, Serkalem Fasil, who is herself an independent publisher, during a nationwide crackdown following the country’s disputed elections. Mr. Nega was charged with treason and genocide and detained for 17 months before Ethiopia’s High Court released him after a series of negotiations. After releasing Mr. Nega in 2007, the government blocked him from publishing in the country. However, Mr. Nega continued to contribute to online media outlets abroad.

Monday, 17 December 2012

Hero Teacher Died Saving Students

 

Out of the chaos and horror emerged an incredible act of selflessness and bravery by one teacher who spent her final moments trying to protect her young students from harm.

Victoria Soto, 27, a first-grade teacher at Sandy Hook Elementary School in Newtown, Conn., ushered her students into a closet, and in so doing placed her body between them and the assailant.

"She was found huddled over her children, her students, doing instinctively what she knew was the right thing," her cousin Jim Wiltsie
tells ABC News.

"I'm just proud that Vicki had the instincts to protect her kids from harm," he continued. "It brings peace to know that Vicki was doing what she loved, protecting the children, and, in our eyes, she's a hero."

Soto was among the six adults, all women, killed in the Friday morning
massacre that also took the lives of 20 children – 12 girls and eight boys. The gunman, identified as 20-year-old Adam Lanza, took his own life. His mother was also found killed in a different location.

Sunday, 16 December 2012

ከኢትዮጲያ ብሔራዊ ሽግግር ምክር ቤት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ

ላለፉት ሀያ አንድ ዓመታት ግፈኛው የህወሃት/ኢሕአዴግ ሥርዓት በአገራችን ኢትዮጵያና ህዝቦችዋ ላይ ያደረሰውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣ በደልና መከራ ሁሉም የሚያውቀው ነው። በአሁኑ ጊዜ ሥርዓቱ “የመለስን ራዕይ እናሳካለን” በሚል  መፈክር/ፈሊጥ፣  የሰብዓዊ  መብት  ረገጣውን  እና  አምባገነናዊ  አገዛዙን  አጠናክሮ  እንደሚቀጥል  አድማጭ እስኪሰለቸው  ድረስ  እየለፈፈ ይገኛል።  የኢትዮጲያ  ብሔራዊ  ሽግግር  ምክር  ቤት  በቅርቡ  ይህ  ዘረኛ  ሥርዓት በወገኖቻችን ላይ ያደረሰውን በርካታ ግፍና በደል በአገር ውስጥና በውጭ አገር ለሚኖሩ ኢትዮጲያዊያንና ለዓለም ዓቀፉ ሕብረተሰብ በማሳወቅ፣ ድርጊቶቹን አጥብቆ እንደሚያወግዝ ይገልፃል። ባሳለፍናቸው ጥቂት ሳምንታት፤ የህወሃት/ኢሕአዴግ አምባገነናዊ አገዛዝ በወገኖቻችን ላይ ካደረሳቸው በርካታ የሰው ልጅ መብት ረገጣዎች፣ ግፍና በደሎቸ  መካከል የሚከተሉት በዋናናት የሚነሱና በጥብቅ የሚወገዙ ናቸው::

1.  የህወሃት/ኢሕአዴግ  ሥርዓት  በአገራችን  ሕዝብ  ላይ  የሚያደርገው  የሰብዓዊ  መብት  ጥሰት  በግልፅ እንዲወጣ ካደረጉት የቅርብ ጊዜ ክስተቶች መሃል ዓብይ የሚባለው፣ በሙስሊም ሀይማኖት ተከታዮች እምነትና የውስጥ አስተዳደር በሚያደርገው ጣልቃ ገብነት ነው። አክራሪነትን ለመዋጋት በሚል ሰበብ፤ የሀይማኖት  መሪዎች  እንዴት  እንደሚመረጡ  በመወስን፣  ይህንን  የተቃወሙ  አማኞችን  በመደብደብ፤ በማሰርና በመግደል፣ “አኬልዳማ” የሚል አሸባሪ የፈጠራ ፊልም በሚቆጣጠረው ቴሌቪዥን በማሳየት፣ መፍትሔ  ለመፈለግ  የተመረጡትን  ግለሰቦች  በማሰር፣  የፈለጋቸውን  የሀይማኖት  መሪዎች  በቀበሌ
በማስመረጥና  በእስር  የሚገኙትን  የመፍትሔ  አፈላላጊ  ኮሚቴ  አባላትን  ለመጠየቅ  የመጡትን  ሰዎች በማንገላታት ለማስፈራራት መሞከሩ። 

2.  የህወሃት/ኢሕአዴግ ሥርዓት፣ የህሊና እስረኞች በሆኑ ወገኖቻችን ላይ በፈጠራ የአሸባሪነት ክስ የተለያየ  የእስራት  ውሳኔ  ከማስተላለፉ  ባሻገር፤  በሕገ  ወጥነትና  በተለመደ  ዘዴው  ሌሎች ተቃዋሚዋችን ለማስፈራራት የእስክንድር ነጋንና የአንዱአለም አራጌን ንብረት መውረሱ፤ ሥርዓቱ ይቃወመኛል ብሎ የሚያምንበትን ግለሰብ ብቻ ሳይሆን ቤተሰቡንም ለመጉዳት፣ በጋራ የተመዘገበን ንብረት መውረሱ ነው።

Saturday, 15 December 2012

ተዘጋጅተን ጠብቀን ዕድል ሳትመጣ ብትቀር ይሻላል ፡፡

ድህነት ባደቀቃት የሚያሚ ቀዬ የተወለደው ሌስ ብራውን በወላጆቹ ስር ለማደግ አልታደለም፡፡ እሱ ብቻ ሳይሆን መንትያ ወንድሙም ከህፃንነቱ ጀምሮ ወላጆቹን አያውቃቸውም፡፡ ሁለቱም በጉዲፈቻ እናታቸው በማሚ ብራውን እንክብካቤ ነው ያደጉት፡፡ ሌስ ቀዥቃዣና ያለ ዕረፍት የሚለፈልፍ ቀባጣሪ ስለነበር ትምህርት የመቀበል ችግር ያለባቸው ልጆች በሚማሩበት ልዩ ት/ቤት ነበር ትምህርቱን የተከታተለው፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ያጠናቀቀውም በዚያው ት/ቤት ነበር፡፡ ከዚያም የሚያሚ ቢች ከተማ የፅዳት ሠራተኛ ሆኖ ተቀጠረ፡፡ የእሱ ህልም ግን ዲጄ መሆን ነበር፡፡ 
  
ማታ ማታ በባትሪ ድንጋይ የሚሰራውን የቤተሰቡን ሬዲዮ ይዞ ወደ አልጋው በመሄድ፣ ከአካባቢው ሬዲዮ ጣቢያ የሚሰራጨውን የዲጄዎች ወሬና ሙዚቃ ያደምጣል፡፡ የወለል ፕላስቲክ ምንጣፉ በተቀደደው ጠባብ ክፍሉ ውስጥ ምናባዊ የሬዲዮ ጣቢያ በመፍጠር፣ የፀጉር ብሩሽ እንደማይክራፎን እየተጠቀመ ዲጄነትን ይለማመዳል - አዳዲስ የወጡ የዘፈን አልበሞችን በህይወት ለሌሉ (ጐስት) አድማጮቹ እያስተዋወቀ፡፡ አሳዳጊ እናቱና ወንድሙ በስሷ ግድግዳ በኩል ስለሚሰሙት “መለፍለፉን ትተህ አርፈህ ተኛ!” እያሉም ይጮሁበት ነበር፡፡ ሌስ ግን ፈፅሞ አይሰማቸውም፡፡ በራሱ አለም ተመስጦ የራሱን ህልም ይኖራል፡፡

አንድ ቀን የከተማውን ሳር አጭዶ ሲያበቃ፣ በምሳ የእረፍት ሰዓቱ በድፍረት ተነስቶ ወደ አካባቢው የሬዲዮ ጣቢያ ይሄዳል፡፡ የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ ቢሮም ይገባና ዲጄ ለመሆን እንደሚፈልግ ይነግረዋል፡፡ ሥራ አስኪያጁ ቁሽሽ ያለ ቱታ የለበሰውንና ኬሻ ባርኔጣ ያጠለቀውን ወጣት ትክ ብሎ እየተመለከተው “ከዚህ በፊት በሬዲዮ ስርጭት ላይ ሰርተሃል?” ሲል ይጠይቀዋል፡፡
ሌስም “በፍፁም ጌታዬ! አልሰራሁም” በማለት ይመልሳል፡፡

Friday, 14 December 2012

ህይወቴ አበበ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

አዲስ አበባ  ታህሳስ 5 2005 ወጣት አርቲስት ህይወቴ አበበ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች። ባለትዳርና የአንዲት ሴት ልጅ እናት የነበረችው አርቲስት ህይወቴ ፥ ታማ በጳውሎስ ሆስፒታል በህክምና ስትረዳ ቆይታ ነው በተወለደች በ31 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው። አርቲስቷ የመቃብር ቁልፎችንና የሰርጉ ዋዜማን ጨምሮ በተለያዩ የመድረክ ቲያትሮች ላይ ሰርታለች። ባለታክሲው፣ ባለቀለም ህልሞችና ሰውዬው ፊልሞች ላይም የሰራች ሲሆን ፥ በርካታ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይም በመሪ ተዋናይነት ጭምር መስራቷን ነው የባልደረባችን ዘካሪያስ ብርሃኑ ዘገባ የሚያመለክተው። ካለፉት ሶስት ወራት በፊት ጀምሮ ኑሮዋን በኡጋንዳ ካምፓላ አድርጋ የነበረችው አርቲስት ህይወቴ የቀብር ስነ ስርዓት ነገ በአዳማ ከተማ ይፈጸማል።
 
 

Thursday, 13 December 2012

ኢትዮጵያ ቤተእስራኤላዉያን


የኢትዮጵያ ቤተእስራኤላዉያን ሴቶች የዛሬ ስምንት ዓመት ወደእስራኤል ከመሄራቸዉ አስቀድሞ የወሊድ መቆጣጠሪያ በግዳጅ ተሰጥቶናል ሲሉ ማመልከታቸዉን ሰሞኑን የእስራኤል የመገናኛ ብዙሃን ይፋ አድርገዋል።  The Time of Israel የተሰኘዉ ድረገፅ እንዳመለከተዉ ጉዳዩን በአንድ የእስራኤል የቴሌቪዥን ጣቢያ ያብራሩት ኢትዮ-ቤተእስራኤላዉያን ወደእስራኤል ለመሄድ ዴፖ ፕሮቬራ የተባለ የወሊድ መቆጣጠሪያ መድሃኒት በመርፌ ተሰጥቷቸዋል። ዘገባዉ ባለፉት አስርት ዓመታት 50 ሺህ ኢትዮጵያዉያን አይሁዶች ወደእስራኤል መግባታቸዉን ጠቅሶ፤ ለወትሮ ብዙ ልጅ መዉለድ የሚወደዉ ይህ ማኅበረሰብ በአማካኝ የወሊድ ቁጥሩ 50 በመቶ ቀንሶ መታየቱን አመልክቷል።
 
DW AMHARIC NEWS
 

Tuesday, 11 December 2012

ተቋርጦ የነበረውና በፍትህ ጋዜጣ አዘጋጅ ላይ የተመሰረተው ክስ ዳግም ተንቀሳቀሰ

አዲስ አበባ ታህሳስ 2  2005 ተቋርጦ የነበረውና በፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝና በጋዜጣው አሳታሚ ማስተዋል የህትመትና ማስታወቂያ ድርጅት ላይ በመገፋፋትና ግዙፍ ያልሆነ የማሰናዳት ተግባር ወንጀል የተመሰረተው ክስ ተንቀሳቀሰ
በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ጉዳያቸው የታየው   የፌደራሉ አቃቢ ህግ በ11 ሶስተኛ ወር 2005 ላይ ክሱ እንዲንቀሳቀስ ያቀረበውን አቤቱታ ተቀብሎ ነው ።
የተከሳሽ ጠበቆች ከችሎቱ 2ኛ ተከሳሽ ባለመቅረቡ ድርጅቱን ወክላችሁ ምላሽ መስጠት ትችላላችሁ? ወይ ተብለው ተጠይቀውም እንደማይመለከታቸው ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል ።
 
ጠበቆቹ ምንም እንኳ አቃቢ ህግ ክስ የመመስረት ፣ የማቋረጥና መልሶ የማንቀሳቀስ ሰልጣን እንዳለው በህግ ቢደነገግም አሁን እንዲንቀሳቀስ የተደረገበት አካሄድ ግን ግልፅ አይደለም ብለዋል ።

አቃቢ ህግ በበኩሉ በቂ ተያያዥ ማስረጃዎችን አደራጅቶ የፍርድ ሂደቱ እንዲቀጥል በማሰብ ክሱን ማቋረጡን ያስረዳ ሲሆን የተለያዩ የህግ አንቀፆችን በማጣቀስ ይርጋ እስካላገደው ድረስ በፈለገበት ሰዓት ክሱን ማንቀሳቀስ እንደሚችል ገልጿል ።

ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ከዚህ በፊት ክሱ ተቋርጦ በነበረበት ወቅት በምን ሁኔታ ላይ ይገኝ እንደነበር እንዲሁም የዋስትና ሁኔታውንም ግልፅ በሆነ ሁኔታ እንዲያስረዳ አቃቢ ህግን ጠይቋል ።

አቃቢ ህግ ክሱ ከተቋረጠ በኋላ ተከሳሹ ግለሰብ ከማረሚያ ቤት በዋስ መውጣታቸውን በማስታወስ ለአሁኑ ጉዳይ ተመጣጣኝ ዋስትና በድጋሚ በማቅረብ ውጭ ሆነው ቢከታተሉ ቅሬታ እንደሌለው አስረድቷል።
በዚሁ መሰረት ችሎቱ ግራ ቀኙን መርምሮ ተከሳሽ ተመስገን ደሳለኝ የ50 ሺህ ብር ዋስ ወይም 50 ሺህ ብር በማስያዝ የዋሰትና መብታቸው እንዲከበር በማዘዝ ፥ ሁለተኛ ተከሳሽ ማስተዋል የህትመትና ማስታወቂያ ድርጅት ለጥር 24 2005 ዓመተ ምህረት መጥሪያ ደርሶት እንዲቀርብ በድጋሚ ታዞል።

Ethiopian Women Claim Joint Distribution Committee And Israel Health Ministry Forced Them To Receive Sterilization Shots

Falash Mura women who immigrated to Israel from Ethiopia eight years ago reportedly told Israel Educational Television’s investigative show Vacuum yesterday that they were forced to receive injections of Depo-Provera, the long-lasting birth control drug, as a condition to allowing their immigration.

The women claimed that Israeli representatives from the Joint Distribution Committee (JDC) and the Health Ministry coerced them by telling them that raising large families in Israel is very difficult, that if you have many children it is hard to find work to support them, and that landlords frequently refuse to rent apartments to large families.

50,000 Ethiopian Jews have immigrated to Israel during the past 10 years. During that time, their birthrate reportedly fell by nearly 50 percent.

The women said they were told they had to take what they thought were vaccinations if they wanted to continue to receive medical care from the JDC and be allowed to immigrate.

Many continued to be given Depo-Provera shots once in Israel despite suffering side effects that included severe headaches and abdominal pains.

One woman with osteoporosis told Vacuum that she has been getting Depo-Provera shots for four years without ever being warned by doctors that Depo-Provera is dangerous for women suffering from it.

A hidden camera in an Israeli health clinic filmed an Ethiopian woman being told by a nurse that this shot is usually given only to Ethiopian women.

“[It’s given] primarily to Ethiopian women,” the nurse said, “because they forget, they don’t understand, and it’s hard to explain to them, so it’s best that they receive a shot once every three months…basically they don’t understand anything.”

The Israeli government denied all of the women’s allegations.

However, Vaccum showed a letter from the Health Ministry to Dr. Rick Hodes, the director of the JDC Medical Programs in Ethiopia. The letter praised the Hodes’ work, noting that while fewer than 5% of Ethiopians use any form of birth control, the rate among Hodes’ patients was 30%.

Rachel Mangoli, the director of the WIZO branch in Pardes Hanna, told Vaccum that in 2006 she started a program for Ethiopian children at her local absorption center. A “warning light” lit up when she realized that no babies were born to the center’s Ethiopian residents that year. She checked with the director of the local health clinic and says she was told that all the Ethiopian women at her absorption center had been given contraceptive shots because they could not be relied on to take birth control pills.

In response to Vaccum’s report, the JDC reportedly called the women’s claims “nonsense.”

“The medical team does not intervene directly or indirectly in economic aid and the Joint is not involved in the aliyah procedures,” the JDC statement noted, claiming that Depo-Provera shots are given to Ethiopian women because the JDC’s studies show that it “is the most popular form of birth control among women in Ethiopia.”
 
 Source ( HAARETZ)
 
 

Monday, 10 December 2012

የተከበሩ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ

 የተከበሩ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በውቅታዊ ጉዳዮች ላለፉት ዓመታት አገራዊ ፋይዳ ያላቸውንና ለህዝባችን ሁለንተናዊ ነጻነት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ የሚንቀሳቀስው የDemocratic Change in Ethiopia Support Organization Norway des. 9.2012 ባደረጉላቸው የክብር እራት ግብዣ  ከደጋፌዎቻቸው ጋር ተገናኝተው በውቅታዊ ጉዳዮች ውይይት አድርገውል::

 

Saturday, 8 December 2012

“ሰው ለሰው” ድራማ በውዝግብ እየተናጠ ነው

ላለፉት ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በየሳምንቱ ዘወትር ረቡእ ሲተላለፍ የቆየው “ሰው ለሰው” ተከታታይ ድራማ በፕሮዱዩሰሮች መካከል በተፈጠረ ግጭት ሊታገድ እንደሚችል ምንጮች ጠቆሙ፡፡ በድራማው ላይ የኢንስፔክተር ፍሬዘር እህት ናርዶስን ሆና የምትጫወተው ብስራት ገመቹ፤ ስሰራ የቆየሁት ገፀ - ባህሪ ለእኔ ሳይነገረኝ ለሌላ ተዋናይ መሰጠቱ አግባብ አይደለም ያለች ሲሆን በድራማው ላይ የባለቤትነት ድርሻ ቢኖራትም ሸሪኮቿ ያለእሷ እውቅና ያሻቸውን እያደረጉ መሆኑን ጠቁማ መብቷን ለማስከበር ክስ መመስረቷን ለአዲስ አድማስ ገልፃለች፡፡ ከድራማው ደራሲ የቀረበልኝን የፍቅር ጥያቄ ባለመቀበሌ ጫና ደርሶብኛል ብላለች - አርቲስት ብስራት፡፡
 
የዛሬ ሁለት አመት ድራማው ሊሰራ ሲታሰብ ዳንኤል ሃይሉ፣ መስፍን ጌታቸው፣ ሠለሞን አለሙ እና ነብዩ ተካልኝ በሙያቸው፣ እሷ ደግሞ የገንዘብ መዋጮ በማድረግ በሽርክና ለመስራት መፈራረማቸውን ትናገራለች፡፡
 
ከድራማው ከሚገኘው ገቢ 16.5 በመቶ ድርሻ ስላላትም ለሁለት አመት ስትሰራበት ለቆየችው ትወና ገንዘብ እንዳልተከፈላት እንዲሁም መኖሪያ ቤቷን የድራማው ዋና ገፀባህሪያት መስፍንና ማህሌት መኖርያ ቤት በማድረግ ለቀረፃ ሲያገለግል መቆየቱን ትናገራለች፡፡ በመኖሪያ ቤቷ ቀረፃ ሲከናወን ከስነምግባር ያፈነገጡ ድርጊቶች ስለነበሩ የአምስት ዓመት ልጇን ላለማሳቀቅ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በተደጋጋሚ በደብዳቤና በቃል ጠይቃ በመጨረሻም በኢቴቪ ጣልቃገብነት ችግሩ ለጊዜው መፈታቱን ብስራት ገልፃለች፡፡ ሆኖም በየጊዜው ችግሮች መፈጠራቸው አልቀረም ትላለች፡፡ በድራማው ላይ የምታያቸውን ድክመቶች ስትናገር እንደ ፕሮዱዩሰር ስላላይዋት ሊሰሟት እንዳልፈቀዱ ትናገራለች፡፡ የአስናቀ ቅጥር ነፍሰ ገዳይ ሆኖ ይጫወት የነበረው አርቲስት እንደተቀየረ፣ እሴተ ሆና የምትሠራውና የአስናቀ ሚስትም ለረጅም ጊዜ በድራማው እንዳትታይ መደረጉን ገልፃ፣ ተመልካቹም በሁኔታው ደስተኛ እንዳልሆነ ብትነግራቸውም ለማሻሻል ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ገልፃለች፡፡
በተለያዩ ጊዜያት ከደራሲው ማስጠንቀቂያ ደብዳቤዎች እንደተፃፈላት የምትገልፀው ብስራት፤ “ለቀረፃ ቤትሽን የማትፈቅጂ ከሆነ እርምጃ እንወስዳለን፣ቀረፃ መቀያየሩን ተረድተሽ የማትመጪ ከሆነና ከቀረፃ በፊት ይነገረኝ የሚለውን ግትር አቋምሽን ካልተውሽ አስፈላጊውን እርምጃ እንወስዳለን” የሚሉ ማስፈራርያዎች እንደደረሳት ትናገራለች፡፡ ሆኖም በወቅቱ “መልህቅ” የተሰኘውን ፊልሟን እየሠራች ስለነበር፣ላለመጨቃጨቅ ብላ ነገሩን ችላ እንዳለችው ገልፃለች - ብስራት፡፡ መስፍን ደራሲ በመሆኑ ለአስር ሳምንት አጠፋሻለሁ ብሎ ከድራማው ውስጥ እንዳጠፋት የምትገልፀው ተዋናይዋ፤ በየጊዜው የሚናገረውን ነገር ሁሉ እንደሚፈፅምባት ጠቁማለች፡፡ ቤቷን ለቀረፃ ፈቅዳ እንደነበር የምትናገረው ብስራት፤ ነገር ግን መስፍን በሚያሳየው የስነምግባር ጉድለት የተነሳ ቤት እንዲቀይሩ ብትጠይቅም፣ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ለሦስት ወር ብቻ እንድትታገስ፣መስፍንም ከድርጊቱ እንዲቆጠብ ተነግሮት እንደነበር ታስታውሳለች፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ እሷ በማታውቀው ሁኔታ የድራማዋ ናርዶስ በሌላ ተዋናይ (ሜሮን ተሾመ) መቀየሯን ቤቷ ቁጭ ብላ ድራማውን ስትከታተል ማየቷን ገልፃለች፡፡
በድራማው ላይ የሚተውኑ አርቲስቶችን በተለያየ ጊዜ ለመቀየር ፍላጎት እንደነበራቸው፣ ሆኖም ህዝቡ አይቀበለውም በሚል መቅረቱን የተናገረችው ብስራት፤ የ“ሰው ለሰው” ተዋናዮች ሽልማት ይሰጣቸው የሚል ሃሳብ ቀርቦም “ይጠግቡብናል” በሚል መቅረቱን ትናገራለች፡፡
የድራማው ሁለተኛ ክፍል ከተጀመረ አንስቶ ምንም አይነት ክፍያ እንዳልተከፈላት የገለፀችው ብስራት፤ በፊት በየሦስት ወሩ ክፍያ ይከፋፈሉ እንደነበር፣አሁን በየወሩ እንደሆነ ጠቁማ ሆኖም ከደራሲውና ከአዘጋጁ በስተቀር ማንም ክፍያ እንዳልትፈፀመለት ተናግራለች፡፡ በውላቸው መሠረት ሁሉም ነገር የሚወሰነው በሸሪኮቹ ፊርማ መሆኑን የምትናገረው ተዋናይዋ፤ ያለእሷ እውቅና የበፊቱ ድርጅት ተቀይሮ በሌላ ድርጅት መተካቱን፣ ሳያሳውቋት ድርጅቱ ቢሮ መልቀቁንና ሳይነገራት ሠራተኛ መቀጠሩም ከውላቸው ውጪ እንደሆነ ገልፃለች፡፡ ይሄም ሳያንስ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ከትወናው መውጣቷ እንዲሁም በሴትነቷ ለደረሰባት ክብረ ነክ ድርጊት ክስ ለመመስረት ወደ ፍርድ ቤት እንዳመራችና ባላት የባለቤትነት ድርሻም ድራማውን ለማሳገድ ጥያቄ እንደምታነሳ ተናግራለች፡፡
የ“ሰው ለሰው” ደራሲ መስፍን ጌታቸውን ስለጉዳዩ በስልክ ጠይቀነው መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ እንዳልሆነ የገለፀልን ሲሆን የድራማው አዘጋጅ ሠለሞን አለሙ በበኩሉ፤ ከተዋናይቱ ጋር ውል የነበረን በፊት እንጂ አሁን አቋርጠናል ብሏል፡፡ ውሉ በምን መልኩ እንደተቋረጠ ግን ለመግለፅ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡




Friday, 7 December 2012

ቴዎድሮስ የት ገባ?”

መለስ በአንደኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡ ለተማሪዎች ንግግር ካደረጉ በኋላ “አሁን ጥያቄ ካላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ” አሉ፡፡ ቴዎድሮስ የተባለው  ተማሪ ተነሳና “ሦስት ጥያቄዎች አሉኝ” በማለት ጀመረ፡፡ መለስም እንዲጠይቅ ፈቀዱለት “1ኛ. እንዴት ኢ ህ ዲ ግ 99.9% ምርጫውን ሊያሸንፍ ቻለ  2ኛ. ለምንድነው የፀረ-ሽብርተኝነት ህጉን የህዝቡን የጋዜጠኞችን እና ጋዜጦችን  ሃሳብን በነፃነት የመግለፅን መበት የምትጠቀሙበት? 3ኛ. ህወሃት ለምን በሰላማዊ መንገድ ስልጣኑን አይለቅም?” ይሄኔ ደወል ተደወለና ተማሪዎቹ ለእረፍት ከክፍሉ ወጡ፡፡ ከእረፍት መልስ መለስ “ቅድም ውይይታችን ስለተቋረጠ አዝናለሁ አሁን የፈለጋችሁት ልትጠይቁኝ ትችላላችሁ” አሉ፡፡ ቅድስት የተባለች ትንሽ ልጅ ተነሳችና “አምስት ጥያቄዎች አሉኝ” አለች፡፡ ቀጥይ አሏት ጠ/ሚ፡፡ “1ኛ. እንዴት ኢ ህ ዲ ግ 99.9% ምርጫውን ሊያሸንፍ ቻለ? 2ኛ. ለምንድነው የፀረ-ሽብርተኝነት ህጉን የጋዜጠኞችን እና ጋዜጦችን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅን መበት ለመገደብ የምትጠቀሙበት?  3ኛ. ህወሃት ለምን በሰላማዊ መንገድ ስልጣኑን አይለቅም?” 4ኛ. ለምን የእረፍት ሰዓት 20 ደቂቃ ቀደም ብሎ ተደወለ? 5ኛ.ቴዎድሮስ የት ገባ?”

Thursday, 6 December 2012

Ethiopia: Meles rules from beyond the grave, but for how long?

Rene Lefort  26 November 2012
The trade-off offered by authoritarianism to its client-constituents is security and high growth rates. After Meles challenges may force change, or build the case domestically for a new strong man.
Meles Zenawi, the former Prime Minister of Ethiopia, has been dead for around three months. But the “Melesmania” personality cult, though discreet in his lifetime, shows no sign of fading. From giant portraits in the streets to stickers on the windscreens of almost any vehicle, a smiling Meles is still everywhere.
The sudden death of Meles shook the whole of Ethiopia. The shock quickly gave way to fear of an unknown and threatening future.
The regime did everything to exploit this fear for its own benefit. It has issued continuous calls for the nation to unite around the memory of the dead leader and, above all, around the project he designed and imposed with an iron hand. The new Prime Minister, Hailemariam Selassie, endlessly repeats that he will pursue “Meles’s legacy without any change”. He has replaced not a single cabinet minister. It could be said that the regime is running on autopilot, with the Meles software driving the leadership computer. Plunged into disarray, the governing team is hanging on to this software like a lifebelt. Why?


Wednesday, 5 December 2012

Mystery shrouds Ethiopian maid’s death by hanging Egyptian worker falls to death

KUWAIT CITY, Dec 4: An Ethiopian housemaid committed suicide by hanging herself with a rope tied to the ceiling of her room at the sponsor’s residence, reports Al-Nahar daily. Security sources said sponsor of the deceased woman had notified the Operations Room about the incident and Criminal Evidences Men accompanied the rescue team to the scene, but reasons for the suicide remain mysterious, so the remains have since been referred to forensics for autopsy.

Meanwhile, A 33-year-old Egyptian expatriate died when he fell from a building under construction in Mahboula.

Reportedly, when securitymen received information about the accident, they rushed to the location with paramedics and discovered he had succumbed to serious injuries. They referred the corpse to Forensics Department. A case was registered.

In another incident, a Sri Lankan lodged a complaint at Taima Police Station against two unidentified persons he accused of stealing his wallet which contained KD 25 and his civil ID, reports Al-Shahid daily.

According to the complainant, he was walking in an undisclosed location when the suspects blocked his way, threatened to hurt him and took his wallet by force. He provided police with a detailed description of the thieves.

Monday, 3 December 2012

አወቃቀሩ የህወሐትን የሥልጣን የበላይነት የሚያስጠብቅ ነው

ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ ለምክር ቤቱ አቅርበው ያፀደቁትን አዲስ የካቢኔ አደረጃጀት እንዴት ያዩታል?  ከዚህ በፊት ሰምቼ ነበር፤ ሶስት ቦታ እንክፈለው የሚለውን፡፡ በዛን ጊዜ ግን ስምምነት ላይ አልተደረሰም፡፡ በአንድ ነገር ላይ ግን ስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር፡፡ አዲስ የሚመጣው ጠ/ሚኒስትር ማንም ይሁን ማን ከዚህ በፊት የነበረው ጠ/ሚ የነበረውን ሃይል ክምችት ይዞ መቀጠል እንደማይችል ተነጋግረው ጨርሰዋል፡፡ ማን ጠ/ሚ ይሆናል የሚለው አይደለም ወሳኙ፤ ህወሓት አካባቢ ማን እየተሾመ ነው የሚል ነው ወሳኙ፡፡ አሁንም ቢሆን ምንም ወዲያና ወዲህ የለኝም፡፡ በእኔ ግምት ሕወሓት አሁንም ቢሆን ስትራቴጂካዊ ቦታ ላይ ተቀምጧል - ጠ/ሚ ለመሆን፡፡ በሁለት መንገድ ነው እየሄዱ ያሉት፡፡ በውጭ ጉዳይም ትክክለኛ የስልጣን ቅብብል ነው የሚባለው ጉዳይ አሁን ጥያቄ ውስጥ የገባ መሰለኝ፡፡

ህወሓት ከያዘው ቁልፍ የሚኒስቴር መ/ቤቶች ስልጣን አኳያ ከሁለት ዓመት ተኩል በኋላ ሊሆን የሚችለውን ለመገመት ስንሞክር አመራሩ እንደ ዱላ ቅብብል ነው የሚባለው ጥያቄ ውስጥ የገባ ይመስለኛል፡፡ ወሳኝ ወሳኝ ቦታዎችን ወስደዋል፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሄዷል፤ እዛው ተመልሶ ቦታው ገብቷል፡፡ ወሳኝ የሚባለው የፋይናንስና ኢኮኖሚው ሄዷል፤ ተመልሶ ቦታው ገብቷል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት የጠ/ሚኒስትርነት ስልጣኑ (ቢሮ) የተጠናከረ ነውና ለሶስት መክፈል አለብን የሚል ሃሳብ ተነስቶ ነበር፡፡በጊዜው ያ ተቀባይነት አላገኘም፡፡ የጠ/ሚ ቦታ ከህወሓት እጅ ከወጣ የህወሓት የበላይነት ያከትማል የሚል ስጋት ነበራቸው፡፡ አሁን እንግዲህ አንድ ጠ/ሚኒስትርና ሦስት ምክትል ጠ/ሚኒስትሮች አሉን ማለት ነው፡፡ እያንዳንዳቸው ደግሞ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በክላስተር ተከፋፍለው አስተባባሪነት ተሾሞባቸዋል፡፡

Sunday, 2 December 2012

ኢትዮጵያ ሃገራችን  ለዓለማችን በርካታ ምሁሮችን ስታፈልቅ አሁንም እያፈለቀች ያለች ወደፊትም የምታፈልቅ ናት  ግን ለዜጎቹ ባለው ንቀት ዛሬ ደግሞ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽ አስተዳደርን የኃይል ሽያጭ፣ የደንበኞች አገልግሎትና አስተዳደርዊ ጉዳዮችን ለእስራኤሉ ኩባንያ ሰጠ፡፡ ፳ መሐንዲሶች በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ መጥተው ሥራውን ይጀምራሉ አለ መንግስት ተብየው