Sunday, 30 September 2012

የጠ/ሚንስትር የአቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በዩኤን ያደረጉትን ንግግር

28 September 2012 – In his maiden speech to the United Nations General Assembly, the Prime Minister of Ethiopia, Hailemarim Desalegn, today said that his country will keep contributing to regional integration efforts, but its success in this regard will depend on conditions being met in two areas: peace and stability and the challenge of extremism, and issues related to its capacity to ensure sustainable development.

ንግድ ባንክ ለሼክ አል አሙዲ ፈቅዶት የነበረው የ850 ሚሊዮን ብር ብድር ታገደ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ በቅርቡ ለሼክ መሐመድ አል አሙዲ የፈቀደው የ850 ሚሊዮን ብር ብድር እንዲታገድ መወሰኑን የንግድ ባንክ ምንጮች ገለጹ፡፡ ንግድ ባንክ ይህን ብድር ለመስጠት ሲስማማ የማበደር አቅሙን አልፈተሸም፣ ዘንድሮ ከባንኩ ብድር የሚፈልጉ እንደ ስኳር ፕሮጀክቶች የመሳሰሉ የመንግሥት የልማት ዕቅዶች የብድር ፍላጎት በአግባቡ አልተጤነም፣ እንዲሁም በአንድ ጊዜ ለአንድ ተበዳሪ ከፍተኛ ገንዘብ ለመልቀቅ መወሰኑ አግባብ አለመሆኑ ስለታመነበት፣ ብድሩ ለጊዜው እንዲቆም መንግሥት መወሰኑን እነዚህ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ተበዳሪው ሼክ አል አሙዲ ብድሩን ለመውሰድ ጥያቄ ያቀረቡት ለአፍሪካ ኅብረት ለሚያሠሩት ባለአምስት ኮከብ ሆቴል ሕንፃ ሊፍት መግዣና መግጠሚያ ነው፡፡ ብድሩም በቀጥታ ሊሰጥ የታቀደው ሊፍቱን ለሚያስመጣው ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ ለተባለው ሌላኛው የሼክ አል አሙዲ ኩባንያ ሲሆን፣ ንግድ ባንክ ለሊፍቱ ማስመጫ ራሱ ኤልሲ ከፍቶ ኮሚሽን ከማግኘት ይልቅ፣ በኤልሲ ኮሚሽን የሚያገኘውን ገቢ ትቶ በቀጥታ ለኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ ብድሩን ለማስተላለፍ መምረጡ፣ የብድር ክፍል ሠራተኞችን ያስገረመ ጉዳይ እንደሆነ የባንኩ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

እሱ ሲያወድሳቸው እነሱ ያንሸራትቱታል የታላቁ ሩጫ ሀብትና ንብረት ሊወረስ ነው

 
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ (Great Ethiopia Run) ላለፉት 12 ዓመታት በአዲስ አበባና በተለያዩ ክልልሎች የጎዳና ላይ ሩጫ ለተለያዩ ዓላማዎች በማካሄድ ያገኘው ሀብት ሕገወጥና ከተመሠረተበት ዓላማ ውጪ ነው ተብሎ ሊወረስ ነው፡፡
 
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴና ጓደኞቹ የተመሠረተ ሲሆን፣ ለትርፍ ያልተቋቋመ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት በመሆንም ከ12 ዓመታት በፊተ በፍትሕ ሚኒስቴር ሥር ተመዝግቦ ዕውቅና አግኝቷል፡፡

ከተመሠረተ ጀምሮ በየዓመቱ በአዲስ አበባ ላይ የ10 ሺሕ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በማከናውን የበለጠ ትኩረትን ያገኘው ታላቁ ሩጫ፣ በአዲሱ የበጎ አድራጎት አዋጅ መሠረትም ተመዝግቦ ዕውቅና አግኝቷል፡፡

Saturday, 29 September 2012

‹‹ተቃዋሚ ፓርቲዎች በመሰባሰብ ትልቅ ጉልበት መፍጠር አለባቸው››


አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ከፍተኛ አመራሮች መስከረም 17 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም በሽብርተኝነት ስም ታስሮ የሚገኘውንና እና የፓርቲው ከፍተኛ አመራር የሆነውን አቶ አንዱዓለም አራጌን ቃሊቲ በመገኘት ከብዙ ጭቅጭቅ በኋላ በአካል በመገኘትና ለመጠየት በቅቷል፡፡  አመራሩ በተጨማሪም የአንድነት ፓርቲ የብሔራዊ ም/ቤት አባል የሆነውንና ቂሊንጦ ታስሮ የሚኘውን አቶ ናትናኤል መኮንንም እንደጠየቀ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ገልጿል፡፡
የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት አያይዞ እንደገለጠው የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አካላት፣ አባላትና ደጋፊዎች ባለፈው አንድ አመት አንዱዓለምንና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞችን ለመጠየቅ ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርጉም ለመጠየቅ ከተመዘገቡ ጥቂት ቤተሰቦች በስተቀር መጠየቅ ሳይቻል ቀርቷል፡፡

አንድ ምሁር በገበሬው ፊት


አንድ በእርሻ ላይ የሚሠራ ዪኒቨርሲቲ መምህር በገበሬው ዙርያ ጥናት ለመሥራት ወደ ገጠር ወጡ፡፡ የአካባቢው የገበሬዎች ማኅበርም በአካባቢው የሚኖሩትን ገበሬዎች ለጥናቱ እንዲተባበሩ ለማድረግ ስብሰባ ጠራ፡፡ ምሁሩም ከገበሬዎቹ ፊት ለፊት ተቀመጡና ስለመጡበት ሥራና ከገበሬዎቹ ስለሚጠበቁ ነገሮችም ማብራራት ጀመሩ፡፡

Friday, 28 September 2012

“ለዚህ መንግሥት ታላቅ ክብር አለኝ”

ሃይሌ! ወደ ፓርላማ?

 
 
“ለኢትዮጵያ የጥምር መንግስት ያስፈልጋታል” በማለት በ1997 ምርጫ አጥብቆ ሲከራከር የነበረውና በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ ኢንቨስትመንት ውስጥ የገባው ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ በኢትዮጵያ ቀደም ሲል ከነበሩት መንግስታትና ትውልዶች ይልቅ አሁን ላለው ትውልድ ከበሬታ እንዳለው በመግለጽ አስተያየቱን ሰነዘረ። የክብር ሪኮርዶቹን በሙሉ ለቀነኒሳ ያስረከበው ሃይሌ በእጁ የሚገኘውን ብቸኛ ሃብቱን (የህዝብ ክብር) እያሟጠጠ መሆኑ እየተገለጸ ነው።

በደቡብ ክልል ” መለስ ዜናዊ እንኳን ሞተ” ብለው ተናግረዋል የተባሉ 80 ሰዎች ታሰሩ

 

487642_201792146621331_1189014075_n




መስከረም ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በደቡብ ኦሞ ዞን በደቡብ አሪ ወረዳ የሚገኙ አርሶአደሮች፣ ” መለስ ዜናዊ እንኳንም ሞተ፣ አናዝንም” በማለት ሲናገሩ ተሰምተዋል በሚል ነው የወረዳው አቃቢ ህግ ክስ ያቀረበባቸው።

የክስ መዝገቡ እንደሚያመለክተው አርሶ አደሮቹ በኢፌዲሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 4 /86 ሀ ላይ የተደነገገውን ተላልፈዋ ል። በመዝገብ ቁጥር 4103/30/2004 ፣ በ ቀን ጻጉሜ 1፣ 2004 በተጻፈው የክስ ቻርጅ ላይ የሰፈረው የወንጀሉ ክስ ዝርዝር ይዘት እንደሚያመለክተው ተከሳሾቹ በ18/ 12 /04 ዓም እለቱ አርብ ጧት 3 ሰአት ላይ በጎይዳመር ቀበሌ ውስጥ አቶ ገዛሀኝ ሀሞሾ ቤት ውስጥ ሀዘንተኛ ለማጽናናት በተሰበሰቡበት 4ቱም ተከሳሾች አንድ ላይ ሆነው “መለስ እንኳን ሞተ አናዝንም፣ መንግስት ሞቷል፣ መንግስት የለም” በማለት ድምጻቸውን ከፍ አድርገው መንግስት እንደሌለ በማሰብ ህዝብ ለማናወጥ በሚችል ሁኔታ ህዝብን በማሳሳት ወንጀል “ተከሰዋል ይላል።
 
ከሸንቃማ ቢሊ፣ ሸንጋማ ወሰት፣ ሌጠር፣ አመር፣ ጉመር ፣ አይዳና ከነአመር ከሚባሉ ቀበሌዎች ወደ ጋዘር ፖሊስ ጣቢያ ከታሰሩት 80 የሚሆኑት ገበሬዎች መካከል አብዛኞቹ ከሳምንታት እስር በሁዋላ ክሳቸው ተቋርጦ በከፍተኛ መስጠንቀቂያና በገደብ የተለቀቁ ሲሆን፣ አቶ ገረሱ ጭሊ የተባሉ የአንድነት ፓርቲ አባል ከስምንት ቤተሰቦቹ ጋር ታስረው የስድስት ወራት እስር ተፈርዶባቸዋል። የአቶ ገረሱ ሌሎች ቤተሰቦቻቸውና ከእስር ሲለቀቁ እርሳቸውና አንድ ወንድ ልጃቸው የስድስት ወር እስራት እንደተፈረደባቸው የደቡብ ኦሞ ዞን አንድነት ፓርቲ ተጠሪ የሆኑት አቶ ስለሺ ጌታቸው ለኢሳት ገልጠዋል ።
 
ውድ ተመልካቾቻችን እና አድማጮቻችን ይህንን አስገራሚ ክስ በተመለከተ የክስ ቻርጁን በኢሳት ድረገጽ ላይ የምናወጣው በመሆኑ ድረገጻችንን እንዲጎበኙት እንጋብዛለን።
 
ከዚሁ ዞን ዜና ሳንወጣ 13 የጂንካ ከተማ ተማሪዎች የተቃውሞ ድምጽ አሰማችሁ በሚል መታሰራቸውን ለማወቅ ተችሎአል።
በወጣት ናትናኤል ጳውሎስ የክስ መዝገብ የተከሰሱት ወጣቶች መታፈሪያ ታዲዮስ፣ ናትናኤል ጳውሎስ፣ ወንድወሰን ካሳ፣ ፍሬው በቀለ፣ ተመስገን ወንድም አገኘሁ፣ ሰለሞን ደጀኔ፣ ተስፋነህ ጋተው ፣ በረከት ደሴ፣ በረከት ታደሰ፣ ፍጹም መተው፣ ማስረሻ በለጠ፣ መኳንንት ወሌ እና መላኩ ካሳሁን ናቸው።
 
የክሱ ርእስ እንደሚያመለክተው ወጣቶቹ የተከሰሱት” የተከለከሉ ቦታዎችን በመድፈር እና የስራ ማስቆም ” በማድረግ ወንጀል ነው። ” ማን ” የተባለ የአስፓልት ተቋራጭ ድርጅት በከተማው ያለውን መንገድ በማፍረስ በአስቸኳይ ለመስራት ባለመቻሉ ወጣቶች ተቃውሞአቸውን በዞኑ መስተዳድር አጥር ላይ ተንጠላጥለው ተቃውሞአቸውን በማሰማታቸው ፣ የማይደፈረውን ቦታ ደፈራችሁ” የሚል ክስ እንደተመሰረተባቸው አቶ ስለሺ ተናግረዋል:

Thursday, 27 September 2012

ቴዲ አፍሮ በሰርጉ ቀን ለአካል ጉዳተኞች በብሄራዊ ቴአትር 100.000 ሺህ ብር ለገሰ::

      

teddy widding1

ቴዲ አፍሮ በሰርጉ ቀን ለአካል ጉዳተኞች በብሄራዊ ቴአትር 100.000 ሺህ ብር ለገሰ ሌሎችም ድንቃድንቅ ስጦታዎች ከአድናቂዎቹ እና ከወዳጆቹ ተሰጠው::ወጣቱ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮን የማይወድ እና የማያደንቅ ወጣት አዛውንት የለም ሆኖም ይህንን የሰርጉን ቀን አስመልክቶ ወዳጅ ዘመዶቹ ታላቅ የደስታ ቀናቸው ነበር። በዛሬው እለት የተፈጸመው ይህ ሰርጉ ደማቅ ከመሆኑም በላይ ታሪክ የተሰራበት እለት መሆኑን ታዳሚዎቹ ገልጸዋል። ብዙ አርቲስቶች የተሳተፉበት ይህ የሰርግ በአል የእርሱን ኩራትም ሆነው በሰርጉ እለት አሳይተውታል።  ቴዲ አፍሮ ለውዱ ባለቤቱ እሱ ከመድረክ ላይ ሆኖ ሙሽሪት ከሚዜዎቿ ጋር ከመድረክ ስር እየጨፈረች ጸባየ ሰናይ የሚለውን ዘፈኑን አቀንቅኖላታል። ከዚያም በላይ አለማየሁ እሸቴ አዲስ አበባ ቤቴ የሚለውን ዘፈን ሲዘፍን ተሰምቷል በዚህም ዘፈን ላይ መድረክ ላይ በመውጣት የጋራ ዳንሳቸውን አሳይተዋል።  

በመጨረሻም የሰርግ ዘፈን ሲዘፈን በታዳሚው ፊትለፊት እየተሳሳሙ የፍቅር ጉያቸውን በሞቀ ትንፋሻቸው አሙቀውታል ሌሎችም የሙዚቃ ባለሙያዎች ስራዎቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን ከሰአት ማጠር የተነሳ ሃይልዬ ታደሰ እና ታምራት ደስታ ብቻ ሳይዘፍኑ ፕሮግራሙ ተጠናቆአል። ይህ የቴዲ አለም ዛሬ ታላቅ ቀን ነበር ያሉት ታዳሚዎቹ ቴዲ ለዚህች አገር እና ለሙዚቃ ወዳጆቹ ብዙ መሰዋእትነትን ከፍሎአል አሁንም በዚህ ክብረ በአሉ ላይ ወዳጆቹ መንገዶችን ሞልተው ሞተር ሳይክል አሸከርካሪዎች በተለያዩ ሾዎች እያሳዩ ፍቅራቸውን ለግሰውታል አድናቆታቸውንም ቸረውታል።

ከዚያ በተለየ መልኩ ሻንበል ሰአሊ ለማ ጉያ አስደናቂ የሆነ ስጦታ ለቴዲ አፍሮ  ያበረከቱ ሲሆን ከስእሎቻቸው መሃል ለዚህ ለሰርጉ ቀን ተብሎ የተሳለ የአጼ ቴዎድሮስን ስእል ከአንበሳ ጋር ያለበትን ታላቅ ስጦታ ሲያበረክቱለት የህዝቡ ስሜት ታላቅ ነበር ብለዋል። በተለይም ለማለዳ ታይምስ የደረሱት ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ በዚህ ስጦታ ላይ ተዲ ሳቅ እና ለቅሶ ሲታይበት ሰአሊውን አቅፎ ለረጂም ሰአት ስሟቸዋል።

ኢዮብ መኮንን (ብረባም ባልረባም ትወጂኛለሽን) ሲያቀነቅን ጎሳዬ ተስፋዬ ከራሱ ዘፈኖች እና ከቴዲ ዘፈን ዘፍኖአል ሸዋንዳኝ የቀረብኝ የለም ሲል አለማየሁ እሸቴ አዲስ አበባ ቤቴ ብሏል ታደለ ገመቹ ኦሮምኛ ሲያዘም ግርማ ካሳ ፣ተሾመ ወልዴ አበጋዝ ክብረ ወርቅ ፣ዳግማዊ አሊ ፣ሳምሶን ጃፋር ፣ፋሲል ውሂብ፣አሸናፊ አሊ ፣አቡጊዳ ባንድ ፣ኤክስፕረስ ባንድ፣ ክብረት ዘኪዎስ ፣ታምራት ሃይሉ እና ሃይልዬ ታደሰ የመድረኩ አጋፋሪዎች ነበሩ ።ከላይ እንደጠቀስነው በፕሮግራሙ መጣበብ ምክንያት ሃይልዬ እና ታምራት ብቻ ሳይዘፍኑ የሰርጉ ሁኔታ ተጠናቆአል። ሁሉም አርቲስቶች በጣም ተደናቂ የሆኑትን እና በህዝብ ዘንድ ተወዳጅ ዘፈኖቻቸውን አቅርበዋል።

ማለዳ ታይምስ


ወጣቱ የኢትዮጵያ ድምጻዊ በ64ኛው ኢሚ አዋርድ ላይ ተሳታፊ ነበር


በ64ኛው የኢሚ አዋርድን ተከትሎ ብዙ ታላላቅ አለም አቀፍ የፊልም ባለሙያዎች ፣ሙዚቀኞች ፣ሲኒማቶግራፈርስ እና የፊልም ኢንዱስትሪ ካምፓኒዎች እን ባለቤቶቻቸው የተሳተፉበት ትልቁን የዚህን አመት አዋርድ ወጣቱ ኢትዮጵያዊ በወጣቶች ዘንድ ከፍተኛን አድናቆት እና እውቅና ያለውን በዘመናዊው ያዘፋፈን ስልቱ እና ከብዙ አርቲስቶች ጋር በፊቸሪንግ በመስራት የሚታቀው ሳሚ ካሳ (ሳምቮድ )የዚሁ እድል ተቋዳሽ እንደነበር ከስፍራው የደረሱን የተለያዩ መረጃዎች ያመለክታሉ:: ሳምቮድ በተለያዩ የሃሊውድ ቲቪ ሾው ፣ፊልሞች እና ማስታወቂያዎች ላይ የተሳተፈ ሲሆን በሃሊውድ የአክተሮች ዩኒየን አባል በመሆን (እስክሪን አክተርስ ጊልድ ) አባል በመሆን ስራዎቹን በመስራት እራሱን በማንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።
 
ሳምቮድ ከሰራቸው የቲቪ ሾው ድርጅቶች ታዋቂው ስክረብስ ፣ አንታራዥ ላይ በመሳተፍ ለመጀመሪያ ጊዜያት በመስራት ወደ ማህበሩ መቀላቀሉን ከዛሬ 3 አመት በፊት ለጠብታ መጽሄት ዝግጅት ክፍል ላደረግነው ቃለመጠይቅ እንደገለጸ ይታወቃል ። በወቅቱም በጣም ከባድ እና ፈታኝ ሆኖ ለራሳቸው ዜጎችም ቢሆን አስቸጋሪ የሆነው ይኸው መንገድ ለእኔ እነዚህ ስራዎቼ ብዙዎቹን መንገዶች ሊጠረጉልኝ ችለዋል ሲል ጠቁሞን ነበር።
 
በአሁን ሰአት የተለያዩ የሃሊውድ ፕሮዳክሽኖች ሶፕአፕራ ቦልድ አንድ ቢዩቲፉል የተሰኘ ቲቪ ሾው ላይ እና በተለያዩ የፊልም ስራዎች ላይ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ። በተወሰነ መልኩ ከመድረክ በስተጀርባ በመሆን እንቅስቃሴዎቹን አሳይቷል ።በተያያዥነትም ሙዚቃዎቹንም ለማሻሻል እና በአለም አቀፍ ደረጃ ለማሳየት ጥረት እያደረገም እንደሆነ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከሚሰራቸው የክሊፕ ስራዎች የጥራት ደረጃቸው ለማየትም ችለናል ።
 
ለዚህም ከዚህ በፊት ወደ ሰሜን አሜሪካ ይዞት ከመጣው አልበሙ “ተይ ተይ “ ዘፈኑ ተመርጦ በቢኢቲ ቻናል ከሆነው አንዱ በካሪቢያን ሙዚቃ ፕሮግራም ቴሌቪዥን ስርጭት (ዊክድ) በመጀመሪያ ደረጃ (ቶፕቴን ሊስት) ለስምንት ሳምንታት በማቅረብ ከፍተኛ ተደማጭነትን እንዲያገኝ አድርጎለታል። ለዚህም ይህ የሙዚቃ ስራው በቢኢቲ የሙዚቃ አዋርድ ፕሮግራም ላይ እንዲጋበዝ አድርጎታል ።
 
ባለፈው አመት በተሰራው በአሜሪካን አየር ፎርስ የፊልም ስራ ላይ የተሳተፈ ሲሆን የኢትዮጵያን ባህል እና እንቅሳቃሴም ትወናን እንደተወነ ገልጾልን ነበር ይህም የፊልም ቀረጻው ለአንድ ወር በሜክሲኮ ሲቲ እንደተከናወነም አክሎ ገልጦአል ።በተለይም የሃሊውድ ጋድ ፋዘር ከተሰኘው ድንቅ አክተር አልፓችኖ ጋር በመሆን አጭር የፊልም ስክሪን እይታም አግኝቶ የሰራ ሲሆን ይህ ፊልም በሚቀጥለው አመት የሚለቀቅ ነው የፊልሙም ርእስ ስታንድ አፕ ጋይስ የተሰኘ ሲሆን ሌላው ትሩ ብለድ( እውነትኛ ደም )በሚሰኘው የኤችቢኦ ቲቪ ሾው ስራዎችን ፕሮድዩስ በሚደረግበት ላይ የራሱን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል።
 
በተለይ ሳምቮድ ከተለያዩ የፊልም ኤጀንቶች ፣ማነጀሮች ፣ፐብሊሲቶች እና ካምፓኒዎች ጥልቅ ግኑኝነት ያለው ይህ ወጣት የወደፊት የኢትዮጵያ የፊልም ራእይ ሊሆን ይችላል ተብሎ ይታሰባል ።በዚህ ወራትም ከሚለቀቁት አዳዲስ ቴክኖሎጂ ካፈራቸው መካከል ከጌም ካምፓኒ ጋር በመስራት በራሱ ስም አዲስ የጌም ጨዋታ በሚቀጥለው ወር ለገበያ እንደሚቀርብ የደረሰን ዘገባ ይጠቁማል።በተለይም ለማለዳ ታይምስ በየወቅቱ የሚያደርሱትን የዚህን ወጣት ባለ ራእይ ስራዎችን አስመልክቶ በቅርበት አብረውን የሚሰሩን ባልደረቦቻችንን ሳናመሰግን አናልፍም ።
 

Wednesday, 26 September 2012

አባቴ የኢህአፓ አባል እና ተራማጅ አስተሳሰብ የነበራቸው ነበሩ።

Interview with Ethiopian PM Hailemariam Desalegn Part 1
 
 
 
Interview with Ethiopian PM Hailemariam Desalegn Part 2
 
 

ወያኔን የማስገደድ አሊያም የማስወገድ ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥላል!

በረከት ስምዖን በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብሎ ኃይለማርያም ደሣለኝና ደመቀ መኮንን የኢሕአዴግ ዋናና ምክትል ሊቀመናብርት ሆነው መመረጣቸውን ተናግሯል። ኃይለማርያም ደሣለኝ ደግሞ የተደረገው “ምደባ” መሆኑን በአጽንዖት ደጋግሞ ሲናገር ተደምጧል። “በምርጫ” እና “በምደባ” መካከል ስላለው ውስጠ ወይራ ለጊዜው እንተወው እና በሚከተሉት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እናትኩር።
 
ኃይለማርያም ደሣለኝና ደመቀ መኮንን የህወሓት አባላት አይደሉም፤ የታላቋ ትግራይ ሪፑብሊክ እቅድ ሲነደፍም በቦታው አልነበሩም። የእነዚህ ሁለት ሰዎች የኢሕአዴግ ዋናና ምክትል ሊቀመናብርት ሆኖ መመረጥ እና በቅርቡም ጠቅላይ ሚኒስትርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሊሰየሙ የሚችሉ መሆኑ በኢትዮጵያ ፓለቲካ ውስጥ የሚኖረው አንድምታ ምንድነው? የእነዚህ ሰዎች ወደ ፊት መምጣት በገዢዎች ቡድን ውስጥ የአስተሳሰብ ለውጥ መምጣቱን የሚያመለክት ነውን? እነዚህና እነዚህን የመሳሰሉ ጥያቄዎች ከየአቅጣጫው እየቀረቡ ነው።

Child Marriage In Ethiopia

                         International Center for Research on Women

AMHARA REGION, Ethiopia – Kasansh squats to make a fire, using one hand to stack wood and the other to steady her daughter, who reaches for her mother’s breast. Since she awoke at 7 a.m., Kasansh has made injera, Ethiopia’s traditional spongy flatbread. She gathered firewood. And she walked about a half-mile to fetch water from a spring, hauling the container across rocky terrain to her home.

There was a time when 17-year-old Kasansh’s mornings would include a walk to school. But that seems like a far away memory these days, ever since her parents halted her studies to make her wed a man she didn’t know. Now Kasansh feels she has no choice: “I have a home and a child,” she says through an interpreter, “so I can’t go back to school now.”
                     

 

Tuesday, 25 September 2012

ኢህአዴግና የተዳፈነው ፍም

(ደረጀ ሀብተወልድ-ሆላንድ)

 
የአቶ መለስን ሞት ተከትሎ በኢህአዴግ ውስጥ የሥልጣን ሽኩቻ እና ሊፈነዳ የደረሰ ቂም እንዳለ በስፋት ይወራል። እርግጥ ነው፤ ባለፉት ዓመታት በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች በተለይም በህወሀት እና በብአዴን መካከል ተዳፍነው የቆዩት የቂም እሳቶች በገሀድ የሚነድዱበት ጊዜ ላይ የደረስን ይመስላል።ስፍር ቁጥር ከሌላቸው የነ አቶ በረከት እና የህወሀቶች ቁርሾዎች መካከል ለዛሬ አንዱን እንመልከት።

በህወሀት ውስጥ በነ ስዬ እና በነ መለስ መካከል የተፈጠረው ክፍፍል በአቶ መለስ ቡድን አሸናፊነት በተጠናቀቀ ማግስት በክፍፍሉ ወቅት ለአቶ መለስ ታማኝነታቸውን ያስመሰከሩት ብአዴናውያን ፤ከአለቃቸው- ቱባ ቱባውን ስልጣን “ጀባ” መባላቸው ይታወሳል። ኢትኦጵ መፅሔት በወቅቱ የቡሔን በዓል አስታክኮ በፊት ገፁ ላይ ያወጣው ካርቱን እስካሁን ትዝ ይለኛል።

ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝም የአራት ኪሎውን ቤተ መንግስት ከሩቅ እያዩት ነው?

(ኢ.ኤም.ኤፍ) በየትኛውም አገር አንድ መንግስት ሲቀየር አዲስ የሚመረጠው አካል፤ ወደ አስተዳደር ቢሮው መግባት ይኖርበታል። በራሺያ የክሬምሊን ቤተ መንግስት ወይም በአሜሪካ ኋይት ሃውስ የመንግስት መቀመጫ ስፍራዎች ናቸው። ለኢትዮጵያ ደግሞ የመንግስት ስራ ማከናወኛ የአራት ኪሎው ምኒልክ ቤተ መንግስት መሆኑ ይታወቃል። ታዲያ በሌሎች አገራት የመንግስት ለውጥ ሲደረግ፤ ፕሬዘዳንቱም ሆነ ጠቅላይ ሚንስትሩ በጨዋ ደንብ ጨርቅ እና ማቃቸውን ይዘው ይወጣሉ። በኢትዮጵያ ግን ይህ አልሆነም። የቀድሞው እመቤት ቤተ መንግስቱን የሙጥኝ እንዳሉት ነው።

አቶ ኃይለማርያም ምኒልክን ቤተ መንግስት ከሩቅ ከማየት ውጪ ከነቤተሰባቸው ወደ ቅጥር ግቢው አልተዛወሩም። ሌላው ቀርቶ በትላንትናው እለት የሁለቱን ሱዳኖች ልዑካን ተቀብለው ያነጋገሩት፤ ፕሬዘዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በሚገኙበት ኢዮቤልዩ ቤተ መንግስት ውስጥ ነበር። ከዚህ በፊት በመለስ ዜናዊ ይደረጉ የነበሩ የእንግዳ አቀባበል ስርአቶች ይፈጸሙ የነበረው በአራት ኪሎው ምኒልክ ቤተ መንግስት ሲሆን፤ አሁን ግን ሴትዮዋ አልወጣም በማለቷ ምክንያት… አቶ ኃይለማርያም ፕሬዘዳንቱ የሚገኙበትን ቤተመንግስት በጋራ ለመጠቀም ተገደዋል።

Monday, 24 September 2012

አይኤምኤፍ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከ6.5 በመቶ በላይ አያድግም አለ

 
• መንግሥት በአዲሱ ዓመት ከብሔራዊ ባንክ የመበደር ዕቅዱን እንዲሰርዝ ጠየቀ
• የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ መደረግ አለበት ብሏል
• ንግድ ባንክ ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች የሰጠው ብድር 60 ቢሊዮን ብር ደርሷል
 
በጋዜጣው ሪፖርተር ባለፈው ሰኔ ወር የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለመገምገም ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ የነበረው የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ልዑክ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከ6.5 በመቶ በላይ አያድግም ሲል በሪፖርቱ አስታወቀ፡፡ የገንዘብ ድርጅቱን በበላይነት ለሚመራው ቦርድ ሪፖርቱን አቅርቦ አፀድቋል፡፡ ስልሳ ሦስት ገጾች ያሉት ሪፖርት በዋናነት ያተኮረው በዓመታዊ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ በገንዘብ ፖሊሲ፣ በበጀት ፖሊሲ፣ በውጭ ምንዛሪ፣ በፋይናንስ ሴክተር፣ በግሉ ዘርፍ እንቅስቃሴና በአገሪቱ የውጭ ብድር እንቅስቃሴዎች ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡

Brev Til Norge og Etiopia


Woyane Put A Hold On The New House


Abebe Belew of Addis Dimts Radio wasn’t honest to his listeners. While he has been preaching for Diaspora not to go to Ethiopia, he sent his wife to Addis to buy them huge Villa at Gift Real Estate.
That was the mother of all hypocrisy!
Since Abebe was convicted in Ethiopian court, Ministry of Justice put a hold on the new house. To clarify issues related to this matter, Ben of EthiopiaFirst interviewed State Minister of Justice. Ben also visited Abebe’s new house at Gift Real Estate. To watch the investigation,


 

Saturday, 22 September 2012

”ወንጭፌን አምጡልኝ!”

 የኢሳቱ ደረጄ ሀብተወልድ 

 “ዳዊት ጎልያድን እንዲገጥም ሲላክ የንጉሥ ሳዖልን ካባና ሰይፍ ነበር ያለበሱት።  ሆኖም ልኩ አልሆነም። ካባውም ሰፋው፣ሰይፉም መሬት ለመሬት ተጎተተ። በዚያ መልኩ ወደ ጎልያድ ቢሄድ ኖሮ የሚጠብቀው ዕድል ሽንፈት ነበር። ዳዊት ግን -የንጉሥ ካባና ሰይፍ ስለሆነ ብቻ ፤ልኩ ያልሆነን ትጥቅ ታጥቆ ወደ ፍልሚያው መግባት አልፈለገም። ለዚህም ነው የሳዖልን ካባና ሰይፍ አውልቆ በመጣል ”ወንጭፌን አምጡልኝ!”ያለው። እናም ወንጭፉን አነገተ፤ ጠጠር በኮሮጆው ጨመረ። በግ ጠባቂው ዳዊት ራሱን ሆነ። የሚያውቀውንና የተለማመደውን ወንጭፍና ኮሮጆ አንግቶ ጎልያድን ገጠመ።አሸነፈም።”
 
ደሬ እንዳላቸው አቶ ሃይሌ ከመለስ ካባ እና ሰይፍ ይልቅ የራሳቸውን ወንጭፍ ይዘው ከፊታቸው የሚጠብቋቸውን በርካታ ጎልያዶች ቢሞክሯቸው ይሻላል።
 
አቶ ኃይለማሪያም ከፊት ለፊታቸው ብዙ ጎልያዶች አሉ። እርሳቸው እና ፓርቲያቸው እንደሚለው ድህነት አንዱ ጎልያድ ነው። የፍትህ ማጣት እንዴት ያለ ጎልያድ እንደሆነ ለማወቅ አንድ ጊዜ ቃሊቲ ወይም ቂሊጦ ኧረ ምን ሩቅ አስኬዳቸው እዝችው ማዕከላዊ ሄድ ብለው ማየት ይበቃቸዋል። ዛሬ በሀገራችን የማንበብ እና የመፃፍ ነፃነት በህገ መንግስቱ ላይ ብቻ ነው ያለው። ይሄም ትልቅ ጎልያድ ነው። መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም የሚለው የህገ መንግስት ቃል መከበሩን ለማረጋገጥም ወንጭፋቸውን ማሰናዳት አለባቸው። ሙስናም ቢሆን ዋዛ የሚባል ጎልያድ አይደለም።
 
ዘርዝረን የማንጨርሳቸው በርካታ ጎልያዶች አሉብን እነዚህን ለመፋለም የአቅማቸውን ወንጭፍ ካላዘጋጁ በስተቀር የአቶ መለስን ካባ ለብሰው በአቶ መለስ ሰይፍ ተፋልመው አይችሉትም። ራስዎን መሆን አለብዎ::

Etiopia stenger svenske nettsider etter avsløring


Nettsidene til den svenske rikskringkastingen STV er blitt stengt i Etiopia etter at TV-kanalen avslørte at Etiopia hadde fabrikkert bevis i saken mot to svenske journalister.
 
 
 
I dagene etter at Martin Schibbye og Johan Persson ble løslatt etter mer enn 13 måneder i etiopisk fangenskap, publiserte SVT flere programmer om hvordan myndighetene i Etiopia bevisst hadde fabrikkert bevis, deriblant flere videofilmer, mot svenskene.
 
Lørdag opplyste kilder i Etiopia at det ikke lenger er mulig å gå inn på SVTs nettsider.
 
- Etiopia er ytterst ubekvemme med den informasjonen vi har publisert i våre innslag. De vet at vi kommer til å publiserer mer, sier SVTs korrespondent i Nairobi, Johan Ripås.
 
SVT har blant annet avslørt at en video som ble brukt under rettssaken, som angivelig viser etiopiske soldater i harde kamper med opprørere under pågripelsen av Schibbye og Persson, er spilt inn i etterkant med statister i stedet for soldater.
 
De to journalistene skal ha blitt holdt fanget i jungelen i flere dager mens videoen ble spilt inn.
Schibbye og Persson ble pågrepet av etiopiske soldater i juli i fjor og tiltalt for terrorvirksomhet og ulovlig innreise til landet. 11. september i år ble de sluppet fri. (©NTB)

Friday, 21 September 2012

Hun Blir Historiens Yngste Statsråd


Stortingsrepresentant Hadia Tajik (Ap) er det eneste nye fjeset i regjeringen. Hun er den første muslimske statsråden i Norge.

 
GLAD OG MOTIVERT: Hadia Tajik ser frem til å ta fatt på Kulturløftet 3.
 







Tajik blir ny kulturminister etter Anniken Huitfeldt. Den 29 år gamle stortingsrepresentanten er oppvokst på Strand i Rogaland, og er utdannet journalist og jurist.
 
Hun arbeidet som journalist i VG og Aftenposten før hun gikk inn i rikspolitikken som tidenes yngste politiske rådgiver i 2006. Nå blir hun både historiens yngste og første muslimske
statsråd. 

የጋራ አመራር መርሆዉን አስቀጥላለሁ። ጠ /ሚኒስትር ኃ /ማሪያም ደሳለኝ

የኢሕአዴግ ፓርላማ   /ሚኒስትር አፀደቀ ::
 
 
 

Thursday, 20 September 2012

ኢትዮጵያ መሰረቱ በተደላደለ ህግ የምትመራ ሃገር ብትሆን ኖሮ፣ እንኳን ሃይለማርያም፣ ሃይሌ ገብረስላሴም ሊመራት በቻለ ነበር።

 የሃይለማርያም አንገት
 
ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ፕሬዚዳንት ሆነው በተመረጡ ጊዜ በመከላከያና በሲቪል የህወሃት አባላት ዘንድ አቧራው ጨሶ እንደነበር አስታውሳለሁ። አባላቱ የፖለቲካውን ጨዋታ አልተረዱትም ነበር። በወቅቱ የነጋሶ ሹመት የይስሙላ መሆኑን ማስረዳት፣ ለህወሃት መሪዎች ፈተና ሆኖባቸው ነበር። ህወሃት አሁንም ተመሳሳይ ችግር ገጥሞታል። ምናልባትም በቀጣዩ የሃይል አሰላለፍ የህወሃት የበላይነት እንደተጠበቀ መሆኑን ማሳመን ካልቻሉ መፈንቅለ መንግስት ሊያጋጥም ይችላል።
 
የህወሃት ሲቪልና የመከላከያ አባላት በአብዛኛው፣ “የኢትዮጵያ ስልጣን ሙሉ በሙሉ ለኛ ይገባል” ብለው ያምናሉ። ለሌሎች የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች የሚሰጡ ሹመቶችን በቀና አይመለከቱም። “አቅም የላቸውም፣ ሰነፎች ናቸው፣ ሌቦች ናቸው” ይሏቸዋል።

የህጻናት ዝግ ቤቶች

(ቀጭኑ ዘ-ቄራ ) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

 
ይህ ሰው ያለውን ኃላፊነት እዚህ ከሚያደርገው ተግባሩ ጋር በማገናዘብ ሳስበው አመመኝ።
እንዲህ ያሉ ብዙ “ትልልቅ ሰዎች” ይመሩናል። በችጋር ይጠብሱናል።
ሲሞቱ በደቦ ያስለቀሱናል። በጀት ከልክለው በረሃብ ያቃጥሉናል።
ሲሞቱ ደግሞ በጀት መድበው ደረት ያስመቱናል።
 “ያገራችሁን ህዳሴ ከእኛ ጠብቁ” እያሉ ያለ ሃፍረት ይሰብኩናል።
አጽማቸውን እናመልክ ዘንድ ይመኛሉ።

Wednesday, 19 September 2012

Ethiopia Can`t Afford The New Nile Dam

nile river, ethiopia, grand millennium dam, egypt

 
Ethiopia insists it will build the Grand Millennium Dam, but there is no money behind the words

Defiant Ethiopia is proceeding with its plan to build the Grand Millennium Dam on the Nile river, but what kind of dam can they build without cash flow? Following the formation of the Entebbe Treaty, which gives the six upstream nations more control over the Nile’s flow, and amidst the political upheaval that has the Pharaoh nation scrambling to keep the country afloat, Egypt has made some conciliatory moves towards Ethiopia. But just how seriously need they take Ethiopia’s posturing?

Tuesday, 18 September 2012

‹‹ኢሕአዴግ ሲወድቅ ደውሉልን››


በተደጋጋሚ የገለጽነውና የምንገልጸው ቁም ነገር አለ፡፡ ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ ድክመት አለበት ማለት ተቃዋሚዎች ግን ጠንካሮች ናቸው፤ ትክክል ናቸው ማለት አይደለም፡፡ ተቃዋሚዎች ደካሞች ናቸው ማለት ደግሞ ገዢው ፓርቲ ግን ጠንካራና ጎበዝ ነው ማለት አይደለም፡፡ ሁሉም በየራሳቸው ማንነትና ተግባር መገምገምና መገለጽ አለባቸው፡፡ ያንዱ መደመር ለሌላው መቀነስ ነው ማለት አይደለም፡፡ ያንዱ መቀነስ ደግሞ ለሌላው መደመር መሆን አይደለም፡፡ ጉዳዩ የሥራህ ያውጣህ ጉዳይ ነው፡፡

ይህንን ካልን ዘንድ በአሁኑ ጊዜ በኅብረተሰባችን ውስጥ ስለሚንሸራሸረው፣ ስለሚነገረውና ስለሚወራው ነገር በግልጽ እናውራበት፤ በግልጽ እንነጋገርበት፡፡

የፍትሕ ሥርዓቱ በመዳከሙ ሴቶችን ይበልጥ እያጠቃ ነው

የኢትዮጵያዊያት ሴቶች ሁኔታ በምን ደረጃ ላይ እንዳለ ለማየት እስቲ አንዳንድ ጥያቄዎችን እናንሳ፡፡

1. ምን አዎንታዊ ነገር አለ?


ችግሮችን ከማየታችን በፊት ሴቶችን የሚመለከት በአገራችን እየታየ ያለውን አዎንታዊ ጎን እንይ፡፡ የሴቶች መብት በሕገ መንግሥት ዋስትናው የተረጋገጠ ነው፡፡ ይህ መሠረታዊና አዎንታዊ ጉዳይ ነው፡፡ በሴቶች መብት ላይ የሚያተኩሩና የሚከታተሉ በመንግሥት በሚኒስቴር ደረጃ፤ በሲቪል ማኅበረሰብ ደግሞ የሴቶች መብት አቀንቃኞችና የሴቶች የሕግ ባለሙያዎች ማኅበራት አሉ፡፡ ይህ አዎታንዊ ነው፡፡

ሴቶችን ራስ ለማስቻልና ወደ ሥራ የሚያስገቧቸው የሴቶች የጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበራትንና ድርጅቶችን ማቋቋም፣ የሴቶችን እንቅስቃሴ የሚደግፉ የገንዘብ አቅራቢ አካላትን መመሥረት በአዎንታዊ ጎኑ ይታያሉ፡፡ ሴቶች ወደ ቢዝነስ ዓለም በመግባት ራስን ለመቻል የሚያደርጉት ጥረትም አዎንታዊ ነው፡፡

Monday, 17 September 2012

የተተኪው ጠቅላይ ሚኒስትር ፈተናዎች

 
ሽግግር - ፓርቲዎች ወደሚፎካከሩበት እውነተኛ ምርጫ

እመርታ - የዜጎችን ኑሮ ወደ ሚያሻሽል የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ

የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብና ማስነገር ብቻውን በቂ አይደለም። በተጨባጭ የዜጎችን ኑሮ የሚያሻሽል የነፃ ገበያ ስርዓት ማስፋፋት ያስፈልጋል - ዘመኑ የቢዝነስ ዘመን ነውና። አመት እየቆጠሩ የፖለቲካ ምርጫ ማካሄድ ብቻውን በቂ አይደለም። የአገራችን የፖለቲካ ምርጫዎች፣ ዜጎች በነፃነት የሚሳተፉበትና ፓርቲዎች የሚፎካከሩበት መሆን አለበት - ዘመኑ የ”ዲሞክራሲ” ዘመን ነውና። አንድ ሁለት የቲቪ ቻናሎችን መጨመርና  የኤፍኤም ጣቢያዎችን ማበራከት ብቻውን በቂ አይደለም። የግል ነፃ ሚዲያ እንዲስፋፋ መፍቀድ ይገባል - ዘመኑ የመረጃ ዘመን ነውና።ዜጎች ህግ አክባሪ እንዲሆኑ መጠበቅ ብቻውን በቂ አይደለም። ከሁሉም በፊት መንግስት ራሱ የህግ ተገዢ በመሆን የህግ የበላይነትን ማስፋፋት ይኖርበታል - ዘመኑ የመንግስት ገናናነትን ሳይሆን የመንግስት ቅነሳን የሚጠይቅ ነውና። ከጓዳ እስከ አደባባይ የዜጎችን ህይወት ለመቆጣጠር ከታች እስከ ላይ “1ለ5” በቡድንና በተዋረድ ከማደራጀት ይልቅ፤ እያንዳንዱ ሰው እንደዝንባሌው እንዲሰራና እንደፈቀደው እንዲተባበር የሚያነቃቃ የነፃነት መንፈስን ማስፈን ያስፈልጋል - ዘመኑ የፈጠራ ዘመን ነውና። በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ፣ በፕሬስ ነፃነት፣ በህግ የበላይነትና በነፃነት መንፈስ ዙሪያ የተጠቀሱት አምስት ፈታኝ ስራዎች በሙሉ፤ ስልጣኔን የመገንባት የረዥም ጊዜ ፈተናዎች ናቸው ማለት ይቻላል።



ዘወትር በአራት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እጸልያለሁ

በጣም የሚወዱትን መዝሙር ይንገሩኝ?

አቶ ኃ/ማርያም፡- ‹‹እኔም እንደ ዳዊት ጨርቄን ልጣልልህ›› የሚለውን

ጉባዔ ገብተው ሲያመልኩ ግን እንደ ባለሥልጣን የፕሮቶኮል ነገር አለ፡፡ የጥበቃ ጉዳይ አለ፡፡ ሌላም ሌላም፡፡ ይሄን ሁሉ ረስተው በነጻነት ለማምለክ አይቸገሩም?

አቶ ኃ/ማርያም፡ ምንም አልቸገርም፡፡ ጉባዔ ውስጥ ካለሁ እኔ ስለ ራሴ ጨርሶ አላስብም፡፡ እነ ንጉሥ ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ጨርቃቸውን ጥለው ያመልኩ ነበር፡፡ እኔስ የማመልከው እግዚአብሔር ፊት እንደሆንኩ እንጂ የማስበው ሌላ ነገር አላስብም ማልቀስ ካለብኝ አለቅሳለሁ፣ መንበርከክ ካለብኝ እንበረከካለሁ፡፡ ጌታ ሁን ያለኝን ሁሉ ለመሆን ዝግጁ ሆኜ ነው የማመልከው፡፡

Sunday, 16 September 2012

የቃላት ድሪቶ

ከጠቅላይ ሚኒስትር ሐይለማሪያም ደሳለኝም  ንግግር የተወሰደ

ለተደረገዉ ምደባ እናመሰግናለን
ምደባዉ ለመሰዋትነት
ምደባዉ የጓዳችንን ለጋሲ ለማስፈፀም
ምደባዉ ህዝቡ ከኢሕአዴግ የሚጠብቀዉን ሁሉ  በሙሉ
መስዕዋትነት ለመፈፀም
ምደባዉ   በሙሉ የምክር ቤቱ አባላት ድጋፍ እና በእናንተ ሙሉ ምክር ከኋላችን እና ከፊታችን በምታደርጉት  አሰተዋፆ  ይቀጥላል::

Kongehuset i sorg


 
Prinsesse Ragnhild, fru Lorentzen har gått bort, 82 år gammel.
Hun døde i sitt hjem i Rio de Janeiro i Brasil, klokken 09.45 lokal tid.
Hans Majestet Kongen har med stor sorg mottatt budskapet, opplyser.
Ragnhild var kong Olavs og kronprinsesse Märthas eldste barn. Hun ble født 9. juni 1930 på slottet i Oslo.

” ክቡራት እና ክቡራን የኢትዮጵያ ህዝቦች “ በሚለው ቃል ይጠቃለል

 ጠቅላይ  ሃይለማርያም ደሳልኝ  ንግግር የተወሰደ
 
የተከበራችሁ ሀገራችን ህዝቦች 
 የተከበራችሁ በዘጠኙ ክልሎች የምትኖሩ ብሔር ብሔረሰቦች
የተከበራችሁ የአዲስ አበባ እና የድሬደዋ ነዋሪዎች
ክቡራን የዲያስፖራ አባላት
የተከበራችሁ የሀገራችን አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች
የተከበራችሁ የኢትዮጵያ  ምሁራኖች የዩኒቨርስቲ መምህራን ተማሪና ተማራማሪዎች
 የተከበራችሁ የጎዳና ተዳዳሪዎች እህቶቻችንና ወንድሞቻችን
የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች
 የተከበራችሁ አካል ጉዳተኞች
 የተከበራችሁ አባት አርበኞች እና ጡረተኞች
 የተከበራችሁ  መካከለኛ ከፍተኛ ባለ ሀብቶች የንግዱ ማህበረሰብ ሰራተኞች
የተከበራችሁ የአነስተኛ እና ጥቃቅን ተቋማት ባለቤቶችና ሰራተኞች
የተከበራችሁ 1ኛ እና  2ኛ ደረጃ መምህራንና ተማሪዎች
የተከበራችሁ የመንግስት  ሰራተኞችና ሀላፊዎች
 የተከበራችሁ በሰላማዊ በህጋዊ መንገድ ለምትሰሩ የፓለቲካ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት
” ክቡራት እና ክቡራን የኢትዮጵያ ህዝቦች “ የሚለው ሃሳብ ሁሉንም ጠቅልሎ መግለጽ ሲችል

How to Make Solar Energy Better Use Spinach

 

Spinach is one of my favorite superfoods.  It’s a delicious, leafy dark green vegetable that’s chock full of vitamins, minerals, proteins and nutrients the human body needs to be well. Popeye told kids spinach would make them grow big and strong. Now, new research from Vanderbilt University suggests spinach can do the same thing for solar energy production.


Saturday, 15 September 2012

ሰበር ዜና

አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የኢሕአዴግ ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን ም/ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ የኢህአዴግ ምክር ቤት ባደረገው መደበኛ ሰብሰባ የግንባሩን ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር መረጠ ። ምክር ቤቱ አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝን የግንባሩ ሊቀመንበር አድርጎ የመረጠ ሲሆን ፥ አቶ ደመቀ መኮንን ደግሞ በምክትል ሊቀመንበርነት መርጧል ።

 

“አባታችን ስላሉኮ ነው ጐዳና የምንተዳደረው”

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት የህዝቡን ሃዘን ከባድ ያደረገው በተለይ እንዲያ በክብር ዘብ ታጅበው ሲፈልጉ ሮጥ ሮጥ ብለው፤ በሌላ ቀን ደግሞ በመሪነት ግርማ ረጋ ብለው፣ ሲመላለሱበት በነበረው አውሮፕላን፤ እንዲያ በከፍተኛ ባለስልጣናት አሸኛኘትና አቀባበል ሲደረግላቸው የነበሩ መሪ፤ በዚያው አየር መንገድ ከል በለበሱ ሃዘንተኞች የታጀበ አስከሬናቸው መምጣቱ ይመስለኛል፡፡
 እናም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት ብዙ ተባለ፡፡ አንዳንዱ “የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት ምክንያቱ ከጋናው ፕሬዚዳንት ጋር የጨረር ጥቃት ተፈጽሞባቸው ነው፡፡ ሌላ አፍሪካዊ ፕሬዚዳንትም የጥቃቱ ሰለባ ሆነው በሞትና በህይወት መሃል ይገኛሉ” ሲል፤ ሌላው ደግሞ “የለም የዋልድባን ገዳም በመዳፈራቸው መነኮሳቱ መቋሚያቸውን ዘቅዝቀው፤ መስቀላቸውን ከዛፍ ላይ ሰቅለው መሪር ሃዘን ስላዘኑ፤ አምላክ ጸሎታቸውን ሰምቶ የሃይማኖት መሪውንና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ቀሰፋቸው” እያለ ወሬውን ሲያጋግል ሰንብቷል፡፡ ያም ሆኖ ሁለቱም ወገኖች ለወሬዎቻቸው “ይህ ነው” የሚሉት ማስረጃ የላቸውም፤ ወይም አላቀረቡም፡፡


Friday, 14 September 2012

Mange barn på asylmottak har det ikke bra


Barn må få en individuell vurdering av sitt beskyttelsesbehov, mener Røde Kors.
Røde Kors har liten tro på at fine ord i regjeringens stortingsmelding uten videre vil bidra til en forandring i behandlingen av asylsaker der barn er involvert. Nå ber de stortingspolitikerne ta ansvar og sørge for at Norge følger barnekonvensjonen.
 
Møter barna på asylmottak

- Vi møter disse barna på mottak hver eneste dag, og vi ser at mange av dem ikke har det bra, sier generalsekretær Åsne Havnelid i Røde Kors til Nettavisen.
Hun vil ikke gå inn og kommentere enkeltsaker eller kritisere regjeringen, men sier dette om stortingsmeldingen:
 
- Det er bra at det settes fokus på barnas beste. Så er det viktig at det klargjøres hva som ligger i «barns beste».

EUMP Ana Comes criticizes EU over conditions in Ethiopia


Thursday, 13 September 2012

የአውጫጭኝ ወጥ

 
By Daniel Kibert

ሴትዮዋ እርሟን አንድ ቀን ወጥ ሠራች አሉ፡፡ ገና ወጡ ከድስቱ ሳይወጣ ጎረቤቱን ሁሉ በነቂስ ጠራችና ወጥ ቅመሱ አለች አሉ፡፡ ሰውም ምን አዲስ ነገር ልታሳየን ይሆን? እያለ ግልብጥ ብሎ ወደ ቤቷ መጣ፡፡ ሴትዮዋም እንጀራውን እያጠፈች ከድስቱ ወጥ እየጨለፈች አቀረበች፡፡

በላተኛውም ግምሹ እያዳነቀ፣ ግማሹም እየሳቀ፣ ግማሹም እየተሳቀቀ፣ ሌላውም በቸርነቷ እያመሰገነ በላ፡፡ እርሷም ከምግቡ በኋላ ቡና አፍልታ የተጋባዦችን አስተያየት ትቀበል ጀመር፡፡ አንዳንዱ በወጡ አሠራር መደነቁን፤ ሌላው በተጠቀመችው ቅመም መማረኩን፤ ሌላውም የጨመረችው ቅቤ ልዩ መሆኑን፤ የቀረውም ሰው በሠራችበት ድስት የተደነቀ መሆኑን ነገራት፡፡ እርሷም ‹‹እርሟን ጠምቃ ሰጠች ጠልቃ›› ሳይሏት ይህ ሁሉ ጎረቤት ተገኝቶ ይህንን  የርሷን  ግብዣ  ማድነቁ  አስደስቷታል፡፡  ከዚህ  በፊት  በሠፈሩ  ያልተደረገ፤  አዲስ  ነገር  መሆኑንም  ጎረቤቶቿ አድንቀውላታል፡፡

የምናዉቀዉ ህወሀት ዘመን ላይመለስ አክትሟል

 በፍስሀ አሸቱ  ( ዶ/ር ) 

ጊዜ የማያሳየን  ነገር የለም፤  ትግስት ካለና አምላክ ከፈቀደ ደሞ የማይሆን  ነገር የለም። እስኪ  ራሳችንን ወደሗላ መለስ  ብለን ሥድስት ወራት  በምናባችን እንመለስና ጊዜን  የሗልዮሽ  እንቃኘዉ።  በዚያን ግዜ እኔ  ለዉጥ  በምን  ያክል  ቅበጽነትና ሁኔታ  ሊመጣ እንደሚችል  አናዉቅም፤ ሰርገኛ  መጣ ብለን ከምንሯሯጥ  ተሰባስበን ለማናቸዉም  አጋጣሚ  እንዘጋጅ  ብዬ ስናገር  በርካቶች  ሰዉዬዉ  አበደ  እንዴ  ሲሉ ነበር።  አንዳንዶቹ አስጠንቁሏል  ሲሉ፤  ሌሎቹ ደሞ የሚያዉቀዉ  ነገር አለ እያሉ  በትንታኔ  ዉድ ጊዜን  አሳለፍን። ወደፊት ሄደን  ዛሬ ላይ ቆም ብለን ያለፉትን  ስድስት ወራት  ስንመለከት ለማመን  የሚያስቸግሩ ስንት  ታአምሮች አየን።  እኛ ስንዳክር  አምላክ ግን ስራዉን ሰራና  ታምራቱን አሳየን። እስኪ  ስንቶቻችን ነን  መለስ ለዚህ  ይበቃል ብለን ቅንጣት እንኳን ጥርጣሬ የነበረን?  የአቡነ  ጳዉሎስና አጠቃላይ የሃገሪቱ ጉዳይስ?  ሁሉም ነገር ፈጽሞ  የማይታመንና እምነት ካለ የማይሆን  ነገር እንደሌለ  በተጨባጭ ያየንበት የበረከት  ወቅትን አሳልፈናል።  የዚህ  ጽሁፌ  አላማ  ስለህልፈተ መለስ  ወይንም አሁን  እየታየ  ስላለዉ  ቴያትር ግለሰባዊ  ትንተና ለመስጠት አይደለም። በአንጻሩ  ግን ከጊዜዉ ተጨባጭ ሁኔታ  በመነሳት  ስለመጪዉ  ሁኔታ  እንደ  አንድ  ዜጋ ሚሰማኝን ለወገኖቼ  ለማካፈል  ነዉ።