Monday, 1 April 2013

የፌስ ቡክ አስተያየት ያስከተለዉ እስራት


በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሙስና ይፈፀማል ብሎ የማኅበራዊ መገናኛ መድረክ በመሆነዉ ፌስ ቡክ የፃፈ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ መታሰሩ ተሰምቷል።

በአዲሱ የአዲስ አበባ ቴክኒዎሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆነዉ ወጣት በዚሁ ምክንያት ታስሮ ወደአርባምንጭ መወሰዱን ወኪላችን የላከልን ዘገባ ያመለክታል። የአርባ ምንጭ ፖሊስ የሰዎች ስም የሚያጎድፍ በማዉጣቱ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከአዲስ አበባ ወስደን ለፍርድ ለማቅረብ ጉዳዩን እያጣራሁ ነዉ ማለቱንም ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር በዘገባዉ ጠቅሷል።

No comments:

Post a Comment