Saturday, 6 April 2013

ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የሃኪምና የህክምና እጥርት ባለበት ያሉትንም ታዋቂ ስፔሺያሊስት ሃኪሞች አምባ ገነኑ ጠራርጎ አስራቸው

ነቀምቴ ላይ አራት ከፍተኛ ሐኪሞች ታሥረዋል፤ አንድ ኮሪያዊ ተሰናብተዋል

1ኛ. ዶ/ር አዳም ለማ፤ የቀዶ ሕክምና ሐኪም፣ 
2ኛ. ዶ/ር ኢሣያስ ብርሃኑና 
3ኛ. ዶ/ር በላይ ቤተማርያም የማኅፀንና የፅንስ ስፔሻሊስቶች፣ 
4ኛ. ዶ/ር ታመነ አበራ፤ ቀድሞ የሆስፒታሉ የሕክምና ዳይሬክተርና አሁን ለስፔሻላይዜሽን የጥቁር አንበሳ ሬዚደንት ሐኪም፣ እንዲሁም 
ዶ/ር ሪም ጆንግ ሆ፤ ኮርያዊ የአጥንት ሐኪም፡፡ ሁሉም በነቀምቴ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ አገልግለዋል፡፡ ዛሬ ኮርያዊው ሐኪም ከሥራ ሲሠናበቱ አራቱ ኢትዮጵያዊያን ግን በቁጥጥር ሥር ውለው ነቀምቴ በሚገኘው ማረሚያ ቤት ውስጥ ይገኛሉ፡፡
ፈታሾች በዶ/ር አዳም ለማ ወላጆች ቤት - አዲስ አበባ 
ፈታሾች በዶ/ር አዳም ለማ ወላጆች ቤት - አዲስ አበባ

የእነዚህ ለረዥም ዓመታት አገልግሎት ሰጥተዋል የሚባሉ ሐኪሞች ከሥራቸውና ከደመወዛቸው መታገድ፣ አልፎም መታሠር መነጋገሪያ እየሆነ ነው፡፡

“
ጥፋታቸው” የተባለው ምን ይሆን? በአካባቢያቸው ያሉ ሰዎችስ “ጥፋተኛ ናቸው” ብለው ያምናሉ?

የተያያዘው ዘገባ የፖሊስን፣ የሆስፒታሉን አስተዳደር፣ የእሥረኞቹን ሐኪሞች ቤተሰቦችና ጠበቃ የሚሉትን ይዞ ዝርዝር መረጃ ይሰጥዎታል፡፡

http://amharic.voanews.com/flashaudio.html


No comments:

Post a Comment