Saturday, 20 April 2013

አምባሳደር መብራት በየነ ከኖርዌይ ተባረረች

ኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ከተለያዮ የኖርዌይ ከተሞች ስታቫንገር ላይ ተሰባሰበው  የአባይን ቦንድ ለመሽጥ የመጡትን   ወያኔዎች አባረሩ የአባይን ቦንድ ለመሽጥ የመጣችው አምባሳደር መብራት በየነ ንግግር ስትጀምር ``የኢትዮጵያዉያን ድምጽ ይሰማ```` አባይን ከመገደብ ሰብዕዊ መብት ጥሰት ይገደብ`` በማለት የተለያዩ መፈክሮች በማሰማት ነዉ  ስብሰባዉ የተጀመረዉ በቅድሚያ ስልጣን ከያዛችሁ ጀምሮ በዘር በሃይማኖት በፖለቲካ ለጨፈጨፉችኋቸዉ ወገኖቻችን የህሊና ጸሎት እናድርግ  የኢትዮጵያ ህዝብ ለዘመናት ያልተመለሱለትን ጥያቄዎች መልሱልን ስለታሰሩትና ስለተፈናቀሉት ወገኖቻችን  ጥያቄ አለን  አባይ ሃገራችን ነው አብረን እናለማለን  በማለት ነበር አቋማቸውን ያስታወቁት   ውጥረቱም ተበብሶ አምባሳደሯ  በጸጥታ ሃይሎች እርዳታ አዳ ራሹ   ውርደቷን ተከናንባ ከነጀሌዎቿ  በፖሊስ ሃይል  አፍረው ተመልሰዋል ኢትዮጵያውያኑም የወያኔን ባንዲራ በኢትዮጵያ ባንዲራ ቀየረው በሃገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ተወያይተው   ለተፈናቀሉት ወገኖቻችንም የገቢ ማሰባሰቢያ አድርገው ሰብሰባቸውን አጠናቀዋል








http://www.aftenbladet.no/nyheter/lokalt/stavanger/Politiet-stoppet-mote-i-Tasta-bydelshus-3162548.html#.UXLv17WBrpe










No comments:

Post a Comment