Friday, 23 November 2012

“ባልና ሚስት ምንድን ናቸው?”

“ባልና ሚስት ምንድን ናቸው?” በሚል ንዑስ ርዕስ ስር፣ የባልና ሚስትን አካላዊና ስነ ልቦናዊ ጥምረት፣ የመንፈስ አንድነት “ባልና ሚስት አብረውና በደስታ ለመኖር የፈለጉ እንደሆነ እያንዳንዳቸው ሶስት ሶስት መሆን አለባቸው”  “መጀመሪያ ባልየው ሌት ተቀን እንደ ሎሌ ታጥቆ የሚሠራ÷ ለቤቱ የሚያስብ በአዳራሽ ሲገኝ ደግሞ ጌታ መስሎ÷ ተኮፍሶ÷ እንግዳውን የሚቀበል÷ ልጆቹን የሚያዝዝ÷ የቤቱን ሥነ-ሥርዓት የሚቃኝ÷ በመኝታ ቤት ግን ተጫዋች መሆን አለበት” 

 “ምሽት የማድቤት ገረድ÷ የሳሉን እመቤት÷ የመኝታ ቤት እብድ መሆን አለባት እንጂ በጠቅላላው የተኮፋፈሱ እንደሆነ ሦስት ባህሪ ከሌላቸው ባልና ምሸት አይሆኑም” ወሲብንና ስነልቦናዊ ጥምረትን በባለትዳሮች ላይ ያላቸውን ሰፊ ቦታ፣ በቅኔያዊ ጨዋታ በብልሃት ለዘብ አድርገው ያስረዱበት መንገድ በርግጥም የደራሲውን ልዩ ብቃት ያመለከተ ይመስለኛል፡፡ 

የአለማየሁ ሞገስ



No comments:

Post a Comment