Monday, 1 October 2012

የፋና ኤፍ ኤም 98.1 ተዘጋ

ወጣቱ ለምን ይሰደዳል በሃገሩ ሰርቶ መኖር ሲችል እያሉ በረሃ ወድቀው በቀሩት ወገኖቻችን ሲሳለቁ የነበሩት የ “ኢትዮፒካ ሊንክ” የመዝናኛና መረጃ ዝግጅት አዘጋጆች ጣቢያዉ ተዘጋባቸው::

ላለፉት አምስት አመታት በአክሱም ፒክቸርስ እየተዘጋጀ በፋና ኤፍ ኤም 98.1 ሲደመጥ የቆየው “ኢትዮፒካ ሊንክ” የመዝናኛና መረጃ ዝግጅት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን፣ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርና በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ በቀረበበት ቅሬታዎች ምክንያት ተዘጋ። ዝግጅቱ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ዜና መዋዕል ለአድማጮች ካቀረበ በኋላ ከጣቢያው ታግዶ የቆየ ሲሆን ለአክሱም ፒክቸርስ የአየር ሰዓት በውል ስምምነት የሰጠው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ኤዲቶሪያል ፖሊሲን እና የሥራ ውል ስምምነታቸውን ዝግጅት ክፍሉ በተደጋጋሚ ጥሶአል በማለት ከነዚህ ቅሬታዎች በፊት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ነበር፡፡
 
“ኢትዮፒካ ሊንክ” ለፋና ገቢ በማስገባት ሁለተኛው ትልቅ ተባባሪ አዘጋጅ እንደነበርም ማወቅ ተችሏል፡፡ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የኤፍ ኤፍ 98.1 ዋና አዘጋጅ አቶ ዘካሪያስ ብርሃኑ ስለ ጉዳዩ ጠይቀናቸው የኢትዮፒካሊንክ ውል ከመስከረም 12 ጀምሮ በመቋረጡ ካሁን በኋላ በጣቢያቸው እንደማይደመጥ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ የኢትዮፒካሊንክ አዘጋጆችን በስልክ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ስልክ ባለማንሳታቸው አልተሳካም፡፡

No comments:

Post a Comment