ወ/ሮ አዜብ ቤተመንግሥቱን በህጉ መሰረት እና በሰላማዊ መንገድ ባለማስረከባቸው ቤተመንግስቱን
ለተተኪው ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲያስረክቡ ማስጠንቀቂያ ደርሶአቸው ነበር
ከተሾሙ ከ20 ቀናት በላይ ያስቆጠሩት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እስካሁን ቤተመንግስት አለመግባታቸው ተገቢ አይደለም እየተባለ ነው፡፡ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ቤተመንግስቱን ለመልቀቅ አለመፍቀዳቸውን የጠቀሱ ምንጮች ጉዳዩ ትክክል አይደለም ሲሉ ተችተዋል፡፡ አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ብስራተ ገብርኤል አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው እየተመላለሱ አገሪቱን ማስተዳደራቸው ለአገሪቷም ክብር ጭምር ተገቢ እንዳልሆነ አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል፡፡ ወ/ሮ አዜብ ቤተመንግሥቱን ማስረከባቸው ላይቀር ውዝግብ ማስነሳቱ ተገቢ አይደለም የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች፤ አገሪቱን የሚያስተዳድሩት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር በውጭ ሆነው እሳቸው ከውስጥ መቀመጣቸው ሌላ ትርጉም ያሰጠዋል ብለዋል፡፡
i would be happy to read it but I can understand amharic, so if you want to increase scope of your typing, you better to write in English (and keep amharic as well, don not dump it !)...
ReplyDelete