Monday, 8 October 2012

ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በኦስሎ

ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ኦክቶበር 18. 2012. ከቀኑ 13፡00 እስከ 15፡00 ሰዓት በኦስሎ ከተማ ይካሄዳል፡፡
 
የሰላማዊ ሰልፉ አላማ፦
 
1- የኖርዌይ መንግስት ትኩረት የነፈገውን የኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ጉዳይ በተመለከተ አስፈላጊውን ጫና በኖርዌይ መንግስት ላይ ለመፍጠር
 
2- አሁን አገራችን ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ለኖርዌይ መንግስት እንዲሁም ለአለም አቀፍ ህብረተሰብ ለማሳየትና ደምፃችንን ለማሰማት ይህ ታላቅና ታሪካዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተዘጋጅቷል፡፡
 
ስለሆነም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በዚህ ሰልፍ ላይ በመገኘት የዜግነት ድርሻውን እንዲወጣ እያሳሰብን በተለይ የኢትዮጵያ መንግስት ከኖርዌይ መንግስት ጋር የስደተኞችን ጉዳይ በተመለከተ የተፈራረሙትን ስምምነት በመቃወም ክስ የመሰረታችሁ እንዲሁም በክሱ ላይ ስማችሁንና መለያ ቁጥራችሁን (DUF number)ያስመዘገባችሁ በዚህ ታሪካዊና ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ መገኘት ውዴታ ብቻ ሳይሆን ግዴታም መሆኑን አውቃችሁ እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡

በሰልፉ ላይ የማይገኝ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ቤተሰብ በፈቃዱ ክሱን እንዳቋረጠ በመቁጠር ከክሱ ሊስት ላይ የሚሰረዝ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡
 
ማሳሰቢያ

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የምትገኙ እውነተኛ ታጋዮች በሰልፉ መጨረሻ ላይ መታወቂያ በመያዝ ስማችሁንና መለያ ቁጥራችሁን ማሰመዝገብ እንዳትረሱ እያሳሰብን ይህ መልክት የደረሳችሁ ሁሉ ላልደረሰው በማዳረስ የዚህ ትግል ተጋሪ ይሁኑ፡፡

በመጨረሻም ሰልፉን በተመለከተ የሚወጡ መመሪያዎችንም ሆነ ውይይቶችን በፓልቶክ ክፍላችን በመታደም ይከተተሉ፡፡

ሰልፉ አስተባባሪ




No comments:

Post a Comment