Saturday, 13 October 2012

ህጻናት በአፍ መፍቻ ቋንቋዎች መናገራቸው እያስቀጣቸው ነው

 
አዲስ አበባ ውስጥ አሁንም በአንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች የሃገር ውስጥ ቋንቋዎችን መናገር እንደወንጀል ተቆጥሮ  እያስቀጣ ነው።
 
በአገራችን በአፍ መፍቻ ቋንቋ አለማስተማር በተደጋጋሚ እንደችግር እየተነሳ ውይይት ቢደረግበትም የሚመለከታቸው አካላትም ችግሩን ሙሉ በሙሉ  አልቀረፉትም።
 
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በበኩሉ፥ ህግ በማያከብሩና የአገሪቱ የትምህርት ፖሊሲ ከሚፈቅደው ውጪ በሚያስተምሩ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ እርምጃ እየወሰድኩ ነው ቢልም በአንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ፥ አሁንም በአማርኛ መናገር  በአገር ውስጥ መጽሀፍት ማስተማር እንደ ወንጀል  እየተቆጠረ መሆኑ ታውቆአል።
 
ይህ ሁኔታ በልጆች ላይ ትልቅ ተጽእኖ እንደሚያሳድር ነው በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ  ምሁራን የገለጹት። በህጻናቱ ላይ የማንነት ቀውስ እንደሚፈጥር እየታወቀ መንግስት የማያዳግም እርምጃ አለመውሰዱ በጣም አሳዛኝ ነው።
 

No comments:

Post a Comment