Wednesday 30 October 2013

“እኔ ወደ ሀገሬ ለመምጣት ከማንም ጋር አልተደራደርኩም”

“እኔ ወደ ሀገሬ ለመምጣት ከማንም ጋር አልተደራደርኩም” ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ

የቀድሞው የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ከሁለት ዓመታት ስደት በኋላ ሰሞኑን ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል። የጋዜጠኛ ዳዊት ወደ ሀገሩ መመለስ የሰሞኑ መነጋገሪያ ጉዳይ ሆኗል።
 
የጋዜጠኛ ዳዊት ወደ ኢትዮጵያ መመለስ በበርካታዎችም ዘንድ የተደበላለቀ ስሜት እንዲፈጠር አድርጓል። “ከመንግስት ጋር ተደራድሮ ነው የመጣው” ከሚለው ጀምሮ “በአክራሪ የዲያስፖራ ፖለቲከኞች ጫና ደርሶበት ነው” እስከሚለው ድረስ ጉዳዩ በማወያየት ላይ ነው። በሀገሪቱ የፖለቲካ ሂደት ውስጥም ጋዜጠኛ ዳዊት ተሰዶ በድፍረት እንደገና ወደ ሀገሩ በመመለሱም እንግዳ ስሜት እንዲፈጠር ያደረገ ይመስላል። በዚህና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችም ባልደረባችን ዘሪሁን ሙሉጌታ አነጋግሮታል።
 
ሰንደቅ፡- በቅድሚያ እንኳን ደህና መጣህ። ከሁለት ዓመታት የስደት ቆይታ  በኋላ ወደ ሀገርህ ለመመለስ የወሰንክበት መሠረታዊ ምክንያት ምንድነው?
 
ጋዜጠኛ ዳዊት፡- የመጣሁበት ዋና ምክንያት በስደት ዓለም በጋዜጠኝነት ሙያ መቀጠል የሚያስችል ሁኔታ ስላጣሁ ነው። በስደት ላይ እያለሁ ድረገፅ ከፍቼ በመስራት ላይ ነበርኩ። ስራውም ምን እንደሚመስል ለመገንዘብ ችያለሁ። በተለይ ስደት ላይ ሆነህ የጋዜጠኝነትን ስራ መስራት እጅግ ከባድ ነው። ሥራው ብዙም የልብ የሚያደርስ ስሜት የለውም። ደስተኛም አትሆንም። ዝም ብለህ ስትመለከተው የይስሙላ ነው የሚሆንብህ። በተለይ ሀገር ቤት በነበርክበት ወቅት በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የነበረውን ሚዲያ ስትመራ ቆይተህ በስደት ላይ ግን የውሸት ወደሚመስል ስራ ስትገባ ዕድሜህንና ጊዜህን ከማባከን ውጪ የምታተርፈው ነገር ስለሌለ ከዚህ በላይ እዛ መቆየቱ ተገቢ መስሎ አልታየኝም። በግሌ ምን ያህል ጊዜ ነው እንደዚህ የምቆየው? ሙያውን እወደዋለሁ፣ በሙያውም መቀጠል እፈልጋለሁ ብዬ እስካመንኩ ድረስ ውስጤ ደስተኛ ሳይሆን፣ መኖር ስላለብኝ ብቻ ከምኖር ብዬ ነው ለመመለስ የወሰንኩት።
ሰንደቅ፡- ምንም እንኳ ሙያዊ ግዴታህን ለመወጣት ከስደት ይልቅ በሀገር ቤት ይሻላል የሚል አቋም እንዳለህ ብትገልፅም፤ ከአንተ ጀርባ የሚነገረው ብዙ ነው። በተለይም በዲያስፖራ በሚገኙ የፖለቲካ ኃይሎች ጋር ግጭት ውስጥ መግባትህ በሰፊው እየተነገረ ነው እናም በዚህ ረገድ የገጠመህ ችግር ምንድነው? ችግሩስ ወደ ሀገርህ እንድትመለስ ተፅዕኖ አድርጎብሃል?
 
ጋዜጠኛ ዳዊት፡- በእርግጠኝነት የምነግርህ ነገር ቢኖር ተፈጥሯል የተባለው ችግር እኔን ወደዚህ እንድመጣ አላደረገኝም። በመሠረቱ ጉዳዩን ካየነው ከስደት የሚያስመልስ አይደለም። በእርግጥ እኔ ከአሜሪካ መንግስት ጋር አይደለም የተጋጨሁት ወይም ደግሞ በአሜሪካ ብሔራዊ የፀጥታ አደጋ ላይ ያነጣጠረ ወንጀል አልተፈፀመም። በሌላ ወገን ደግሞ በአሜሪካ የሚኖር ስደተኛ ፖለቲከኛ ቅር ስለተሰኘብህ ብቻ ብድግ ብለህ የምትመጣበት ምክንያት የለም። ትልቁ ነገር ከእነዚህ ሰዎች ጋር ያለኝ መሠረታዊ ልዩነት ከፕሬስ ነፃነት ጋር የተያያዘ ጉዳይ ነው። ዋናውም ልዩነት ይሄው ነው። እኔ ከሀገሬ ተሰድጄ ስሄድ በወቅቱ በምሰራቸው ነገሮች ደስተኛ ያልሆኑ የመንግስት ኃላፊዎች ነበሩ። ደስተኛ አለመሆናቸውንም የሚገልፁት በመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ነበር። በወቅቱ ዘመቻው ሲካሄድ ሙያው ነፃ መሆን አለበት ብዬ ነፃነትን ፍለጋ ነበር የተሰደድኩት። ስለዚህ 10ሺህ ኪሎ ሜትር ተሰድጄ ነፃነቴ እንደገና የማስረክብበት ምክንያት የለም።
 

Friday 25 October 2013

Exiled Awramba Times Editor going back to Ethiopia


Awramba Times (Washington DC) – Dawit Kebede, editor -in- Chief of the Awramba Times website is going back home after two years of stay as a political asylee in the United States.
In an interview with political analyst Yared Tibebu, in Washington DC, Dawit officially announced his decision to end his political asylum and head back home tomorrow, October 25, 2013.
Editor Dawit iterated his assessment that good journalism cannot be done away from the homeland and going back to the roots is important. Responding to the questions whether recent disagreements with some diaspora based political ‘activists’ had any weight in his decision to go back to Ethiopia, Dawit insisted that his love for the profession and his inability to excel in the field given immigrant life is the only decisive factor in his decision to go back to Ethiopia. Please watch his interview below.

Tuesday 22 October 2013

እኔ ማነኝ?

እኔ ማነኝ? 
ማሳሰቢያ 

ይህን አነስተኛ ሰነድ የተወሰደው ከ220 ገጾች በላይ ርዝማኔ ካለው የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የፖለቲካ ስልጠና ሰነድ ነው። ዋናው የስልጠናው ሰነድ እኔ፣ እኛና ህዝባዊ ሰራዊቱ፣ ሃገራችን ኢትዮጵያ፣ የፖለቲካና የፍልስፍና ጽንጸ ሃሳቦችና ንድፈ-ሃሳቦች በሚሉ 4 ምእራፎች የተከፋፈለ  ነው።  በዚህ ተቀንጭቦ በቀረበው ሰነድ ውስጥ የተነሱ ጉዳዮች አንዳቸውም ሳይቀሩ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይል ድርጅትና አባላት ብቻ ጉዳዮች ናቸው ብለን አናምን። የሁሉም የሃገራችን የፖለቲካ ድርጅቶችና አባሎቻቸው፣ እንዲሁም የአጠቃላይ የማህበረሰባችን ጉዳዮች ናቸው ብለን እናምናለን። በዚህ ሰነድ ውስጥ በተነሱ ጉዳዮች ላይ የግንቦት 7  ህዝባዊ ሃይል አባላት የሚያደርጉትን ሰፊና ጥልቅ ውይይት በትንሹም ቢሆን በማህበረሰባችን ውስጥ እንዲደረግ ካስቻልን ለሁላችንም ጠቀሜታ የሚኖረው መስሎናል። በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ የምንፈልገው በዚህ ሰነድ ውስጥ የተነሱ ችግሮች በመሰረቱ ሊቃለሉ የሚችሉት ተገቢ የሆኑ የስርአት ለውጦችና ተገቢው የሆኑ ተቋማት ሲመሰረቱ እንደሆነ እናውቃለን።  ቁልፍ  የሆኑት ከፖለቲካው ጋር የተያያዙ የስርአትና የተቋማት ለውጦች ናቸው። ከዚህ አንጻር ነገሮችን ካየናቸው ይህን አይነቱ ሰነድ ወይም ሌላ ምንም አይነት ሰበካ፣ ትንታኔ፣ ውይይት፣ የንባብና የምርምር ጥረት መሰረታዊ የሆነውን ለውጥ ለብቻቸው ያመጣሉ ብለን አናምንም።  ችግሩ  ያለው  የምንመኛቸውን  መሰረታዊ  ለውጥ  ሊያመጡ  የሚችሉ  ስርአቶችና  ተቋማት  በሃገራችን  የሉም።  እነሱን  ደግሞ  የምንፈጥራቸው እኛው የሃገሪቱ ዜጎች ነን። ይህ ሰነድ ሌላው ሁሉ ቢቀር በግለሰብ፣ በቡድንና በድርጅት ደረጃ ችግሮቻችን ምን ያህል ጥልቅና ውስብስብ  እንደሆኑ  መገንዘብ  እንድንችል  ያደርገናል  የሚል  እምነት  አለን።  ችግሮቹን  ከተገነዘብን  የመፍትሄዎቻቸውን  ፍንጭ  ለማየት አያዳግተንም።  

የፖለቲካ  ስልጠና 
ምእራፍ 1. እኔ 

የፖለቲካ ሥልጠና ትምህርታችን የሚጀምረው እኔ በሚለው ርዕስ ነው። ለምን ይህ ርዕስ ከሁሉም ርዕሶች ቀደመ? በዚህ ርዕስ ሥር ምን  ጉዳዮች እናነሳለን? በመጨረሻም የዚህን ርዕስ ወይይት ስንጨርስ ምን መጨበጥ ወይም ማግኘት ይቻላል ብለን እናምናለን? የሚቀጥለው  ሃተታ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥ ይሆናል። 

1.  ለምን እኔ በሚለው ርዕስ  ጀመርን? 

መልሱ ቀላል ነው። ሁላችንም ወደ ግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ስንመጣ በግላችን ነው የመጣነው። ከሌሎች ጓደኞቻችን ጋር ብንመጣም ሕዝባዊ   ኃይሉን እንቀላቀል የሚለውን ውሳኔ  የወሰንነው እያንዳንዳችን በተናጠል ነው። ብዙዎቻችን ከዚህ በፊት አንተዋወቅም። የመጣነው እያንዳንዳችን ከሌላው ጋር ሆነን፣ ድርጅት ፈጥረን፣ ወያኔን ተዋግተን እናስወግዳለን ብለን አስበን ነው። ከተሰባሰብን በኋላ ከተናጠል ወደ ብዙሃን ተቀይረናል። ከእኔ እኛ ሆነናል። የእኛነታችን መሠረት ግን እኔ ነው። የእኛነታችን መነሻ እኔ ሆኖ መድረሻችን ደግሞ እኛ ሆኗል። መነሻውን የማያውቅ መድረሻውን አያውቅም ይባላል። እኔን ሳናውቅ እኛን ማወቅና እኛን መሆን አይቻልም። በመሆኑም እኔ ማነኝ የሚለውን ጥያቄ በቅድሚያ በሚገባ ለራሴ መመለስ መቻል ይኖርብኛል።  ከሌሎቹ ጓዶቼ የሚቀርብልኝ አንተ ማነህ የሚል ጥያቄ  በሚገባ መመለስ የምችለው ስለራሴ ከሚኖረኝ ጥልቅ እውቀት በመነሳት ብቻ  ነው። እውን ስንቶቻችን ነን እራሳችን በደንብ የምናውቅ? እኔ ማነኝ ለሚለው ጥያቄ  የተሟላ መልስ ለመስጠት ትልቅ ድፍረትና ከራስ ጋር መፋጠጥን ይጠይቃል። ጀግንነትን ይጠይቃል።  ከራስ ስሜት፣ ዝንባሌና ፍላጎት ጋር መሟገት ያስፈልጋል። የራስን አእምሮና ነፍስ መበርበር ያስፈልጋል።  

እኔ ማነኝ ለሚለው ጥያቄ በሚገባ መልስ ስሰጥ ነው ነገ በጦር ሜዳ ጓዴን ጥዬ እንደማልሸሽ፣ ወንድሜን በሰላሳ ሽልንግ እንደማልሸጥ እርግጠኛ የምሆነው። ወያኔ እንዳደረገው ነፃ አወጣዋለሁ የምለውን ሕዝብ መልሼ ረጋጭ መሆን እንደማልችል የማውቀው። ዘራፊ፣ ገፋፊ፣ አስገድዶ ደፋሪ እንደማልሆን እርግጠኛ መሆን የምችለው። ሰለ ሀገሬ ስለወገኔ መዋረድ የማነበንባቸውን ቃላት፣ ጉልበቱ እድሉ ስልጣኑ ሲኖረኝ ወደ በጎ ተግባራት እንደምቀይራቸው እርግጠኛ የምሆነው ራሴን በሚገባ ሳውቅ ነው። ጽናት ኖሮኝ የምዘልቅ፣ ምንም ፈተናና ችግር ወያኔን ከመደምሰስ ሊያስቆመኝ እንደማይችል እርግጠኛ የምሆነው እራሴን በሚገባ ሳውቅ ብቻ ነው:: ለጓዴ፣ ለድርጅቴ ለሃገሬ ሰዎችና ለሃገሬ የገባሁትን ቃል የማላጥፍ እንደሆነ  እርግጠኛ የምሆነው እኔ ማነኝ ለሚለው ጥያቄ አጥጋቢ መልስ ስሰጥ ነው። 

 እኔ ማነኝ የሚለውን ጥያቄ በሚገባ ለራሴ ስመልስ ከጓዶቼ የሚቀርብልኝን አንተ ማነህ የሚል ጥያቄ በቀላሉና በእርግጠኛነት መመለስ እችላለሁ። እኔ፣ የእኛ የግንቦት 7 ሕዝባዊ አባላት ስብስብና ድርጅት፣ ከዛም አልፎ የማኅበረሰባችንና የሀገራችን የመሠረት ድንጋይ ነው። የመሠረት  ድንጋይ ብቻ አይደለም። ድርጅታችንን፣ ማኅበረሰባችንና ሀገራችንን የምንገነባበት እያንዳንዱ ጡብ እኔ ነው። እኔ በደንብ ካልተገነባ፣ እኔ በደንብ  ካልታነጸ፣ እኔ ነካ ሲያደርጉት የሚፈርስ፣ እፍ ሲሉት ብን የሚል ከሆነ፣ እኔ የሚያዝ የሚጨበጥ የሌለው ሙልጭልጭ፣ እኔ መርህ- የለሽ  ልክስክስ፣ አከርካሪ የለሽ ልምጥምጥ ከሆነ እኛም የለንም። ድርጅት አይኖርም። ማኅበረሰብ መማቀቁ፣ ሀገር መውደሙ አይቀርም።  

እንደ ወያኔ ድርጅት በሚያጭበረብሩ መሪዎችና ተከታዮች የተገነባ ድርጅት በለስ ቀንቶት ወያኔን ቢያስወግድ የሚፈጥረው ሀገራዊና  መንግሥታዊ ሥርዓት የአጭበርባሪዎች ይሆናል። አድሎን፣ የድርጅትን ንብረት እንደራስ አድርጎ አለማየትን፣ ራስ ማስቀደምን፣ መስገብገብን፣ ወታደራዊ ፖሊስ ወይ ጓዶቼ አያዩኝም በሚል በጋራ ያጸደቁትን ሕግ ሥርዓትና ደንብ የሚጥሱ፣ ለጓዶቻቸው ደህንነትና ጤንነት የማይጨነቁ፣ እርስ በርስ  የማይፋቀሩ፣ የግል ድሎትንና ምቾትን ብቻ ማሰላሰልን ሥራዬ ብለው የያዙ አባላት የተሰባሰቡበት ድርጅት ታግሎ አታጋይ መሆን አይችልም።  እንደ ድርጅትም መዝለቅ አይችልም። ነጻ ወጥቶ ሌላውን ነጻ ማውጣት አይችልም። በአንድ ተአምር ወያኔን ማስወገድ ቢሳካለት ከወያኔ በላይ ሕዝብ አስመርሮ ወያኔ ማረኝ የሚል ዘመን እንዲመጣ ማድረጉ አይቀርም። በሀገራችን ታሪክ የሆነው ይህ ነው። ደርግን ያየ ሃይለስላሴ ማረኝ አለ። ወያኔን ያየ ደርግ ማረኝ አለ። እኛን ያየ ወያኔ ማረኝ የሚልበትን ሁኔታ ልንፈጥር አይደለም ትግል ውስጥ የገባነው። እኛ ትግል ውስጥ የገባነው መንግሥት ተቀይሮ መንግሥት በመጣ ቁጥር ካለፈው ሥርዓት አዲሱ እየባሰበት የሕዝብ ስቃይ የረዘመበትን የታሪክ ጉዞ ለመቅጨት ነው። እያንዳንዳችን ወደ ትግል የገባነው የሕዝብ እሮሮና ስቃይን ለአንዴና ለመጨረሻው እልባት ወይም መቋጫ ልናበጅለት ነው። ይህ ማድረግ የምንችለው በምንገነባው ድርጅት አማካይነት ነው። የምንገነባው ድርጅት የሚሰራው ከሲሚንቶና ከአሸዋ ወይም ከሌሎች ቁሳቁሶች አይደለም። በሰው ነው። በእኔ ነው። ሰው እንደሸክላ እንደ ብሎኬት ከአሸዋና ከሲሚንቶ የሚሰራ ወይም እንደ እንስሳ የምናራባው ፍጥረት አይደለም። ሰውን ሌላው ሰው አይሰራውም። ሰው ራሱን በራሱ ብቻ የሚሰራ ፍጥረት ነው። እኔ ፈቃደኛ ካልሆንኩ፣ ለመማር ዝግጁ ካልሆንኩ ሌላው ሰው ላስተምርህ፣ ልምከርህ ቢለኝ ዋጋ የለውም። 

ዛሬ እኔነታችንን ወደፊት ለማምጣት ለምንፈልገው ሀገራዊና ማኅበረሰባዊ ለውጥ እንዲመች አድርገን በሚገባ እዚሁ ካላነጽነው መጨረሻችን አሳፋሪ ውድቀት ነው። የሀገር እጣ፣ የ90 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን እጣ የሚወሰነው እዚህ እኛ መሃል እያንዳንዳችን በምንላበሰው ስብእና፣ በሚኖረን ሰብአዊ ሥነሥርዓትና ጥብቅነት፣ በምንገነባው የአብሮነትና የአንድነት ስሜት፣ በምንሸምተው እውቀትና ክህሎት ላይ ተመስረቶ ነው። እባብ ከሆነን የርግብ እንቁላል አንጥልም። የእባብ ፍልፈሎች እንጂ። ለዚህ ነው ከማናቸውም ጉዳዮች በላይ በግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ውስጥ እኔ ማነኝ ለሚለው ጥያቄ ቅድሚያ የሰጠነው። እኔ ማነኝ ወይም አንተ ማነህ ለሚለው ጥያቄ በጣም ቀላል ከሆኑ ነገሮች ተነስተን መልስ መስጠት እንችላለን። የእኔ ማነኝ ጥያቄ ምላሽ ግን እንደምናስበው ቀላል እንዳልሆነ ቀጥለን እንመለከታለን። 

2.  እኔ ማነኝ 

“አንተ ማነህ?  
“እኔ?” 
“አወን፣ አንተ” 
“እኔማ ከበደ አበበ ነኝ፣ እንደ ሰው በማልቆጠርበት ኢትዮጵያ በምትባል ሀገር የምኖር ሰው ነኝ” 
“ሰው መሆንክን አውቃለሁ። እሱ ምን ችግር አለው። ስምም የሁላችንም ነው። ሃገርም እንደዛው። ከዚህ ውጭ ሌላ ነገር ስለራስህ ንገረኝ።” 
“እንደምታየኝ ወጣት ኢትዮጵያዊ ነኝ። እድሜዬ 30 አመት ነው። የተወለድኩት ጎንደር፣ አዲስ ዘመን ነው። እስከ 12ኝ ክፍል ተምሬአለሁ። በውትድርና ሙያ ሰርቻለሁ። 3 ወንድሞች 2 እህቶች አሉኝ። እኔ የመጨረሻው ልጅ ነኝ። የመጀመሪያው ወንድሜ ታላቃችን አዲስ አበባ ውስጥ በምርጫ 97 ወቅት በወያኔ ተገድሏል። ሁለቱ እህቶቼ በሃገራቸው ስራ አጥተው አረብ ሀገር ሥራ ብለው ሄደዋል። እናቴ በውንድሜ ሞት ሃዘን የተነሳ ብዙም ሳትቆይ አርፋላች። አባቴ ነጋዴ ነው። በሕይወት አለ። ወያኔ  ከምርጫ 97 በኋላ ተቃዋሚ ትደግፋለህ ብሎ አሰረኝ። ከዛም ከሠራዊቱ ተባረሃል ብሎ ፈታኝ። መጀመሪያውኑ የወያኔ ወታደር መሆን አልነበረብኝም። በሠራዊቱ ውስጥ ያየሁት የዘር አድሎና መጠቃቀም ቆሽቴን ያበግነው ነበር። የከፍተኛ መኮንኖቹ እጅግ የሚገርም በዘር ላይ የተመሰረተ የዘረፋና የቅንጦት ህይወትና የተራው ወታደር ሬት ሬት የሚል ህይወት አንገሽግሾኝ ነበር። መባረሩን በደስታ ነው የተቀበልኩት። ችግሩ ሌላ ሥራ ማግኘት አልቻኩም። በመንግሥት መስሪያ ቤት እንዳልቀጠር በጸረ_መንግሥትነት የሚፈርጅ ደብዳቤ ሰጥተው ነው ከሰራዊቱ ያባረሩኝ። ያንን ደብዳቤ እያየ ማንም የሚቀጥረኝ ጠፋ። በግል ሥራ እዛም እዚህም ሁሉን ነገር ሞከርኩት። ነገር ግን የኑሮ ውድነቱ፣ መተንፈሻ  የነሳኝ የሰላዩ ብዛትና አፈናው፣ የወንድሜና የናቴ ደም መና ሆኖ መቅረቱ፣ በአረብ ሃገር በእህቶቼ ላይ የሚደርሰው ውርደትና ስቃይ፣ ወያኔዎች ሲፋፉ እኔ እንደ ስልክ እንጨት መድረቄ ሌላውም ተደራርቦ ወያኔን መታገል አለብኝ ወደሚል መደምደሚያ አደረሰኝ። የግንቦት7 ሕዝባዊ ኃይል መቋቋሙን ሰማሁ። መጣሁ። ተቀላቀልኩ። የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል አባል ነኝ” 
 ከዚህ በላይ እንደተመለከትነው እኔ ማነኝ ወይም አንተ ማነህ የሚለው ጥያቄ በዚህ መልኩ ሊመለስ ይችላል። ይህ ምላሽ ግን ሁላችንም በየግላችን እንደማንነታችን የምንመልሰው ምላሽ ነው። ይህን አይነት ምላሽ ለመስጠት ሁላችንም ብዙ አይቸግረንም። ሁላችንም በየግላችን ስለራሳችን  ታሪክ በቀላሉ የምናየው ጭብጥ ነው። ስማችን፣ የተወለድንበት ቦታ፣ እድሜያችን ወዘተ አይቀየርም። ስለወያኔም ሥርዓት የምንናገረው ጭብጥ  እንዲሁ ለሁላችንም አንድ ነው። በወያኔ  የደረሰብን በደል ይለያይ እንጂ ሁላችንም በደል ደርሶብናል። የምሬታችን ደረጃ ይለያይ እንጂ ሁላችንም መሮናል። ይህ ምሬት ሁላችንንም ወያኔን እንድንታገለው ገፍቶን በግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ውስጥ አሰባስቦናል። ወደ ግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ስንመጣ ደረቅ ስማችን፣ የግልና የቤተሰብ ታሪካችንን፣ የግል ብሶታችንን ብቻ ግን ይዘን አልመጣንም። ቀጥለን እንደምንመለከተው ብዙ  ነገር ይዘን መጥተናል። 

እኔ ማነኝ? 

ወደ ግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ስመጣ ምን ይዤ መጣሁ? ስሜን ብቻ ነውን? በወያኔ ላይ ያለኝ ምሬትና ጥላቻ ብቻ ነውን? በደል የወለደው ምሬትንና መንገፍገፍ ብቻ ነውን? መንገፍገፍ የወለደው እልህና ቁጭት ብቻ ነውን? እነዚህ ብቻ አይደሉም። ሌሎችም ነገሮች ይዤ መጥቻለሁ። እያንዳንዳችን የተለያዩ ሙያዎቻችንን  ይዘን መጥተናል። የወታደራዊ፣ የሂሳብ ሠራተኛነት፣ የጋዜጠኛነት፣ የሃኪምነት፣ የግንበኛነት፣ የገበሬነትና የአስተማሪነት ወዘተ የመሳሰሉትን ሙያዎች ይዘን መጥተናል። ግን እነዚህን ብቻ ነውን ይዘን  የመጣነው? የለበስኩትን ልብስ ብቻ ነው ወይስ መቀየሪያ ጭምር፣  ገንዘብ፣ መሣሪያ፣ ሞባይል፣ መጽሃፍ ይዤ መጥቻለሁን? በሽታ፣ ህመምና ቁስል ይዤ መጥቻለሁን? የሲጋራ፣ የመጠጥ፣ የጫት ሱስ ይዜ መጥቻለሁን? ሌላም ጥያቄ ማንሳት ይቻላል። 

 ከዚህ በላይ የተጠቀሱት እኔ ወደ ግንቦት 7  ሕዝባዊ ኃይል ይዣቸው የመጣኋቸው ወይም ላመጣቸው የሚችሉ ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ። እነዚህ ነገሮች የተለያዩ ጥቅምና ጉዳት አላቸው። ስሜ  ታሪኬ ማንም አይጎዳም። ሙያዬ ይዤ  የመጣሁት ንብረት ገንዘብ ወዘተ የኃይሉን አባላትና ድርጅታችንን ይጠቅማል። በሽታ፣ ህመም  ቁስል ይዤ ከመጣሁ ቆራጥነቱና ጽናቱ እስካለኝ  ድረስ ጤናዬንና  አቅሜን የሚመጥን ተግባር እያከናወንኩ ለትግሉ የድርሻየን አበረክታለሁ።  ከነህመሜ የጓዶቼ መመኪያ መሆን እችላለሁ። ይዤ  የመጣሁት ሱስ ካለ ግን ምንም ጠቀሜታ  የለውም። በዚህ ሱስ የተነሳ  እራሴን እጎዳለሁ። ጓዶቼን እጎዳለሁ። የሱስ ምርኮኛ  መሆን ሱስ ለማርካት ሲባል የማያመጣብኝ ፈተና አይኖርም። ሱስ አላስፈላጊ የደህንነት አደጋ ያለበት ሁኔታ  ውስጥ ይጨምረኛል። ሱስ ልመናን ውርደት ያስከትላል። ሱስ የድርጅትን የአደራን ገንዘብና ንብረት ማባከንንና ሌባ መባልን ያስከትላል። ሱሱ ምሱን ካላገኘ ማንቀላፋት፣ መንገላጀጅ፣ ትእግስት የሌለን፣ የምንነጫነጭ፣ የምንቀዠቀዠ ወይንም የምንደበት ያደርገናል። ሱስ ሰው እራሱ ጥሮ ግሮ ወይም ሌሎች ጓዶቹ ጥረው ግረው ላባቸውን አንቆርቁረው ያሰባሰቡትን ሃብት በከንቱ እንዲባክን የሚያስደርግ ነው። እንኳን ለትልቅ ዓላማ አባላት በተሰባሰቡበት ድርጅት ውስጥ ቀርቶ የግል ሕይወት በሚኖርበት ሁኔታ ይህ ብክነት አሳዛኝ ነው። ከዚህም በተጨማሪ የተጠቀሱት ሱሶች በተለያየ  ደረጃ  በጤንነታችን ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ናቸው። ሲጋር በቀጥታ  ከሳምባና ከልብ ጋር፣ መጠጥ ከልብ፣ ከጉበት፣ ከኩላሊት ወዘተ ጋር፣ ጫት ከሆድ ከአእምሮ  ጋር የተያዙ የጤንነት ጉዳት አላቸው። ይህ ጉዳት እያንዳንዱ ሱስ ያለበትን ሰው በተለየ  የሚጎዳ ቢሆንም የርሱ መጎዳት በሌሎች ላይ ጉዳት ያስከትላል።  ጤና  የሌለው፣ የአእምሮና የአካል ብቃት የሌለው ታጋይ ከሌሎች ጓዶቹ ጋር በእኩልነት መንቀሳቀስ አይችልም። በጉዞ  መድከም፣ መፍዘዝ ይመጣል።  እነዚህ ሱሶች የየግለሰቡ ናቸው ብለን የማንተዋቸው ለዚህ ነው። ሌሎችንም ጉዳት ላይ የሚጥሉ መዘዞች አላቸው። እኔ  ማነኝ ስንል እነዚህ አይነት ሱሶች ካሉን  እነዚህ ሱሶች ያሉኝ ግለሰብ ነኝ የሚል ተጨማሪ ምላሽ ይኖረዋል። እኔ ማነኝ የሚለው ጥያቄ ግን በነዚህ ስለራሴ ባቀርብኳቸው ጭብጦች ብቻ የሚጠቃለል አይደለም። የተሟላ ምላሽ ለማግኘት ብዙ የሚቀረው ነጥቦች አሉ።  

እኔ ማነኝ? 

እኔ ማለት ስሜ፣ ንብረቴ፣ ሱሶቼ፣ እድሜ፣ የትውልድ ቦታዬ፣ ጎሳዬ  ዘሬ፣ ሃይማኖቴ  ብቻ ናቸው ወይ? ወይንስ ሌሎች ጓዶቼ በቀላሉ ሊደርሱባቸው የማይቹላቸውና  የማያዩዋቸው እኔ ግን ለብቻዬ የማውቃቸው ነገሮችም ይዤ መጥቻለሁ። እነዚህ ጓዶቼ  በቀላሉ ለማየት የማይችሏቸው ነገሮች ግን እኔ የማውቃቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?  ድፍረት፣ ጀግንነት፣ ቆራጥነት፣ ታማኝነት፣ ፍቅርን፣ ትእግስትን፣ ጽናትን ወዘተ ይዤ መጥቻለሁ? ሌሎችስ የነዚህ ተቃራኒ የሆኑ። ፈሪነትን መሠሪነትን፣ ክፋትን፣ ተንኮልን፣ መዋሸትን፣ ወላዋይነትን፣ ተራ ቅናትን፣ አሉባልተኛነትን ወሬኛነትን፣ አጭበርባሪነትን፣ ተላታሚነትን፣ ጠብ ጫሪነትን፣ መለገምን፣ መስገብገብንስ፣ ቱግ ማለትን ግብዝነትን ይዤ መጥቻለሁ? እየዋልን እያደርን መተዋወቅ ስንጀምር ለነዚህ ጥያቄዎች አንዳችን ስለ
አንዳችን የምንለው ነገር ይኖረን ይሆናል። ገና ሕዝባዊ ኃይሉን ስንቀላቀል ግን በነዚህ ጉዳዮች ላይ ስለእኔ ከኔ በስተቀር ማንም የሚያውቅ ሰው አይኖርም። ፈሪ ልሁን ደፋር፣ ሃቀኛ ልሁን አጭበርባሪ የማውቀው እኔ  ብቻ  ነኝ። ደፋር፣ ሃቀኛ፣ ጀግና፣ ታማኝ፣ ጓዱን አፍቃሪ የሆኑ ባህሪዎቼ ለጎዶቼና ለድርጅቴ ጥንካሬዎች ናቸው። ሌሎች ባህሪዎቼ፣ ለምሳሌ መዋሸት፣ መወላወል፣ ተላታሚነት፣ አምባገነንነት፣ ሌብነት፣ ስግብግብነት ግለሰበኛነት፣ ወዘተ የሕዝባዊ አባላቱንና ድርጅቱን  የሚጎዱ አደጋ ላይ የሚጥሉ መጥፎ ባህሪዎች ናቸው። ቀደም ብለን ከጠቀስናቸው ከሱስ ጋር ተያያዥነት ካላቸው ችግሮች እጅግ የከፉ ናቸው። ለምን ብለን እንጠይቅ። 

አሉባልተኛ ሰው ድርጅት ያምሳል። በአሉባልታው የተነሳ ግለሰቦችና ቡድኖች እርስበርሳቸው ሊጋጩ፣ በመሃከላቸው መተማመን ሊጠፋ  ይችላል።  ብሎም  ድርጅት እስከማፍረስ ሊደርስ ይችላል። የሲጋራ ሱስ ወይም የመጠጥ ሱስ ያለበት ሰው ራሱን በቅድሚያ ይጎዳል። ድርጅቱንም ይጎዳል ግን ድርጊቱ ድርጅት የሚያፈርስ አይሆንም። ሲጋራ የሚያጨስ ሰው በጀግንነት ሊዋጋ ይችላል። ወላዋይ ሰው ግን ጓዶቹን በጦር ሜዳ ጥሎ ሊፈረጥጥ ይችላል። ሌሎችም ጎጂ የሆኑ ባህርይዎቻችንና  ባህሎቻችን እያንዳንዳንችን ቤተስብ፣ ሃብት፣ ቤትና ንብረት በትነን እዚህ የተሰባሰብንለትን ዓላማ  እንዳናሳካ የሚያደርግ አቅም አላቸው። ዋናውን ጠላት ወያኔን ትተን እርስ በርስ እንድንባላ፣ ወያኔ እስካሁን ካደረሰብን በደል በላይ የከፋ በደል እንዲያደርስብን የሚያደርጉ ናቸው። ይህ የከፋ በደልና ጥቃት ምን ሊመስል እንደሚችል ሁላችንም በቀላሉ ልንገምተው የምንችለው ነው።  

ይህ በመሆኑም እያንዳንዳችን ወደ ሕዝባዊ ኃይሉ ስንመጣ ይዘናቸው የመጣናቸውን ጎጂ ባህሎችና ባህርይዎች ያለምንም መወላወል መጋፈጥና  ከሁላችንም ውስጥ አጥበን ማውጣት ይኖርብናል።   

የግንቦት  7  ሕዝባዊ ኃይል እነዚህን አይነት ጎጂ ባህሎች እንታገል ሲል የመጀመሪያው ድርጅት አይደለም። በሀገራችን የፖለቲካ ድርጅቶች ከተፈጠሩ ጀምሮ እነዚህ ጎጂ ባህሎች በየፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ ተነግሮ  የማያልቅ ውድመት አስከትለዋል። እየዋለ እያደረ በበርካታ የሀገራችን  የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ የእነዚህን ጎጂ ባህሎች አውዳሚነት እየታወቀ መጥቷል። ሆኖም ግን ተገቢውን ትኩረት በመስጠት እነዚህ ባህሎች በየድርጅቱ ውስጥ እንዳይሳፋፉና ሥር እንዳይሰዱ ማድረግ የቻለ ድርጅት እስካሁን  የለም። በየመድረኩ የተለያዩ ድርጅቶች መሪዎች እነዚህን   ጎጂ ባህሎችና ባህሪዎች እንታገላላን በማለት ቃል ቢገቡም እስካሁን ግን አንድም የተሳካለት ድርጅት አልተገኘም። ይህ ትግል ቀላል ስላልሆነ  ብዙዎቹ ድርጅቶች በገዛ አባሎቻቸው የውስጥ ሽኩቻ፣ የርስበርስ መጠላለፍ፣ ሲወድሙ ሲሰነጣጠቁ ሥራ የማይሰሩ በድኖች ሆነው ሲቀሩ አይተናል። 

ከ1966ቱ አብዮት ጋር ብቅ ካሉት ድርጅቶች ጀምረን ታሪካቸውን መቃኘት እንችላለን። ኢህአፓ፣ ኢዲዩ፣ መኢሶን፣ ኢሰፓ፣ ኦነግ ወዘተ በራሳቸው ድርጅትና ከሌሎች ድርጅቶችጋር የገቡበት ሽኩቻና መጠላለፍ ነው ያወደማቸው ወይም ከሞት አፋፍ ላይ ያስቀመጣቸው። የወያኔ አይነት ድርጅት ዘረኛነትን መሰባሰቢያ በማድረጉና የሰዎችን ግንኙነት በዘር ሙጫ ለማጣበቅ በመቻሉ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ሲወዳደር ብዙም የውስጥ መጠላለፍ አልታየበትም። በሌሎችም ላይ የበላይነት ያገኘው ዘረኛ በሆነ ዓላማ ዙሪያ የተሰባሰቡት ከፍተኛ መሪዎች ለዘር አጀንዳቸው ቅድሚያ ሰጥተው አንድ ሆነው እንዲንቀሳቀሱ በማስቻሉ ነው። ይህም ሆኖም ወያኔም ቢሆን የድርጅት ውስጥ ሽኩቻና ሴራ መጠላለፍ ያልነበረበት ድርጅት አይደለም። አሁንም ቢሆን መጠላለፉ የሌለበት ድርጅት ነው ማለት አይደለም። በቅረቡ እየታየ ያለው የወያኔ መዳከም በተቃዋሚ   ጥንካሬ የመጣ አይደለም። የድርጅቱ ውስጣዊ መበስበስ፣ የቡድኖችና የግለሰቦች የሥልጣን፣ የጥቅም፣ የከንቱ  ክብርና ዝና ሸኩቻ ነው። 

በወቅቱ በሚገኙት የተቃዋሚ ድርጅቶች ጎራ ያለውን ጉድ ሁላችንም እናውቀዋለን። ዛሬ  ትብብር፣ ቅንጅትና ኅብረት ፈጥሮ  ነገ  መበታተን የተለመደ ነው። በየቀኑ ድርጅት   መፈልፈል ነው። ዛሬ ተመሥርተው፣  በማግስቱ  መሰነጣጠቅ  መፍረስ እጣቸው የሆነው የሀገራችን ድርጅቶች ይህን መራራ ጽዋ በመጎንጨት ላይ ያሉት  በወያኔ የስለላ ችሎታና ሌላም ክህሎት አይደለም። የየድርጅቶቹ መሪዎችና  አባላት ደካማና ጎጂ የሆኑ ባህሎቻቸውንና ባህሪዎቻቸውን በደንብ መገንዘብና ማስወገድ ስላልቻሉ ነው። ሃገርና ወገን የመሳሰሉ እጅግ ክቡር  የሆኑ ነገሮችን ከተራ የግል ስም፣ ክብር ጥቅምና ፍላጎት በታች አድርጎ  ለማየት የማይፈልጉ አባላት ድርጅቶች በማቀፋቸው እነዚህ አሳፋሪና አሳዛኝ የመሰነጣጠቅ ችግሮች ሲከሰቱ አይተናል። እኛስ? እነዚህን ከየአንዳንዳችን ማንነት የሚፈልቁትን ጎጂ ባህሎች አስወግደን የጓዶቻችን የወገናችን የሕዝባችን ተስፋ መሆን እንችላለን? የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ትልቁ ፈተና ይህ ነው።  

አናሳ ቁጥራችንን በሂደት ማብዛት እንችላለን። ወታደራዊ ሙያ የሌላቸውን ጓዶቻችንን ከፍተኛ ወታደራዊ ሥልጠና እንዲወስዱ ማድረግ እንችላለን። የታሪክ፣ የፖለቲካና የሥነ መራር  እውቀት የሌላቸውን እውቀቱን በቀላሉ እንዲላበሱ ማድረግ እንችላለን። የቀለም ትምህርት ለሌላቸው እዚሁ በረሃ ውስጥ ከየትኛውም የሀገራችን ት/ቤት ወይም ኮሌጅ በላይ ጥራቱ የጠበቀ ትምህርት መስጠት እንችላለን። ይህን ሁሉ  ማድረግ መቻላችን ግን ጎጂ ባህሎቻችን ከሚያስከትሉብን ውድቀት አያተርፉንም። ብዙ የወታደራዊ ሳይንስ እውቀት የነበራቸው፣ ወታደራዊ መሪዎች የያዘ መንግሥት አነስተኛ ወታደራዊ እውቀትና  ልምድ ባላቸው ግለሰቦችና መሃይሞች በሚመራ ጦር ሲፈታ አይተናል። በተለያዩ  የእውቀት ዘርፎች ሊቃውንት ሊባሉና  እንዲሁም በእድሜና  በተመክሮ  በከበዱ ምሁራን የታጨቁ ድርጅቶች ወያኔን የመሰለ የሀገር ተምች አስቀምጠው እንደ ባለጌ ኮማሪት በአደባባይ ሲዘላላፉ፣ ሲዘራጠጡ፣  ራሳቸውን አዋርደው የኛ  ናቸው ያላቸውን ሕዝብ ሲያዋርዱ አይተናል።  

ለድርጅቶች መዳከም ወይም መውደም ምክንያቶቹ  ክህደት፣ ጭቅጭቅ፣ መጠላለፍ የመሳሰሉት በሰዎች መሃከል መልካም ግንኙነት እንዳይኖር እንቅፋት የሆኑ ባህሪዎች ብቻ አይደሉም ። አድርባይነት፣ አጎብዳጅነት፣ ዝርክርክነት፣ ተጨንቆና  ተጠቦ አለማቀድ፣ የግብር ይውጣ አሰራር ፣ጀብደኛነትና ወዘተ የመሳሰሉት ባህሎቻችን ለድርጅቶች መዳከም መውደም የራሳቸው አስተዋጸኦ አድርገዋል።እኛስ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል አባላት እስካሁን በሀገራችን ውስጥ ከበቀሉት ድርጅቶች የተሻለ እጣና ታሪክ እንዲኖረን ምን ማድረግ አለብን? መልሱ በሌሎች  ጥያቄዎችና ምለሾች የሚገኝ ነው። በቅድሚያ ራሳችንን መጠየቅ የሚገባን፣  ቀደም ብለን የጠቀስናቸውና  ሌሎችም ጎጂ እና  አፍራሽ ባህርያት በተለያየ ደረጃም ቢሆን በውስጣችን እንዳሉ እንገነዘባለን ወይ? ለዚህ ጥያቄ የሉም የሚል ምላሽ መስጠት አንችልም። ምንም ያህል ብጹእና  የበቃን ብንሆንም ህጸጽና ድክመት አያጡንም። የሰው መሆን አንዱ ትርጉሙ የሚሳሳት የሚያጠፋ የሚል ነውና። እነዚህ ጎጂ የምንላቸው የግለሰቦች የቡድኖች ባህርያትና  ልምዶች   ምንድን ናቸው? እውን በደንብ እናውቃቸዋለን? ለምንድነው እነዚህ ባህርያት ልምዶች በማኅበራችንና  በሀገራችን ውስጥ ከሌላው ማኅበረሰብና ሀገር ውስጥ ከሚታየው በላይ ሥር ሰደውና ደንድነው የሚገኙት? የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ከዚህ የባህልና የባህርይ 
ነቀርሳ ለማምለጥ ምን ማድረግ አለበት? ለመሆኑ እነዚህን  ጎጂ የምንላቸውን ባህርያትና   ልምዶች በደንብ  እናውቃቸዋለን? 

3.  የግለሰብ እና የቡድን ጎጂ ባህሎችና ባህርያት የምንላቸው የትኛዎቹ  ናቸው?

የእነዚህ ባህሎችና  ባህርያት ዝርዝር ብዙ ሊሆን ይችላል። በሁሉም ላይ ስምምነት ላይኖር ይችላል። ብዙዎቹ ተመሳሳይነት ተወራራሽነት ሊኖራቸው ይችላል። በአንድነት ሰብሰበን ብናቀርባቸው በመሃከላቸው ያለውን ረቂቅ ልዩነት ማየት ያስቸግረናል። አብዛናዎቹ ከግለሰብ ባህሪዎች ጋር የተሳሰሩ ሲሆኑ ጥቂቶቹ ደግሞ  ከድርጅቶች ጎጂ ባህርያት ጋር  የተሳሰሩ  ናቸው። የምንችለውን ያህል ዘርዝረን ማቅረቡ ይጠቅማል ብለን ስላሰብን እንደሚከተለው እናቀርባቸዋለን። 

1.  ገደብ የሌለው ተጠራጣሪነት፤ 
2.  ታማኝነት የሌለው ሆኖ መገኘት፤ 
3.  ንቀት፤ 
4.  ከሚገባው በላይ ለስም ለክብር መጨነቅ፤ 
5.  ትእግስት ማጣት፣ ቱግ ባይነት፤ 
6.  ተነጫናጭነት፤ 
7.  ውሸታምነት፤ 
8.  ሁሉን አውቃለሁ ባይነት፤ 
9.  ኩርፊያ፤ 
10.  ንትርክ፣ ጭቅጭቅ፣ እሰጣገባ፤ 
11.  ስድብ፣ ጠብ፣ አምባጓሮ፤ 
12.  እኔ ያልኩት የፈለግሁት ካልሆነ ባይነት፤ 
13.  ተላታሚነት፣ በአካል ጓድን ለመጉዳት መሽቀዳደም፤ 
14.  ብልግናና ጋጠወጥነት የተሞላውን ባህርይ ከደፋርነትና ከቆራጥነት ጋር ማምታት፤ 
15.  ጥላቻ፤ 
16.  ጉልበተኛ፣ አስፈራሪ ፣አዋካቢ ሆኖ መገኘት፤ 
17.  የመንፈስ ጩቅነት፤ 
18.  አዋራጅነት፣ ቅስም ሰባሪነት፤ 
19.  ወሬኛነት፣ አሉባልተኛነት ፤ 
20.  ሴረኛነት፣ ተንኮለኛነት፤ 
21.  ከኔ  በላይ ነፋስ አመለካከት፣ከጓዶቼ  በፊት እኔ  ብቻ፤  
22.  አድሎኛነት፣ አንድን ቡድን ወይም ግለሰብን ለይቶ ጥቃት ማድረስ ፣ በመንፈስ በአካል በጥቅም በመብት መጉዳት፤ 
23. ሁሌም መጥፎ መጥፎውን ማየት፣ ሊሆን የሚችለውን በጎ ነገር ትቶ ላይሆን የሚችለውን መጥፎ  ነገር እስከማሰብ መሄድ፤ 
24.  ራስን አሳንሶ  ማየት፣ እኔ ትልልቅ ነገሮች ለማከናወን  አልተፈጠርኩም፣ እሱ የሌሎች ስራ  ነው ማለት፤ 
25.  የግልና የድርጅት ንብረትን አለመንከባከብ፤ 
26.  አንፋቃቂነት፤  
27.   ድጋፍና እርዳታ ለሚያስፈልገው ድጋፍን እርዳታን መከልከል፤ 
28.  ትልቁን የጋራ የሆነውን ነገር ረስቶ የግል ጉልትን፣ ግቢን፣ ቤትን መከላከል። ይህ የግል ጉልት  ስሜት፣ ፍላጎት፣ ዝንባሌን መከላከል ሊሆን ይችላል፤ 
29.   የማይገባንን ዝና ክብር ስም መውሰድ፣ በጋራ ለተሰራ ወይም  በሌላ ግለሰብ ለተሰራ ሥራ፣  ክንውን፣ ግኝት፣ ሃሳብና ወዘተ በመውሰድ ሊሆን ይችላል፤ 
30.  የአንድን ሰው አቋም አጣሞ ማቅረብ። አንድ ሰው ሲናገር አለማዳመጥ። ሰውየው ተናግሮ  ሲጨርስ ተራ ጠብቆ የራስን ከውይይቱ ጋር ተያያዥነት ይኑረው አይኑረው ንግግር ብቻ ለማድረግ መዘጋጀት። ሳያዳምጡ የተባለውን ጭብጥ ሳይዙ መልስ ለመስጠት መሞከር፤ 
31.  መልእክቱን ሳይሆን መልእክተኛው  መቀጥቀጥ ወይ በመልክተኛው ላይ መተኮስ። የአንድን ሰው አመለካከት ወይም ሃሳብ እንደመተቸት   ሃሳቡ ያቀረበውን ሰው ከሃሳቡ ጋር ግንኙነት በሌለው መንገድ መቀጥቀጥ። አንድ ሃሳብ ከየትም ይምጣ ማንም ያምጣው  ሃሳቡ ላይ ብቻ   ትኩረት ሰጥቶ የሃሳቡን ዋጋ በሚገባ አለመመዘን፤ 
32.  ሌሎች በሚገባ ያቀረቡትን ተደጋጋሚ ሃሳብ እንደ አዲስ ሃሳብ አድርጎ መልሶ ያንኑ ማቅረብ ፤  
33.   አቅምና  ችሎታን  እያወቁ በማይችሉት የኃላፊነት የሥራ ቦታ ዝም ብሎ መቀመጥ፤ 
34.  የማይገባ ሹመት እድገት መፈለግ፤ 
35.   ለጥራት ደንታ የሌለው መሆን፤ 
36.  ለዝርዝር ጥቃቅን ለሆኑ ነገሮች በቂ ትኩረት አለመስጠት፤ 
37.  የግል ችግርና ጉዳይ  የሥራ ቅልጥፍናን የኃላፊነት ስሜትን እስኪያስረሳ ድረስ ልቅ መልቀቅ፤ 
38.  የራስ ወይም የቡድን ስሜቶችን፣ አመለካከቶችን፣ እምነትን፣ ዘርን ወዘተ በተለየ መንገድ መመልከት ለሌላው ሰው ክብር፣ ትእግስት፣ የሌለው የሚያጣጥል ሆኖ  መገኘት፤  
39.  ሥርዓት ለማበጀት ፈጽሞ አለመፈለግ፣ በደንብ በሕግ በሥርዓት ለመሄድ አለመፍቀድ፤ 
40.  ከሚገባው በላይ ለሥርዓትና ደንብ እንደባሪያ ተገዥ መሆን፤ 
41.  ተነሳሽነት ማጣት፣ የጠባቂነት መንፈስ፤ 
42.  የሚነገረውን እንጂ ቁምነገሩን አለማድመጥ፤ 
43.  ሚስጥር መቋጠር አለመቻል፤ 
44.  ሥራ ሰሪ መስሎ  መታየት/ አስመሳይ ሰራተኛነት/፤ 
45.  ለግል ጥሩ በሆነውና  ለድርጅት ጥሩ በሆነው መሃል ውዥንብር ውስጥ መውደቅ፤ 
46.  መጥፎ መጥፎ  ወሬዎችንና  ዜናዎችን ብቻ  ማናፈስ፤ 
47.  ግዜ በከንቱ ማባከን፤ 
48.  ሁሌ ስህተት እየፈጸሙ እግዚአብሄርን ወይም ጓዶችን ምስክርነት መጥራት። ፈጣሪ ምስክሬ  ነው። እገሌ ምስክሬ  ነው ወዘተ፤ 
49.  ለመጋፈጥ አለመፈለግ፣ ሰውን  ሁኔታዎችን ሊሆን ይችላል፤ 
50.  ተገቢ ያልሆነ ከሚያስፈልገው ደረጃ ያለፈ ለውጥ መፍራት፤ 
51.  ከሚገባው በላይ ፍጹምነትና ትክክለኛነትን መፈለግ፣  ከሚገባው በላይ ስህተት ላላመስራት መጨነቅና በስጋት ታስሮ አለመስራት፤ 
52.  በወቅቱ በተደረሰበት  የብቃት፣ ችሎታ፣ የድልና የሥልጣን ደረጃ ከሚገባው በላይ ረክቶ በእብሪት መወጠር ፤ 
53.  ከሚገባው በላይ መኩራራት መንጠባረር፤ 
54.  አላስፈላጊ የሆነ ሁሉን ነገር የበላይ አካል እንዲወሥነው እንዲሰራው ማሰብና  መተግበር፤  
55.  ሲሰሩ ከመታየት በስተቀር ሥራውን በሚገባ እንዲሰራ አስቦ  አለመሥራት፤ 
56.  አላስፈጊ የሆነ ጥድፊያ ላይ ማተኮር፤ 
57.  ምሁራዊ ዘረፈ ብዙነት ማጣት፤ 
58.  እኩል እድል ከመስጠት ፈንታ እኩል ውጤት ላይ ማተኮር። እያንዳንዱ በተሰጠው እድል ለሚያበረክተው ግልጋሎት እውቅና አለመስጠት፤ 
59.  ከአቅም በላይ ቃል መግባትና በተግባር አንሶ  መገኘት፣ በቃልና  በተግባር መሃከል ሰፊ ልዩ ነት ማሳየት፣ ግብዝነት፤ 
60.   ጉራ፤ 
61.  ባህሪያቸው አስቸጋሪ የሆኑ ሰዎችን እሹሩሩ በማለት ድርጅቱና  ሌሎች ስራ መስራት የሚፈልጉ አባላት ሥራቸውን እንዳይሰሩ፣ ሥነምግባር እንዲሸረሸረ፣ የስራ ባህል በድርጅት ውስጥ እንዲቦረቦር ማድረግ፤ 
62.  ትንተና ማብዛት፣  በትንተና ሽባ  ሆኖ  ወደ ተግባር መግባት አለመቻል፤ 
63.   ድርጅቱ ምን ይፈልጋል ሳይሆን በአድርባይነት እየተነዱ ሰው ሁሉ ምን ይፈልጋል በሚል በግብር ይውጣ ሥራን መሥራት፤ 
64.  ጓዳዊ ግንኙነት የሌለው ወይም መፍጠር የማይችል ሆኖ መገኘት፣ ሲቀርቡት የሚርቅ፣ ሲያፈቅሩት የሚጠላ፣ ሲስሙት የሚናከስ፤ 
65.  በድርጅቱ ውስጥ ቀድሞ ሲሰራበት ወይም ሌሎች ሲሰሩበት የነበረን የቆየ ሃሳብ በየግዜው እንደ አዲስ ማቅረብ፤ 
66.  ከሚገባው በላይ ውጤት ተኮር ሆኖ  መገኘት፣ ከውጤት ውጭ ለተገኙ መልካም ክንውኖች ቦታ አለመስጠት፣ ከውድቀት ለተገኙ ትምርቶች ቦታ አለመስጠት፤ 
67.  ዝግ ሩቅ ሌሎች የማይደሩስበት የማያውቁት ድፍን ሰው ሆኖ መገኘት፤ 
68.  ለሁሉም የሰዎች ድርጊቶች፣ ንግግሮችና ሃሳቦች ግለሰቦቹን ውስጣዊና  ድብቅ ዓላማ እንዳላቸው ዝም ብሎ መጠርጠር፣ ድብቅ እምነትና ፍላጎት አላቸው በሚል መላ መምታትና  መጠንቆል፣  የራስን እምነትና  ፍላጎት መለጠፍ፤ 
69.  ሃብትንና  መረጃን መደበቅ። ሃብት የሰው ኃይል ገንዘብ ቁሳቁስ እውቀት ሙያ  ሊሆን ይችላል፤  
70.   ትርጉም የማይሰጥ መዋቅራዊ ድርጅታዊ ለውጥ ማድረግ ሁሉንም ሰው በአንድ አይነት መንገድ ማስተናገድ፣ አቅምን እድሜን ችሎታን የአይምሮ ና የአካል ብቃትን እምነትን ባህልን ግምት ውስጥ ያላስገባ  ሁሉንም በአንድ አይነት መንገድ ስሱ ሳይሆኑ መመልከት ፤ 
71.  የሰዎችን ችሎታና አቅም ግምት ውስጥ ያላስገባ ኮታ ለማሟላት ብቻ  ሲባል ለሰዎች ኃላፊነት መስጠት፤ 



4.  ሥር የሰደዱ የጎጂ ባህሪዎቻችን፣ ልምዶቻችንና ባህሎቻችን ምክንያቶች ምንድን ናቸው? 

ይህን ጥያቄ እጅግ ግዙፍ ነው። ምክንያቱም የአንድ ሰው ባህርይ፣ልምድ ወይም ባህል የሚያንጹት ጉዳዮች ብዙ ናቸውና። ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ የመጡ ልምዶችና ባህሎች ተጽእኖ  ሊያደርጉበት ይችላሉ። ቤተሰቦቹ፣ ማኅበረሰቡ፣ መንግሥታዊ ና የትምህርት ሥርዓቱ፣ ሃይማኖቱ የአደገበትና የኖረበት አካባቢ ተፈጥሮ፣ የእድሜ  እኩዮቹ ወዘተ ተጽእኖ ሊያደርጉበት ይችላሉ። በሌላ በኩል ደግሞ  ግለሰቡ ለማንም ያልነገራቸው በውስጡ አምቆ የየያዛቸው የራሱ ልዩ  የሆኑ የሕይወት ተመክሮች ተጽእኖ ሊያደርጉበት ይችላሉ። አንዳንዶቹ ተመክሮዎች በረጅም ግዜ ተደጋጋሚ ሂደት ተጽእኖ  ማድረግ የሚችሉ ሲሆኑ አንዳንዶቹ ግን የአንድ ግዜ ብቻ ገጠመኝ ሊሆኑ ይችላሉ። የረጅም ግዜ ሂደት ላልነው የሚከተለው ምሳሌ ሊገልጠው ይችላል። በህጻንነቱ እናቱ ሞታበት እጅግ ጨካኝ በሆነች እንጀራ እናት ለረጅም ግዜ  አሰቃቂ በደል የደረሰበት ወይም በየምሽቱ እየሰከረ እየመጣ በሰበብ አስባቡ ቤተሰቡን  የሚያሰቃይ አባት አሳድጎት ይሆናል።  

የደግነትና የርህሩነት ባህርይ ይዞ  ያደገ ሰው በአንድ ወቅት በደረሰበት ከፍተኛ ጭካኔ  የተሞላ ድርጊት የተነሳ ወደ እጅግ ጨካኝ ሰው ሊቀየር ይችላል። በአንድ ወቅት  አንድ ነገር እጅግ በሚያስፈራ መንገድ ያስደነገጠው ህጻን የፈሪነት ባህርይ ተላብሶ ሊያድግ ይችላል። ሰው ውስብስብ ፍጥረት ስለሆነ ማንነቱን፣ ባህርያቱን  የቀረጹት እነዚህ ነገሮች ናቸው ብሎ መናገር ቀላል አይደለም። 2+2 ይሆናል 4 እንደሚለው የሂሳብ ስሌት አንድን ሰው አጭበርባሪ፣ አድርባይ፣ ንፉግ፣ ጨካኝ ወይም ፈሪ የሆንከው በነዚህ ምክንያቶች ነው ብሎ  እርግጠኛ  ሆኖ  መናገር አይቻልም። አንድን ሰው ለሁላችንም የጋራ የሆኑ ጉዳዮች ማለትም ያደግንባቸው ትምህርታዊ ሃይማኖታዊ መንግሥታዊ ሥርዓቶች፣ እንደሁላችንም ተጽእኖ አድርገው ማንነቱን ሊቀርጹት ይችላሉ። ከአንድ ወንዝ ስለተቀዳን ማለትም  ማኅበረሰባችን፣ መንግሥታዊ ሥርዓታችን፣ እምነታችን ታሪካችን አንድ ስለሆነ  ወይም ስለሚቀራረብ፣ በብዙ ባህሪዎቻችን ልንመሳሰል እንችላለን። በሌላ  በኩል ደግሞ  እያንዳንዳችን እራሳችን የቻልን ፍጥረቶች ነን። የመመርመር የማሰላሰል ተፈጥሮዎች ስላሉን የጋራ ተመክሮዎቻችን የምንተረጉምበት የራሳችን መነጽር ይኖረናል።  አንድ አይነት አስተዳደግ ካላቸው ሰዎች መሃል አንዱ ግፍ ሲበዛበት ያምጻል። ሌላው ግፍ ሲበዛበት የበለጠ አጎብድዶ ለመኖር ይወስናል፡፡ ለምን ለሚለው ጥያቄ በቀላሉ መልስ መስጠት አይቻልም። ሃቁ ግን ሁለት ሰዎች አንድ አይነት አስተዳደግ  ስላላቸው ብቻ አንድ አይነት ሰዎች ሆነው እንደማይወጡ  ነው።  

የጋራ ሆነ ወይም  የግል ጎጂ ባህርያትና  ባህሎች ምንጭ ጥናት ጥልቅ የሆነ የታሪክ፣ የሥነልቦናና የሥነ ማኅበረሰብ እውቀት የሚጠይቅ ነው።ከዚህ ቀጥሎ  የሚቀርበው ሃተታ ላነሳነው ግዙፍ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት አይደለም። አይቻልምም። ሙከራችን እያንዳንዱ የግንቦት 7  ሕዝባዊ ሃይል አባል የራሱን  ባህሪዎች ሊፈትሽባቸው የሚችሉ ፍንጮችን፣ መኮርኮሪያዎችን ማቀበል ብቻ ነው። ጎጂ ባህርያትና  ባህል በማለት የዘረዘርናቸውን ነጥቦች አንዳንዶቹን በተናጠል አንዳንዶቹን በቡድን እያደረግን የነዚህ ባህርይዎችና  ባህሎች መነሻ ምንጭ ምን ሊሆን እንደሚችል የሚመስለንን መግለጫ እናቀርባለን። ቀደም ብለን እንዳልነው የሚቀርበው መግለጫ እንደ ተሟላ መልስ መታየት የለበትም። ውይይት መጫሪያና ራስን በሚገባ ለመፈተሻ ብቻ የቀረበ  ተደርጎ  መወሰድ ይኖርበታል። 


ገደብ የሌለው ተጠራጣሪነት  

ገደብ የሌለው ተጠራጠሪነት ከሚለው ጎጂ ባህርይ  እንጀምራለም።  ማኅበረሰባችን እጅግ ተጠራጣሪ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ የተጠራጣሪነት ባህል ረጅም እድሜ አለው። ይህ የተጠራጣሪነት ባህል በሁሉም የሀገራቱ ክልል በአንድ ግዜ በአንድ አይነት ጥልቀት የተስፋፋ አይደለም።እንደታሪካችን፣እንደማኅበራዊ አኗኗራችን፣ አስተዳደራዊ ሥርዓታችን፣ የሃይማኖት አስተምህሮታችን፣ ከአካባቢ አካባቢ፣ ከማኅበረሰብ ማኅበረሰብ ይለያይ ይሆናል። ደረጃ  በደረጃ በየግዜው እየተስፋፋ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ባህርይ ሆኗል ማለት እንችላለን።  እዚህ ላይ የምናተኩረው ብዙዎቻችንን የሚመለከቱ ጭብጦች ላይ ይሆናል። 

ማለቂያ  የሌለው ከውጭ ወራሪዎች ጋር የተካሄዱ በርካታ ጦርነቶችና እነዚህ ጋር ተያይዘው የመጡ እልቂቶች መፈናቀሎች ማንንም የውጭ ሃገር  ሰው በተለይ አረብንና  ነጭን  እንዲሁም እምነቱ የተለየ የሚመስለንን ሰው እንድጠራጠር አድርጎናል። እንደ ሀገር እንደ ሕዝብ እንደ መንግሥት የውጭ የሆነን ነገር እንጠራጠራለን። ለኢትዮጵያ  በጎ  የሚመኝ መንግሥት ይኖራል ብለን አናስበም። የውጭ ፖሊሲዎቻችን ለረጅም ዘመን ከዚህ ጥርጣሬ  ጋር ተያይዞ  የተቀረጸ ነው። ሁሉም ሊያጠቃን እንደሚፈልግ አድርገን ነው የምናየው። ይህ ደግሞ በተወሰነ  ደረጃ  እውነትነት አለው። ከውጭ ወረራ ቀጥሎ  ማኅበረሰባችን ማለቂያ  በሌላቸው የውስጥ ጦርነቶች፣ የርስ በርስ ግጭቶች ተጠምዶ  እስካለንበት ዘመን ደርሷል። እነዚህ ጦርነቶችም ሞትን፣ መዘረፍን፣ መፈናቀልን መፈንገልን፣ መገፈፍን በስፋት በማኅበረሰባችን ውስጥ ያስከተሉ ናቸው። ግጭቱ እስከ አውራጃ  ወረዳ ድረስ ይወርዳል። እንኳን በሀገር አቀፍ ደረጃ በመንደር ደረጃ መተማማን የለም። የአንዱ ወረዳ ሕዝብ  የሌላውን አያምን። ዛሬ ከአንዱ ንጉስ ጋር ወይም  መስፍን ጋር የነበረው  ነገ  በሹመት በሃብት በጋብቻ  ተደልሎ  ባላንጣ  ሆኖ  የሚገዛውን ሕዝብ አስከትሎ  ይዘምትብሃል። መገበር ማስገበር፣ መክዳት ተመልሶ  መግባት፣ እንዲሁ እንደአዙሪት ሲያዞሩት የኖረ ማኅበረሰብ ስለሆነ በማኅበረሰብ ደረጃ መጠራጠር የተለመደ ነው። ዘርን ጎሳን እምነትን   ጠርቶ  እነሱ አይታመኑም። እነሱን ማመን ቀብሮ ነው የሚል አባባል የተለመደ ነው። አንዱ ባንዱ ላይ ይለዋል። 

ለረጅም ግዜ  የዘለቀው አስተዳደራዊ ሥርዓት ገበሬን በመዝረፍ በመቀማት ላይ የተመሠረተ ነበር። ዛሬም አልተቀየረም። መንግሥትንና  የመንግሥት ባላስልጣናትን መጠርጠር የተለመደ  ነው። መንግስትና  ባለስልጣናቱ ለጥፋትና  ለዘረፋ  እንጅ ለበጎ  ነገር አይፈልጉንም ብሎ  ሕዝብ ያስባል። ጌቶች መጥተው ማር፣ ሙክት፣ አጃ፣ ጌሾ   አምጣ ይላሉ። ወታደሩ መጥቶ  ነጭ ኑግ፣ ጥቁር ወተት ውለድ ይላል። ሚስቱን “ ይች እህትህ እንዴት ታምራለቸ “ ቁንጅናዋን አድንቆ ከገዛ ባሏ ፊት ይደፍራታል። ደስ ሲለውም ይዟት ይሄዳል።የሰው ልጅም እንደከብት ይዘረፋል። ለጦርነት ወጣቶች ጎልማሶች ይዘረፋሉ። ታዲያ  ወታደር መጣ የመንግሥት ተወካይ መጣ ሲባል ጥርጥሬ ይሰፍናል። ወታደሮችና ጌቶች ያለህን የእህል ብዛትና የደበቅበትን ቦታ እንዳያውቁ፣ ማርና  ቅቤ የቀበርክበትን ጉርጓድ እንዳይደርሱበት ጎረቤትህም ማዋቅ ስለሌለበት ከጎረቤትህ ተደብቀህ ተጠንቅቀህ ትደብቃለህ። ጎረቤቴ  አይቶኝ ይሆን አይሆን እያለክ ትጠራጠለህ። በአጋጣሚ የደበቅክውን ይደርስበት ይሆን በሚል ስጋት 
ጎረቤትህን ትጠረጥራለህ።  

የመሬት ስሪቱ እንዲሁ በወረራ የሚያዝ፣ በተወላጅነት የመካፈልና  የማካፈል መብትና  ግዴታ የነበረበት ነበር።  በባእድ የመወረር  ስጋት ብቻ  አይደለም  የነበረው ዝምድና አለኝ ያለን ሁሉ መሬት ማካፈልን የግድ ይላል። የመሬት ክርክር ሙግት ግጭት የተስፋፋ ነበር። መሬት ይገባኛል ባዩ ብዙ ነው። ባላንጣ  ብዙ ነው።  ዘመድ ቤተሰብ ሆኖ  ይጋብዝሃል። ብላልኝ ጠጣልኝ ይልሃል። ለመሬት ሲል በምግቡና በመጠጡ ውስጥ መርዝ ጨምሮ  ይገልሃል። ሽባ ያደርግሃል። ከፍተኛ  የአካል ጉዳት ያደርስብሃል። ወገን አይታመንም። እንጀራ ቆርሶ  ወጥ ጠቅሶ  ካልቀመስ አንተ  አትበላም። ያቀረበልህን ጠላ ወይም ጠጅ እጁ ላይ ፈሰስ አድርጎ  ቀድሞ ካልቀመሰው አንተ አትጠጣም። በድንበር ገፋህኝ የሚቀሰቅሰው ጭቅጭቅ ወደ ስድብ አምቧጓሮ ይቀየራል። ተሰደብኩ ተመታሁ ያለው የበቀል እርምጃ  ይወስዳል። ደም መቃባት ይመጣል። ዘር ማንዘር እየተቆጠረ መፋጀት ነው። የጥርጣሬን ጠቀሜታ ለመግለጽ  

ግደሉ ግደሉ ሰው መግደል ይበጃል 
ሰው ያልገደለ ሰው ሲሄድ ያንጎላጃል። ተብሎ ይዘፈናል። 
  
ሰው ገድሎ  በጥርጣሬ እንደሚዳቋ እየደነበሩ እንደ ቆቅ እየበረገጉ መኖር የሚጥም ሕይወት ሆኖ  ስንኝ የተቋጠረለት ጉዳይ ሆኗል። ኅብረተሰቡ የደረሰበትን የሥነልቦና ቀውስ ከእነዚህ ስንኞች በላይ መግለጥ አይቻልም። 

 ይህ ባህል የመሬት ስሪት ሥርዓቱ ከጠፋም ከ50 አመት በኋላም በገጠር ብቻ አይደለም በከተማም ይሠራበታል። ቀመስ አርጎ ገበታ  ማቅረብ ዛሬም ይሰራበታል። ሁሉም፣ አንዱ ሌላውን የሚጠረጠርበት አጠቃላይ ሁኔታ  በሰፈነበት ማኅበራዊና መንግሥታዊ ሥርዓት ለሽህ አመታት  ተኖረ። መንግሥት አይታመንም። የመንግሥት ባላሟል አይታመንም። ጎረቤት አይታመንም። ዘመድ ወገን አይታመንም። ያልጠረጠረ ተመነጠረ። ሰውን ማማን ቀብሮ ነው። ጠርጥር፣ ካደረ ገንፎ  አይጠፋም ስንጥር፣ የሚሉ አባባሎችና  ሌሎችም የመጠርጠር ትክክለኛነት በማኅበሩ አባላት ሥነ ልቦና  ውስጥ ሲያስፋፉ  ኑረዋል።  

የመሳፍንቱ ዘመንና  የመሳፍንቱ የርስ በርስ ግጭት ካባቃ በኋላም ኢትዮጵያ የውጭ ወረራ  ያልተለያት ሀገር ናት። ይህ የእንግሊዞች፣ የቱርኮች፣ የግብጾች፣ የጣሊያኖች፣ የሱማሌዎች ወረራ፣  የቅርቡ የኢትዮ ኤርትራያ ጦርነት የቅርብና  የሩቅ ሃገሮችን መጠርጠራችንን እንድንቀጥል ያደረገ ነው። ሁለተኛው የጣልያን ወረራ  ኅብረተሰቡን በከሃዲ ወይም በባንዳና  በአርበኛ ከፍሎ፣የዘርና  የእምነት  ልዩነቶች አራግቦ፣አለመተማመን ጥርጣሬን የበለጠ ቆስቁሶ  ነው ያለፈው።  

ወራሪዎችን በጀግንነት እንደመመከታችን ሁሉ፣ ነገስታት በንጉሶቻቸው በራሶቻቸው በፊትአውራሪዎቻቸው ሲከዱ አይተናል። የክህደቱ ደረጃ ይለያይ እንጅ ይጠቅመኛል ብሎ  ካሰበ ትልቁም ትንሹም ለመክዳት አይመለስም። ቴዎድሮስ በዮሃንስ፣ ዮሃንስ በምኒሊክ፣ ምኒሊክ በመንገሻ ወዘተ። መአከላዊ መንግሥት  ተጠናክሮ   የመንግሥትና የሕዝብ ግንኙነት መልክ ይዟል በሚባልባቸው ዘመናት የመሬት ስሪቱ እንደ መሳፍንቱ ዘመን መቀጠሉ የሥርዓቱን የገዥዎችን ሥልጣን ጥቅም የሚያስከብረው የነጭ ለባሽ፣ የጆሮ  ጠቢ፣ የስለላ  መዋቅር መስፋፋቱ  በሰዎች መሃከል አለመተማመኑ እንደነበረ ቀጥሏል።  በቅርብ ግዜም ቢሆን ይህ የመከዳዳት  ባህል በጦር ጄነራሎቹ በፖለቲካ  ሰዎች አካባቢ እንደተፈጸመ ነው። የመንግስቱ ነዋይ፣  የደርግ  ዘመንና  የወያኔ ዘመን   ጸረ መንግስት  የሆኑ የአመጽ ሴራዎች የከሸፉት   በመከዳዳት   ነው። በቅንጅትና  በህብረት ሰዎች ፣ በራሳቸው በቅንጅትና በህብረት ድርጅቶች ውስጥ የተከሰተው ችግር ከመከዳዳት ጋር ይያያዛል።  

በማኅበረሰባችን ውስጥ ለአጭር  ግዜም ቢሆን ከጥርጣሬ በተወሰነ  ደረጃ  ነፃ የሆነ የማኅበረስብ ክፍል መፍጠር ተጀምሮ  የነበረው በተማረው የሰው ኃይል መሃል ነበር። የምሁሩና የተማሪው ክፍል ዘር ሳይለይ እርሱ በርሱ ሳይፈራራና ሳይጠራጠር በማኅበረሰባችን ታስቦ  የማያውቅ ብዙ ሽህ ሰዎችን  በሀገርና በውጭ ሀገር በጋራ አሰባስቦ  መንግሥትና  ሥርዓት ለመቀየር የሚያስችል ንቅናቄ መፍጠር ችሎ  ነበር። ለዚህ ለውጥ መፈጠር ምሁሩና ተማሪው የገበየው ዘመናዊ እውቀት የራሱ ድርሻ ነበረው።  የተማሪው ከወጣትነት የመጣ ንጽህና በጥቅም በሥልጣን ወዘተ ሊያጋጭ የሚችል ነገር በመሃሉ አለመኖሩ ሌላው ምክንያት ነበር።  ትምህርት ቤት ተማሪዎች በብዛት መገናኘት የሚችሉበት ቦታ መሆኑ ጥርጣሬን በመቀነስ መቀራረብና መተዋወቅ በማሳደግ  ሁሉም በጋራ መምከር  የሚችሉበትን ሁኔታ በማመቻቸት የራሱ አስተዋጽኦ አድርጓል። ለ1966ቱ አብዮት መፈንዳት ሊጠቀሱ ከሚገባቸው ዋና  ምክንያቶች መሃል ከጥርጣሬ በአንጻራዊነት ነፃ  የሆነ  ትውልድ መምጣት መቻሉ አንዱ ነው። ይህ እርሱ በርሱ የሚተማማን ትውልድ ግን የጀመረውን እንዳይጨርስ ያደረገው ራሱን ከግለሰቦች፣ ከቡድኖችና  ከድርጅቶች የርስበርስ ጥርጣሬና መካካድ ነፃ ማድረግ ባላመቻሉ ነው። ጥርጣሬና መካካድ ብቻ አይደለም። ያ ትውልድ ተመልሶ እራሱ በማኅበረሰቡ ውስጥ ሥር ከሰደዱ ጎጂ ባህርያት ነጻ ባላመሆኑ እንኳን ሕዝብንና  ሀገርን ሊታደግ፣ ነጻ ሊያወጣ እራሱን ከአጠቃላይ ውድመት ማትረፍ ሳይችል ቀርቷል። 
አብዮቱ ንጉሱን በልቶ ለሽህ አመታት የጥርጣሬ  ምንጭ የሆነው የመሬት ስሪት አጥፍቶ  ሲያበቃ ይዞት የመጣው መህበረሰብ ይበልጥኑ ርስ በርሱ ተጠራጣሪ ሆነ። ደርግ በራሱ ውስጥና ከሌሎች ተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር ተላተመ።  ተቃዋሚዎችም ከደርግ ጋር፣ ርስበርሳቸውና  በራሳቸው ውስጥ የከፈቱት የመበላላትና  የእልቂት  ጦርነት ተቀጣጠለ። ሁሉም ድርጅቶች ያሰማሯቸው  ስውር ነፍሰ ገዳዮችና ሰላዮች ብዛት ሰው እንኳን ጓደኛውንና ጎረቤቱን የራሱን ጥላ ማመን ከማይችለበት ደረጃ አደረሰው።  እናት አባት  ባል ሚስት ወንድም እህት ልጆች እርስ በርሳቸው የማይተማመኑበትና እርስ በርስ  የሚጠራጠሩበት  የከፋ ሁኔታ  እንዲመጣ  አደረገ። ቀደም ባሉት  ዘመናት  ማኅበረሰባችን የፈለገውን  ያህል በጥርጣሬ  የተሞላ  ቢሆንም እናትና  አባት ልጆቻቸውን፣ ባል ሚስቱን አንዱ በሌላው ላይ የሚሰልሉ፣ በሌላ ባእድ አካል ተልከው ሊገድሉን ይችላሉ ብለው አስበውት አልመውት አያውቁም ነበር። አብዮቱ ግን ይህ ሁሉ ጉድ የመጣበት ዘመን ሆነ።  

አብዮቱ በመሬት ስሪቱ ላይ ያመጣው ለውጥ ገበሬውን ከባላባቱ ጢሰኛነት ወደ መንግስት ጢሰኛነት ቀየረው እንጂ ከመሬት ስሪቱ ጋር የቆየውን ጥርጣሬ አላስወገደውም። መሬት የሚከፋፈፈለው በደርግና በወያኔ ካድሬዎች በመሆኑ ለእነዚህ ስርአቶች ታማኝ ሆኖ  አለመገኘት መዘዙ በመሬት ክፍያው መበደል ወይም ፈጽሞ  መሬት እስካላማግኘት ሊደርስ ቻለ። አንዱ  ገበሬ በሌላው ገበሬ  ላይ እንዲሰልል የሚያስችል የፖለቲካ አደረጃጀት ተበጀ። ዛሬም እንደትናንቱ መንግስት ካዝናው ሲጎድል፣ ተቀናቃኝና ጠላት ሲነሳበት አሁንም የሚዘረፈው የፈረደበትን ደሃ ገበሬ ልጆችና ጎተራ ነው። ወታደር መጣ ካድሬ መጣ ያው እንደጥንቱ የሚታዩት በጥርጣሬ ነው።  የአንዱ የአብዮቱና የተከተሉት ዘመናት  ቅርስ የማኅበረሰቡን አንድነት የበለጠ አናግቶ ጥርጣሬን በማኅበረሰቡ ውስጥ ጥልቀት እንዲኖረው ማድረግ ነው።  

ወያኔ  እጅግ አናሳ የሆነ  የኅብረተሰብ ክፍል ተወካይ ሆኖ  ያለምንም ተቃውሞ  ሥልጣን ሊይዝና  ሊጠናከር የቻለው በአብዮቱ ወቅትና ከዛም  በኋላ ሰዎች በጋራ  እጣቸው ላይ በጋራ ተማምነው  እንዳይሰባሰቡና  እንዳይመክሩ  የደርግ  ሥርዓት ያስፋፋው የጥርጣሬ ባህል  ከዋና ዋና ምክንያቶቹ አንዱ ነው። ሁሉም በየቤቱ እህህህ ይላል። ያርራል።  ይቃጠላል። አንዱ ከአንዱ ጋር ግን በድፍረት አይመክርም። በዚህ ሀገራዊና ማኅበረሰባዊ  ሁኔታ ላይ  የመጣው  ወያኔ   ኅብረተሰቡ  የበለጠ በጥርጣሬ   እንዲሞላ የበለጠ እንዲሰነጣጠቅ የዘርና  የሃይማኖት ልዩነት ቤንዚን  አርከፈከበት። እሳት ለኮሰበት ::  የስለላ መዋቅሩን ከደርግ ግዜ  በላይ  አስፋፋው። የህዝቡ በድህነት መራቆት፣ በደርግ ዘመን በተካሄደበት የሽብርና የሰቆቃ  ትውስታ የገባበትን መሰቀቅ በመጠቀም የወሬ አቀባዮንና አሳባቂውን ቁጥር በገንዘብ በመደለልና  በማስፈራራት አሳደገው። የመንደር ሰላይ፣ የቀበሌ፣  የአንድ ለአምስት ቤተሰቦችና፣  የቤተሰብ ውስጥ ሰላይ ሳይቀር አደራጀበት። ከመቼውም ዘመን በከፋ  መልኩ በወያኔ  ዘመን ሀገርና  ሕዝብ በሚሰቀጥጥ ደረጃ ተዋርዶ፣ ሃገርና ህዝብ ከመቼውም  በላይ ተዘርፈው፣ ሕዝብ በድህነት ተቆራምዶ፣  የተስፋ  ጭላንጭል አልታይ ያለው በገፍ በስደት ሲጋዝና ሲያልቅ በወያኔና  ላይ ሰብሰብ ብሎ  ጠንካራ  ተቃውሞ  ለማደራጀት ያልተቻለው የዘመናት የተጠራጣሪነት ማኅበረሰባዊ ባህላችን የደርግን ክፉ ዘመን አልፎ  በወያኔ ዘመን ፋፍቶ  መገኘቱ ነው። 

በወያኔ  ዘመን ወያኔን ለመቃወም የተነሱ ተቃዋሚዎችም ምን ሳይፈይዱ ውልቅልቃቸው የሚወጣው፣ በጃቸው የሚገኝ ወያኔን የማስወገድ መልካም አጋጣሚ የሚያልፋቸው ከጥርጣሬ መስፈን ጋር የተያያዘ ነው። በምርጫ 97 ወያኔ ተሸንፎ  ሥልጣን እንደማይለቅ ግልጽ በሆነበት ወቅት ቅንጅት ሕጋዊ በሆነ መንገድ ሊፈታ የማይችልን ችግር በሕግ ለመፍታት ከመሯራጥ ይልቅ ሕዝብን የወያኔን ፈቃድ ለማያስፈልገው ተቃውሞ  እንዲነሳ፣ ለዚህ ተቃውሞ  የሚያስፈልጉ ዝግጅቶችን በሚስጥርና በህቡእ ማደራጀት ያልቻለው ሃሳቡን ሰዎች ሳያስቡት ቀርተው አልነበረም። እንዲህ አይነቱን ሃሳብ ማን ማንን አምኖ  ለውይይት ያቀርበዋል ?። ማን እንደሚከዳ ማን ለወያኔ ወስዶ  እቅዱን ሊናገር እንደሚይችል ባልታወቀበት ሰአት ማን ለማን ደፍሮ ይናገራል?። እንደታየውም ይህ ሃሳብ ቀርቦ ቢሆን ኖሮ  ወያኔ በቅንጅት ውስጥ ባሰረጋቸው ሰዎቹ ወይንም ይህን መረጃ  ለወያኔ  በመስጠት ጥቅም እናገኛለን ብለው በሚያስቡ ሰዎች ወይም ሊከዱኝ ስለሚችሉ ቀድሜ ልክዳቸው በሚል ስሌት በሚያስቡ ሰዎች አማካይነት ለወያኔ ይደርሰው ነበር። ቅንጅቶች እርስበርሳቸው ተፈራርተውና ተጠራጥረው በከፍተኛ ደረጃ ድጋፉን የሰጣቸውን ሕዝብ ለመብቱ እንዲታገል በቂ ዝግጅትና በዚህ ዝግጅት ላይ የተመሠረተ ጥሪ ሳያደርጉ ቀሩ። እነሱም ተሰብሰበው ወህኒ ወረዱ። ደጋፊያቸውም ገሚሱ ውድ ህይወቱ አለፈች።  የተቀረው ተጋዘ፣ ታሰረ፣  ተሰደደ። 

ኅብረተሰባችን በጥርጣሬ አሲድ ተበልቶ እያለቀ ነው። የወያኔ አይነቶቹ አናሳ  አፋኝና  ዘረኛ ሥርዓቶች ደግሞ ዋንኛዎቹ የዚህ አሲድ አምራቾች ናቸው። አናሳ ሃይሎች በሥልጣን መቆየት የሚችሉት ብዙሃኑን ከፋፍሎ በመግዛት ነው።አንድ ማኅበረሰብ ውስጥ ማኅበራዊ ለውጥ፣ እድገትና የመብት ማስከበር ትግል መካሄድ የሚቻለው በተናጠል በሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች አማካይነት አይደለም። አንድ ግለሰብ በግሉ ለብቻው ሥርዓት   ልታገል ማላት ይችላል። ነገር ግን ከሥርዓቱ ጋር ከመላተምና ከመታሰር ወይም ከመሞት ሌላ ሥርዓት ሊቀይር አይችልም። የሥርዓት ለውጥ ለማምጣት የሚተማመኑ በርካታ  ሰዎችን፣ ዜጎችን ማሰባሰብን ይጠይቃል። በሀገራችን  የተዘራው የጥርጣሬ ባህል በዚህ ባህል የተበከለው የዜጎች ሥነልቦና ቀላል አይደለም።ጓዳዊ ግንኙነት የሌለው ወይም መፍጠር የማይችል ፣ ሲቀርቡት የሚርቅ፣ ሲያፈቅሩት የሚጠላ፣  ሲስሙት የሚናከስ፣ዝግ ሩቅ ሌሎች የማይደሩስበት የማያውቁት ድፍን ሰው ሆኖ መገኘት በማለት ባለፉት ገጾች የዘረዘርናቸው ጎጂ ባህርያት በአንድ ገጻቸው የተጠራጣሪት ውጤቶች ናቸው። 

ባምነው ሊሸጠኝ ይችላል። ባምነው ሊከዳኝ ይችላል። ባምነው መገልገያ  መረማማጃ  ሊያደርገኝ ይችላል። የሚፈልገኝ ለጥቅሙ እንጂ ለኔ ወይም ለጋራ ዓላማችን ብሎ አይደለም።  ለማስመሰል ነው የሚናገረው፣ ውስጥ ውስጡን ከጠላት ጋር ይገናኛል።  ወዘተ የሚሉ በማስረጃና በምክንያት ላይ ያልተመሠረቱ የጥርጣሬ ስሜቶች ተገዥ እስከሆንን ድረስ በጋራ  ተሰባስበን የሁላችንንም መብትና ጥቅም ጠላት በሆነው ኃይል ላይ በጋራ  ልንዘምትበት አንችልም።  

ጥርጣሬ  የሚወስደን ወደ በለጠ አዘቅት ነው። በጋራ የጋራ  ችግራችንን መፍታት ሲያቅተን፣ በገዛ ሀገራችን በሶስተኛ የዜግነት ደረጃ ለሚያዩን የወያኔ  ወራሪዎች ተላላኪ ሆነን ማደር እንጀምራለን። መልካም ባህርያችንና  ሥነምግባራችን አራግፈን ለመኖር  ስንል ወደ ሌብነትና ሥርቆት እንገባለን። የሌለ ጠላት፣ የሌላ ሴራ በዙሪያችን እያየን በአእምሮ በሽተኛነት ሊያስመድብ የሚያስችል በርጋጊዎች እንሆናለን። የስንት ጀግኖችና አርበኞች ልጆች ሆነን  ሳለ ወያኔ  ሀገር ሲሸጥ የድርሻችንን እንጠይቃለን። በስንት መከራ ቀደምቶቻችን ያተረፉልን ሀገር ለባንዳ ርዝራዦች ትተን ዘመዶቻችንን ጥለን መድረሻንን እንኳን በውል ወደማናውቀው ቦታ የዘመናዊ ባርነት ሕይወት ለመግፋት እንሰደዳለን። ተሰደንም በምንገኝበት ቦታም ገደብ  የሌለው የተጠራጣሪነታችን ጎጂ ባህል አብሮን ተሰዷል። የአላማ ልዩነት በሌላቸው በርካታ ድርጅቶች ተከፋፍለን ዋናውን የኢትዮጵያን ህዝብ ጠላት ወያኔን ትተን እርስ በርስ ስንባላ እንኖራለን።  ይህ ሁሉ ጣጣ  መቆም የሚችለው ጥርጣሬን  ከመሃከላችን አስወግደን  ርስበርስ መተማመን በጋራ መምከር የጋራ ችግራችንን በጋራ መፍታት ስንችል ብቻ  ነው።  

ባሁኑ ግዜ በማህበረሰባችን ውስጥ ሰውን ማመን ክፍተኛ  ዋጋ  ያስከፍላል። ክህደትና ሸፍጥን የሚያስቆመው የሞራል ልጓም ጠፍቷል። በእንዲህ አይነቱ አሳዛኝ ዘመንም ከአለንበት የስቃይና  የውርድት ማጥ መውጣት የምንችለው ለመተማመን እድል ስንሰጥ ብቻ  ነው። መተማመን  ዋጋ  ያስከፍላል ብለን ካሰብን እስቲ ያለመተማመን እስካሁን ካስከፈለንና  ወደፊት ከሚያስከፍለው ዋጋ  ጋር እናወዳድረው። ባላመተማመን የደረሰብን ጥፋት አይተነዋል። ወደፊት የሚያስከፍለን ዋጋ ካላፈው የባሰ እንጅ ያነሰ አይሆንም። ያለመተማመን ግለሰቦችን ብቻ አያጠፋም። ውሎ  አድሮ  ማኅበረሰብንና ሀገርን ያወድማል። ባለመተማመን የምንጠፋ  ከሆነ ለመተማመን እድል ሰጥተን ብንጠፋ  ይሻላል። ከተሞክሯችን ተነስተን ባለመተማመን የሚመጣውን የጋራ  ውርደትና ሞት በርግጠኛነት መናገር ችለናል። በመተማመን ግን ውርደትንም ሞትን ማምለጥ የምንችልበትን እድል ይዞ ይመጣል። ካልተማመንም የትም ነቅነቅ ማለት እንደማንችል አጠቃላይ ውድመታችን የግዜ  ጉዳይ ብቻ እንደሆነ ነፍሳችን ይነግረናል። መጥፋታችን  የማይቀር መሆኑን ከተገነዘብን  ለመተማመን እድል ሰጥተን እንሞክረው።  

መተማመን መስዋዕትነት እንደሚያስከፍል እናውቃለን። በረሃብ በስደት በውርደት መስዋዕትነት እየከፈልን ከማለቅ ለመተማመን መስዋዕትነት መክፈሉና ውጤቱን በተስፋ መጠበቅ አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን  የሚያመላክት ዘመን ላይ ደርሰናል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በሚኖሩበት ሀገር፣ መታፈኔ፣ መብቴ መገፈፉ፣ ወገኔና ሃገሬ መዋረዳቸው አንጀቴ ድረስ ዘልቆ የሚሰማኝ እኔ ብቻ ነኝ ማለት እራሱ ግብዝነት ነው። ሌላው ቢቀር አንድ ሌላ ሰው ይጠፋል ብለን እንዴት ማሰብ ያቅተናል? እኛ ምን አይነት ልዩ ፍጥረቶች ብንሆን እንደ እኔ የሀገር ውርደት የሚሰማው፣  መረገጡ የሚንገፈግፈው ሌላ ሰው  የለም ከሚል መደምደሚያ  ላይ የምንደርሰው። እንደኔ የሚያስብና  የሚሰማው ሁለተኛ  ሰው ከተገኘ ሶስተኛ ሰው  የማይገኝበት ምን ምክንያት አለ። እንዲህ እየተባለ መሰባሰብ ይቻላል። የድርጅት መሠረት መጣል ይቻላል። ሶስት አራት እየተሆነ ማደግ ይቻላል።   

የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል አባላት  ከዚህ በላይ የተባለውን በጥሞና ተገንዝበን ጥርጣሬ  የትም እንደማያደርሰን አውቀን ከማኅበረሰባችን ከግል  ህይወታችንና  ተመክሯችን ይዘነው የመጣነውን  የተጠራጣሪነት ባህል አውልቀን ከመጣል ውጭ አማራጭ የለንም። መንግሥትን እንዳናምን ተደርገናል። የፖለቲካ ድርጅቶችን እንዳናምን ተደርገናል። የማኅበረሰባችን  አባላት እንዳናምን ተደርገናል። ከዛም አልፎ ጓደኞቻችንን  እንዳናምን ተደርገነል። ነገር ግን እዚህ የተሰባሰብነው በተወሰነ ደረጃ ቢሆን አንዳችን አንዳችንን አምነን ነው። እንደ እኔ የከፋቸው ሊኖሩ ይችላሉ ብለን ነው። ይህ እምነት ግን በየግዜው በትንሹም በትልቁም አጋጣሚ ሊፈተን ይችላል። ያለመተማመን ባህልና ባህርይ በማኅበረሰባችን ሥር በመስደዱ የተነሳ ይህ ጎጂ ባህል  በጋራ ለመሰዋት በተሰባሰብነው ሃይሎችም ውስጥ ሳይቀር በቀላሉ አይጠፋም።  

ለጥርጣሬ እድል መስጠት  የወያኔን እድሜ  ማራዘም ነው ። በኛ አለመተማመን ተጠቃሚው ወያኔ  ብቻ ነው። ወያኔን ለመታገል ያውም በወታደራዊ ኃይል ለመታገል የቆረጡ አባላት ጥርጣሬን ከውስጣቸው ሙሉ በሙሉ ካላስወገዱ መድረሻቸው አይደለም መነሻቸውም አያምርም። አንድ ታጋይ ወደ ኋላ የገዛ ጓዱን በጥርጣሬ  እያየ እንዴት አድርጎ ወያኔን ለማጥቃት ጥይት እየዘነበበት ወደፊት መጓዝ ይችላል። አይችልም።  

ገደብ የሌለው ጥርጣሬ ሲጠፋ ሌሎች ከጥርጣሬ  ጋር ተያያዥነት ያላቸው ወይም ጥርጣሬን ተገን አድርገው የፋፉ መጥፎ ባህሪዎቻችን አብረው ይጠፋሉ። በኅብረተሰባችን ውስጥ የጠፋው የመተሳሰብ፣ የመዋደድ፣ የአንተን ክፉ አያሳየኝ፣ እኔ  ካንተ ልቅደም ባህሎች መፋፋት ይጀምራሉ። የሚዋደዱ ሰዎች በትንሽ በትልቁ አይጣሉም። ጭቅጭቅ ንትርክ አይኖርም። ሴራ ማሴር ሸር መጠንሰስ ያበቃለታል። የሚተሳሰቡ ጓዶች በጥሞና  ለመደማመጥ ይችላሉ። የተሻለውን ሃሳብ የጋራቸው አድርገው ተስማምተው ይሰራሉ። መጯጯህ ያበቃለታል። ያላቸውን ተካፍለው ይበላሉ ይጠጣሉ። ሁሉም የየግሉን በማሰብ የሚታዩ  የስግብግብነት ባህርዮች ይጠፋሉ። አቅምና ጤና የሌለውን ይደግፋሉ። አንዱ ባንዱ ላይ አያሳብቅም። አንዱ ለሃለፊነት ቢታጭ ሌላው መጥፎ ቅናት ውስጥ አይወድቅም። የጥርጣሬ  መወገድ እጅግ በርካታ  የሆኑ በጋራ የሚሰሩ ሥራዎችን እንዳይሳኩ ሊያደርግ  የሚችሉ ጎጂ ባህርይዎችን አስወግዶ  ለበርካታ በጎ ባህርያት ማበብ ምቹ ሁኔታ ይፈጠራል።  

ቀደም ብለን ከዘረዘርናቸው 72 ጎጂ ባህርይዎች መሃል ጥርጣሬ አንደኛ  የሆነው ያለምን ምክንያት አይደለም። አሁን በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ መተማመን ማስፋት መጠራጠርን ማስወገድ የሀገራችን የማኅበረሰባችን  ህልውና የማስከበር ወይም ያለማስከበር ያህል ክብደት የሚሰጠው ጉዳይ ስለሆነ  ነው።  

አንድ መጥፎ ባህርይ ማጥፋት የሚከፍታቸው መልካም እድሎች ብዙ ናቸው ብለናል። መጠርጠር አቆምን ማላት ልባችን አእምሯችን ለጓዳችን  ክፍት አደረግን፣  አጸዳን ማለት ነው። በንጹህ ልብ ውስጥ ጥላቻ ቅናት ምቀኛነት፣ ጠብ ጫሪነት፣ ያዙን ልቀቁኝ ባይነት አይኖሩም። የሚበቅለውና  የሚያብበው ፍቅር ነው። የማፍቀር አቅምና ጉልበት ያለው ሰው በውስጡ የሚሰማውን ፍስሃና ምሉእነት ማፍቀር የቻሉ ብቻ ናቸው የሚናገሩት። “ገሃነም ምን ይመስላል” ለሚለው ጥያቄ ማን ነበር “ለማፍቀር የማይችልን ልብ ይመስላል” ብሎ የመለሰው? በፍቅር ሰንሰለት የተሳሰሩን ጓዶች ምንም ምድራዊ ኃይል ሊለያያቸው አይችልም። ደስታቸውም ልባዊና  የጋራ ሃዘናቸውም የጋራና ጥልቅ ይሆናል። ፍቅር የአንድነት  መሠረቱ ነው። ፍቅር በሚፈጥረው አንድነት በጋራ ለምናከናውነው ሥራና ለምንደርስበት የውጤት ደረጃ ገደብ አይኖረውም።  

 ከዚህ ቀጥሎ ሌሎችን ቀደም ብለን የዘረዘርናቸውን ጎጅ ባህርያት፣ ልምዶችና ባህሎች የሚያመነጩ ምክንያቶችን እንይ። 

Wednesday 16 October 2013

Seminar om Barneoppdragelse Oslo

Seminar Om Barneoppdragelse Oktober 05, 2013 Oslo



Seminar Om Barneoppdragelse Oktober 05, 2013 Oslo




Wednesday 9 October 2013

አንዲት ሴት በአደጋው ግዜ እንደውለደች የሚገመት የተገኘችው ህጻኑ ከናቱ ጋር ከነትብቱ እንደተያያዝ ነው አሳዛኝ ሞተ አብረው አልፉ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስቴርና የኢሮፕያን ኮሚሽን ፕሬዝዴንት ላባዱዛ ተገኝተው አስከሬኑን ሲሰናበቱ ደስ የሚለው የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስቴር ለቲ አስክሬኑን ተንበርክከው ሲሰናበቱ ያሳያል ማምሻዉ ላይ የተገኘው አስከሬን መጠን ወደ 300 ተጠግቶአል በጣም የሚያሳዝነው ከተገኘው መካከ ንዲት ሴት በአደጋው ግዜ እንደውለደች የሚገመት የተገኘችው ህጻኑ ከናቱ ጋር ከነትብቱ እንደተያያዝ ነው አሳዛኝ ሞተ አብረው አልፉ

Wednesday 2 October 2013

ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በአፍሪካ የአደና ጉዞ ላይ

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

 የአፍሪካ “የዘር አደን”፤ የዘር ካርድ፤ እና የአፍሪካን እጀ ሰቦች/አመጸኞች ማደን?

ሃይለማርያም ደሰለኝ፤ የኢትዮጵያ የስም ብቻ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይ ሲ ሲ) በአፍሪካ አደን ላይ ነው ይላል፡፡ እንደ ቢቢሲ ራድዮ አባባል ራድዮ በግንቦት (ሜይ) 2013 ሃይለማርያም ሲናገር ‹‹በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ከተወነጀሉት መሃል 99% የአፍሪካ መሪዎች ናቸው፡፡ ይህም በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት አሰራር ላይ ጉድለት እንዳለ የሚጠቁም በመሀሆኑ ይህንን እንቃወማለን፡፡ ሂደቱ የዘር አደን ጥቁር አፍሪካኖችን ላይ ሰላቶኮረ ብሉሽነት ይታይበታል::›› ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ የገዢው ፓርቲ አፈ(ረ) ቀላ(ው)ጤ: ሲዘላብድ አንዲህ አለ: ‹‹የዓለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አሰራር በተለይም አፍሪካያን ገዢዎችንና አመራራቸውን በተመለከተ በሚወስደው እርምጃ ላይ በማንቋሸሽ እና በማንኳሰስ ላይ በመሆኑ መቼም አድንቀነው አናውቀውም፡፡››

በዚህ ወር መጀመርያ ግድም ሃይለማርያም ደሳለኝ በኬንያው ፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታና ምክትላቸው ዊሊያም ሩቶ ላይ ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የመሰረተውን ክስ በስርአት እንዲያነሳ ለአይ ሲ ሲ ሲጽፍ በግልባጩም የተባበሩት መንግሥታት እንዲያውቀው አድረጓል፡፡ የአፍሪካ መሪዎች ከሮም አለም አቀፍ ዉል (ዘር ማጥፋትን፤ሰብአዊ መብት ገፈፋን፤የጦር ወንጀልንና ወረራን የሚቀጣ ድንጋጌ ) የመሰረተውን ለቀን እንወጣለን በማለት የማስፈራራት እብደት ተጠናውቷቸዋል፡፡ በዚሁ የወፈፍታ ልክፍት ላይ ለመነጋገር አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ ለማካሄድ በአዲስ አበባው የመሪዎች መሰብሰቢያ ‹‹አማኑኤል›› ለመገናኘት ለአክቶበር 13 2013  ቀጠሮ አድርገዋል፡፡

የዓለም አቀፉ ችሎት አቃቤ ሕግ ጋምቢያዊዋ ዓለም አቀፍ ጠበቃ ፋቱ ቤንሱዳ፤ በተደጋጋሚ አብዛኛዎቹ በአፍሪካ ላይ የተመሰረቱት ክሶች ከአፍሪካ ሃገራት ጋር በተደረሰ ስምምነት ነው በማለት አሳስበዋል፡፡ አይ ሲ ሲ አፍሪካውያንን በተለይ በመምረጥ ክስ ሰርቷል የሚለውን የቅዠት አስተሳሰብ ዉድቅ አርገዉታል፡፡ የአፈሪካውያን ከአይ ሲ ሲ የመውጣት ዋነኛ መንስኤያቸው፤ ‹‹የዘር አደን›› ነው በማለት ነው፡፡ ስለ ዘር መሳቢያ/ ማታለያ፤ ስለዘርልዩነት፤ስለ ዘር ምልክት፤ ሰምቻለሁ፡፡ ስለ‹‹ዘር ማደን›› ግን ጨርሶ አልሰማሁም፡፡

ሃይለማርያም በዚህ የትንኮሳ ቴአትራዊ ጥቅሱ አይ ሲ ሲ በአፍሪካ የአደን ዘመቻ በማድረግ ሰላማዊ አፍሪካውያንን እየወነጀለ ነው ማለቱ ነው? አይ ሲ ሲ ‹‹ተበላሽቶ›› የነጮች ዘረኝነት ሕገወጥ ግድያን ቡድን ውስጥ በመግባት ሕጋዊውን ኢንስቲቲዩሽን በመጠቀም ለማሳደድ፤ለማሰር፤ከወንጀልና ከጥፋት ነጻ የሆኑትን የአፍሪካ መሪዎችን ይከሳል ለማለት ነው? ከተወነጀሉት ማሀል 99% የሚሆኑት አፍሪካውያን በመሆናቸው አይ ሲ ሲ የተቋቋመው አፍሪካውያንን ለመወንጀል ነው ሊለን ነው? የምእራብ ሃገራት አይ ሲ ሲን በመጠቀም ከምእራቡ ጋር ለመፋለም መጥረቢያ ያነሱትን የአፍሪካን መሪዎች በመነጠል ለመቅጣት አልመዋል ነው የሚለን? ለመሆኑ እነዚህ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ችሎት ክስ የተመሰረተባቸው 99% የዘር አደን የሚካሄድባቸውና  ክስ የተመሰረተባቸው እነማን ናቸው?