Friday 27 December 2013

እኛና እነሱ/ ዝቅ እንበል/

Norway











 ጠቅላይ ሚኒስቴር  የንስ ስቶልተንበርግ  የገና ዛፍ  ሲሸጡ
ጌዲዮን ከኖርዎይ
በአለም ላይ ካሉ ሃገሮች ውስጥ ስልጣን የሌለበት ሃገር ቢኖር ወይም ባለስልጣኑ ህዝብ የሆነበት ሃገር ቢኖር ሳላጋንን ኖርዎይ የምትባለው ሃገር ናት ማለት እችላለሁ፥፥ በግልፅ ህዝቡ የሚፈልገውን፥ ያስተዳድረኝ እገዛለታለሁ ብሎ አምኖ ድምፁን የሚሰጥለት መሪ፥፥ መሪውም ከልቡ እራሱን ዝቅ አርጎ ለሃገሩ፥ ለወገኑ የሚሰራበት ሃገር፥፣ ህገመንግስቱ ወይም በኖርዌጅያኑ አጠራር /GrunnLov/ ለሁሉም እኩል የሚሰራና ተፈፃሚ የሚሆን በቃ ዋናው ነገር ህገመንግስቱን አትንካ ነው፥፥አስታውሳለሁ በአንድ ወቅት የአለም መንግስታት ተባብረው ቢንላዲንን ለመደብደብ ብለው አፍጋኒስታንን በሚደበድቡበት ወቅት የኖርዎይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተለያየ የስራ ጉዳይ በሚል በብዛት ወደ አፍጋኒስታን ይመላለሱ ነበርና እዛም ሲመላለሱ በአፍጋኒስታኖቹ ባህል ስጦታ የተለመሰ ነገር በመሆኑ ለካ አቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርዬ አንድ ምንጣፍ በስጦታ አጊንተው ሲመለሱ ስጦታው ወደድ ያለ ሆኖ እያለ ለኖርዌጂያን ግብር ስብሳቢ ቢሮ ወይንም /tax Administration/ ማስመዝገብ ሲገባቸው ዘንግተውት በኖርዎይ ትልቅ መነጋገሪያ ርእስ ሆኖ ሚዲያዎች ቁም ስቅላቸውን ሲያበሉአቸው ነበር፥ እንዲሁም ባንድ ወቅት የትራንስፖርት ሚኒስትርዋ  አነስተኛ መርከብ ለመመረቅ ተጋብዘው በሄዱበት ወቅት ከአንድ ባለሃብት የእጅ ሰንሰለት የወርቅ በስጦታ አጊንተው እሳቸውም ዋጋው ውድ መሆኑን በለመረዳት ይመስላል ሳያስመዘግቡ በመቅረታቸው ሚዲያዎች ነገሩን ይደርሱበትና ካራገቡት በኋላ ታክስ አስቆርጠውባቸዋል ሚኒስቴርዋም ስጦታውን በመቀበላቸው እንደተፀፀቱ ለህዝባቸው ተናግረዋል፥፥
አሁን ግን ይህችን አጭር ፅሁፍ ለመፃፍ ያነሳሳኝ ከዚሁ ከኖርዎይ ሳልወጣ በዚህ በፈረንጆች ገና ዋዜማ በኖርዎይ ውስጥ ሆነውን በሃገራችን ህልም ሳይሆን ቅዠት ወደሆነብኝ ነገር ልውሰዳችሁ፥፥ ከሶስት ወር በፊት በሴፕቴምበር 2013 በኖርዎይ በተደረገው የጠቅላይ ሚኒስቴር ምርጫ ተሸንፈው ስጣናቸውን ያስረከቡት በኖርዎይ ምናልባትም ቁጥር አንድ ተወዳጅ ናቸው የሚባልላቸው የንስ ስቶልተንበርግ እንደውም ለምርጫው ጊዜ ታክሲ ሾፌር ሆነው ቅስቀሳ ሲያረጉ በነበረበት ጊዜ በኢሳት፥ በቢቢሲ የተዘገበላቸው http://ethsat.com/video/esat-kignet-taxi-shofieru-prime-minister/ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስቴ ለአሁኑ ገና በአል ዋዜማ ስራ ከለቀቁ በኋላ የመጀመርያ ስራቸው ያረጉት የገና ዛፍ መሸጥ ነበር፥፥ዜናውን ሳየው ብዙም አልደነገጥኩም፥ ግን ቅናት አደረብኝ እንደውም ተስፋ ነው የቆረጥኩት፥፥

ሰውዬው እንዳልኩት በአንድ ወቅት በተለይ ኢኮኖሚ ክራይስስ ተብሎ አውሮፓውያኑ እየተጨናነቁ በነበረበት ወቅት ሃገራቸውን በብቃት ችግሩ ባጠገቧም ሳይደርስ ስላሳለፉት የሃገሪቷ ቁጥር አንድ ተወዳጅ ሰው ከንጉሱም በላይ ተብሎ ሚዲያ ላይ ወቶ እንደነበር አስታውሳለሁ፥ ሃብታም ናቸው፥ እውቀት አላቸው በነገራችን ላይ አባታቸውም የኖርዎይ ጠቅላይሚኒስቴር ሆነው አገልግለዋል፥፥ ብቻ ለማጠቃለል ያህል ሰዎቹ ከራሳቸው በላይ የሚያስቀድሙት ብዙ ነገር ዓላቸው፥ ህዝባቸው፥ ሃገራቸው፥ አላማቸው፥ ግባቸው፥ ሌላም ሌላም
እንግዲህ እስካሁን ስለ እነሱ ነው ያወራሁት ግን እኛስ?

እኛ ማን ነን?
ለምንድነው የምንታገለው?
ለማን ነው የምንታገለው?
ምንድነው አላማችንና ግባችን?
ወደኛ ሲመጣ ይህ ጥያቄ ለሁላችን በግለሰብ ደረጃ መልስ ሊያገኝ የሚገባው ጥያቄ ይመስለኛል፥፥
ዝቅ እንበል!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

Monday 16 December 2013

10ሩ የማንዴላ ድንቅ አባባሎች

1,የአመታት እስር ነፃ ከመውጣት አያግደንም፡፡ የአመታት ጭቆናና ግፍም አያስቆመንም፤ እናም  ትግላችንን አናቆምም፡፡

2, ህይወትን እናንተ ከምትወዱት ባነሰ ደረጃ የምወድ አይደለሁ፤ ሆኖም በተፈጥሮ ያገኘሁትን መብት መሸጥ እንዲሁም ህዝቤ በተፈጥሮ ያገኘውን ነፃ የመሆን መብት የመሸጥ ፍላጎት የለኝም፡፡ (እ.ኤ.አ 1984-1989 የአፓርታይድ ፕሬዝዳንት የነበሩት ፒትረ ዊለልመ ቦንታ ከእስር ወጥቶ ትግሉን በመተው አርፎ እንዲቀመጥ ሲጠይቁት የሰጠው ምላሽ)

3.ፊታችሁ የቆምኩት እንደነብይ ሳይሆን እንደ ትሁት አገልጋያችሁ ነው፡፡ እዚህ እንቆም ያበቃኝ ያለመታከት በጀግንነት የከፈላችሁት ዋጋ ነው፡፡ ስለሆነም ቀሪው እድሜዬ በናንተ እጅ ነው፡፡ (ከእስር ሲወጣ የተናገረው) 

4.ከእስር ከወጣሁ ጀምሮ ይበልጥ የተገነዘብኩት ትክክለኞቹ ታሪክ ሰሪዎች የሀገራችን ተራ ዜጎች መሆናቸውን ነው፤ ወደ ፊት በሁሉም ውሳኔዎች ላይ የሚኖራቸው ተሳትፎ እውነተኛው የዴሞክራሲና የነፃነት ዋስትናችን ነው፡፡ (ከእስር ሲወጣ የተናገረው)

5.ወደ ፊት ለምናደርገው ውሳኔ ያለፈው ተሞክሮ ግብአት ሊሆነን ይችላል፤ ሆኖም ምርጫችንን አይወስነውም፡፡ ያለፈውን በመመልከት መልካሙን በመያዝ መጥፎውን ወደኋላ እንተዋለን፡፡ 

6.ትግል ህይወቴ ነው፤ እስከ ህይወቴ ማብቂያ ለነፃነት እታገላለሁ፡፡

7.ለብዙሀኑ ድምፅ እንቆማለን እንጂ ለጥቁሮች የበላይነት አንቆምም፡፡

8.ወደ ነፃነት የሚደረግ ቀላል ጉዞ የለም፤ የምንፈልገው የተራራ አምባ ላይ ከመውጣችን አስቀድሞ የትም ቢሆን ብዙዎቻችን በተደጋጋሚ በሞት ሸለቆ ማለፍ ግድ ይለናል፡፡ (በኤ.ኤን.ሲ ኮንፈረነስ ላይ የተናገረው) 

9.አንድ ታላቅ ኮረብታን ስወጣ የሚገለጥልኝ ምስጢር ሌሎች የምወጣቸው በርካታ ኮረብቶች እንዳሉ ነው፡፡ 

10.የሰው መልካምነት ሊከለል የሚችል ሆኖም የማይጠፋ ብርሃን ነው፡፡

Sunday 15 December 2013

Scientists Discover 4M-Year-Old Horse Fossil In Ethiopia



















Image Credit: Thinkstock.com
Lee Rannals for redOrbit.com – Your Universe Online
Scientists have discovered a new species of a small horse that lived 4.4 million years ago in Ethiopia.
The Eurygnathohippus woldegabrieli fossils were found in the Gona area of the Afar region in 2001. The ancient horse was among a diverse array of animals that lived in the same areas as the ancient human ancestor Ardipithecus ramidus, or Ardi.
The ancient horse species was about the size of a small zebra and had three-toed hooves. Scientists say the E. woldegabrieli grazed the grasslands and shrubby woods.
Scott Simpson, professor of anatomy at Case Western Reserve’s School of Medicine, said the horse fills in a gap in the evolution of horses. He added this is an important discovery for documenting how old a fossil locality is and in reconstructing habitats of human forebears of the time.
“This horse is one piece of a very complex puzzle that has many, many pieces,” Simpson, who is co-author of the study published in the Journal of Vertebrate Paleontology, said in a statement. “The fossil search team spreads out to survey for fossils in the now arid badlands of the Ethiopian desert. Among the many fossils we found are the two ends of the foreleg bone—the canon—brilliant white and well preserved in the red-tinted earth.”
The researchers also found part of the connecting shaft, which was split lengthwise but provided the crucial full length of the bone. The bone indicates this species was an adept runner, similar to modern zebras. Researchers also performed analysis of the teeth, revealing the species relied heavily on eating grasses.
The horse had longer legs than other ancestral horses that lived and fed in forests about six million to 10 million years ago. This evolutionary change helped the horse cover longer distances and flee from predators like sabre-tooth cats and hyenas.
The teeth are taller than their descendants and have crowns that are worn flatter, which is a sign the horses adapted to a grazing lifestyle. An analysis of the isotopic composition of the enamel confirmed the horse subsisted on grass.
“Grasses are like sandpaper,” Simpson said. “They wear the teeth down and leave a characteristic signature of pits and scratches on the teeth so we can reliably reconstruct their ancient diets.”
The remains showed this horse was a significantly different animal than the horses from earlier than five million years ago, as well as those from later than 3.5 million years ago. The researchers said members of the youngest group are taller and have longer noses, which are even more beneficial characteristics for open grassland living.

Source: Lee Rannals for redOrbit.com - Your Universe Online


Saturday 7 December 2013

በመዲናዋ ምስጢራዊ የወሲብ ገበያ ደርቷል

የትላልቅ ድርጅቶች ፀሃፊዎች፣ ሞዴሎችና ተዋናዮች አሉበት ድንግልናን 10 ብር የሚያሻሽጡ ደላሎች ሞልተዋል የከተማዋ ቱባ ባለሃብቶችየአገልግሎቱተጠቃሚዎች ናቸው

ሲኤምሲ ሣሚት ማዞሪያ አካባቢ ካሉት ዘመናዊ ቪላ ቤቶች በአንደኛው 12 ብር ወርሃዊ ኪራይ እየከፈለች ትኖራለች፡፡ የምታሽከረክረው ኤክስኪዩቲቭ ቶዮታ፣ በየዕለቱ የምትቀያይራቸው እጅግ ውድ ዋጋ ያላቸው አልባሳቶቿና በየመዝናኛ ሥፍራው የምትመዘው ረብጣ ብር የተንደላቀቀ ኑሮ እንደምትመራ ይመሰክራሉ፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናትና መዲናችን አለማቀፋዊ ስብሰባዎችን በምናስተናግድበት ጊዜያት እሷን ፈልጐ ማግኘት የማይታሰብ ነው፡፡

ቦሌ ፍሬንድሽፕ ሕንፃ ላይ በከፈተችው ቡቲክ የምታገኘው ገቢ ይሄን ያህል ሊያዝናናት እንደማይችል የታወቀ ነው፡፡ ገቢ ወጪዋን አጥብቃ የማትቆጣጠርበትን ይህንኑ ቡቲኳን ታናሽ እህቷ ትውልበታለች፡፡ እሷም አልፎ አልፎሥራበማይኖራት ጊዜ ብቅ እያለች ትጐበኘዋለች፡፡ ታናሽ እህቷ ቤተሰቡን ሁሉ ቀጥ አድርጋ የምታስተዳድረው እህቷ፤ ስለምትሰራው ምስጢራዊ ሥራ አንዳችም የምታውቀው ነገር ያለ አይመስልም፡፡ እሷ የምታውቀው ከተለያዩ የውጪ አገር ሰዎች ጋር የአየር ባየር ንግድ እንደምታጧጡፍና በየጊዜው ወደተለያዩ አገራት ለሥራ ጉዳይ እንደምትመላለስ ብቻ ነው። ሥራዋ የግል ሚስጢሯ ብቻ ሆኖ እንዲኖር የምትፈልገው ህሊና (ስሟ ለዚህ ጽሑፍ የተቀየረ) ይህንን የእህቷን እምነት አጥብቃ ትፈልገዋለች። በተለያዩ የመዝናኛ ሥፍራዎች ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር ደንበኞቿ ጋር እየከረመች በመጣች ቁጥር ለእህቷ የተለያዩ ቸኮሌቶችና ስጦታዎችን እየያዘችላት መምጣቷ የእህቷን እምነት አጠናክሮላታል፡፡

እሷቢዝነስብላ የገባችበት ህይወት ገቢ፣ እህቷ ቀኑን ሙሉ ተገትራ ከምትውልበት ቡቲክ ገቢ ጋር ሊወዳደር እንደማይችል ስለሚገባትሥራውንአጥብቃ መያዙን ትፈልገዋለች፡፡ የንግድ ፍቃድ እድሣት፣ ቫት ምዝገባ፣ ሪሲት ማሽን፣ ቀረጥና ታክስ የሚሉ ዝባዝንኬዎች የሌሉበት፣ራስን እያስደሰቱ ሌሎችን በማዝናናትበቀን የሚገኝ ረብጣ ብር ከቡቲኳ ወርሃዊ ገቢ በእጅጉ ይልቃል። ተፈጥሮ ያደላትን ውበትና ማራኪ ቁመናዋን ለገበያ እያቀረቡ በተሻለ ገንዘብ ለመሸጥና ጠቀም ያለ የኮሚሽን ገንዘብ ለመቀበል አሰፍስፈው የሚጠባበቁ ደላላ ደንበኞች አሏት፡፡ ለዚህ ተግባር ብቻ የምትጠቀምበት የሞባይል ስልኳ ሲጮህሥራእንደተገኘ እርግጠኛ ትሆናለች። ቅያሬ ልብሶችን የምትይዘበትና ሁሌም ለጉዞ ዝግጁ የምታደርገውን ቦርሣዋን አንጠልጥላ ውልቅ ነው። አብዛኛውን ጊዜ ወደ ሥራ የምትንቀሳቀሰው በደላሎቹ መኪና ነው። ደላላው እሷን ካለችበት ወስዶ ወደምትፈለግበት፣ ሥራዋን ስትጨርስ ደግሞ ወደነበረችበት የመመለስ ግዴታ አለበት፡፡ የኮሚሽን ክፍያው እነዚህን አገልግሎቶች ያካተተ ነው፡፡ ህሊና ይህንን ህይወት ላለፉት አራት አመታት ኖራበታለች። ከዚህ ህይወት ስለመውጣትና ቢዝነሱን ስለመተው ለአፍታም አስባ አታውቅም፡፡