Thursday 10 July 2014

ETHIOPIA: MISSING BRITISH MAN AT RISK OF TORTURE

https://www.amnesty.org.uk/actions/ethiopia-andargachew-tsige-torture?utm_source=SMS&utm_medium=SMS_action&utm_campaign=IAR&utm_content=ethiopia_SMS

PLACE SIGN HERE

Andargachew Tsige, a British national, disappeared on 24 June at a Yemen airport. He has been taken to Ethiopia, where he is at high risk of torture.
Every second his exact location is unknown puts him at greater risk. Demand his safety now.

Monday 7 July 2014

የካምብሪጅ ጠበቆች ቡድን ከእንግሊዝ ውጪ ጉዳይ ባለስልጣናት ጋር ነገ በአንዳርጋቸው ዙሪያ ይሰበሰባል

ኢትዮጵያውያን ጫናቸውን መቀጠል አለባቸው፡፤ እንበርታ ።

አንድአርጋቸው ቴዲ አፍሮ ወይንም ብርቱካን ሚደቅሳ አይደለም !!!ወያኔዎች አንዳርጋቸውን አስረው የፖለቲካ ትርፍ የሚያገኙ መስሏቸዋል። አንዳርጋቸው ሳይታሰር ከሚፈጥረው ተጽእኖ ይልቅ ታስሮ የሚፈጥረው ተጽእኖ ቀላል አይደለም ፡ በውጪ ከሚታገለው እጥፍ በላይ በወህኒ በሚከፍለው መስዋትነት በወያኔ ላይ ትልቅ ተጽእኖ ይፈጥራል።
አንዳርጋቸውን በማሰራቸው የሚጸጸቱበት ቀን ሩቅ አይደለም ። ወያኔ ዝም ያለው የህዝብን ቁጣ በመፍራት ሲሆን በሚስጥር የተበተኑ ደህንነቶች የሕዝቡን ትኩሳት እየለኩ መሆኑን ታውቋል፤ ሃይለማርያም ደሳለኝም ሆነ ሌሎች የወያኔ ባለስልጣናት የአንዳርጋቸውን መታፈን የሰሙት ከግንቦት ስባት መግለጫ መሆኑ ተረጋግጧል። የወያኔ ድህረ ገጾች ላለፍት 2 ሳምንታት ዝምታን መርጠዋል፡ ይህ የሚያመለክተው ወያኔ በራስ መተማመኑ ምን ያህል እንዳጣ ነው፡ ይህ ማለት ፕሮፌሰር አስራትን የያዙበት ግዜ አይነት አይደለም ዘመኑ አሁን የበሰለ ነው ሲሉ መረጃውን ያመጡት ተናግረዋል።
ነገ የሚሰበሰበው የካምብሪጅ የጠበቆች ቡድን ለ እንግሊዝ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ከባድ እና ህጋዊ ማስጠንቀቂያ በመስጠቱ ይህንን እንደሚያደርግ የሚጠብቀው ቢሮው የጠበቆቹን ቡድን አስከትሎ ክፍተኛ ሚኒስትርን ወደ አዲስ አበባ ይልካል ፤ በእንግሊዝ የሚገኘው ታዋቂ የካምብሪጅ የጠበቆች ቡድን ከባድ ማስጠንቀቂያ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰጥቷል።
በመላው አለም የምንገኝ ኢትዮጵያውያን እስከድል ጫፎች ድረስ ጫናችንን መቀጠል አለብን ።

Saturday 5 July 2014

“ልጆቼ ሆይ!... ከ182 ሚ. ፓውንድ ሃብቴ ሽራፊ ሳንቲም አላወርሳችሁም!” - ታዋቂው ሙዚቀኛ ስቲንግ

ልጆቼ ሆይ!... 182 . ፓውንድ ሃብቴ ሽራፊ ሳንቲም አላወርሳችሁም!”   - ታዋቂው ሙዚቀኛ ስቲንግ


በፍጹም!” አለ ስቲንግ፡፡
በፍጹም አላደርገውም!... ይሄን ሁሉ ሃብትና ንብረቴን አውርሼ፣ በልጆቼ ላይ እንደመርግ የከበደ ጫና አላስቀምጥም!” በማለት እቅጩን ለጋዜጠኞች ተናገረ፡፡ ይህን የሰሙ የዓለማችን ታዋቂ ጋዜጦችና ድረ-ገጾችም፣ ያሳለፍነውን ሳምንት ነገሩን እየተቀባበሉ አሰራጩት። ስቲንግ እንዲህ አለ የሚሉ ዘገባዎች በስፋት ተነበቡ፡፡
ስቲንግ ማን ነው?


በቅጽል ስሙ ስቲንግ እየተባለ የሚጠራው ጎርደን ሰምነር፣ በሰሜናዊ ቲንሳይድ ዋልሴንድ የተባለች ከተማ ውስጥ የተወለደ እንግሊዛዊ ነው፡፡ አራት ልጆች ለነበሯቸው ወላጆቹ የበኩር ልጅ የሆነው ስቲንግ፣ እናቱ ጸጉር ሰሪ አባቱ መሃንዲስ ነበሩ፡፡ አባትዬው ከስራቸው ጎን ለጎንም ከብት ያልቡ ነበርና፣ ስቲንግም ልጅነቱን የገፋው አባቱ የሚያልቡትን ወተት በየሰፈሩ እየዞረ በማደል ነበር፡፡ 

ገና በልጅነቱ የሙዚቃ ስሜት በውስጡ ያደረበት ስቲንግ፤ 10 አመት ልጅ ሳለ ጀምሮ ነበር የአባቱን ጓደኛ ጊታር አንስቶ ክሮቹን መነካካት የጀመረው። ሙዚቃ እንጀራው እስክትሆን ድረስ፣ ሌላ የእንጀራ መብያ ስራ መስራት ነበረበትና፣ ሳያማርጥ ስራዎችን ሰርቷል፡፡ በህንጻ ግንባታዎች የቀን ሰራተኛ ሆኖ አሸዋና ጠጠር አመላልሷል፡፡ የቀረጥ ሰብሳቢ ድርጅት ሰራተኛ ሆኖ ሌት ተቀን በትጋት ሰርቷል፡፡ ጎን ለጎን ትምህርቱን በመከታተልም፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን አጠናቆ ኖርዘርን ካውንቲስ ኮሌጅ በመግባት በመምህርነት ተመርቋል፤ ለሁለት አመታትም አስተምሯል፡፡ 

ስቲንግ ከአባቱ የከብቶች በረት ራሱን አውጥቶ፣ ህይወቱን ወደተሻለ አቅጣጫ ለማምራት ከልጅነት እስከ እውቀት ታትሯል፡፡ ኑሮውን ለማሸነፍ ደፋ ቀና ሲል ኖሯል፡፡ ከልጅነቱ አንስቶ በውስጡ የነበረው የሙዚቃ ፍቅር ግን፣ ወደኋላ ላይ ራሱን ከፍ ወዳለ ደረጃ የምታወጣው መክሊቱ ሆነች፡፡ በተውሶ ጊታር ጣቶቹን ማፍታታት የጀመረው ብላቴና፤ ቀስ በቀስ ራሱን አሰልጥኖ፣ በተለያዩ የምሽት ክለቦች ሙዚቃዎቹን ማቅረብ ቀጠለ፡፡ እንዲህ እንዲህ እያለም በአገረ እንግሊዝ ስማቸው ጎልቶ ከሚጠቀስ አርቲስቶች ጎራ ተቀላቀለ፡፡ በሂደትም በጃዝ፣ ሮክ፣ ሂፕ ሆፕና በተለያዩ ስልቶች የተቀነቀኑ 17 በላይ የቡድንና የነጠላ የሙዚቃ አልበሞችን ለአድማጭ አበረከተ፡፡ አለማቀፍ ኮንሰርቶችን በግሉና በቡድን በማቅረብ ዝናው ናኘ፡፡ በበርካታ ፊልሞችና የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይ በተዋናይነት ተሳትፎ የጥበብ ክህሎቱን አስመሰከረ፡፡ 

በህይወቱና በስራዎቹ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ 6 መጽሃፍት የተጻፉለት 62 ዓመቱ ዝነኛ እንግሊዛዊ ድምጻዊ፣ የፊልም ተዋናይና ፕሮዲዩሰር ጎርደን ሰምነር (ስቲንግ) 16 የግራሚ ሽልማቶችን ተቀብሏል፤ የብሪት፣ ጎልደን ግሎብ፣ ኤሚ ተሸላሚ ሆኗል፤ የኦስካር ዕጩም ለመሆን በቅቷል፡፡ ሰውዬው በረጅሙ የሙያ ጉዞው ከፍተኛ ዝናን ብቻም አይደለም የተጎናጸፈው፣ ከባለጠጎች ተርታ የሚያስመድበውን ሃብት ጭምር እንጂ፡፡ የሙዚቃ ስራዎቹ በመቶ ሚሊዮን ኮፒ በአለም ዙሪያ ተቸብችበዋል፡፡ ወተት ሲያመላልስ ያደገው ድሃ አደግ ብላቴና፣ አሁን 182 ሚሊዮን ፓውንድ የሚገመት ሃብት ያፈራ ባለጸጋ ነው፡፡ሰንደይ ታይምስየአመቱ የእንግሊዝ 100 ቀዳሚ ባለጸጎች ብሎ ከመረጣቸው ሰዎች ተርታ ያሰለፈው፣ ከሶስት አመታት በፊት ነበር፡፡ በወቅቱ በእንግሊዝ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከፍተኛ ሃብት ካፈሩ አስር ዝነኛ አርቲስቶች አንዱ ስቲንግ ስለመሆኑ ተመስክሮለታል፡፡ ስለዝናውም ስለ ሃብቱም ብዙ ተዘግቦለታል፡፡

ከሰሞኑ ደግሞ መገናኛ ብዙሃን ስለዚሁ ባለጸጋ አርቲስት ሌላ ዘገባ አሰራጭተዋል - “ስቲንግ ሃብቴን ለልጆቼ አላወርስም አለየሚል፡፡ 182 ሚሊዮን ፓውንድ ባለጸጋው ስቲንግ፣ ባሳለፍነው እሁድ ከታዋቂው ደይሊ ሜይልጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ነበር፣ ልጆቹ የሃብት ንብረቱ ወራሾች እንደማይሆኑ በግልጽ የተናገረው፡፡

ይሄን ሁሉ ገንዘብ ለልጆቼ ማውረስ፣ መጥቀም ሳይሆን መጉዳት ነው!... ሰርተው ያላገኙትን የውርስ ገንዘብ ለልጆቼ መስጠት፣ ሊሸከሙት የማይችሉትንና የሚያጠፋቸውን ከባድ ጫና በአንገታቸው ላይ እንደማሰር ነው የምቆጥረው፡፡ብሏል ስቲንግ ለጋዜጠኞች፡፡ይሄን የሰሙ ሌሎች መገናኛ ብዙሃንም ነገሩን እየተቀባበሉ አስተጋቡት፡፡ የሚያወርሱት የተትረፈረፈ ሃብት ይዞ፣ ለልጆች ላለማውረስ መወሰን ለእኛ እንጂ ለውጪው አለም አዲስ ባይሆንም፣ የስቲንግ ውሳኔ ግን የመገናኛ ብዙሃን ቀዳሚ ወሬ መሆኑ አልቀረም፡፡ስቲንግ ውሳኔውን ያሳለፈው ለልጆቹ የማያስብ ጨካኝ አባት ሆኖ አይደለም፡፡ ሃብቱን ሳይሆን ትጋቱን ቢወርሱ እንደሚበጃቸው ስለተሰማው እንጂ። የራሳቸውን ህልም አልመው ቢነሱ የተሻለ ውጤታማ እንደሚሆኑ በማመኑ እንጂ፡፡ ይህን እምነት ደግሞ ከራሱ የህይወት ተመክሮ ነው የቀዳው፡፡ ልጆቹ አባታቸው ባፈራው የውርስ ሃብት ሳይሆን፣ የራሳቸውን መንገድ ተከትለው ተግተው በመስራት ውጤታማ መሆን አለባቸው ብሎ የሚያምነው ስቲንግ፤ እሱም በዚህ መንገድ ራሱን ወደ ስኬት ማድረሱን ያስታውሳል፡፡ እሱ የሚወረስ ሃብት ያፈራ አባት ያሳደገው ልጅ አይደለም፡፡ አባቱ የሚያልበውን ወተት በየቤቱ ሲያመላልስ፣ በቀን ሰራተኛነት የራሱን ጥሩ ቀን ለመፍጠር ሲባዝን ነው ያደገው፡፡ በአባቱ ውርስ ሳይሆን በራሱ ህልም ራሱን ሰው ለማድረግ ቃል ገብቶ ነው ረጅሙን ጉዞ የጀመረው፡፡

ትዝ ይለዋል፡፡ ልጅ እያለ አንድ ዕለት አንዲት የተከበሩ እንግዳ ወደሚኖርበት አካባቢ ለጉብኝት መምጣታቸውን ሰማ፡፡ ማናት ሴትዮዋ ሲል ጠየቀ፡፡ የእንግሊዟ ንግስት መሆናቸው ተነገረው፡፡ ብላቴናው ስቲንግ ወደጉብኝቱ ስፍራ አመራ፡፡ በግርግሩ ውስጥ ተሽሎክሉኮም አይኖቹን አሻግሮ ላከ፡፡ ንግስቲቱ በርቀት ታዩት፡፡ አሻግሮ እያያቸው ድምጹን ዝቅ አድርጎ የህይወቱን ግብ የተለመባትን ነገር ለራሱ ተናገረ - “ሃብታም፣ ታዋቂና ስኬታማ ሰው እሆናለሁ!... እኔም እንደ ንግስቲቷ ዘመናዊ ሮልስ ሮይስ መኪና እነዳለሁ!” በማለት፡፡ስቲንግ እሆናለሁ ያለውን ሆነ፡፡ አሻግሮ ያማተራትን ስኬት ተግቶ ደረሰባት፡፡ ብዙ ዝና፣ ብዙ ክብር፣ ብዙ ሃብት አካበተ፡፡ ስቲንግ እዚህ የደረሰው በራሱ ጥረት እንደሆነ ያምናል፡፡ ይሄን ሁሉ ሃብት ያፈራው፣ በላቡ መሆኑን ያውቃል፡፡ ይሄን ስለሚያውቅና እንዲህ ስለሚያምን ነው፣ በእጆቹ የያዘውን ሃብት ለልጆቹ ላለማውረስ የወሰነው፡፡

ሶስት ወንድ እና ሶስት ሴት ልጆቹ እንደ እሱ ስኬታማ እንዲሆኑ፣ የእሱን መንገድ መከተል እንጂ የእሱን ሃብት መጠበቅ እንደሌለባቸው ነግሯቸዋል፡፡ ከአባታቸው ጥረትን እንጂ ጥሪትን እንዳይወርሱ አበክሮ መክሯቸዋል፡፡ በጥንታዊ አሰራር የተሰራው የእንግሊዙ ማራኪ ቤቱም ዊልትሻየር ውስጥ የሚገኘውን ዘመናዊ ቪላውን፣ በገጠራማዋ የእንግሊዝ የሃይቆች አውራጃ የሚገኘው የተንጣለለ ቤቱን፣ የኒውዮርኩን ዘመናዊ ቤቱንም ሆነ የጣሊያኑን የሪል ስቴት መኖሪያውንሁሉንም እንወርሳለን ብለው እንዳያስቡ ከአሁኑ እቅጩን ነግሯቸዋል፡፡ልጆቼ ተግተው መስራት እንዳለባቸው ነው የማምነው፡፡ ይህንንም ስለሚያውቁ፣ ሁሉም ልጆቼ አልፎ አልፎ ካልሆነ በቀር ምንም አይነት ድጋፍ አጠይቁኝም። ይህ ደግሞ ይበል የሚያሰኝ ነገር ነው፡፡ ችግር ውስጥ ካልሆኑ በቀር፣ የገንዘብ ድጋፍ አድርጌላቸው አላውቅም። በራሳቸው ተሰጥኦና ችሎታ ተጠቅመው ስኬታማ የመሆን ፍላጎት የሚያሳድርባቸውን ይሄን አካሄድ ነው የሚከተሉት፡፡ብሏል ስቲንግ፤ ስለልጆቹ ሲናገር፡፡

ይሄን ሁሉ ገንዘብ ለልጆቼ ማውረስ፣ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ በራሳቸው አቅም ሃብት መፍጠር እንዲችሉ ማገዝ እንጂ፣ የኔን ሃብት በማውረስ ልጆቼን ማኮላሸት አልፈልግም፡፡ ሰርተው ያላገኙትን በመቶ ሚሊዮኖች ፓውንድ የውርስ ገንዘብ ለልጆቼ መስጠት፣ ሊሸከሙት የማይችሉትንና የሚያጠፋቸውን ከባድ ጫና በላያቸው ላይ መጫን ነው፡፡ብሏል፤ ሃብቱን ከልጆቹ ይልቅ ለበጎ አድራጎት ስራ ለመስጠት የወሰነው ስቲንግ ለጋዜጠኞች፡፡

እንዲህ እንደ ስቲንግ ሃብታቸውን ለልጆቻቸው ላለማውረስ የወሰኑ በርካታ የዓለማችን ባለጸጎች አሉ። ከእነዚህ አንዱ የአለማችን ባለጸጎች ፊታውራሪ የማክሮሶፍት ኩባንያ መስራች ቢል ጌትስ ነው። ቢል ጌትስ 76 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሃብቱን ለልጆቹ እንደማያወርስና እነሱም እንወርሳለን ብለው እንደማይጠብቁ ተናግረዋል፡፡225 ሚሊዮን ዶላር ሃብት ያፈራው ዝነኛው የሙዚቃ ተሰጥኦ ውድድር ዳኛ ሲሞን ኮዌልም፣ በዚህ አመት መጀመሪያ ለወለደው ልጁ ለኤሪክ ሳይሆን፣ ለበጎ አድራጎት እንደሚያውለው ተናግሯል - “ሀብትን ዘር ቆጥሮ ከትውልድ ወደ ትውልድ በውርስ መልክ በማስተላለፍ አላምንምበማለት፡፡

ቦዲ ሾፕ የተባለው ታዋቂ ኩባንያ መስራች የሆነችው አኒታ ሮዲክም ብትሆን፣ ጥሪት ሳልተውላቸው ብሞት ምን ይውጣቸው ይሆን ብላ ሳትሰጋ 51 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ሃብቷን ሙሉ ለሙሉ ለበጎ አድራጎት ስራ ሰጥታለች፡ ለዚህች ሴት፣ ሃብት ንብረትን ለልጅ ወይም ለሌላ የቤተሰብ አባላት ማውረስ፣ አሳፋሪና ነውር ድርጊት ነው፡፡ኤኦ ዶት ኮም የተባለውን ትርፋማ ኩባንያ በዋና ስራ አስፈጻሚነት የሚመራው ጆን ሮበርትስም፣ 500 ሚሊዮን ዶላር ሃብቱን የአብራኩ ክፋይ ለሆኑት ልጆቹ እንደማያወርስ አፍ አውጥቶ ከተናገረ ቆይቷል፡፡ ሰውዬው ይሄን ውሳኔ ያስተላለፈው፣ በልጆቹ የሚጨክን ክፉ አባት ስለሆነ አይደለም፡፡ ስለልጆቹ የሚጨነቅ አርቆ አሳቢ በመሆኑ እንጂ፡፡ ሃብቱን ለልጆቹ የማያወርሰው የወደፊት ህይወታቸው ሰላማዊ እንዲሆንና የስኬታማነት ስሜት እንዲፈጠር በማሰብ መሆኑን ነው ሮበርትስ የተናገረው፡፡