Tuesday 12 March 2019

Ethiopian Airlines




ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ምን እናድርግህ?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ  ምን እናድርግህ?
(አሌክስ አብረሃም)




የእውነት እንወድሃለን እናከብርሃለን መላው የኢትዮጲያ ህዝብ እንኳን ስጋውን ነፍሱን ላንተ ለመስጠት እስከማይሳሳ ያለውን ፍቅር ሰጥቶሃል ! ላንተ በተወረወረ ቦንብ እግሩ ተቆርጦ ሆስፒታል የተኛ ወጣት ስቃዩን ችሎ "አብይን አደራ" ሲል አይተሃል! ወገባቸው የሚንቀጠቀጥ አቅመደካሞች በምርኩዝ ደግፈውህ ወጥተዋል ሁሉም ህዝብ ያን ያህል ወዶሃል አምኖሃል! ለአገሩ ሙሉ እድሜውን በስደት የከፈለ ህዝብ በፍቅርህ የወደዳትን አገር ስላከበርክ በውስጥህ ስሟን ላነገስካት አገሩ እግርህ ስር ተንበርክኳል ! የገዛ ወገኖችህ ግን ለቁራጭ መሬት እንደይሁዳ ሊሸጡህ ወደዱ! አንተን ሰቅለው ከወንድሞቻቸው ጋር ደም ሊያፋስስ ያሰፈሰፈ በርባን አነገሱ ! ዛሬ ላይ ተው ያላቸው ሁሉ ጠላት ግፉ ያላቸው ሁሉ ታዳጊያቸው መስሎ ታያቸው! እንደትላንቶቹ ጭፍኖች ዛሬም በማን አለብኝነት እጃቸው በገጀራ ታመነ ፣ሁሉንም የኛ አሉ የነሱም የኛም የሆንከውን አንተን ግን ከራሳቸው የደም መሬትም ከኛ ልብም ገፍተው ሊጥሉህ ረፍት አጥተው ናወዙ! ዓብይ ምን እናድርግህ?በእውነት ለዚች አገር አንድነት ለዚች አገር ህልውና ምን እናድርግ?