Sunday 23 March 2014

icipe Director General, Dr Segenet Kelemu to receive L’Oréal-UNESCO For Women in Science award

icipe Director General, Dr Segenet Kelemu, is among five outstanding women scientists who will receive the 2014 L’Oréal-UNESCO For Women in Science awards, at a ceremony to be held in Paris, France on March 19.
The L’Oréal-UNESCO For Women in Science awards are presented each year to honour women scientists who represent unique career paths combining exceptional talent, a deep commitment to their profession and remarkable courage in a field still largely dominated by men.
Dr Kelemu, who is the 2014 laureate for Africa and the Arab States, is being honoured for her research on how microorganisms living in symbiosis with forage grasses can improve their capacity to resist disease and adapt to environmental and climate change. Her work is providing new solutions for ecologically responsible food crop production, especially by local, small-scale farmers.

Saturday 15 March 2014

አትሌት አበባ አረጋዊ ከስዊድን እንድትባረር የስዊድን ሚዲያዎች ዘመቻ ከፍተዋል

ሃሰተኛ ጋብቻ ፈፅማ ዜግነቷን ቀይራለች፤ ፍቺውንም ለ10 ወራት በምስጥር ይዛ ቆይታለች፡፡ ታክስ አጭበርብራለች… - የስዊድን ሚዲያዎች
በትውልድ ኢትዮጵያዊ የነበረችውና ዜግነቷን በመቀየር ስዊድናዊ ሆና በመወዳደር ሁለተኛ ዓመቷን የያዘችው አትሌት አበባ አረጋዊ በትዳሯ ዙርያ በተፈጠሩ አወዛጋቢ ሁኔታዎች በለቅሶ እና ሃዘን መሰንበቷን የተናገረችው በሳምንቱ መግቢያ ላይ ነው፡፡ አትሌቷ ስዊድናዊ ለመሆን ሃሰተኛ የጋብቻ ሰነድ በማስረጃነት በመጠቀም አጭበርብራለች በሚል ዘገባ ከ6 ወራት በፊት ያብጠለጠላት  ታዋቂ የስዊድን  ጋዜጣ ኤክስፕረሰን፤ በፖላንድ ሳፖት የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ  ሻምፒዮና አትሌቷ በ1500 ሜትር የወርቅ ሜዳልያ ከመጎናፀፏ አራት ቀናት በፊት ባወጣው ልዩ ዘገባ አበባ አረጋዊ ስዊድናዊ ዜግነት ያለውና አሰልጣኟ ከነበረው  ሄኖክ ወልደገብሬል ጋር  ባለትዳር ያደረጋትን ሃሰተኛ የጋብቻ ሰነድ በማቅረብ ዜግነት መቀየሯን አስታውሶ ፤ ትዳሩ በፍቺ ከፈረሰ 10 ወራት ማለፉን በመጥቀስ የውዝግብ አቅጣጫውን  አክርሮታል፡፡   የፍቺው ወሬ  በተሰማበት ወቅት በስዊድን ሚዲያዎች  አትሌት አበባ አረጋዊ ማብራርያ ስትጠየቅ የግል ህይወቷን ማብጠልጠላቸውን እንዲያቆሙ ተማፅና፤ ስለ ጉዳዩ ብዙም መናገር እንደማትፈልግ በመግለፅ ትኩረቷ በስፖርቱ በመወዳደር ውጤት ማምጣት መሆኑን ተናግራ ነበር፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት ስዊድናዊ ሆና በ3 ትልልቅ ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮች በ1500 ሜትር  3 የወርቅ ሜዳልያ ድሎች በማስመዝገብ የተሳካላት አትሌት አበባ አረጋዊ በስዊድን ህዝብ የጥረት ተምሳሌት ሆና እንደ ጀግና ስትከበር ብትቆይም፤ በስዊድን ሚዲያዎች   እንድትብጠለጠልና ዜግነቷን ተነጥቃ  እንድትባረር  ዘመቻ የተቆሰቆሰው    ከስፖርቱ ጋር ጎን ጎን ሲወሳሰብ በቆየው የትዳር ህይወቷ ነው፡፡ አትሌት አበባ አረጋዊ   በፖላንዱ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ወቅት በለቅሶ እና በሃዘን እየታወከች ዝምታ ውስጥ ነበረች፡፡ ባለፈው ማክሰኞ ግን አትሌቷ ዝምታዋን ሰብራዋለች፡፡ ፒ4 ኤክስትራ  ከተባለ የስዊድን ሬድዮ ጋር በስፋት ቃለምምልልስ ያደረገችው አበባ አረጋዊ በአወዛጋቢው የትዳር ህይወቷ ዙርያ የቀረቡላትን ከባባድ ጥያቄዎች በልበሙሉነት ምላሽ ሰጥታባቸዋለች፡፡ ለመሆኑ የአበባ አረጋዊን የአትሌቲክስ ገድልና የትዳር ህይወቷን ያወሳሰበው ጉዳይ ምንድነው? እውነት ዜግነቷን ለመቀየር ሃሰተኛ የጋብቻ ሰነድ ተጠቅማ አጭበርብራለች? ከምታገኘው ገቢስ ለስዊድን መንግስት ሆን ብላ የገቢ ቀረጥ አልከፈለችም ወይ? ወደፊት ስዊድናዊ ሆና በዓለም የአትሌቲክስ መድረኮች መወዳደሯን ትቀጥላለች?  እነዚህና ሌሎች ጥያቄዎችን በማስመልከት ስፖርት አድማስ በሞስኮ 14ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ከአትሌቷ ጋር በተያያዘ በግንባር የነበረውን ተመክሮ በመከለስ፤ ባለፉት ሶስት ሳምንታት በስዊዲሽ ቋንቋ ለንባብ ከበቁት  የድረገፅ ህትመቶች ኤክስፕረሰንና ስፖርትብሌድን ዘገባዎች ተርጉሞ በማንበብ እና አትሌት አበባ አረጋዊ በፒ4 ኤክስትራ ሬድዮ የሰጠችውን ቃል በመንተራስ ከዚህ በታች የቀረበውን ዘገባ ያቀርባል፡፡