Sunday 29 September 2013

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ለኢትዮጵያውያን፣ ለአባሎቹ እና ለደጋፊዎቹ ያስተላለፈው የምስጋና መልእክት














ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን እንደ ወያኔ ዘመን የተዋረዱበት የተናቁበትና የተበደሉበት ጊዜ የለም። በአሁኑ ወቅት አገሪቱና ህዝቧ ከፊታቸው የተጋረጠው ችግር የመሰረታዊ የዲሞክራሲና የሰብኣዊ መብቶች አለመከበር ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የሕልውና ጥያቄና ኢትዮጵያ እንደ አገር የመቀጠልና ያለመቀጠል ጉዳይ ሆኖዋል። በመሆኑም ዛሬ የነጻነት ታጋዮች ህይወታቸውን በመሰዋት አገራችንን እንደ አገር ለማስቀጠል እና ህዝቧን ነጻ ለማውጣት ቆርጠው ተነስተዋል። 

በመሆኑም በኖርዌይ የምንኖር ኢትዮጵያውያን ይህንን ወቅቱ የሚጠይቀውን ታሪካዊ እና አንጸባራቂ የትግል ድጋፍ ጥያቄ አቅማችን በፈቀደው መንገድ በቁርጠኝነት በመደገፍ ለግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል የድጋፍ ፕሮግራም በዛሬው ለት ማለትም ሰብቴምበር 28፣2013 ከቀኑ 16፣00 እስከ 01፣00 ሰአት በተሳካና፣ ባንጸባረቀ እንዲሁም የነጻነት ሓይሎችን ባኮራ እና አለምን ባስደመመ ታሪካዊ ሁኔታ ተገባዷል።

ለዚህ መሳካት የድጋፍ ድርጅችን ማህበረሰባችን ላሳየው ታሪካዊ እና ወቅታዊ አመርቂ ምላሽ አክብሮቱን እና አድናቆቱን እየገለጸ ለቀጣይም ወቅቱን ለጠበቀ ታሪካዊ አገርን የማዳን እና የደጀንነት ጥሪ የትግሉን ግንባር ቀደም ቦታ በመያዝ አስፈላጊውን መስዋእትነት እንደምንከፍል የተዘጋጀን መሆኑን አስመስክሯል።

በማያያዝም በተደጋጋሚ እዚህ በኖርዌይ ምድር አከርካሪያቸው የተሰበረው የወያኔ ቡችሎች እና ሎሌዎች የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይልን የድጋፍ ፕሮግራም ለማስተጓጎል ያደረጉት ሙከራ በማህበረሰባችን ሙሉ የነቃ ተሳትፎና ክትትል ከንቱ ሊሆን ያቻለ ሲሆን።

በማጠቃለያም ይህንን ከፍተኛ አላፊነት በመሸከም ፕሮግራሙ ለዚህ መሳካት ያበቃችሁ ያአብይ ኮሚቴና የተለያዩ የሰብ ኮሚቴዎች አባላት፣ በተለያየ ቡድን ለስራው መሳካት የተሰለፋችሁ ወገኖች፣ በመላ አለም እንዲሁም በኖርዌይ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን፣ የድርጅታችን አባላቶች እንዲሁም ደጋፊዎች በሙሉ የድጋፍ ድርጅታችን ለናንተ ያለውን አድናቆት እና አክብሮት በምስጋና ይገልጻል። 

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!
የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ
ኖርዌይ፣ ኦስሎ ሰፕቴምበር 29፣ 2013

No comments:

Post a Comment