Monday 11 February 2013

ኦስሎ በታማኝ በየነ ደምቃ አመሽች


የኢሳት ኖርዌይ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ዕሑድ የካቲት 10  ቀን 2013 በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል አዳራሹን ሞልተው በጉጉት የጠበቁት የኖርዌይ ኢትዮጵያውያንም ተወዳጁ የኪነ ጥበብ ሰው ታማኝ በየነ ወደ አዳራሹ ሲገባ በጋለ ስሜት  ደማቅ አቀባበል አድርገውለታል  የተለያዩ የእንኳን ደህና መጣህ  ንግግሮች ተደርገዋል
ተወዳጁ የኪነ ጥበብ ሰው ታማኝ በየነ  በሃገርና በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለው የመብት ረገጣ አስመልክቶ በመረጃ የተደገፉ ትንታኔዎችን አቅርቧል።
በቀጣይ የጥበብ ሰው አርቲስት ታማኝ በየነ ወደ ዋናው የገቢ ማሰባሰቢያ የጨረታ መርሃ ግብር ተሸጋገረ ለጨረታ የቀረበው የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ነበር ጨረታውን ለማሸነፍ የነበረው ፉክክር ሞቅ ያለ ነበር ሞቅ አድርጉት እያለ ሞቅ ባለ ዋጋ ባለ ዕድሉ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ  በክብር ተረክበውታል
በአርቲስት እንዳለ እና በወጣቶች የተዝጋጀ የምርጫ 97 ድምፃችን ይመለስ በሚል ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው የተገደሉ ወጣት ሰላሚዊ ሰልፈኞችን ሁኔታ ያስታወስ ታሪካዊ ድራማ እና  በየዝግጅቱ ጣልቃ አዝናኝ ሙዚቃዎች ቀርቦአል።  ኢትዮጵያዊነት አንድነት እና ፍቅር የታየበት የተዋጣለት ዝግጅት ነበር

No comments:

Post a Comment