Thursday 21 November 2013

ዓለምአቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት በሳኡዲ አረቢያ

ዓለምአቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት በሳኡዲ አረቢያ

Global Alliance for the Rights of Ethiopians in Saudi Arabia


ህዳር 6 ቀን 2006 ዓ.ም.


አስቸኳይ መግለጫ


በቅርቡ፤ በተከታታይና በሚዘገንን ደረጃ በሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚካሄደውን እልቂት ለማስቆም ብሄራዊግብረ ኃይል እአ በ November 12, 2013 በተደረገ አስቸኳይ ስብሰባ ተመሰርቷል። 

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን፤ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለሰብአዊ መብቶች፤ ለሰዎች ክብርና የህይወት ክቡርነትየቆሙ ሁሉ የሳውዺ የጦር፤ የፖሊስ፤ የጥበቃና ሌሎች በመንግሥት የተደራጁ ወጣት ቡድኖች በሰላማዊ ኢትዮጵያዊያን ላይየሚያደርጉት ግድያ፤ አስገድዶ መደፈር፤ ግለሰቦችን በገመድ አንቆ ዛፍ ላይ መስቀል፤ ገረፋ፤ በ21ኛ መቶ ክፍለ ዘመንከሰለጠነ መንግሥት በማይጠበቅ ደረጃ ግለሰቦችን እንደ እንሰሳ አስሮ በመንገድ መጎተት ወዘተ ለህሊና የሚቀፍ ድርጊት እኛም በንፁሕ ኢትዮጵያዊያን ላይ መፈፀሙ አስቆጥቶናል፤ አሳዝኖላን፤ አበሳጭቶናል፤ ቀስቅሶናል፤ ለወገኖቻችን መብት እንድንነሳና ከሚመለከታቸው ጋር አብረን ድምጻችንን እንድናሰማ አስገድዶናል።

በመጀመሪያ ደረጃ የምንጠይቀው፤ የሳውዲ መንግሥት ሃላፊነቱን በመወጣት ይህ አሰቃቂ እልቂት እንዲቆም ማድረግ ነው።ከዚህ ጋር አብረን የምናሳስበው ለሰብእነትና ለሰው ክብር የቆመው የዓለም ህብረተሰብ ሁሉ ይህን አሰቃቂ ድርጊትተቀዳሚነት በመስጠት እንዲቆም ማድረግ የሞራል ሃላፊነት አለበት የሚል ነው። የኢትዮጵያዊያን ህይወት እንደ ማንኛውምሰባዊ ፍጡር ትልቅ ዋጋ ያለው መሆኑን እናሳስባለን። ይህን የተቀደሰ ዓላማ ስኬታማ ለማድረግ የሚከተሉትን ለሰብአዊ መብት፤ ለሰው ክብርና ነጻነት፤ለእውነተኛ እኩልነት የቆሙ ሶስት ግለሰቦች በአሰባሳቢነት መርጠናል፤

1. አቶ አበበ ገላው
2. አቶ ብርሃኑ ዳምጤ (አባ መላ) እና
3. አቶ ታማኝ በየነ

ኢትዮጵያዊያን፤ በተለይ ወጣት ወንዶችና ሴቶች በሳውዲ አረቢያና በሌሎች የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች በገፍየሚሰደዱበትና በሰላም ሰርተው ለመኖር የሚፈልጉበት ምክንያት በአገራቸው የስራ፤ በሰላም የመኖር፤ የራሳቸውን ስራየመፍጠር፤ መብታቸውን የማስከበር እድል ስለሌላቸው ነው። ስለሆነም፤ የሳውዲ አረብያ የጥበቃ፤ ፖሊስና ወጣት አፋኝቡድኖች በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደርጉት ግድያ፤ አፈናና፣ አስገድዶመድፈርና ማሳደድ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ፤ለህሊና የሚቀፍ፤ በተባበሩት መንግሥታት ውሎች የተከለከለ፤ የሰለጠነው ዓለም የማይቀበለው በሰብእነት ላይ የተፈፀመወንጀል ነው። ይህን አሰቃቂ ድርጊት የአይን ምስክሮች፤ የቢቢሲ፤ የአልጀዚራና የግል ታዛቢዎች በቪዲዮ ቀርፀው ለዓለምሕዝብ አሰራጭተውታል። ከዚህ የበለጠ ምስክር ሊኖር አይችልም። የሳውዲ አረቢያ መንግሥት ሆነ ብሎ የሚያደርገው ህገ  ወጥ ድርጊት መሆኑን አንጠራጠርም፤ ስለሆነም፤ ይህን አሰቃቂ ተግባር ማቆም ያለበት የሳውዲ አረቢያ መንግሥት መሆኑን  በጥብቅ እናሳስባለን።

ከላይ እንዳሳየነው፤ ኢትዮጵያዊያን አገራቸውን ለቀው እንዲሰደዱ፤ ሲሰደዱ አሰቃቂና ለህሊና የሚዘገንን ግድያ፤ እስራትናሌላ ኢ-ሰብአዊ ወንጀል የሚፈፀምባቸው ወደው አይደለም። አብዛኛው የኢትዮጵያ ወጣት ትውልድ በአገሩ ህይወቱንናቤተሰቡን የሚደግፍበት ስራ የለውም፤ የኑሮ ዋስትና የለውም። የሕግ የበላይነት ስለሌለ፤ ከሕግ ውጭ የሆነ አፈና፤ ግድያ፤እስራት፤ ኢ-ሰብአዊ ቅጣት፤ የውስጥና የውጭ ስደት፤ መባረር ወዘተ እጣው ሆኗል። ስለዚህ ነው ብዙ ሽህ ኢትዮጵያዊያንብዙ ሽህ ብር ከፍለው ለህይወታቸው አደጋን የሚጋብዝ ጉዞ የሚያደርጉት። አሰቃቂ ሆኖ ያገኘነው፤ ኑሯችንን እናሻሽል ይሆናል ብለው ያደረጉት ተስፋ ወደ ጨለማ መርቶ ለህይወታቸው መጥፊያ፤ ለአካለ ስንኩልነት፤ ለክብራቸው መገፈፊያ ወዘተ ምክንያት መሆኑ ነው። ይህ በሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን የመጣ “የባርነት” ሁኔታ መፈጠሩን ያመለክተናል፤መቆም አለበት የምንለው የእነዚህ ወገኖቻችን መዋረድ የሁላችንም ክብር መገፈፍ መሆኑን ስለምንረዳ ጭምር ነው።

ኢትዮጵያዊያን በያሉበት በመገናኛ ብዙሃን፤ በድህረገጾች፤ በሰላማዊ ሰልፍና በሌሎች መንገዶች የሚያሳዩት ጥረት የሚያኮራጅምር ነው። በዚሁ መሰረት የሳውዲ አረቢያ መንግሥት የሚያደርገውን አሰቃቂ ግፍለዓለም ህብረተሰብ ለማጋለጥ፤ወንጀሉን የፈፀሙ ሁሉ በሃላፊነት ለፍትህ ለማቅረብ የሚደረገው ተግባር በተከታታይና አስተማማኝነት ባለው ደረጃ እንዲካሄድ ቆርጠን ተነስተናል። የተቋቋመው ግብረ ኃይል ዋና ሚና በሳውዲ አረቢያ የሚካሄደውን ወንጀል ለሚመለከታቸው የዓለም ህብረተሰብ የሰብአዊ መብቶች፤ የፍትህ ተቋሞች፤ የለጋሽ ድርጅቶችና ሃላፊዎች ማሳወቅ፤ ቅስቀሳ  ማድረግ፤ የገንዘብና ሌላ ቁሳቁስ ድጋፍ ለወገኖቻችን ለማቅረብ ጥረት ማድራግን ይጨምራል። በዚህም መሰረት፤ ግብረኃይሉ፤ እውቅና፤ ተቀባይነትና አስተማማኝ የሆኑ የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶችን፤ ሊቆችን፤ ጠበቃዎችን ወዘተ፤ በመቅረብና በመቀስቀስ፤ የሳውዲ መንግሥት በሰብአዊነት ላይ ያደረገውንና የሚያደርገውን ወንጀል (Crimes against humanity)ለፍትህ ለማቅረብ የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል። በተጨማሪ፤ በሳውዲ አረቢያ ያለውን ሁኔታ በቀጥታ ለመመራመርናእውነተኛውን ዝርዝር ሁኔታና ስእል ለመገንዘብ አንድ ቡድን ለመላክ አቅዷል።

ይህ የተቀደሰና ሁሉም ኢትዮጵያዊያን፤ የሰው ክብርና መብቶች ደጋፊ የሆኑ ድርጅቶችና ግለሰቦች እንዲሁም መንግሥታትበያሉበት የሚጋሩት አስቸኳይ ጥሪ ፋታ አይሰጥም። ግድያው፤ ገረፋው፤ እስራቱ፤ የሴቶች ክብር ድፍረቱ ወዘተ የሁላችንምስለሆነ ዓለም አቀፍ ጥረት ያስፈልገዋል። ሁላችን ሌሎችን በመቀስቀስ ይህ ግፍ በፍጥነት እንዲቆም በተግባር ማሳየትየሞራል ግዴታችን ነው። ወንጀሉን የፈፀሙት የሳውዲ አረቢያ ባለስልጣናትና ሌሎች ተሳታፊዎች በሃላፊነት ተጠያቂ መሆንአለባቸው።

የሳውዲ መንግሥት ባለስልጣናት የኢትዮጵያዊያንን መብቶች ገፈው፤ ገድለው፤ አዋርደው፤ አሳደው፤ ሰቅለው፤ ክብር ገፈው በኢትዮጵያ ያላቸውን ዘላቂ ጥቅም ለማስከበር እንደማይችሉ ማመን አለባቸው። ይህን ማሳመን መቻል አለብን። የተፈጸመውን አሰቃቂ ግድያ፤ ድፍረትና ሰቆቃ ኢትዮጵያውያንና የዓለም ሕብረተሰብ እንዲያወግዝልን ድርጅታችን ጥሪውን ያቀርባል። በተጨማሪም፤ በኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ አስከፊና ኢሰብአዊ ድርጊት የፈጸሙት ሁሉ ተጠያቂ እንዲሆኑ እናሳስባለን። እንዲሁም፤ በመረጃና ተሞክሮ መጋራት፤ ኢትዮጵያውያንን ከሳውዲዎች ሰቆቃና ግድያ ለማትረፍ ስለሚያስፈልገው እርዳታ ሁሉ ኢትዮጵያውያንና ለሰብአዊ መብት የሚታገሉ ድርጅቶች እንዲተባበሩን ከአደራ ጋር እንጠይቃለን።

ይህን ለማድረግ የምንችለው ለዚህ ዓላማ በያለንበት ስንነሳ፤ አብረን ተባብረን ስንሰራ፤ ለወገኖቻችን መቆማችንን በተግባር  ስናሳይ፤ ዜና፤ ሃሳብ፤ እውቀት፤ ልምድ፤ ስንለዋወጥ፤ የገንዘብ ሆነ ሌላ አስተዋፅኦ ስናደርግ ነው። ይህን በተቀነባበረና ስልት  ባለው መንገድ ከሰራን በወገኖቻችን ላይ የደረሰውንና የሚደርሰውን እልቂት ለማቆም እንችላለን። የወገኖቻችንን ክብር
በመታደግ፤ የራሳችንን ክብር ለማስከበር እንችላለን።
ሁሉም ህይወት እኩል ዋጋ አለው!!!

Contact information:
Telephone: (877)RING-ETHIOPIA or (877)746 -4384
Email address: Alliance4rightsofethiopians.sa@gmail.com

No comments:

Post a Comment