Monday 17 June 2013

ጫትና ሺሻ በአዳማ ከተማ ለሴተኛ አዳሪነት መስፋፋት ምክንያት እየሆኑ ነው ተባለ

በአዳማ ከተማ  የጫት መሸጪያ ሱቆች በከፍተኛ ደረጃ እተስፋፉና የቃሚውም  ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው ተባለ  መኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ ከመለስተኛ አንስቶ እስከ አለም አቀፍ ሆቴሎች ድረስም በዚህ የጫት ማስቃምና የሺሻ ማስጨስ ተግባር ውስጥ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ የከተማው ነዋሪዎች ልጆቻችን በዚህ ችግር ውስጥ እየወደቁ ነው በዚህ ምክንያትም ለጎዳና ተዳዳሪነት የሚዳረጉና የታዳጊ ህፃናት ሴተኛ አዳሪነትም በከተማዋ እየተስፋፋ ነው ይላሉ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጠው በማሳሰብ።በዚህ ችግር ውስጥ የአዳማ ዩንቨርስቲ ተማሪዎችም ግንባር ቀደም ተሳታፊ እየሆኑ መምጣታቸው ጉዳዩን አሳሳቢ አድርጎታል ይህ የጫት አቅርቦት ጉዳይ የአዳማ ዩንቨርስቲን ጨምሮ በከተማው በሚገኙ ኮሌጆችና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አቅራቢያ ጭምር በብዛት ይስተዋላል በአዳማ አብዛኛዎቹ ሆቴሎች  ውስጥ መቃሚያ ክፍሎችን በማዘጋጀት ለህገ-ወጥ ገቢ ማግኛ መጠቀም የተለመደ ነው ይባስ ብሎም አንዳንድ የከተማዋ  ሆቴሎች ማስታወቂያዎችን ጭምር በመለጠፍ ማስቃሚያ ቦታ እንዳላቸው ያስተዋውቃሉ ቡናውን የሚያፈሉና ሺሻውን ለተጠቃሚዎቹ  የሚያቀርቡት ደግሞ ታዳጊ ሴቶች ናቸው በተለይ አርብ ቅዳሜና እሁድ  ለዚሁ ተግባር ከአዲስ አበባና ሌሎች የአቅራቢያ ከተሞች ወደ አዳማ  የሚገባው ሰው ቁጥርም ከፍተኛ ነው ጉዳዩን አስመልክቶ  የአዳማ ከተማ አስተዳደር  ምክትል ከንቲባ አቶ አህመድ የሱፍ  ችግሩ መኖሩን አምነው ይህም ለከተማዋ ፀጥታ ጭምር አሳሳቢ መሆኑን ያነሳሉ ይህ ጉዳይ ከዚህ በፊት በከተማው አስፋፍቶት የነበረውን ወንጀል በማስታወስ አቶ አህመድ እንደሚሉትና ህብረተሰቡም እንዳነሳው በሆቴል ቤቶች የሚቅሙት  የከተማ አስተዳደሩ ሰራተኞችም ጭምር ናቸው በመሆኑም በዚህ ድርጊት ውስጥ የተገኙ ሰራተኞችን ባለፈው ወር ከስራ አግደናል ይላሉ ምክትል ከንቲባው ይህንን  ችግር ለመፍታትም ትልልቅ ሆቴሎችን ጨምሮ የተለያዩ  ጫት በማስቃም ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ አካላትን ፈቃዳቸውን እስከመሰረዝና ከአዳማ ዩኒቨርስቲ ጋር በጋራ መስራት የሚቻልበትን  ሁኔታ ለመጀመር እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ ነው ፡፡

No comments:

Post a Comment