Thursday 13 December 2012

ኢትዮጵያ ቤተእስራኤላዉያን


የኢትዮጵያ ቤተእስራኤላዉያን ሴቶች የዛሬ ስምንት ዓመት ወደእስራኤል ከመሄራቸዉ አስቀድሞ የወሊድ መቆጣጠሪያ በግዳጅ ተሰጥቶናል ሲሉ ማመልከታቸዉን ሰሞኑን የእስራኤል የመገናኛ ብዙሃን ይፋ አድርገዋል።  The Time of Israel የተሰኘዉ ድረገፅ እንዳመለከተዉ ጉዳዩን በአንድ የእስራኤል የቴሌቪዥን ጣቢያ ያብራሩት ኢትዮ-ቤተእስራኤላዉያን ወደእስራኤል ለመሄድ ዴፖ ፕሮቬራ የተባለ የወሊድ መቆጣጠሪያ መድሃኒት በመርፌ ተሰጥቷቸዋል። ዘገባዉ ባለፉት አስርት ዓመታት 50 ሺህ ኢትዮጵያዉያን አይሁዶች ወደእስራኤል መግባታቸዉን ጠቅሶ፤ ለወትሮ ብዙ ልጅ መዉለድ የሚወደዉ ይህ ማኅበረሰብ በአማካኝ የወሊድ ቁጥሩ 50 በመቶ ቀንሶ መታየቱን አመልክቷል።
 
DW AMHARIC NEWS
 

No comments:

Post a Comment