Friday 7 December 2012

ቴዎድሮስ የት ገባ?”

መለስ በአንደኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡ ለተማሪዎች ንግግር ካደረጉ በኋላ “አሁን ጥያቄ ካላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ” አሉ፡፡ ቴዎድሮስ የተባለው  ተማሪ ተነሳና “ሦስት ጥያቄዎች አሉኝ” በማለት ጀመረ፡፡ መለስም እንዲጠይቅ ፈቀዱለት “1ኛ. እንዴት ኢ ህ ዲ ግ 99.9% ምርጫውን ሊያሸንፍ ቻለ  2ኛ. ለምንድነው የፀረ-ሽብርተኝነት ህጉን የህዝቡን የጋዜጠኞችን እና ጋዜጦችን  ሃሳብን በነፃነት የመግለፅን መበት የምትጠቀሙበት? 3ኛ. ህወሃት ለምን በሰላማዊ መንገድ ስልጣኑን አይለቅም?” ይሄኔ ደወል ተደወለና ተማሪዎቹ ለእረፍት ከክፍሉ ወጡ፡፡ ከእረፍት መልስ መለስ “ቅድም ውይይታችን ስለተቋረጠ አዝናለሁ አሁን የፈለጋችሁት ልትጠይቁኝ ትችላላችሁ” አሉ፡፡ ቅድስት የተባለች ትንሽ ልጅ ተነሳችና “አምስት ጥያቄዎች አሉኝ” አለች፡፡ ቀጥይ አሏት ጠ/ሚ፡፡ “1ኛ. እንዴት ኢ ህ ዲ ግ 99.9% ምርጫውን ሊያሸንፍ ቻለ? 2ኛ. ለምንድነው የፀረ-ሽብርተኝነት ህጉን የጋዜጠኞችን እና ጋዜጦችን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅን መበት ለመገደብ የምትጠቀሙበት?  3ኛ. ህወሃት ለምን በሰላማዊ መንገድ ስልጣኑን አይለቅም?” 4ኛ. ለምን የእረፍት ሰዓት 20 ደቂቃ ቀደም ብሎ ተደወለ? 5ኛ.ቴዎድሮስ የት ገባ?”

No comments:

Post a Comment