Thursday 11 April 2013

ህግ በብርሃን ፍጥነት ሲወጣ

የአንድ ሀገር ፓርላማ የሀገሪቱን ከፍተኛ የስልጣን ዕርከን እና የህዝቡን ውክልና የያዘ ነው ስንል በቀጥታ ለሀገሪቱ ብሎም ለህዝቡ ጥቅም የቆመ ነው ማለት ነው። እንደ አለመታደል ሆኖ ግን ምንም ሀገራዊ ወይም ህዝባዊ ጥቅም የሌለው በተቃራኒው ግን ሀዝብን ብሎም ሀገርን እያወቀ ለዘላቂ ጉዳት የሚዳርግ ህግ በብርሃን ፍጥነት ሲወጣ እንደው ለመሆኑ እነዚያ ህግ አውጪ ተብዬዎች ዜግነታቸው የየት ሀገር ይሆን ያስብላል።
ዕድሜ ለ1997 ምርጫ ስለ ምርጫ ዕምነት ባጣው ህዝብ ህሊና የዴሞክራሲ ትርጉም ስለጨለመበት ወያኔ ብቻውን ያለተቀናቃኝ የማጭበርበር ስራ ሰርቶ 99%  የፓርላማ መቀመጫውን ተኛበት።

No comments:

Post a Comment