Thursday 11 April 2013

የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር የመለስ ምስል ነው እንዴ?

የአቶ መለስ ዜናዊን ስምና ምስል መጠቀም የሚከለክልና የሚፈቅድ መመርያ ሊወጣ ነው
የአቶ መለስ ዜናዊን ስም፣ ምስልና ሥራዎቻቸውን በተለያዩ ሁኔታዎችና ጊዜያት መጠቀምን የሚከለክልና የሚፈቅድ የመመርያ ረቂቅ ቀረበ፡፡
የመመሪያው ረቂቅ ሊቀርብ የቻለው የመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን በአዋጅ ቁጥር 781/2005 አንቀጽ ዘጠኝ ንዑስ አንቀጽ ሁለት (ሰ) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት መሆኑን ረቂቁ ይገልጻል፡፡ 


የአቶ መለስ ማንኛውም ከመንግሥትና ከፓርቲ ሥራዎች ጋር ያልተያያዙ ምስሎች ወይም ፎቶግራፎች ባለቤትነት የቤተሰቦቻቸው መሆኑን የሚገልጸው ረቂቅ መመርያው፣ ማንኛውም ሰው ገንዘብ ለማሰባሰብ፣ ለሽያጭ፣ ለባዛር፣ ለጨረታ ወይም ለማንኛውም ዓይነት ጥቅም ማስገኛነት ሊሰቅል፣ ሊለጥፍ፣ ሊቀርጽ ወይም ሊያስቀምጥ እንደማይችል ይከለክላል፡፡ 

የአቶ መለስን ፍቅርና ክብር ለመግለጽ የሚፈልጉ ምስላቸውን በመኖሪያ ቤታቸው ግድግዳ ላይ ሊሰቅሉ፣ በአልበም ውስጥ፣ በቦርሳቸው፣ በኪሳቸው፣ በተሽከርካሪያቸው ወይም በሌላ የግል መጠቀሚያቸው ሊይዙ እንደሚችሉ ደግሞ መመርያው ይፈቅዳል፡፡ 

ከፋውንዴሽኑ ቦርድና ከቤተሰቡ በቅድሚያ ፈቃድ በመጠየቅ ስማቸውን ለአርዓያነት፣ ለማስተማሪያነትና ለመታሰቢያነት ማንኛውም ሰው መጠቀም እንደሚችሉ የመመርያው ረቂቅ ያስረዳል፡፡ በተለየ ሁኔታ ለሕዝባዊ ዓላማም ከሆነ ፈቃድ ጠይቆ ገንዘብ ማሰባሰብም እንደሚቻል በረቂቁ ተጠቁሟል፡፡ 

በአቶ መለስ ስም የታተሙም ሆነ ያልታተሙ ሥራዎች ለቤተሰባቸው እንደሚሆኑ የሚገልጸው ረቂቅ መመርያው፣ በመንግሥት ወይም በፓርቲ ኃላፊነታቸው የሠሯቸው ማናቸውም ሥራዎች ባለመብት መንግሥት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብና አባል ድርጅቶች መሆናቸውን ገልጿል፡፡

ለውይይት የቀረበው ረቂቅ መመርያው አራት ምዕራፎችና 19 አንቀጾች ሲኖሩት፣ ቦርዱ ተወይይቶበት እንደሚፀድቅ ተገልጿል፡፡ 

No comments:

Post a Comment