Thursday 27 September 2012

ወጣቱ የኢትዮጵያ ድምጻዊ በ64ኛው ኢሚ አዋርድ ላይ ተሳታፊ ነበር


በ64ኛው የኢሚ አዋርድን ተከትሎ ብዙ ታላላቅ አለም አቀፍ የፊልም ባለሙያዎች ፣ሙዚቀኞች ፣ሲኒማቶግራፈርስ እና የፊልም ኢንዱስትሪ ካምፓኒዎች እን ባለቤቶቻቸው የተሳተፉበት ትልቁን የዚህን አመት አዋርድ ወጣቱ ኢትዮጵያዊ በወጣቶች ዘንድ ከፍተኛን አድናቆት እና እውቅና ያለውን በዘመናዊው ያዘፋፈን ስልቱ እና ከብዙ አርቲስቶች ጋር በፊቸሪንግ በመስራት የሚታቀው ሳሚ ካሳ (ሳምቮድ )የዚሁ እድል ተቋዳሽ እንደነበር ከስፍራው የደረሱን የተለያዩ መረጃዎች ያመለክታሉ:: ሳምቮድ በተለያዩ የሃሊውድ ቲቪ ሾው ፣ፊልሞች እና ማስታወቂያዎች ላይ የተሳተፈ ሲሆን በሃሊውድ የአክተሮች ዩኒየን አባል በመሆን (እስክሪን አክተርስ ጊልድ ) አባል በመሆን ስራዎቹን በመስራት እራሱን በማንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።
 
ሳምቮድ ከሰራቸው የቲቪ ሾው ድርጅቶች ታዋቂው ስክረብስ ፣ አንታራዥ ላይ በመሳተፍ ለመጀመሪያ ጊዜያት በመስራት ወደ ማህበሩ መቀላቀሉን ከዛሬ 3 አመት በፊት ለጠብታ መጽሄት ዝግጅት ክፍል ላደረግነው ቃለመጠይቅ እንደገለጸ ይታወቃል ። በወቅቱም በጣም ከባድ እና ፈታኝ ሆኖ ለራሳቸው ዜጎችም ቢሆን አስቸጋሪ የሆነው ይኸው መንገድ ለእኔ እነዚህ ስራዎቼ ብዙዎቹን መንገዶች ሊጠረጉልኝ ችለዋል ሲል ጠቁሞን ነበር።
 
በአሁን ሰአት የተለያዩ የሃሊውድ ፕሮዳክሽኖች ሶፕአፕራ ቦልድ አንድ ቢዩቲፉል የተሰኘ ቲቪ ሾው ላይ እና በተለያዩ የፊልም ስራዎች ላይ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ። በተወሰነ መልኩ ከመድረክ በስተጀርባ በመሆን እንቅስቃሴዎቹን አሳይቷል ።በተያያዥነትም ሙዚቃዎቹንም ለማሻሻል እና በአለም አቀፍ ደረጃ ለማሳየት ጥረት እያደረገም እንደሆነ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከሚሰራቸው የክሊፕ ስራዎች የጥራት ደረጃቸው ለማየትም ችለናል ።
 
ለዚህም ከዚህ በፊት ወደ ሰሜን አሜሪካ ይዞት ከመጣው አልበሙ “ተይ ተይ “ ዘፈኑ ተመርጦ በቢኢቲ ቻናል ከሆነው አንዱ በካሪቢያን ሙዚቃ ፕሮግራም ቴሌቪዥን ስርጭት (ዊክድ) በመጀመሪያ ደረጃ (ቶፕቴን ሊስት) ለስምንት ሳምንታት በማቅረብ ከፍተኛ ተደማጭነትን እንዲያገኝ አድርጎለታል። ለዚህም ይህ የሙዚቃ ስራው በቢኢቲ የሙዚቃ አዋርድ ፕሮግራም ላይ እንዲጋበዝ አድርጎታል ።
 
ባለፈው አመት በተሰራው በአሜሪካን አየር ፎርስ የፊልም ስራ ላይ የተሳተፈ ሲሆን የኢትዮጵያን ባህል እና እንቅሳቃሴም ትወናን እንደተወነ ገልጾልን ነበር ይህም የፊልም ቀረጻው ለአንድ ወር በሜክሲኮ ሲቲ እንደተከናወነም አክሎ ገልጦአል ።በተለይም የሃሊውድ ጋድ ፋዘር ከተሰኘው ድንቅ አክተር አልፓችኖ ጋር በመሆን አጭር የፊልም ስክሪን እይታም አግኝቶ የሰራ ሲሆን ይህ ፊልም በሚቀጥለው አመት የሚለቀቅ ነው የፊልሙም ርእስ ስታንድ አፕ ጋይስ የተሰኘ ሲሆን ሌላው ትሩ ብለድ( እውነትኛ ደም )በሚሰኘው የኤችቢኦ ቲቪ ሾው ስራዎችን ፕሮድዩስ በሚደረግበት ላይ የራሱን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል።
 
በተለይ ሳምቮድ ከተለያዩ የፊልም ኤጀንቶች ፣ማነጀሮች ፣ፐብሊሲቶች እና ካምፓኒዎች ጥልቅ ግኑኝነት ያለው ይህ ወጣት የወደፊት የኢትዮጵያ የፊልም ራእይ ሊሆን ይችላል ተብሎ ይታሰባል ።በዚህ ወራትም ከሚለቀቁት አዳዲስ ቴክኖሎጂ ካፈራቸው መካከል ከጌም ካምፓኒ ጋር በመስራት በራሱ ስም አዲስ የጌም ጨዋታ በሚቀጥለው ወር ለገበያ እንደሚቀርብ የደረሰን ዘገባ ይጠቁማል።በተለይም ለማለዳ ታይምስ በየወቅቱ የሚያደርሱትን የዚህን ወጣት ባለ ራእይ ስራዎችን አስመልክቶ በቅርበት አብረውን የሚሰሩን ባልደረቦቻችንን ሳናመሰግን አናልፍም ።
 

No comments:

Post a Comment