Sunday 28 October 2012

ይህ ጊዜ

በታሪካችን ውስጥ ያለው የጊዜው ዕንቆቅልሽ ህንፃዎቻችን ረዥም መሆናቸውና ትዕግስታችን ማጠሩ መንገዶቻችን ሰፊ መሆናቸውና አመለካከታችን መጥበቡ ነው   

ብዙ ገንዘብ እናጠፋለን ግን ያለን ትንሽ ነው  ብዙ እንገዛለን ግን እርካታችን ዝቅተኛ ነው ትላልቅ ቤቶች አሉን ግን ቤተሰቦቻችን ትንሽ ናቸው  የተመቻቹ ሁኔታዎች አሉ ግን የጊዜ እጥረት አለብን

ብዙ ዲግሪ አለን ግን ዝቅተኛ ምክንያታዊነት አለን  እውቀታችን ብዙ ነው ነገር ግን ግምታችን ዝቅተኛ ነው  ብዙ አዋቂዎች ቢኖሩንም ችግራችን ብዙ ነው  ብዙ መድሀኒቶች አሉን ግን ፈውሳችን ዝቅተኛ ነው  

ብዙ እንጠጣለን ብዙ እናጨሳለን  በግድ የለሽነት ገንዘብ እናጠፋለን  የምንስቀው ግን ትንሽ ነው በፍጥነት መኪና እንነዳለን  በቀላሉ እንናደዳለን አርፍደን ነው የምንተኛው ተዳክመን ከእንቅልፍ እንነቃለን  ትንሽ ነው የምናነበው ቴሌቪዥን ብዙ እናያለን ብዙ ግን አንፀልይም 

ሕይወታችንን ማራዘም ችለናል ግን ኑሯችንንን ናሳጥራለን  ወደ ጨረቃ ተጉዘን ተመልሰናል ነገር ግን መንገድ ቋርጠን ዲስ ጎረቤት ለማየት ንቸገራለን  የውጭውን ለም ተቆጣጥረናል ውስጣችንን ግን ልተቆጣጠርነውም ::  

ትላልቅ ነገሮችን ሰርተናል ነገር ግን የተሻሉ ነገሮችን አልሰራንም አየሩን አፅድተናል ነገር ግን መንፈሳችንን በክለናል አቶምን ተገንዝበናል ነገር ግን ወገናዊነትን አልተገነዘብንም  ብዙ እንፅፋለን ግን ትንሽ ነው የምንማረው

የምናቅደው ብዙ ሲሆን የምንፅፈው ግን ትንሽ ነው መጣደፍን ተምረናል ነገር ግን መታገስን ልተማርንም  ብዙ መረጃዎችን የሚይዙና ከምንፈልገው በላይ ብዙ ኮፒ የሚያደርጉ ኮምፒተሮች ሰርተናል ነገር ግን የርስ በርስ ግንኙነታችን ዝቅተኛ ነው 

ይህ ዘመን ምግብ በቅፅበት የሚገኝበትና የበላነው ምግብ ቶሎ የማይፈጭበት ዘመን ነው  ይህ ዘመን የታላላቅ ሰዎች ግን የዘቀጠ ፀባይ  የከፍተኛ ትርፍ ግን የአልባሌ ግንኙነት ዘመን ነው  ይህ ዘመን እጥፍ ድርብ የቤተሰብ ገቢ ነገር ግን ብዙ ፍች የደልቃቃ ቤቶች ግን የሀዘንተኛ ኗሪዎች ዘመን ነው ::  

እነዚህ ጊዜዎች ጉዞ ቅፅበታዊ የሆነበት  የህፃናት መፀዳጃ ጨርቆች ተጠቅመን የሚጣሉበት የቆሸሸ ግብረ ገብነት  የአንድ ሌሊት ወሲባዊ ግንኙነት ብዙ ወፍራም ሰዎች ያሉበት  ጉደኛ የሆኑ ኪኒኖች ባንድ ጊዜ ሊያስደስቱን ዝም ሊያሰኙን ወይንም ሊገሉን የሚችሉበት ጊዜ ነው 

ይህ መጋዘን ውስጥ ምንም ነገር ሳይኖር ለህዝብ በማሳያው ክፍል ውስጥ ብዙ ዕቃ የሚቀርብበት ጊዜ ነው 
ይህ ጊዜ ቴክኖሎጂ ዕንዲህ ያለውን ጽሁፍ አምጥቶልን ሀሳቡን ከሌሎች ጋር ለመካፈል የምንወስንበት ወይንም መሰረዣውን "ዲሊት " የሚለውን ቁልፍ ተጭነትን
መልዕክቱን የምናጠፋበት ጊዜ ነው ::    
                      ________________

No comments:

Post a Comment