Wednesday 24 October 2012

የሐረር ሬዲዮ ጣቢያ ሥርጭት ተቋረጠ

ጥር ፪ ቀን ፩፱፮፭ ዓ ም የተመሰረተው የሀረር ሬዲዮ ጣቢያ በኦሮሚኛ ኋላም በሶማሊኛና ሀረሪ ቋንቋዎች ሲያስተላልፋቸው የነበሩ አካባቢያዊ ስርጭቶች መቋረጣቸውን ተከትሎ በምስራቁ የሀገሪቱ ክፍል ነዋሪዎች ቅሬታ በማሰማት ላይ ናቸው። ከጠቅላዩ ሞት ጀምሮ ሬዲዮ ጣቢያው ሶስቱን የአካባቢያዊ ስርጭቶች በመዝጋት የሀገራዊ ስርጭቱን ብቻ ተቀብሎ በማስተላለፍ ላይ ይገኛል። ሬዲዮ ጣቢያው በተለይ በመዝናኛ ዝግጅቱ የሕብረተሰቡን የዕለት ከዕለት ህይወት በመዳሰስ ተወዳጅና ተደማጭ ነበር።



 Deutsche Welle









 

No comments:

Post a Comment